Monday, December 31, 2012

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ

-    የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የኢሕአዴግ ዕጩ ሆነው የተወዳደሩበትን ሰነድ አቀረቡ
 -    የምርጫ አስፈጻሚዎች ለኢሕአዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ አለን ይላሉ
 -    አንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋለ ነው በማለት ኮነኑ

በየማነ ናግሽ

መድረክንና መኢአድን ጨምሮ ዋነኛ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡበት 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለፓርላማው አፈ ጉባዔ ክስ እንደመሠረቱበት ገልጸው፣ አገኘናቸው ያሉዋቸውን አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ግንባር (መድረክ) ጽሕፈት ቤት የፓርቲዎቹ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባለፈው ሐሙስ ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አንዳንድ ሚስጥራዊ ያላቸውን ሾልከው የወጡ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ለቅሬታቸው ማስረጃ የላቸውም ማለቱን አስተባብለዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላቀረብናቸው 18 ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ቦርዱ የገዥው ፓርቲ ወገንተኛና ጉዳይ አስፈጻሚ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፤” በሚል ርዕሰ ጊዜያዊ ኮሚቴው ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቀጣዩ ምርጫ ፍትሐዊ እንዲሆን እንነጋገርበት በሚል ለቦርዱ 18 የቅሬታ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም፣ “አንዳቸውም በማስረጃ የተደገፉ አይደለም” በሚል በተሰጣቸው ምላሽ ውድቅ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበለትን ቅሬታ ለአንድ ወር ያህል ከገመገምኩ በኋላ በሚል የሰጠው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በሕዝብ የሚያስጠይቅ ነው ያሉ ሲሆን፣ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሳይጠይቃቸውና ተወካዮቻቸውን ሳያነጋግር ውሳኔውን ያሳወቃቸው ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጠበት ወቅት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በምርጫ ቦርድ ምላሽና በምላሽ አሰጣጡ አግባብነት የተበሳጨው የ33 ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ ቦርዱን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ አፈ ጉባዔው ላይ ክስ እንደመሠረተበት አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ማስረጃ ያላቸውን ለጋዜጠኞች ይፋ አድርጓል፡፡ “በታሪክም በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊትም የሚያስተዛዝብና የሚያስጠይቅ ነው፤” ባለበት በዚሁ መግለጫ፣ “ለመሆኑ መቼ መድረኩ ተከፍቶ ተወያይተን? ማስረጃ ለማቅረብ ተጠይቀን ማቅረብ አለመቻላችን ታየና ነው እንዲህ ሊባል የተቻለው?” በማለት በጥያቄ ለተነሳው ጉዳይ የኮሚቴው አባላት ምላሽ የሰጡት ማስረጃ ያሉትን በማቅረብ ነበር፡፡

የኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለ መግለጫውን አንብበው ከጨረሱ በኋላ፣ “ማስረጃችሁ ምንድን ነው? ምን አዲስ ነገር ይዛችኋል?” በሚል ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀድመው ምላሽ የሰጡት የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ፣ “አንድም ማስረጃ የሌለው ቅሬታ አላቀረብንም፡፡ ቦርዱ ግን የኢሕአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኗል፡፡ ፈጽሞ አላነጋገረንም፤ ማስረጃ እንድናቀርብም አልጠየቀንም፤” ብለዋል፡፡

የኮሚቴው አባልና የመድረክ አመራር አባል አቶ ገብሩ ገብረማርያም በበኩላቸው፣ ለእያንዳንዱ ቅሬታ ማስረጃ መያዛቸውን ያረጋገጡት፣ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺ ፈቃደ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደ ኢሕአዴግ ሆነው ሲከራከሩዋቸው ቆይተው አሁን የኢሕአዴግ አባል የሆኑበት ማስረጃ መገኘቱን በማሳወቅ ነበር፡፡

“በወይዘሮ የሺ ላይ ግላዊ ጥላቻ ኖሮን አይደለም፡፡ ነገር ግን የኢሕአዴግ አባላት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑበት ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ምርጫ ማከናወን አይችልም፤” ብለዋል፡፡ በኃላፊዋ ላይ ለምን እንዳተኮሩ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ማስረጃውን ይዘዋል የተባሉት የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ንግግራቸውን የጀመሩት በእጃቸው አንድ ሰነድ ከፍ አድርገው በማመልከት ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ “የክልል ምክር ቤት አባላት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት መተማመኛ” በሚል የምርጫ ቦርድ ዓርማ ያለበት ሰነድ የዕጩ ተወዳዳሪዋ የወይዘሮዋ የሺ ፈቃደ ስም የሚገኝበት፣ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ያገኙት የድምፅ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበትና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሃን ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

ወይዘሮ የሺ በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው፣ “ይህ ማስረጃ ለምርጫ ቦርድ አልቀረበም፡፡ የምሠራው ለቦርዱ ነው፡፡ ቦርዱ ይህ ማስረጃ ቀርቦለት ጥያቄ ሲያቀርብልኝ ብቻ ምላሽ የምሰጥበት ይሆናል፤” በማለት የቀረበው ማስረጃ እውነተኛ ነው አይደለም ሳይሉ ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

ሌላ የኮሚቴው አባል አቶ ለገሠ ላንቃም የሲዳማ ዓርነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተወካይ ሲሆኑ፣ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ክልል የቦርባ ምርጫ ክልል ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሠሩ የቆዩት አቶ ዮሐንስ አብርሃም የተባሉ ግለሰብ፣ የደኢሕዴን (ኢሕአዴግ) አባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ ይገኝበታል፡፡ ብዙዎቹ ምርጫ አስፈጻሚዎች የፓርቲ አባላት መሆናቸውን ማሳያ ነው በማለት ነበር ያቀረቡት፡፡ ሌሎች ማስረጃዎች እንዳሏቸው በመጠቆም ጭምር፡፡ በምርጫ 2002 የነበረው ሁኔታ ምንም አለመቀየሩንና በተመሳሳይ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት አቶ ለገሠ፣ በተለይ “በወቅቱ የአርቤጎና ወረዳ ምርጫ ሥራን ለማሳካት የወጣ አጭር ማስፈጸሚያ ቼክ ሊስት” በሚለው ሰነድ፣ የክልሉ ገዥው ፓርቲ ከወረዳ ማዕከል እስከ ቀበሌ የሚሠሩ ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡ “ለልማት የፈጠርነውን የልማት ሠራዊት ወደ ምርጫ ተግባር አንድ ለአምስት በማዟዟር” በሚል የአንድ ሳምንት አደረጃጀት እንዴት ለቅስቀሳና ለምርጫ እንደሚውል፣ የሴቶችና የወጣቶችን የቀበሌ አደረጃጀቶች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ትምህርት ቤቶችንና የሃይማኖት ተቋማት እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የሚያብራራ ጽሑፍም አሳይተዋል፡፡ ይኼው ሰነድ ፓርቲውን ሳያወላውል የሚመርጠውን “A” አቋሙ ተለይቶ ያልታወቀውን “B” በማለት፣ ፈጽሞ የለየለትን ተቃዋሚ ደግሞ “C” እንደሰጠ ገልጸው፣ ወደ “A” ለማምጣት ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ካሉ በኋላ፣ የማይመርጡትን ምን እንደሚሠሩ “በዓይነ ቁራኛ” የቅርብ ክትትል ማድረግ ይጠይቃል በማለት አስረድተዋል፡፡

ሌሎች አባላትም ባለፈው ምርጫ ቤታቸው የተቃጠለባቸውን፣ ተገደሉ ያሉዋቸውን ሰዎችና ለእስር የተዳረጉትን ስም እየጠቀሱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይኼም እስካሁን በግልጽ  እየተሠራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

“መንግሥት አንድ ፓርቲ አንድ አገር ብሎ ያውጅና ቁርጣችንን እንወቅ፤” ያሉት አቶ ገብሩ ገብረማርያም፣ “ጥያቄያችን ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ ኢሕአዴጋዊያን ያልሆኑ ለምርጫ ቦርድ ይሥሩ የሚል ነው፤” በማለት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይኼንን የተበላሸ የምርጫ ሥርዓትና አምባገነንነት በመቃወም ከጐናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው አቤቱታዎችም ሆኑ ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉና ብዙዎችም በ2002 ምርጫ ማግስት በፍርድ ቤት ሳይቀር መልስ የተሰጠባቸው ናቸው ይላል፡፡ ቦርዱ አሁንም የቀረቡለትን ቅሬታዎች በዝርዝር ካየ በኋላ ማጣራቱን ገልጾ፣ ፓርቲዎቹ አላነጋገረንም የሚሉት ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡

ቦርዱ ሁሉንም ፓርቲዎች እኩል እያገለገለ እንደሚገኝ አስረድቶ፣ የሚተዳደርባቸው ደንቦችና መመርያዎች በፓርቲዎች ተሳትፎ የወጡ በመሆናቸው ወገንተኛ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም በማለት አስረድቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከማንም ፓርቲ ጋር የመወገን ዓላማ እንደሌለውና ሕጉም እንደማይፈቅድለት እየተናገረ ነው፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት “ምርጫ ለመድረክ ግንባርነት ዕውቅና ሰጠ” በሚል ርዕስ በወጣው ዜና “… መድረክን የፖለቲካ አጀንዳውንና የገንዘብ አቅሙን በመገምገም ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ያቀረበው ጥያቄ በቦርዱ ተቀባይነት ማግኘቱን ወይዘሮ የሺ ገልጸዋል፤” የሚለው ዓረፍተ ነገር ከቦርዱ ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በመሆኑ በዚህ መሠረት ተስተካክሎ እንዲነበብ እንጠይቃለን፡፡

ethiopianreporter.com

posted by Dawit Demelash

ሕገወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ የሚከለክል ጥብቅ ሕግሕገወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ የሚከለክል ጥብቅ ሕግ ሊወጣ ነው

   ሕገወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ የሚከለክል ጥብቅ ሕግሕገወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ የሚከለክል ጥብቅ ሕግ ሊወጣ ነው              


 ለፖለቲካ ተፅዕኖ የተጋለጡ ግለሰቦች ሀብት ምንጭ እንዲመረመር ያስገድዳል


በዮሐንስ አንበርብር

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን (መኒ ላውንድሪንግ) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚል ስያሜ የተሰጠው ረቂቅ አዋጅ በዚህ ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ ተመሳሳይ ስያሜ ያለውንና በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘውን ‹‹የመኒ ላውንድሪንግ›› እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚከላከል አዋጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሲሆን፣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 684 ሙሉ ለሙሉ ይሰረዛል፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ማለት ለወንጀል ፍሬ ምንጭ የሆነና ቢያንስ የአንድ ዓመት ቀላል እስራት ከሚያስቀጣ ወንጀል ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የተገናኘ ነው ሲል አዋጁ ያብራራል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም ሰው ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የንብረቱን ሕገወጥ ምንጭ ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን ንብረቱን የለወጠ ወይም ያስተላለፈ እንደሆነ፣ ከ10 እስከ 15 ዓመታት በሚደርስ እስራትና ከአንድ መቶ ሺሕ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

በተመሳሳይ ማንኛውም ሰው ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ንብረቱን፣ የንብረቱን ትክክለኛነት፣ ምንጩን፣ ቦታውን፣ ዝውውሩን ወይም የባለቤትነት መብቱን የደበቀ ወይም እንዳይታወቅ ያደረገ እንደሆነ ተመሳሳይ ቅጣት ይጣልበታል፡፡

ንብረቱን የተረከበ፣ ይዞታው ያደረገ ወይም የተጠቀመ እንደሆነም በተመሳሳይ ከ10 አስከ 15 ዓመተት እስራትና እስከ አንድ መቶ ሺሕ ብር ይቀጣል፡፡

በ2001 ዓ.ም. የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ የፀደቀ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ለፓርላማ የቀረበው ‹‹የመኒ ላውንድሪንግ›› ሕግ ግን ተጨማሪ ትርጉሞችን ለሽብርተኝነት ይሰጣል፡፡ በሥራ ላይ የሚገኘው የፀረ ሽብር አዋጅ የሽብርተኝነት ድርጊትን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የተፈጸመ አድርጐ ነው የሚቆጥረው፡፡ ይኼኛው ረቂቅ አዋጅ ግን የሽብርተኝነት ድርጊትን፤ ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላ ቦታ የተፈጸመ እ.ኤ.አ በ1999 ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል በወጣው ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን አባሪ ከሆኑት ስምምነቶች በአንዱ የተፈጻሚነት ወሰንና ትርጓሜዎች የሚሸፈን የወንጀል ድርጊት›› በማለት ዓለም አቀፍ ትርጓሜ ይሰጠዋል፡፡

የተጠቀሱትን ወንጀሎች ከመፈጸማቸው በፊት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ተቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው ረቂቅ አዋጁ፣ ለወንጀሉ ተጋላጭ የሆኑ የገንዘብ ተቋማትና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የንግድና የሙያ ሥራዎችን በዋናነት ቁጥጥር እንዲያደርጉ ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡ የገንዘብ ተቋማት ማለት ባንክ፣ መድን ሰጪ ኩባንያ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም፣ የፖስታ፣ የቁጠባ ድርጅት፣ የሐዋላ ድርጅት ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው ሕግ የሚሰየም ድርጅት ናቸው፡፡

የሪል ስቴት ወኪሎችና ደላሎች፣ የከበሩ ድንጋዮች ወይም የከበሩ ብረቶች ነጋዴዎች፣ ሪል ስቴት መግዛትና መሸጥ፣ የደንበኛውን ገንዘብ፣ የገንዘብ ሰነዶች የማስተዳደር፣ ራሳቸውን ችለው የሚሠሩ የሒሳብ ባለሙያዎች ጠበቆችና ሌሎችንም ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የንግድና የሙያ ሥራዎች በማለት ይሰይማቸዋል፡፡

በመሆኑም ገንዘብ ነክ የሆኑትም ሆኑ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ዘርፎች ከደንበኛ ጋር የንግድ ግንኙነት ከመመሥረታቸው ወይም ሒሳብ ከመክፈቸው በፊት፣ በአገር ውስጥ ወይም ወደ ውጭ በኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ለማስተላለፍ ከሚፈልግ ደንበኛ ጋር ግብይት ከመጀመሩ በፊት፣ ቀደም ሲል የተወሰደ ደንበኛ መረጃ ትክክለኛ ወይም ያልተሟላ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ሲፈጠር የደንበኛን ማንነት ለማወቅ የሚያስችሉ የጥንቃቄ ዕርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

ለፖለቲካ ተፅዕኖ ተጋለጭ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት ከመጀመራቸው በፊት የድርጅቱን የሥራ ኃላፊ ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው፣ እንዲሁም ከእንደዚህ ዓይነት ግለሰብ ጋር ግንኙነት ከተመሠረተ የሀብት ምንጮችን የመመርመር ግዴታ አለባቸው፡፡

ለፖለቲካ ተፅዕኖ የተጋለጠ ሰው ማለት በማንኛውም አገር ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ኃላፊነት የተሰጠው ወይም ተሰጥቶት የነበረ ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ሲሆን፣ የእዚህን ሰው ቤተሰብ አባል ወይም ከዚህ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለውን ማንኛውም ሰው ይጨምራል በማለት ረቂቅ ሕጉ ይተረጉመዋል፡፡

posted by Dawit Demelash

Friday, December 28, 2012

                                    በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

 ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
 ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
 የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
 40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
 ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።

 የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ።  ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።
 ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።
 ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።
 የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።
 ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ  ይታወሳል።
 በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

Sunday, December 23, 2012

“Neutral” Ethiopian Orthodox Tewahedo Churches in the Diaspora


“Neutral” Ethiopian Orthodox Tewahedo Churches (EOTCs) in the Diaspora: Is it not High Time to Take a Principled Stand? 

by Walle Engedayehu, Ph.D.
Introduction
St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, Nazret, Ethiopia
St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, Nazret, Ethiopia
In this brief commentary, the writer attempts to show the extent to which the recently-concluded peace and unity mediation of bringing the two EOTC Holy Synods into one was doomed from the start, and why it miserably failed despite the gallant effort of the mediators. Furthermore, the author posits that the time is now ripe for the “neutral” EOTCs to join their sister churches of the Holy Synod in exile in light of the failure of the peace mission. Using the facts that came to light during the course of the mediation, the writer makes an objective assessment of the issues affecting the status of unity within the EOTC, both in the Diaspora and in Ethiopia. Critical for this analysis are recent reports that have characterized both the haste with which the Home Synod is preparing to install a new Patriarch in Ethiopia, and the Ethiopian government’s continued policy of meddling in the affairs of the Church. This turn of event has come despite the seemingly promising pronouncement made by the representatives of the two squabbling Holy Synods in the aftermath of their peace and unity confab in Dallas, Texas.
The Context and Failure of the Mediation Mission
During the last three years, peace and unity mediators, consisting of concerned EOTC clergymen assisted by a few members of the laity, have made a genuine effort to bring the division between the two Holy Synods to a close, while aiming to restore the sanctity of the Church that has been severely damaged by the division. However, the three rounds of talks that took place in the U.S. did not substantively alter the status of the schism within the Church, which has profoundly bedeviled it for more than two decades. The major cause of the division, of course, was the Ethiopian regime’s installment of the late Abune Paulos in 1991 as the Patriarch of the EOTC illegally and in contravention of the Orthodox canon law. This was done by replacing Archbishop Abune Merkorios, the reigning Head of the Church at the time. The government’s action led subsequently to the establishment, in North America, of a Synod in exile led by the dethroned Patriarch, with a group of Archbishops and other clergymen supporting his cause. Since then, the Church has been in a state of paralysis, as EOTCs throughout the Diaspora became highly consumed with the crisis, and, in many cases, even embroiled with further division of their own, as they became either the supporters of the Synod in exile or of the Synod at home. Some among these churches also took a neutral stand, which has no canonical basis in Oriental Orthodoxy, to which all EOTCs are supposed to prescribe in theory as well as in practice.
The breakthrough that was expected of the meeting between the teams of the representatives of the two Holy Synods in Dallas in the first week of December 2012 never materialized. Nonetheless, the members of the Council of Peace and Unity of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church should still be applauded for their effort. In retrospect, however, their mission was simply based on what may be termed as “wishful thinking,” which in essence was an exaggerated sense of faith and trust in the role that mediation has played historically to resolve disputes in Ethiopia. At the same time, the mediators seemed to have failed in recognizing this fact: the prevalence in Ethiopia today, and for the most part during the last 21 years, of a regime that gives not even an inch of compromise on anything that has the potential of changing the status quo, which, in effect, means maintaining the supremacy of its minority rule over all other Ethiopian ethnic groups without any limit to its domination. In other words, the mediators were under the false illusion that the members of the Holy Synod in Ethiopia were free to determine the fate of the return of the exiled Patriarch without realizing that the regime has been the driving force, all along, in determining whether Patriarch Abune Merkorios was to be reinstated to his former position or not. It has become clearer to all keen observers now that the regime has its own Patriarch in mind. The fact that the Tigrean People Liberation Front (TPLF)-dominated government in Addis Ababa had made the decision to install a Patriarch of its choice, replacing the deceased Abune Paulos, a Tigrean, with another of the same ethnicity, was in itself the cause d’être for the failure of the peace and unity mediation.

Tuesday, December 4, 2012

UN: Noncompetitive Elections Weaken Rights Council


Newly Elected Countries Should Do More to Respect Rights
NOVEMBER 12, 2012
To call the vote in the General Assembly an ‘election’ gives this process way too much credit. Until there is real competition for seats in the Human Rights Council, its membership standards will remain more rhetoric than reality.
Peggy Hicks, global advocacy director
(New York) – Limited competition in elections for the United Nations Human Rights Council undermines membership standards set for the body by the UN General Assembly, Human Rights Watch, FORUM-ASIA, and the East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project said today. Although the General Assembly elected 18 countries to the Human Rights Council on November 12, 2012, only three faced challengers in their bids for a seat. 

“To call the vote in the General Assembly an ‘election’ gives this process way too much credit,” said Peggy Hicks, global advocacy director at Human Rights Watch. “Until there is real competition for seats in the Human Rights Council, its membership standards will remain more rhetoric than reality.” 

Seats on the Council are allotted by regional group. Only the Western Europe and Other Group (WEOG) put forward more candidates than the number of seats available. Germany, Greece, Ireland, Sweden, and the United States vied for three seats, which ultimately went to Germany, Ireland, and the US.

The other countries elected in the other regional groups are Côte d’Ivoire, Ethiopia, Gabon, Kenya, and Sierra Leone from the Africa Group; Japan, Kazakhstan, Pakistan, South Korea, and the United Arab Emirates (UAE) from the Asia Group; Estonia and Montenegro from the Eastern European Group; and Argentina, Brazil, and Venezuela from the Latin America and Caribbean Group.

Human Rights Council members are expected to “uphold the highest standards” of human rights and “fully cooperate” with the Council under General Assembly Resolution 60/251, which established the body. 

A group of nongovernmental organizations that work on improving the Human Rights Council had called on some of the countries seeking seats on the Council – EthiopiaPakistanthe UAE, andVenezuela – to take specific steps to improve their human rights records in light of their candidacies, given the extent of human rights concerns in those countries.

“States elected to the Human Rights Council should take real steps to address rights concerns at home before taking up their seats in Geneva next January,” said Yap Swee Seng, executive director of Asian Forum for Human Rights and Development (FORUM-ASIA). “Pakistan, for one, should show up at the Council having demonstrated tangible improvements in the prevention of discrimination and attacks against religious minorities, the protection of human rights defenders and journalists, and ending enforced disappearances.”

By using a rotation system that virtually guarantees seats to countries whether or not they meet membership standards, the African Group has effectively rejected the principle of competitive elections. Countries with stronger human rights records in Africa have been unwilling to challenge the African Group’s standing practice of putting forward “closed” slates.

When Kenya declared its candidacy for the Human Rights Council at the end of July, it briefly appeared that the African Group might buck this trend. However, Sudan withdrew its bid for a seat in September under pressure, leaving Africa again with a “closed slate” of five candidates for five seats.

“Year in and year out, the African Group’s  rotation system has virtually guaranteed the election of countries like Ethiopia that are serious human rights violators,” said Hassan Shire, executive director of the East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project (EHAHRDP). “Injecting a healthy dose of competition into the elections would make for a stronger membership and a more effective Human Rights Council.”

In past years, human rights organizations mounted successful campaigns against the candidacies ofBelarus (2007), Sri Lanka (2008), and Azerbaijan (2009), while Iran (2010) and Syria (2011) withdrew their candidacies under pressure from human rights groups. However, a number of states with repressive human rights records have been elected without facing competition, including Libya in 2010, as well as Cuba and Saudi Arabia in 2009.