Wednesday, September 25, 2013

የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች መሪያችንን ፓሊስ ቢያስርብንም የቅስቀሳ ስራቸውንን አጠናክረው ቀጥለናል ( ቪዲዬ )

መስከም 15/2006 ዓ/ም


ሰበር ዜና ከአዲስ አበባ፤ ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት አሰረ

september 25.2013

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩ የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፈታትወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ‹‹ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም፣ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ››ብለዋል፡፡
ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን ለቅቋቸዋል፡፡

 Posted By.Dawit Demelash


Tuesday, September 24, 2013

ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት

september 24.2013

ውሳኔው የሙርሲን “ቅርንጫፍ” ድርጅቶችንም ይጨምራል

m b


የካይሮው አስቸኳይ ጉዳዮች ፍርድቤት የሙስሊም ወንድማማችን እና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሙሉ ከማንኛውም እንቅስቃሴ አገደ፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጃዚራ እንደገለጸው ዕገዳው መሐመድ ሙርሲ ይመሩት የነበረውን እና ከሙስሊም ወንድማማች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለውን የእስላማዊው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ክንፍ የነጻነትና ፍትሕ ፓርቲንም ሊጨምር ይችላል፡፡
በሕዝብ ድምጽ ሥልጣን የተረከቡትን መሐመድ ሙርሲ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎችና ከፍተኛ አመራሮች አሁንም እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛል፡፡
ከፖሊስና፣ ከደኅንነትና ከመፈንቅለ መንግሥቱ ደጋፊዎች ጋር የሚደረገው ውዝግብ ደም አፋሳሽ ከመሆን አልፎ በወንድማማቾቹ እንቅስቃሴ ላይ “የአሸባሪነት” ታርጋ አስለጥፎበታል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፈው ወር በተከሰተው ግጭት የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎች ከ600 በላይ ክርስቲያኖችን መግደላቸውና ቤ/ክናትን ማቃጠላቸው እንደሚገባው አልተዘገበም በማለት አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ወቀሳ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡
የሰኞው ዕለት ዕገዳ በአሁኑ ጊዜ በወንድማማች ኅብረቱ ላይ የሚካሄደውን የተፋፋመ ወከባ በሕጋዊ መልኩ ያጠናክረዋል የሚል ግምት እየተሰጠበት ቢሆንም የግብጽ አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ሁኔታው እንደዚያ እንዳልሆነ ለአልጃዚራ ዘጋቢ ተናግሯል፡፡ “በአሁኑ ጊዜ እየተካሄዱ ያሉት የተቃውሞ ሰልፎች ሰላማዊ እስከሆኑ ድረስ መቀጠል ይችላሉ፤” ሆኖም የሙርሲን መነሳት በመቃወም አስመስለው የሽብር ተግባር ለመፈጸም የሚፈልጉ ሁሉ የትም ሊያመልጡ እንደማይችሉ አስጠንቅቋል፡፡
85ዓመታትን ያስቆጠረው እስላማዊው እንቅስቃሴ በ1946 በሕግ ታግዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ሕጋዊነቱን አግኝቶ ወደ ግብጽ ፖለቲካ ውስጥ ከገባ በኋላ የበርካታዎችን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ የዚህም ውጤት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በግብጽ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ የፓርላማውን አብላጫ ወንበርና የፕሬዚዳንትነቱን መንበር መቆጣጠር ችሏል፡፡
በካይሮው አስቸኳይ ጉዳዮች ፍርድቤት የተላለፈው ውሳኔ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበርን፣ በመያድ ስም የተመዘገቡት የሙስሊም ወንድማማች ድርጅቶችን እንዲሁም “ማንኛውም ከሙስሊም ወንድማማች ጋር የተገናኘ ድርጅት ወይም ንብረት ወይም የገንዘብ ዕርዳታ የሚያገኝ ተቋም” ላይ ዕገዳው የተላለፈበት መሆኑን ይናገራል፡፡ ሆኖም በወንድማማቹ ማኅበር ሥር ያሉትን ትምህርትቤቶችና ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች የማኅበራዊ ተቋማት ዕገዳው እንደሚመለከታቸው ግልጽ አልሆነም፡፡
ውሳኔውን አስመልክቶ የወንድማማች ማኅበሩ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኢብራሂም ሙኒር ዕገዳውን “አምባገነናዊ ውሳኔ” ያሉት ሲሆን በዚህም ውሳኔ እንኳን ቢሆን ማኅበሩ እንደማይጠፋ ተናግረዋል፡፡ ሲቀጥሉም “በአላህ ዕርዳታ እንጂ በአል-ሲሲ (የጦር ኃይሎች ዋና ኃላፊ የሆኑትን ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ሲሲን ማለታቸው ነው) የፍርድቤት ትዕዛዝ የሚፈርስ አይደለም” ብለዋል፡፡
በብያኔው ወቅት ያስቻሉት ዳኛ፤ የማኅበሩ “ገንዘብ፣ ንብረትና ህንጻዎች እንዲወረሱ” ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ በግብጽ ካቢኔ ገለልተኛ ኮሚቴ ተቋቁሞ ፍርድቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ አሁን የሚወረሰውን ሃብት እንዲያስተዳድርም ተወስኗል፡፡ ውሳኔውን ይግባኝ ማለት እንደሚቻል አብሮ ተጠቁሟል፡፡
ከአባላቱ በሚገኝ መዋጮ የሚተዳደረው የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር “አላህ ዓላማችን፤ ቁርዓን ሕጋችን፤ ነቢዩ መሪያችን፤ ጂሃድ መንገዳችን ናቸው፡፡” በሚሉ መሠረታዊ መመሪያዎች እንደሚተዳደር ይታወቃል፡፡ (ፎቶ: news.yahoo.com)

Sunday, September 22, 2013

ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ

Sunday, September 22, 2013

(ዘ-ሐበሻ) የጦር ሃይሎች የሎጂስቲክስ ዋና ሐላፊ የነበሩት ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ስዊድን መግባታቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባስተላለፈው መረጃ አመለከተ። አብርሃም ገዛኢ ከሃገር የወጡት በጡረታ ለተገለሉ በኋላ ነው  በማላት  ”የህወሓት ሃላፊዎችማ የያዙትን ይዘው ከሀገር እየወጡ ነው። የተቸገሩ ታችኞቹ ካድሬዎች ናቸው። እንደ አለቆቻቸው ወደ ዉጭ በመኮብለል የግል ደህንነታቸው መጠበቅ አይችሉም።” ሲል ትችቱን አስፍሯል።
ጄነራል ገዛኢ አበራ በሱዳን አቢ ግዛት ሰፍሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የመሩ ናቸው።

ከአንድ ዓመት በፊት የግንቦት 7 የኢትዮጵያ የጥናት ቡድን ባሰራጨው ምስጢራዊ መረጃ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን የጦር አለቆች ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዲያካብቱና ዘረፋ እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለተለያዩት የጦር መኮንኖች ሟቹ ጠ/ሚ/ር በ1989 ለአ/አበባ አስተዳደርና ለመከላከያ ሚ/ር መ/ቤት ለ25 የወያኔ የጦር መኮንኖች፣ ለእያንዳንዳቸው በሽልማት በአዲስ አበባ ውስጥ 500 ካሬ ሜትር 1ኛ ደረጃ መሬት እንዲሰጣቸው ትእዛዝ በሰጡት መሰረት ይህን መሬት የተቀበሉት ሌ/ጄነራል ገዛኢ አበራ በወር 170 ሺህ ብር የሚከራይ ቤት ቦሌ አካባቢ ሠርተው እንደሚያከራዩ ተጋልጦ ነበር።
ግንቦት 7 በአንድ ዓመት በፊት እንዳጋለጠው፦

የወያኔ የጦር መኮንኖች የአዲስ አበባን ከተማ በመዝረፍ ያከማቹት ሃብት


ተራ/ቁማእረግስምቦታው የሚገኝበትወርሃዊ ኪራይ በብርየዘውግ መግለጫ
1ሌ/ጄጻድቃን ገ/ትንሳኤቦሌ25,000 ከ4 ዓመት በፊትትግሬ
2ጄኔሳሞራ የኑስቦሌ28,000ትግሬ
3ሌ/ጄታደሰ ወረደቦሌ38,000ትግሬ
4ሌ/ጄገዛኢ Aበራቦሌ170.000ትግሬ
5ሌ/ጄብርሃነ ነጋሽቦሌ38,000ትግሬ
6ሌ/ጄሳእረ መኮንንቦሌ35,000ትግሬ
7ሌ/ጄአበባው ታደሰቦሌ1,2 ሚሊየን መሬቱን የሽጠአገው
8ሜ/ጄአበበ ተ/ሃይማኖትቦሌ2.5 ሚሊዮን መሬቱን የሽጠትግሬ
9ሜ/ጄአብርሃ ው/ገብርኤልቦሌ34,000ትግሬ
10ሜ/ጄዮሃንስ ገ/መስቀልቦሌ28,000ትግሬ
11ሜ/ጄአባ ዱላ ገመዳቦሌ45,000ትግሬ/ኦርሞ
12ሜ/ጄአለሙ አየለቦሌመሬቱን በ1.7 ሚሊዮን የሸጠአገው
13ሜ/ጄስዮም ሃጎስቦሌ28,000ትግሬ
14ሜ/ጄሃየሎም አርAያቦሌ?ትግሬ
15ሜ/ጄገ/እግዚአብሄር መብራቱቦሌ40,000ትግሬ
16ሜ/ጄባጫ ደበሌቦሌ20,000ኦሮሞ
17ብ/ጄታደሰ ጋውናቦሌመሬቱን 1.2 ሚሊዮን ብር የሽጠትግሬ
18ብ/ጄተክላይ አሽብርቦሌ60,000ትግሬ
19ብ/ጄፍስሃ ኪዳነቦሌ30,000ትግሬ
20ብ/ጄፓትሪስቦሌ34,000ትግሬ
21ብ/ጄመስፍን አማረቦሌ23,000ትግሬ
22ብ/ጄምግበ ሃይለቦሌ20,000ትግሬ
23ብ/ጄሃለፎም ቸንቶቦሌ22,000ትግሬ
24ኮ/ልታደስ ንጉሴቦሌ48,000ትግሬ
25ኮ/ልጸሃየ መንጁስቦሌመሬቱን 1.2 ሚሊዮን የሽጠትግሬ
ከእነዚህ የጦር አለቆች ውስጥ ባሁኑ ሰዓት በተራ ቁጥር 1, 8, እና 17 ከስርአቱ ውጭ ሲሆኑ፣ በተራ ቁጥር 14 እና 24 ያሉት ደግሞ በህይወት የሌሉ ናቸው።
ከላይ  ከተጠቀሰው  በተጨማሪ  ወያኔ  ለጦር  አለቆቹ  የሚሰጠው  ጥቅማ  ጥቅም  የሚከተለውን  ይመስላል።
  1. እነዚህ የጦር አለቆች በነጻ መሬት ወስደው ቤት በዘረፋ ከሰሩ በህዋላም በከተማው ውስጥ በመንግስት እጅ ከሚገኙ ምርጥ ቪላዎች መሃል ተመርጦ በተሰጣቸው ቤቶች ውስጥ በነጻ መኖር ቀጥለዋል።
  2. የውሃ የመብራት የስልክ ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ የወያኔ መንግስት ይከፍላል። እነዚህ ሞልቃቃና ቅምጥል የጦር አለቆች በሚኖሩበት ቪላ ውስጥ ብርዱን አልቻልንም በማለት ቤታችውን ሙሉ በሙሉ በውድ ምንጣፍ ማሽፈናቸው አልበቃ ብሉዋቸው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሃይል ፍጆታ የሚያስፈልጋችው የኤሌትሪክ የቤት ማሞቂያ መሳሪያዎች በየክፍሉ አስገጥመዋል። ምንጣፍ ለሚጠርገው የኤሌትሪክ መጥረጊያ ሆነ ለኤሌትሪክ ማሞቂያዎቹ የሚወጣው ክፍተኛ ወጪ፣ እንዲሁም እንዳሻቸው ለሚያፈሱት ውሃ በነጻ ተገልጋዮች እንዲሆኑ ተደርገዋል። በእዚህ ላይ ነጻ የሆነውን የሞባይልና የቤት ስልክ አገልገሎት ስንጨምርው በነጻ የሚያገኙት አገልግሎት በሽዎች የሚቆጠር ብር ይደርሳል።
  3. የጦር አለቆቹ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው፣ ከእዚህም አልፎ አባትና እናቶቻቸው ሳይቀሩ እሰከ ውጭ ሃገር ድረስ በመሄድ የሚሰጥ ነጻ ህክምና ያገኛሉ።
  4. ሁሉም የጦር አለቆች ተጨማሪ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በመቀሌ በባህር ዳር፣ አንዳንዶቹም በአ/አበባ ከተማ፣ በድጋሚ መሬት እንዲወስዱና እንዲገነቡ ተደርገዋል። ከእዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በዱከም በናዝሬትና በሌሎች ቦታዎች ለንግድና ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ ቦታዎች በመውሰድ ይህን መሬት በቀላሉ ለማያገኙ ሌላ የሃገሪቱ ዜጎች በከፍተኛ ዋጋ በመቸብቸብ ያካበቱት ሃብት ገደብ የሌለው ሆንዋል። ታደስ ወረደ፣ ወዲ እምቤቲ፣ ፍስሃ ኪዳነ፣ ገዛኢ አበራ የተባሉት የጦር አለቆች በዚህ ድርጊት በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መሃል ናችው።
  5. ይህ አልብቃ ብሎ እነዚህ የጦር አለቆች በመከላከያ ሚኒስትር በተያዘ ከፍተኛ የመስተንገዶ በጀት በመጠቀም የሚኖሩትን የቅንጦት ኑሮ ለተመለከተ ሃገራችን በምን አይነት የቀን ጅቦች እንደተወረረች ለማየት የሚያስችል ይሆናል። በ1992 ዓ/ም መከላከያ ሚኒስቴረ ለመስተንግዶ ብቻ የመደበው በጀት 280,000,000 (280 ሚሊዮን) ብር ነበር። በእዚሁ በ1992 ዓ/ም የሶማሊያ ክልል አመታዊ በጀት በተመሳሳይ 280 ሚሊዮን ብር እንደነበር ስናስታውስ፣ ይህ ለጦር አለቆቹ የተመደበው በጀት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መረዳት ይችላል የሚል እምነት አለን። በእዚህ የመስተንግዶ በጀት በመጠቀም የጦር አለቆቹ በየቀኑ ብፌ እያዘጋጁ ራሳቸውን ሲቀልቡ ከእዚህም አልፈው እንደጥንቶቹ መሳፍንት ግብር እንዲያበሉ፣ ውድ የሆኑ የውስኪ አይነቶች እንደ ውሃ እያፈሰሱ የሚኖሩበትን ሁኔታ አመቻችቶላቸዋል።
  6. በእዚህ የመስተንግዶ በጀት አማካይነት የወያኔ የጦር አለቆች ከትንሹ ሹካና ማንኪያ ጀምሮ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች የምግብ ጠረጴዛዎች አልጋዎችና ሌሎችም በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ታዋቂ ሃብታም ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያኖች የሚገልገሉባቸውን የቤት ቁሳቁሶች መግዛት ችለዋል። የጦር አለቆቹ እነዚህን የቤት ቁስቁሶች በየአመቱ የመቀየር መብት ስለተሰጣችው በእዚህ መብት ስም የሚያባክኑት የህዝብ ሃብት እጅግ በርካታ ነው።
  7. እያንዳንዱ የወያኔ የጦር አለቃ ከሁለት በላይ ውድና ዘመናዊ መኪናዎች ተሰጥቶታል። እነዚህ መኪናዎች በየአመቱ በአዲስ ሞዴል መኪናዎች ይተካሉ። የወያኔ ጄኔራል አንድ መኪና ለራሱ ሌላ መኪና ለሚስቱና ለልጆቹ በመውሰድ፣ እነዚህን መኪናዎች በግላቸው ያለምንም ወጪ እንዳሻቸው ከመገልገል አልፎ የኮንትሮባንድ እቃዎች ማመላለሻ አድርገው ይገለገሉባቸዋል። የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከድሬደዋ፣ ሃረር፣ ጅጅጋ አርቲሸክና ሞያሌ በማመላለሱ ስራ ተሰማርተው ከሚገኙት መሃል ጎልተው የሚታወቁት ሌ/ጄ ታደስ ወረደ፣ ሌ/ጄ ሳረ መኮንን፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ ሙሉጌታ በርሀ፣ ሜ/ጄ አለሙ አየለና ሌሎችም በርካታዎች ናቸው። በሌላ መንገድም የተሰጣቸውን መኪና፣ ከመንግስት ያለምንም ገደብ ከሚወስዱት ነጻ ነዳጅ ጋር እያከራዩ የሚጠቀሙ ጄነራሎች ብዙ ናቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት በርካታዎች መሃል ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብርን መጥቀስ ይቻላል። የመከላከያ ሚኒስቴር በ1993 አ/ም ብቻ በአንድ ግዜ ለመለስ የጦር አለቆች መገልገያ የሚሆኑ 300 ኮብራ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር አስገብተዋል። ኢትዮጵያን በመሰለ ደሃ ሃገር ውስጥ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአንድ ግዜ ብቻ ይህንን ያህል የውጭ ምንዛሪ ሲባክን አይቶ የማይደነግጥ ሃገር ወዳድ ዜጋ ይኖራል የሚል እምነት የለንም።
  8. ከእዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ስር ያሉ ወታደራዊ መደቦችና ክበቦች የወያኔ የጦር አለቆች የግል ንብረቶችና መገልገያዎች እንዲሆኑ ተደርገዋል። የጎልፍ ክበብ፣ መኮንኖች ክበብ፣ ደብረዘይት የአየር ሃይል ክበብና በየክልሉ የሚገኙ ትላልቅ ክበቦችን ጨምሮ እነዚህ የጦር መኮንኖች እንዳሻችው ያለምንም ወጪ የሚሰክሩባቸውና የሚዝናኑባቸው ናቸው። ወታደራዊ መደብሮቹ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲያስግቡ የተፈቀደላቸው በመሆናቸው ማንኛውም የውስጥ እቃዎቻቸውና ድርጅታቸው በልዩ በጀት የተሙዋሉላቸው በመሆናቸው ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አትራፊዎች ናቸው። ይህ ትርፍ፣ በየጦር ሰፈሩ የሚሸጠው ሳር፣ ዛፍ፣ አትክልት፣ ውዳቂ ብረታ ብረትና አላቂ እቃዎች፣ የሚረቡ የወተት ከብቶችና የሚደልቡ የስጋ በሬዎች በሙሉ የውያኔ የጦር አለቆች ተጨማሪ የግል ገቢዎች ምንጮች ናቸው።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7622

     Posted By.Dawit Demelash

የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በድምቀት ተካሄደ! (ፖሊስ ከ4 ኪሎ እንዳያልፉ አድርጓል)

september 22.2013

በአሁኑ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ ከሶሰት ወር በፊት የጠራውን ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል:: ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ ነበር የሰልፉ መድረሻ መሰቀል አደባባይ ቢሆንም ሕዝቡ አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ሰልፈኛውን ወደ መሰቀል አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ የፌድራል ፓሊስ ደግሞ በርቀት እየተመለከተ ነው::ሰልፈኞቹ ወደ ስማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዲመለስ ተደርጓል ሕዝቡ ግን ድምጹን ከማሰማት ወደኋላ አላለም::
ርዮት ትፈታ! ውብሽት ይፈታ! እሰክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡበከር ይፈታ! ፍትህን መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም!! ነፃነት እንፈልጋለን !! እኛ አሽባሪ አይደልንም! ፍትሕ እንፈልጋለን! የሙሰሊም ኮሚቴ ይፈቱ! ዜጎችን ማፈናቀል አግባብ አይደለም! አንለያይም! አንለያይም! ፍትህን ያሉ ቃልቲ ገቡ!! አሽባሪ አይደለንም! ፍትህ ናፈቀኝ! ድምፃችን ይሰማ!! ፍትሕ እያሉ ቃልቲ ገቡ! ውሽት ሰለቸን! ፍትህ ናፈቀን!
ሰማያዊ ፓርቲ ወያኔ የሚረግጡትን መሬትና የማይረግጡትን ምድር ወስኖ ሰልፈኛውን ከቦ እንዳሰቡት መስቀል አደባባይ መድረስና ከህዝብ መገናኘት እንዳይችሉ በማድረጉ ወደ ቢሮ በመመለስ የሰልፉን በሰላም መጠናቀቅ አብስረዋል፡፡ ይህ ትልቅ የአመራር ብቃትን፤ ሀላፊነትንና ለህዝብ ወገንተኝነትን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ወያኔዎች ሰልፉን ለማቆም ባትወስኑ ኖሮ ህዝብ ላይ መተኮስን እንደልማዳቸ ይፈፀሙት ነበር፡፡ብስለት የተሞላው አመራር በማድርጋችሁ አድናቆት ይገባችኀል፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ህዝብ ያሸንፋል!









Friday, September 20, 2013

አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት! "ህይወት እንደዋዛ"

the pic


ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።
ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል።
የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ በተከታታይ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህልፈተ ህይወት መሰማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደንግጦል።
በተለይ ትላንት ማለዳ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 አካባቢ አስከሬንዋ ጊዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ህመሙ አገርሽቶባት ስታቃስት «ጣዕረሞት ስታሰማ»፡ እንደ ነበር የሚናገሩ ወገኖች ዲፕሎማቱ ትብብር እንዲያደርጉላት ስልክ ቢደወልላቸውም በወቅቱ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወጣቷ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉን ይገልጻሉ።
ሟች እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዲፕሎማቱ በኤምባሲው ሃላፊነት ወደ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመር እና ህይወቷን ከሞት መታደግ ሲችሉ ባሳዩት ግዴለሽነት እና ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው አሰራር የወጣቷ ህይወት እዚህ በረሃ ላይ ቀርቷል ብለዋል። ወጣቷን ወደዚህ ግዜያዊ መጠለያ ግቢ ዲፕሎማቱ ከአሰሪዎችዋ ተረክበው ሲያመጧት “ሃኪም ቤት ውሰዱኝ ህይወቴን አጣሁ!! አድኑኝ ኧረ የወገን ያለህ!! ኧረ ያህገር ያለህ!! አናቴ ድረሺልኝ!!” እያለች ትማጸናቸው እንደነበረ በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። የወጣቷ የሰውነት አቋም እና አጠቃላይ ሁኔታ ያዩ አንዳንድ ታዛቢዎች በውስጥዋ የቆየ በሽታ እንደሌለባት እና ወጣቷ አንጀቴ ተቃጠለ ውሃ ውሃ ስትል እንደነበር እና ሃኪም ቤት ውሰዱኝ እያለች ልብ በሚነካ ሁኔታ ስትማፀን የታዘቡ ወገኖች ምናልባትም ከምግብ ጋር የተቀልላቀለ መርዝ ነክ ነገር በልታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ያጎላሉ።
በማያያዝ ዲፕሎማቱ ወጣቷን ከአሰሪዎቾ ተቀበለው ወደ መጠለያ ሲያመጧት ለአመታት የደከመኩበትን የወር ደሞዜን እባካቹ ከአስሪዪ ላይ ተቀበሉልኝ እያለች ትጮህ እንደ ነበረ እና ወደ መጨረሻ አካባቢ እየደከመች ስትመጣ ሟች በሚያሳዝን አንደበት ሆስፒታል በር ላይ ወስዳችሁ ጣሉኝ፡ የወግን ያለህ እያለች እስከ ዕለት ሞቷ ታለቅስ እንደ ነበረ እና ይህንንም ተማጽኖ ዲፕሎማቶቹ «የመንፈስ ጭንቀት ነው» ፡ «ስራ በዝቷባት ነው» ፡«ሃገር መግባት ፈልጋ ነው» ስታጭበረብር ነው» ወዘተ . . . በሚል ፌዝ በጭካኔ ሌሎችን ሰላም ትነሳለች በሚል ለብቻዋ ኮንቴነር ውስጥ፡ አስገብተው እንደቆለፉባት እና በነጋታው ወጣቷ ሞታ ማደሯን አንዳንድ የኮሚኒቲው አባላት እንባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል ።
ይህ በዚህ እንዳለ ትላንት 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ አካባቢ በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ የወጣቷ አስከሬን በሳውዲ የማዘጋጃ ሰራተኞች ተነስቶ ወደ አልታወቀ ስፍራ እንደተወሰደ እነዚህ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል።
(Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል የላኩልን – ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ)
    Posted Dawit Demelash

ወያኔም በስደት




መቼም እንደወያኔ አገዛዝ ስደት የሰፈነበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም፥፥ ምሁራን፥ ተማሪ፥ ሰራተኛ፥ የሃይማኖት አባቶች፥ ገበሬው፥ ወጣት ወንድሞችና እህቶች፥ ብቻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሰዷል፥ አሁንም በመሰደድላይ ነው፥፥ ብዛት ያላቸው ወንድሞችና እህቶቻችንም ከተሰደዱ በኋላም ወይ መንገድ ላይ ወይ ሰው ሃገር ከገቡ በኌላ ህይወታቸውን ያጣሉ ይሰቃያሉ፥፥
በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከገዛ ሃገራቸው በወያኔ/ህወሃት አፋኝ ስርአት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፥የዲሞክራሲና የነፃነት እጦት፥ የዘረኝነት መስፋፋት፥ የህግ የበላይነት አለመከበር፥ የኑሮው ከአቅም በላይ መሆንና በሌሎችም በበርካታ ምክንያቶች በግፍ ከገዛ ሃገራቸው ተሰደው ከወጡ በኋላ በሚኖሩበትን ሃገር የመናገር የመፃፍና ሃሳባቸውንበነፃ የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀም፥ የወያኔ መንግስትንእኩይ ተግባር ለማጋለጥ ይሞከራል፥፥ ይሁንና ይህ እንቅስቃሴ የወያኔ ማህበርን እንቅልፍ እንደሚነሳ ደሞ አያጠያይቅም፥፥
በዚህም ምክንያት ሃገር ቤት ሃሳባቸውን በድፍረት መግለፅ የቻሉት በሙሉ ማለት ይቻላል አሸባሪ የሚል ቅፅል ስም ተለጥፎባቸው በየእስር ቤቱ በማጎር ሰዎችን ለማፈን ቢሞከርም ኢትዮጵያ ደሞሁል ግዜ ሰው አላትና ተተኪው ብቅ ማለቱ አቀረም፥፥ ወደውጩ ልመለስና የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ምን ሊያረጉት ይችላሉ አይሉኝም፥
ይኅውልዎት፥ አንድ ነገር ላስታውስዎት፥ በኦክቶበር 09-10, 2011 ዓ/ም አቶ መለስ ዜናዊ ወደ ኦስሎ/ኖርዎይ Energy for all በሚል ስያሜ በተጠራው አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ እሳቸውን ጨምሮ የብዙ ሃገራት መሪዎች ተገኝተው ነበር፥፥ እናም ከዛ ሁሉ የአለም መሪውስጥ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ብቻ ነበር የተቃውሞ ሰልፍ የተነሳው፥፥ እናም በኖርዎይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ተየቌቸው፥ ለምንድነው ይሄ ሁሉ የአለም መንገስት ተቃውሞ ሳይደርስበት በርስዎ ላይ ብቻ ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ ብሎ ቢጠይቃቸው፥ እሳቸውም አሉ ተዋቸው ይሄ ሁሉ የምታየው የሚንጫጫው ህዝብ እንደጉም በኖ ይጠፋል ብለውት እርፍ፥፥ የሚገርመው ግን እሳቸው እራሳቸው ይህን ባሉ በአመታቸው ብን ብለው ጠፉ፥፥
ዞሮ ዞሮ በዚህ ተቃውሞ ሰልፈኛ እንቅልፍ ያጡት እሳቸውና ተባባሪዎቻቸው እንደጉም በነው ይጠፋሉብለው በዛቱት መሰረት ስደተኛውን ፀጥ ሊያረገው ይችላል ብለው ባሰቡት መሰረት ከኖርዎይ መንግስት ጋር ስደተኞችን ወዳገራቸው መመለስ የሚያስችል ስምምነት አርገው እንደጉም ለመበታተን ሞከሩ፥፣
እንደኔ አመለካከት ለምሳሌ በኖርዎይ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማብረድ በተለመደው የማስፈራራት የዛቻ መንፈስ ሳይሆን አይቀርም፥
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን በኖርዎይ ሃገር ባለው የመናገር፥ የመሰብሰብና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጠቀም የወያኔን ስራ ባላቸው አቅም ሁሉ በመዋጋት ላይ ይገኛሉ፥፥ በዚህም ምክንያት ወያኔ ደሞ ማን ምን እንደሆነ ምን እንደሚያረግ በመከታተል 24 ሰዓት ስራ ይሰራል፥፥ ይህም ምክንያት ነው ሰዎች ወዳገራቸው ቢመለሱ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው የሚያስብለው፥፥
ለመጋለጣቸው ምክንያት የሚሆነው ደሞ ወያኔ ኢትዮጵያውያን በተሰደዱበት ሃገርም ጭምር ድረስ የተቃዋሚ ሃይሎችን እንቅስቃሴ በመከታተል የተለያዩ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚገለገልባቸው የራሱ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች በማስገባት ስደተኞችን የመሰለል ስራ ከመስራቱም በላይ ማስፈራራት፥ ዛቻ፥ ብዙ ነገር ይሞከራል፥፥
ለምሳሌ አንድ በቅርብ ቀን ከኖርዌጂያን የስለላ መስሪያ ቤት ማለትም PST /Police security service/ Acting Head of Section for counter-intelligence in the Police Security Service የሆኑት Mr. Ole Børresen በ 01.08.2013 በኖርዎይ ከሚገኝ NRK ከተባለ የሃገሪቱ ዋና የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉትቃለ ምልልስ ላይ በግልፅ ተናግረዋል፥፥
Mr. Ole Børresen እንደሚሉት በኖርዎይ ውስጥ ከ5 እስከ 10 የሚሆኑ ሃገሮች ስደተኞችን በመሰለል ስራ ላይ እንደተሰማሩ መረጃው አላቸው፥፥ እሳቸው እንደሚሉት አገር ቤት በሚገኙ በስደተኛ ቤተሰቦች ላይ የተለያዩ ማስፈራራት፥ እንግልት፥ ድብደባና ዛቻ በአምባገነን መሪዎች የሚደረጉ ዋነኛ መሳሪያዎች ናቸው፥፥
Mr. Ole በመቀጠልም ሲናገሩ PST ላለፉት አመታቶች በነዚህ ስደተኞችን በመሰለል ዙሪያ ብዙ ክሶችና አቤቱታዎች እንደደረሳቸውና በስደተኛ ቤተሰቦች ላይም በደረሱ ችግሮች መረጃ እንዳላቸው ለNRK ገልፀዋል፥፥ አክለውም እነዚህ ሁኔታዎች የሚከሰቱትም ከኖርዎይ ውጭ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ለመግባት አስቸጋሪ እንደሚያረገው ተናግረዋል፥፥
Mr. Ole የትኞቹ የስደተኛ ግሩፖች ናቸው የበለጠ ለዚህ ችግር በኖርዎይ ውስጥ የተጋለጡት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲያብራሩ፥ ሲመልሱ በዋነኝነት በተቃውሞ እንቅስቃሴ አክቲቭ ሆነው እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ማለትም መንግስታቸውን በተለያየ መንገድ የሚቃወሙትንና በተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚሳተፉ የበለጠ የተጠቁ ናቸው ብለዋል፥፥
ዋናው ነጥብ እነዚህ አምባገነን መሪዎች ከዚህ ለማግኘት የሚሞክሩት ዋነኛው ውጤት በውጭ ሃገር የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶችን በፀጥታ እንዲቀመጡ በማረግ እንዲሁም በሃገር ቤት በሚገኙ የስደተኛ በተሰቦችም ላይ ጫና ማረግ በተጨማሪ የሚጠቀሙዋቸው ዘዴዎች መካከል ሲሆኑ እነዚህ መንግስታት ስራቸውን ለማስፈፀም ከሚጠቀሙዋቸው ዘዴዎች መካከል፣
• የራሳቸውን የስለላ ሰዎች ወደ ኖርዎይ በመላክ መሰለል
• የራሳቸው ዜጎች ላይ ጫና በማረግ ወደዚህ ስራ ማስገባት
• ስደተኞችን በየካምፑ መመልመል ወይንም የራሳቸውን ሰላዮች ስደተኛ አስመስሎ በመላክ
• የስደተኞችን ኮምፒዩተሮች ሃክ በማረግ መረጃዎችን መሰብሰብ
• በየኢምባሲዎቻቸው ያሉ ሰራተኞችን ለስለላ መጠቀምን ያካትታል፥ በመሆኑም ባለፉት አመታት በዚህ ዙሪያ በዛ ባሉ አቤቱታዎችና ክሶች ላይ እንደመስራታችን መጠን በኖርዎይ ውስጥ ያለማቋረጥ እየተከናወነ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል ብለዋል፥፥
በመጨረሻም ስደተኛን በኖርዎይ ውስጥ የሚሰልሉት ሃገራት እነማናቸው ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሙሉ መረጃ ለመስጠት ፍቃድ ባያሳዩም ግን ኢትዮጵያ፥ ኤሪትሪያና ኢራን በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ግዜ ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ እንደሆኑ ገልፀዋል፥፥
በመቀጠልም እስካሁን ኖርዎይ ውስጥ ሆኖ ሲሰል የተያዘ 1 ሰው ብቻ እንደሆነ ገልፀው የሱዳን ዜግነት ያለው የ 38 አመት ሰው እንደሆነ ገልፀው ስደተኞችን የሚሰልሉ ግለሰቦችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልፀው ለዚህ የተጋለጡ ስደተኞችም በሃገራቸው ውስጥ ባለው የህግ ከለላ እምነት ከማጣታቸው የተነሳና መጥፎ ኤክስፒርያንስ የተነሳ እዚህ ሃገር ወደ ፖሊስ በመሄድ ፖሊስን ኢንፎርሜሽን ለመስጠት አይደፍሩም ብለዋል፥፥ ይህንንም በመረዳት PST በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰዎች በምን አይነት መንገድ ሰላዮችን ሊያቁ እንደሚችሉና እንዴት ባገራቸው መንግስታት እንደሚሰለሉ ምክር መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል፥፥ በሌላ በኩልም ቢሮአቸው ግለሰቦችንም በግል በመጥራት አንዳንድ የሚሰሩ ስራዎች በኖርዎይ ውስጥ ህገወጥ እንደሆኑ እንደሚናገሩም አስገንዝበዋል፥፥ ይህም የሚደረግበት ምክንያት አንዳንድ ሰዎች የሚሄዱት አካሄድ የሃገራችንን ህግ ካለመረዳት ነው ከሚል ሃሳብ የመነጨ እንደሆነ ተናግረዋል፥፥
ይህም ማለት ግለሰቦቹ ከሃገራቸው መንግስት እዚህ ያለውን እንቅስቃሴ መረጃ እንዲሰጡ የታዘዙ ቢሆንም ግን ደግሞ ይህን ስራ በኖርዎይ ውስጥ ሆኖ ማከናዎን ስለሚያስከትለው ህግና ቅጣት እንነግራቸዋለን ብለዋል፥፥ ይሁን እንጂ የተጣራ መረጃ በተገኘበት ግዜም ኖርዎይ በቀጥታ ለሚመለከተው ሃገር አቤቱታ ወይንም ማስጠንቀቂያ ትልካለች ብለዋል፥፥
ይሁን እንጂ እነዚህ የምናረጋቸው የምክርና የኢንፎርሜሽን አገልግሎቶች በተወሰነ መልኩ ውጤት ቢያሳዩም PST በግለሰቦች ላይ ለሚደርሰው በሲኪዩሪቲ ጉዳይ ላይ የስደተኞችን መሰለል ጉዳይ በተመለከተ አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል፥፥
ስለላው ስደተኞችን በመሰለል ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ባገር ቤት የሚገኙ የስደተኞች በተሰቦች ላይ እንግልትና ጫና በአምባገነን መንግስታት ይፈፀማል በማለት ተናግረዋል፥፥
ለማንኛውም እንበርታ፥ እንጠንቀቅ፥ ለነፃነታችን ሃገራችንም ላይ ሆነ በተሰደድንበት ሃገር እንታገል፥ የነፃነት ቀን ቅርብ ነው፥፥
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

september 20.2013
ጌድዬን ከኖርዎይ

Wednesday, September 18, 2013

4 የኢትዬጵያ አየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ


መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን  ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው ናቸው።
በ1998 ኣም በሶማሊያ ከእስላማዊ  ህብረት ሀይሎች ጋር በተደረገው ውጊያ ተሰታፊ እንዲሁም በዳርፉር የሰራዊት ማስከበር ተልእኮ የዘመቱት እነዚህ የበረራ ባለሙያዎች ሁለቱ ለከፍተኛ ትምህርት ከተላኩት ቻይና ተመልሰው  ትግሉን መቀላቀላቸውን ሲገልጹ ሁለቱ ደግሞ ከሳምንት በፊት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ሀይል ምድብ ተነስተው ስርአቱን መክዳታቸው ተመልክቷል።
በቅርቡ የመረጃ መኮንን የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ግንቦት7ትን መቀላቀሉን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወጣቶች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አንዳንድ እግረኛ የሰራዊት አባላትም ድርጅቱን እየተቀላቀሉና ለመቀላቀልም ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
    Posted By.Dawit Demelash

ታላቅ የሕዝባዊ ውይይት መድረክ (ግንቦት7)

September 18, 2013

የወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታና ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል ይዞታ ላይ ገለፃ ይደረጋል::ስፊ የጥያቄና መልስ ክፍለግዜ ይኖረናል::Ginbot 7 logo
Ethiopia G7 1
Ethiopia G7 2

Monday, September 16, 2013

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ  94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር  ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ  ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የ12 ሚሊዮን ብር እና የ34 ሚሊዮን ብር ህገወጥ ብድርን እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት በቂ የሰነድ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ቢገለጽም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቱዋል፡፡
በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከመመሪያና አሰራር ውጪ ለግለሰቦች የስልክ መስመር እንዲዘረጋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ስልክ በማስደወል በመስሪያ ቤቱ ላይ 14 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱን የተመለከተ  ሁለት ምርመራዎች ተጠናቀው በክስ ሂደት ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሚፈጥሩት ጫና ክሱ እየተጓተተ ነው።
በትግራይ ክልል የሚገኘው በሼባ የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ መብራት ሀይል ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ  65 ሚሊዮን 300 ሺ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጣርቶ ለወሳኝ አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
በተመሳሳይ በኦሮምያ ክልል በደብረዘይት የሚገኝ የግል የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረሱ ምርመራው አጣርቶ የፀረ ሙስና ኮሚሺን ቢልክም የፍትህ መጓተት ታይቶበታል።
በመብራት ሀይል አላግባብ በ 248 ሚሊዮን 900 ሺ ብር የተፈጸመ የ4 ሺ4 መቶ 70 ትራንስፎርመሮች አለም አቀፍ ግዢ በሁለት የምርመራ መዝገቦች የተጣራ ቢሆንም ውሳኔ አልተሰጠበትም።
ንብረቱ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኑፋክቸሪንግ ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የሆነ ግምቱ  4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ የብርና የነሃስ ሜዳልያ ከግምጃ ቤት በመጥፋቱ ተመርምሮ የተረጋገጠ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
በተንዳሆ ፕሮጀክት ከግብር ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ     ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ተመስርቷል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሊዝ እንዲስተናገድ የተወሰነለትን የመኖሪያ ቤት ኅ/ሥ/ማ ያለ ሊዝ በማስተናገድ የተሰጠ 30 ሺ 3 መቶ 32 ካ/ሜ ቦታ ምርመራ ተጠናቆ ክስ የተመሰረተ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
ለብሄራዊ ባንክ በሽያጭ ከሚቀርብ ወርቅ ጋር በተያያዘ የባንኩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች በመመሳጠር 63 ሚሊዮን ብር በመመዝበር አስቀድሞ ተከሰው የነበሩ አሁን ጥፋተኛ ተብለው ጉዳዩ ለቅጣት ውሳኔ ተቀጥሯል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ በልማት ተነሺዎች ስም ከመመሪያ ውጪ ግምቱ 13 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ የሆነ 2, ሺ 1 መቶ 45 ካ/ሜትር ትርፍ መሬት አላግባብ በተሰጣቸው እና ከካሳ ክፍያም ጋር በተያያዘ  5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር በትርፍ የተከፈላቸው ግለሰቦች ጉዳይ፤ በኢትዮጵያ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሀዋሳ ቅርንጫፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሃኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተደረገ የ100 ሚሊዮን የእህል ግዢ ጨረታ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑ በተደረገው ምርመራ በመረጋገጡ ጨረታው እንዲሰረዝና በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት የተደረገባቸው በጥቅሉ ከህዝብ በግብር የተሰበሰበ በርካታ ገንዘብ በአንድም በሌላ መልኩ በከፍተኛ አመራሮች ተጽእኖ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ተጣርቶ ለፍርድ ሰጭው አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ቀርተዋል፡፡
ከ 7 መቶ ሚሊዮን  ብር በላይ የመዘበሩ የስራ ሃፊዎች አልተቀጡም ሲል ከፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ አሀዙ በ2005 የተፈጸመውን ሙስና አላካተተም።
ባለፉት 22 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት የተፈጸሙና በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተጣራ በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ይገመታል።
 Posted By.Dawit Demelash

Friday, September 13, 2013

Ethiopian journalist on hunger strike

International Women’s Media Foundation calls for reinstatement of visitation privileges
September 13, 2013 — As stories about the political crisis in Cairo have been dominating the news from Egypt, there has been limited coverage on a brewing international conflict between Egypt and Ethiopia – two countries that do not share a border but are indivisibly connected by the Nile, the world’s longest river.
Amid works to construct a giant hydro-electric dam, and much to the anger of the Egyptian government, Ethiopia has started diverting the Blue Nile, a tributary of the Nile, prompting a furious debate about if and how the “Great Ethiopian Renaissance Dam” will affect Egypt’s water security.
While there may not be a definite answer anytime soon on whether this dam will have any impact on water security in Egypt, there is no doubt that it has already negatively impacted press freedom in Ethiopia. Earlier this summer, for instance, the Committee to Protect Journalists reported that Ethiopian officials arrested a reporter seeking to interview people evicted from their homes in the region where the contentious hydro-electric dam is being built. More notable, however, was the arrest of Ethiopian columnist Reeyot Alemu more than two years ago.
A critic of the government writing for the now-defunct newspaper Feteh, Alemu had raised questions about the funding and merits of the dam shortly before she was arrested on bogus terrorism charges and sentenced to 14 years in jail.
Although two of the three terrorism charges against her were later dropped on appeal and her sentence reduced to five years, Alemu continues to suffer from her government’s efforts to silence dissenting voices and scare independent journalists into self-censorship. A tumor in Alemu’s breast remains untreated as she is denied access to medical care, and threats of solitary confinement linger over her every move in Ethiopia’s notoriously ill-maintained Kaliti prison.
While the Ethiopian leadership insists on the country’s adherence to the rule of law, there seems to be little doubt in the international community that Alemu’s arrest and conviction was politically motivated: The International Women’s Media Foundation honored Alemu with its Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) recognized her “commitment to freedom of expression” with its Guillermo Cano World Press Freedom Prize. In July, a delegation of the European Parliament’s Subcommittee on Human Rights, scheduled to meet with Alemu, was denied access to Kaliti prison, prompting questions by members of the European Parliament over Ethiopia’s commitment to human rights.
According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia jailed more journalists than any other country in Africa in 2012 (with the exception of Eritrea), and 45 Ethiopian journalists have been forced into exile since 2008. Swedish journalist Martin Schibbye who gained first-hand experience with Ethiopia’s crackdown on press freedom after being arrested there himself in June 2011, delivers a damning verdict on the rule of law in Ethiopia: “There is no such thing as an independent justice system, it’s completely politicized. If the order comes from the federal level that Reeyot is to let go, she will be free. But if they feel that they gain more from keeping her in prison, they will keep her locked up. This decision lies entirely in the hands of the Ethiopian government,” he said.
But the Ethiopian authorities seem to be determined to keep Alemu silenced. Earlier this week, as Ethiopians were preparing for their New Year’s celebration, prison officials denied Alemu visits from anyone but her parents. It remains unclear whether the decision to keep her separated from her friends, siblings, and fiance is in response to an open letter Alemu wrote in August, criticizing Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation, but it appears to be unlikely that the timing of the new restrictions is coincidence.
Protesting the prison’s decision to deny her visits from friends and relatives, Alemu has gone on hunger strike. The IWMF is deeply concerned about Alemu’s health and well-being, and calls on the decision-makers at Kaliti prison to re-instate Alemu’s full visitation privileges immediately.
   
  Posted By.Dawit Demelash

Thursday, September 12, 2013

” ርዕዮቶች ብታልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “


 የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ
ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡
ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡
ዛሬ በዐል ስለሆነ ምን አልባት ሊያስገቡን ይችላሉ ብለን ነበር ሁላችንም ወደ ቃሊቲ የሔድነዉ፡፡ የሆነዉ ግን በጣም አሳዛኝ ነበር፡፡ በር ላይ ደርሰን ስንጠይቅ (ቤተሰቦችዋና ጓደኞችዋ) አሚናዘር ላስፈቅድ ብላ በር ላይ ያለችዉ ፖሊስ ወደ ዉሰጥ ገባች ትንሽ ቆየት ብላ ተመለሰችና አባትና እናት ብቻ ነዉ የሚገቡት ያልችዉ አሚናዘር ብላ እኔና ስለሺ ጓደኞችዋንም ጨምሮ መግባት እንደማንችል ተነገረን የዚን ጊዜ አባታችን “የእነሱን ህገወጥ ስራ እንደማይተባበር እና እኛ ተከልክለን እሱ እንደማይገባ ነገራቸዉ” እናታችን እንድትገባና ሁኔታዋን አይታ እንድትነግረን የያዝነዉን ምግብ ይዛ ገባች፡፡ በጣም በሀዘን የያዘችዉን ምግብ ይዛ ተመለሰች ምነዉ ስንላት ርዕዮት የርሃብ አድማ እንዳደረገች እና ቤተሰብ የማይገባላት ከሆነ አድማዉን እንደምትቀጥል እንደነገረቻት እናም በጣም ያስደነገጠንን ዜና ነገረችን “አጠገቡዋ ኮ/ል ሐይማኖት (የ ገብሩዋድ ባለቤት) እንዳመጡዋትና የርዕዮትን አልጋ በማስጠጋት እሱዋነ ከጎንዋ አድረገዋት እሱዋም ሙሉ ለሊት እየሰደበቻትና እየዛተች እንዳሳደረቻት ህይወትዋ አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ነገር ቢፈጠር በህመም እንዳልሆነ እንድታዉቁት እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ” የሚል መልእክት ነገረችን፡፡
አስረዉ ሲያበቁ እንኳን ምነዉ ቢተዋት? በዚህ ከቀጠለ እህቴን ነገ ለማግኘቴ ምን ያህል እርግጠኛ እንደምሆን አላዉቅም!!!!!
ሉሉዬ የሚታልፊበት መከራሽን አምላክ ይይልሽ!!!!
* ይህ ጽሁፍ በተለያዩ የፌስ ቡክ አድራሻዎች የተስተናገደ አሳዛኝ ማስታወሻ ነው። ጽሁፉን በዋናነት ያተመ ትክክለኛ ምንጭ ካለ ለማረም ዝግጁ ነን። ጽሁፉን እንድናስተናግድ ለላክልን ደንበኛችን እናመሰግናለን። ርዕየትና ሌሎች ውድ ወገኖቻችንን እናስባቸው!


    Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, September 11, 2013

በህገ-ወጥ ርምጃ ሕጋዊው ሰላማዊ ሰልፋችን አይቀለበስም!!!

September 11.2013

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ላለፉት ሦስት ወራት ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል በመላ ኢትዮጵያ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅንካ፣ በፍቼና አዳማ ከተሞች ሕዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ያጋጠሙ የገዥው ፓርቲ እንቅፋቶችን እየተራመደ በተሳካ ሁኔታ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችንም አከናውኗል፡፡ ፓርቲያችን የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ለማጠናቀቅም በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም የሚካሄደውን የመጀመሪያው ምዕራፍ የማጠቃለያ የተቃውሞ ሰልፍ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለማካሄድ ወስኖ ይህንንም ውሳኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማሳወቅ ሰፊ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡ በዚህ ሂደትም አመራሩና የፓቲው አባላት በከፈሉት መስዋዕትነትና ግፊት ህዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰልፎች እንደጅምር አበረታች ናቸው ብለን ብናምንም የህዝቦች መብት ሳይሸራረፍ እስከሚከበር ድረስ፣ ነፃነታችን እስከሚረጋገጥ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ በአዲስ አበባ የምናካሂደውን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን ከማሳወቅ ጀምሮ የገጠመን ውጣ ውረድና ማደናቀፍ ትልቋ ከተማችን ሃላፊነት በማይሰማቸው አስተዳዳሪዎች የምትመራ መሆኑንም ያረጋገጥንበት አጋጣሚም ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ላለመቀበል ከማስቸገርም በላይ የቢሮ ሓላፊዎችና ሌሎች በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስልጠና፣ ስብሰባ፣ እንግዳ ለመቀበልና ሌሎችን ተልካሻ ምክንያቶች በመደርደር ለማደናቀፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ ደብዳቤ ፈርሞ መቀበል የማይችል አካል ሃላፊነት የማይሰማው ነው ከማለትም ባለፈ በህግ የሚያስጠይቅ ሀላፊነትን ባግባቡ አለመወጣትን የሚያመለክት ድርጊት ነው፡፡ ከንቲባውና የከንቲባው ፅ/ቤትም በአግባቡ ካለማስተናገድም በላይ የአንድነትን ከፍተኛ አመራሮች (ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራ ጣሴን) ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ ስለሰላማዊ ሰልፉ እንደራደር በማለት አመላልሰዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ በቂ ቢሆንም ከከንቲባው ጋር መነጋገር ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ለፖሊስ በሚሰጥ የውስጥ መመሪያ እየተካሄደ ያለው ማደናቀፍ እንዲቆም፣ መስተዳድሩ መመሪያ ብሎ ያወጣውና ለወረቀት ብተና፣ ፖስተር ልጠፋ፣ የመኪና ላይ ቅስቀሳና ፔቲሽን ለማስፈረም ልዩ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የሚያዝ፤ ይህ ካሆነ ፖሊስ ርምጃ እንዲወስድ የሚያደርገውን ሕገ-መንግስት የሚጥስ መመሪያ በተመለከተ ነበር፡፡ ምንግዜም ህጋዊ መስመር ተከትሎ ከማስተዳደር ይልቅ በህገ-ወጥ መንገድ ማፈንና ማደናቀፍ የሚመርጠው ገዥ ፓርቲ ለህጋዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄያችን የመረጠው መንገድ ህገ-ወጥነትን ነው፡፡ ይህ ህገወጥነትም መንግስትን ዋጋ ያስከፍለዋል፡፡ ስለዚህ፡- 1ኛ. ሰላማዊ ሰልፋችንን ለማድረግ ከነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ያሳወቅን በመሆኑ በታቀደው ቀን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠኋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይደረጋል፡፡ 2ኛ. ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳና ሂደት ላይ ለሚከሰቱ ማናቸውም ጉዳቶች ተጠያቂው መስተዳድሩና መንግስት ነው፡፡ 3ኛ. ሕገ-መንግስቱን የማስከበር ተልዕኮ ያለው ፖሊስ በህገ ወጥ መመሪያ አባሎቻችንን ከማሰርና ማዋከብ እንዲቆጠብ እንዲሁም ህጋዊ መሰረት ያለውን ሰላማዊ ሰልፋችንን ፀጥታ የማስከበር ሃላፊነት እንዳለበት እያሳሰብን ቅስቀሳ በሚደረግበት ወቅት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣና የህግ የበላይነትን እንዲያስጠብቅ ከአደራ ጋር እናሳስባለን፡፡ ህዝቡም መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ እንዲያሰማ ሃገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!


  Posted By,Dawit Demelash

Sunday, September 8, 2013

የአዳማ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል!!! የኢቴቪ ድራማ ከሸፈ

September 8.2013


በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በአንድነት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ መሆኑ ታውቋል። የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ የማይቀር መሆኑን የተገነዘቡት የክልል መስተዳድሮች ሰልፉ የሚጀመርበትን አካባቢ በፌደራል አድማ በታኝና በፖሊሶች እንዲከበብ አድርገዋል፡፡ አስገራሚው ነገር ግን ወደ ሰልፉ መጀመሪያ ቦታ እየተመመ የሚገኘው ህዝብ በዙሪያው እየተከናወነ ለሚገኘው ነገር ቁብ ሳይሰጥ የተዘጋጁ መፈክሮችን እይሰማ መንገዱን ቀጥሏል፡፡ የፖሊሶችና የአድማ በታኞቹ ከበባ የህዝቡን ስነ ልቦና በፍርሃት ለመሙላት እንደሆነ የተረዱ የአንድነት አመራሮች በቁርጠኝነት ያለ ምንም ስጋት ህዝቡ እንዲቀላቀላቸው በማበረታት ሕዝቡም የፍርሀትን ጠርሙስ ሰበሮ ሰልፉን በቆራጥነት ተቀላቅሏል። ሆኖም በአዳማ በተደረገው ሰልፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ፖሊስ ከፊት በማስቆም ‹‹እኔ የደረሰኝ በዋናው መንገድ እንደማትጠቀሙ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መንገድ ማለፍ አትችሉም›› ይላል፡፡ በዚህ ና በዚያ መንገድ በማለት በዚህ ሰዓት መከልከል እንደማይችሉ በመጥቀስ ሰልፈኞቹ በመንገዱ ተቃውሟቸውን በማሰማት ቀጥለዋል፡፡
ሌላው አስገራሚ ትዕይንት በአዳማ አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ተገን አድርጎ የኦሮሚያ ቴሌቭዥን በአዳማ ሊሰራው የነበረው ድራማ ከወያኔው ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጎን ለጎን የተደናቀፈበት መሆኑ ታውቋል:: በዚሁ ሰልፍ ላይ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋና ፣የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ ንግግራቸውን ያሰሙ ሲሆን በመጨረሻም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር አድርገዋል፡፡

 Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, September 4, 2013

የመከላከያ ሰራዊቱ የሰባት አመት የኮንትራት ውል የማስፈረም/የማደስ ተግባር ውጥረት ፈጥሯል::

በመከላከያ ደረጃ አየተካሄደ ባለው የሰባት ዓመት ኮንትራት ውል የማስፈረምና የማደስ ተግባር በሰራዊቱ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የሰራዊቱ አዛዦች ውጥረት ውስጥ ገብተዋል::በተለያዩ ግምባሮችን ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል በፌርማቸው ኣንዲያረጋግጡ ቢጠይቁም ፈቃደኛ ሆነው አልተገኙም ። በሁኔታው የተደናገጡ የሰራዊቱ አዛዦች ኮንትራቱን የፈረመ ወታደር በሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ዳርፉር ይላካል ፥ የርቀት ትምህርት እድል ይሰጠዋል፥ የሞያ ስልጠና ቅድሚያ እንዲያገኝ ይደረጋል ወዘተ በሚል የማይተገበር መደለያ በማደናገር ለማታለል እየሞከሩ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል::በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወታደሮች በውትድርና ሞያ እንዲቀጥሉ በኢህአዴግ ስርዓት እየተደረገባቸው ያለን ጫና በመቃወም ክፍላቸውን ጥለው በመጥፋት ላይ ናቸው ። በአማካይ ሲታይ ከአንድ ሃይል ከ 22 እስከ 23 ወታደሮች ኮንትራቱን የማደስ ውል በመቃወም እንደጠፉ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል::

Posted By.Dawit Demelash

Monday, September 2, 2013

በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም !!

September 2, 2013
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች አስፈላጊው ምላሽ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ይህ ካልሆነ ግን ከሦስት ወር በኋላ ተቃዉሞውን ከፍ ባለ ደረጃ እንደሚያቀርብ በመጋለፅ ሰልፉን አጠናቋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች የተገኘ ምላሽ ባለመኖሩ ፓርቲው ለሕዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃዉም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሔድ በመወሰን በሕግም ሆነ በሥራ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማጠናቀቅ እለቱን በመጠበቅ ላይ እያለ ምንም አይነት መለዮ ባልለበሱ ግለሰቦች የሚመራ የፖሊስ መለዮ ለባሽ ታጣቂዎች ከሕግ ውጭ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ የፓርቲውን ቢሮ ጥሰው በመግባት ፓርቲው ይጠቀምባቸው የነበሩ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችና ሌሎች የፓርቲውን ንብረቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወርሰዋል፡፡ በፓርቲው ፅ/ቤት የነበሩ አባላትን እና መሪዎችን በጠመንጃ በማስገደድ ወደተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፋፍሎ በመውሰድ አስረዋል፣ ዘልፈዋል፣ አስፈራርተዋል እንዲሁም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ደብድበዋል፡፡ አንዳንዶችን በጭቃ ላይ ጭምር አንከባለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሕገ ወጥና አረመኔያዊ ድርጊት ሕገ መንግስታዊ የሆነውን መብታቸውን በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ሲፈፀምና በሕግ ማስከበር ስም በቁጥጥር ሥር በዋሉ ዜጎች ላይ የግል ጥላቻን መወጣጫ እስኪመስል ድረስ ማንኛዉንም የማንአለብኝነት ድርጊት ሲፈፅሙ ማየት ያልታጠቁ ዜጎችን አቅመ ቢስነትና የሕግ ከለላ ማጣትን ገሃድ አድርጎታል፡፡ ይሕ አይነቱ የጡንቻ ሥራ በአንድ በኩል ልብን በሐዘን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን በሌላ በኩል ለነፃነትና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እጅግ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ አድረጓል፡፡ የአስፈፃሚው አካላት በሕግ ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባር በመውጣት የፈለጉትን ለማድረግ መብት እንደሌላቸው ማሳዬት ፓርቲያችን ከተመሰረተባቸው አብይ መርሆች አንዱ በመሆኑ፤
1ኛ. በአዲስ አበባ ከተማ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባንና ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ተቀብሎ በሕግ በተወሰነው መሰረት አስፈላጊውን ሁሉ ማከናወን የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በፓርቲው ላይ ለደረሰው የአካል፣ የንብረትና የሞራል ጉዳት ምክንያት በመሆኑ በሕግ እንጠይቃለን፤
2ኛ. የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፓርቲ መሪዎችን በማስፈራራት ከሰልፍ ለማስቀረት የሚያደርገው ድርጊት ከህግ ውጭ በመሆኑና በፖሊስ መለዮ ለባሾች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፓርቲውን ቢሮ በመውረር ለፈፀሙት የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም ፓርቲው ባቀደውና በተዘጋጀበት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፉን እንዳያካሂድ በማደናቀፉ በሕግ እንጠይቃለን፤
3ኛ. በሐገራችን ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድርና እንዲከታተል ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸው በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ እንዲህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑን እንዲያውቀው እናደርጋለን፤
4ኛ. የፖለቲካ ትግላችንን በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችንን የትኛውም የአስፈፃሚ አካል የመከልከል መብት ስለሌለው የተቃውሞ ሰልፈችንን ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሕዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በዛሬው ዕለት አሳውቀናል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀደም ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በዚህች ታሪካዊት ሐገር የሕግ የበላይነት ግብዓተ መሬት ከመፈፀሙ በፊት እንድንደርስላት ለዘመቻ የሕግ የበላይነት ትግላችን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራትና ዜጉች በአጠቃላይ ከጎናችን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በመንግስታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!!!!
ነሐሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ