Sunday, March 30, 2014

በነገሌ ቦረናው ግጭት ከ30 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፤ ግጭቱ አልቆመም


ነገሌ ቦረና (ፎቶ ፋይል)

ምንሊክ ሳልሳዊ በደቡብ ኢትዮጵያ በነገሌ ቦረና ከከተማው ስም ስያሜ ጋር በተያያዘ በጉጂ እና በቦረና ማህበረሰቦች መካከል በነገሌ ቦረና አካባቢ በተነሳ ግጭት 30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን እና ግጭቱም አለመቆሙን የአከባቢው ባለስልጣናት ምንጮች ማምሻውን በላኩልን መረጃ ገለጹ። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ በአከባቢው የተነሳው ግጭት በመስፋፋት ከፍተኛ የሆነ ንብረት ያወደመ ከመሆኑም በላይ ከነገሌ ከተማ ውጪ ለጉላ እና አርዶታ በተባሉ አከባቢዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ መቀጠሉ ታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ ግዛቴ ግጭቱ ዘልቆ ሊገባ ይሽላል በሚል ፍራቻ ኬንያ ወታደሮቿን በድንበር አከባቢ አስፍራል እያስጠበቀች መሆኑ ታውቋል።


የኢሕአዴግ ፌዴራል ፖሊሶች እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶች በቦታው ደርሰው የነበረ ቢሆንም የአከባቢው ህብረተሰብ ቀየውን በመልቀቅ እየተሰደደ መሆኑን ታውቋል። በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውና የጎሳ ፌዴራሊስም ፖለቲካ ውጤት የሆነው ይህ ግጭት በአካባቢው ባለስልጣናት እና የሃገር ሽማግሌዎች ለመፍታት ቢሞከርም ሳይሳካ ግጭቱ እንደቀጠለ ታውቋል።

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13976

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው

ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው
religions


ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።
ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።
የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡
ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል።
   http://www.goolgule.com/eprdf-to-enforce-strict-religious-laws/

Saturday, March 29, 2014

የዓረና መሪዎች በእንደርታ ኲሓ ከተማ በፖሊስ ታሰሩ

     አብርሃ ደስታ ከመቀሌ 
የዓረና አመራር አባላት የሆኑት አቶ ብርሃኑ በርሀ፣ መምህር የማነ ንጉሰና አቶ ፅጋቡ ቆባዕ በፖሊስ ተደበደቡ፤ በመጨረሻም በኲሓ ከተማ ፖሊስ ታሰሩ። የታሰሩበት ምክንያት ለስብሰባ በማይክሮፎን ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ነገ እሁድ በኲሓ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ስብሰባ ለማድረግ የተፈቀደልን ሲሆን ቅስቀሳ ለማካሄድ ግን ተከልክለናል። ዛሬ ጧት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴና መምህር ዮሃንስ ካሕሳይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በዓይናለም ከተማ ለሰዓታት ታስረው ተለቀዋል። የህወሓት ካድሬዎች ዓረና የማዳበርያ ዕዳ እንደሚሰርዝ፣ መሬት የህዝብ እንደሚያደርግ፣ የሊዝ አዋጅ እንደሚያስቀር ወዘተ በማይክሮፎን እንዳይናገር አስጠንቅቁት ተብለናል ሲሉ የህወሓት ካድሬዎች ራሳቸው አረጋግጠውልናል። አሁን የኲሓ ከተማ ቅስቀሳችን በአባሎቻችን መደብደብና መታሰር ምክንያት ለግዜው ቁሟል። ስብሰባው ግን ነገ ይካሄዳል።

ዓረና ፓርቲ ነገ እሁድ ከእንደርታ ህዝብ ጋር በኲሓ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ። ህወሓቶች ህዝባዊ ስብሰባ እንድናደርግ የፈቀዱልን ሲሆን ህዝቡን ለማሳወቅ ቅስቀሳ ማድረግ ግን አይፈቀድም አሉን። ህወሓቶችን ያስፈራ ጉዳይ የትግራይ አርሶአደሮች የብድር ብዝበዛ ያቀጣጠለው የህዝብ ተቃውሞ ነው። ቅስቀሳው ግን ይቀጥላል። ህዝብ አማራጭ ሐሳብ የመስማት መብት አለው። የህወሓት ዓፈና እንቃወማለን።

በሌላ በኩል ደቡብ ሕብረት-ኢሦዴፓ ፓርቲ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 20, 2006 ዓም በሀዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። ዓረና ፓርቲም ተጋብዟል። የዓረና ተወካይ አቶ ካሕሳይ ዘገየ ንግግር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ደቡብ ሕብረት -ኢሦዴፓ በደቡብ ክልል እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚያኮራ ነው። የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲም በኦሮምያ ክልል ቅስቀሳ እንደሚጀምር ይጠበቃል። 

     https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13959

Friday, March 28, 2014

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደረገ::

March 28, 2014
ሳዲቅ አህመድ
በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስኪድን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ዋናዋና ከተሞች ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!›› በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ እያካሄደው ያለው መስጂድ ተኮር የዘመቻ እንቅስቃሴ አካል የሆነው እና የዘመቻው ማጠናቀቂያ የጁምኣ የተቃውሞ ትእይንት በደመቀ መልኩ ተካሂዷል::Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa (March 28, 2014)
ህዝቡን ከመስጂዱ ለመነጠል በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ስራም ለራሱ ተረድቶ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማትና መስጂዶቹን በዒባዳ በማድመቅ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ወቅታዊና አንገብጋቢ የመስጂድ ባለቤትነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ የመንግስትን እና የመጅሊስን ሴረኞች እንቅልፍ ማሳጣቱንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የውስጥ መረጃዎች እያጋለጡ ነው፡፡ ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!››ዘመቻ የዛሬው ጁሙአ ድረስ ቀጥሎ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል መስጂዶች ላይም አስቀድሞ የነበሩንን ቋሚ ትዝታ ጥለው ያለፉ ግዙፍ ተቃውሞዎችን በሚያስታውስ መልኩ የደመቀ የተቃውሞ ስነስርአት በማድረግ በሰላማዊ ሁኔታ ዘመቻው መጠናቀቁ ታውቋል::
በዚህም መሰረት ከቀኑ ስድሰት ጀምሮ በአዲስ ወደ አዲስ አበባ አንዋር መስኪድ እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የተቃውሞ ወደተመረጡ መስኪዶች የተመመው ህዝበ ሙስሊሙ የመስኪዶችን ውስጥ እና ደጅ በመሙላት መስኪዶቹ የራሱ ሃብት መሆናቸውን እና ሙስሊሙ ህዝብ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በደመቀ ተቃውሞ ነጭ ምልክቶችን በማውለብለብ ገልጿል::
        Part.1
                              Part.2

ህዝበ ሙስሊሙ ዘመቻውን በተሳካ መልኩ በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ከኮሚቴው ጎን ዛሬም ቃሉን አክብሮ እንደቆመ በማሳየት በሰላም መመለሱን ለማረጋገጥ ተችሏል::
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11586/
                                                ተጨማሪ ፎቶዎች