Saturday, January 30, 2016

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ ውጥረቱ እንዳየለ ነው በርካቶች በቦምብ ፍንዳታ ቆስለዋል

ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባለፈው ሀሙስ በጋምቤላ በኑዌር እና በአኝዋክ ብሄረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት የሟቾች ቁጥር 6 መድረሱን መዘገቧ ይታወሳል:: ግጭቱ እስከ ዛሬ ድረስ መቀጠሉ ተዝግቦ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል::


አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው በጋምቤላ ክልል በኑዌርና በአኝዋክ ብሔሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት የክልሉ የፀጥታ ሃይል አባላትን ጨምሮ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች በቦንብ ፍንዳታ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በግጭቱ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ባንኮችና የንግድ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን ትናንት ረፋድ ላይም በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ግርግር ተከስቶ እንደነበር ታውቋል፡፡

ለቀናት በዘለቀው ግጭት የክልሉ የትራንስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 8 ሰዎች መሞታቸውንና በከተማዋ ሁለት ቦታ በፈነዳ ቦንብም በርካቶች መቁሰላቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የክልሉ ልዩ የፖሊስ ኃይልን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማረጋጋት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው በትናንትናው ዕለትም ከተማዋ በውጥረትና ግርግር ስትዋከብ መዋሏን ገልፀዋል፡፡


የግጭቱ መነሻ ከ15 ቀናት በፊት በክልሉ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲንና በክልሉ ም/ፕሬዚዳንት ሹፌር መካከል በመኖሪያ ቤት መሬት ጉዳይ በተፈጠረ የግል ፀብ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ጠቡን ተከትሎ ም/ዲኑ የአኙዋክ ተወላጅ ሹፌሩን እጁ ላይ በጥይት መተው ማቁሰላቸውን ገልፀው በዚህም ሳቢያ ጉዳዩ የብሄር ግጭት መልክ እንደያዘና ወደ ተማሪዎች የቡድን ፀብ እንደተዛመተ አስረድተዋል፡፡


ግጭቱ ከእለት እለት እየተባባሰ ቀጥሎም አንዲት የኑዌር ተወላጅ ተማሪ በግጭቱ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተከታተለች ሳለ ህይወቷ በማለፉ ግጭቱ መካረሩን የጠቆሙት ምንጮች፤ የኑዌርና የአኙዋክ ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች የእርስ በእርስ ግጭት መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡


የክልሉ ልዩ ሃይል ግጭቱን ለማርገብ ሙከራ ሲያደርግ ቢቆይም ሁኔታው ባለመረጋጋቱ የመከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት በከተማዋ ተሰማርቶ ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡


በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ም/ኃላፊ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም በትናንትናው ዕለት ኃላፊው አዲስ አበባ መምጣታቸውን ገልፀው፤ “መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀውልናል ሲል አዲስ አድማስ ዘገባውን አጠናቋል::


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50460

Wednesday, January 27, 2016

‹‹የትም ብሆን ስለመብቴና ስለሀገሬ ያገባኛል›› እስክንድር ነጋ

(ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በነገው ዕለት ለዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን በማስመልከት ህዳር 19/2007 ዓ.ም ለ10 ደቂቃዎች ያህል እስክንድርን ቃሊቲ ስናገኘው የተናገረውን በሚመለከት ከተጻፈው ለማስታወስ….)

በላይ ማናዬ

‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››

ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ህዳር 19/2007 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡

በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡

ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡

ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ 
ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡

አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡
አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡


ቂሊንጦ ከእነ በፍቃዱ ጋር ስንጨዋወት ስለእስክንድር ነጋ ትሁትነት፣ አስተዋይነት፣ ሰላማዊነት እያነሱ ሰላምታ እንዳደርስላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እስክንድር ነጋን ሳውቀው በትሁትነቱ፣ በአስተዋይነቱና በሰላማዊነቱ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተበሳጭቶ ነበር የተመለከትኩት፡፡ ያ ፈገግታው ከፊቱ ብን ብሎ ጠፍቶ ‹‹ያገባኛል!›› ሲልበት የነበረውን ስሜት ግር አለኝ፡፡
ካልነኩት የማይነካ ሰው ሲነኩት ትንታግ ነው፡፡ እስክንድር እዛ ስሜት ውስጥ የገባው ተገድዶ ነበር፡፡ ሊጠይቁት የመጡትን ሰዎች አብዛኞቹን አላስገባም ማለታቸው ሳያንስ ከገቡትም መካከል የምታወራውን እኔ ልምረጥልህ በሚል ግብዝነት አባርረዋል፡፡ 
እስክንድር ይህን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም፡፡ ስለሆነም እንዲህ አለ፤ ‹‹…እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው! ስለሀገሬ ያገባኛል!››

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50330

Tuesday, January 26, 2016

ፍ/ቤቱ በአቶ ዮናታን ተስፋየ ላይ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ

‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡

ዛሬ ጥር 17/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ዮናታን ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በሚል የጠየቀበትን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋየ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ፖሊስ በአቶ ዮናታን ላይ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ ‹‹የቴክኒክ መረጃዎችን መሰብሰብ ይቀረናል፤ ያልተያዙ ግብረ አበሮችንም አሉ›› የሚል ምክንያት ማቅረቡን የተጠርጣሪ ጠበቃ ገልጸዋል፡፡


አቶ ዮናታን ተስፋየ በጠበቃ እና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ እንደተከለከለና ከታሰረበት ክፍል መታፈን የተነሳ የጤና እከል ቢገጥመውም ህክምና እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን አድምጦ በጠበቃውም ሆነ በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ እንዲፈቀድለትና ህክምናም እንዲያገኝ ትዕዛዝ መስጠቱን ከጠበቃው ለማወቅ ተችሏል፡፡


አቶ ዮናታን ከችሎት ሲወጣ በስፍራው ለነበሩት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያለውን ፍቅር ገልጾ ‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር ተደምጧል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50317


Friday, January 22, 2016

ክርስቲያኖችን ከአክራሪዎች ጥቃት ሲታደግ መሰዋት የሆነው ሙስሊም ብሔራዊ ጀግና ተባለ

ሳሊህ ፋሪህ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን በሙያው ደግሞ መምህር ነበር።ታዲያ ባለፈው ታህሳስ 2015 አኤ አ የሶማሊያው ነውጠኛው እና አክራሪ ቡደን አልሽባብ ኬኒያ ውስጥ ማንዲራ ከተባለ አካባቢ ወደ ናይሮቢ ለሃይማኖታዊ በአል በሕዝብ መጓጓዣ መኪና ተሳፍረው የነበሩ ተሳፋሪዎችን በማሰቆም ክርስቲያንኖችን ከሙስሊም ተሳፋሪዎች በመለየት ሙስሊም የሆኑትን በነጻ በመልቀቅ 28ቱ ክርስቲያኖችን ወዲያውኑ ሲገደሏቸው የእሰልምና ሃይማኖት ተከታዩ ሳሊህ ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ነበር ። ይሁን እና ሳሊህ “ክርስቲያን ወገኖቻችንን ለአክራሪዎች አሳልፈን አንሰጥም “ ከሚሉ ሙስሊም ወገኖቹ ጋር በመሰለፉ ከአክራሪው አልሸባብ ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት በእጁ እና በታፋው ላይ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ናይሮቢ ከተማ ውስጥ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ባለፈው ሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ። 

ሰማእቱ ሳሊህ በወቅቱ ሰለነበረው መጥፎ ሁኔታ ለቢቢሲ ራዲዮ በሰጠው አማኝነት “ አሸባሪዎቹ ወደ ተሳፈርንበት መኪና መጥተው ሙሲሊሞች ካላችሁ እራሳችሁን ከክርስቲያኖች ባስቸኳይ ለዩ እናነተን አንነካችሁም ፣ በነጻ መሄድም ተችላላችሁ አሉን። እኛ ግን 62ታችን ተሳፋሪዎችን ልቀቁን አለበለዚያ ሁላችንንም እዚሁ ግደሉን አልናቸው ታጣቂዎቹ ተደናግጠው ያገኙትን ገደለው እኔንም በጥይት አቁስለውኝ ከሰፍራው ተሰውሩ ። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የሃይማኖት ልዩነት ካለሆነ በቀር ሁላችንም አንድ በመሆናችን ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ሊንከባከቡ ክርስቲያኖችም ሙስሊሞችን ከጥቃት በመታደግ በሰላም እና በጋራ መኖር የግድ ይለናል ።” ሲል ሰለ ሰላም እና መቻቻል የነበረውን ጽኑ አቋሙን ተናገሯል ።

በሙስሊም ሃይማኖት ስረአት እና ደንብ መሰረት ማንዲራ ከተማ ውስጥ ማክሰኞ እለት ስርአተ ቀብሩ የተፈጸመው ሰማእቱ ሳሊህ በኬኒያ መንግስት ዘንድ እውነተኛ ብሔራዊ ጀግና የሚል ስያሚ የተሰጠው ሲሆን የሞምባሳ አካባቢ የሙስሊሞች ካውንስል ሰብሳቤ የሆኑት ሺክ ጁማ ናጎው “ፋራህ ቅዱስ ቁራን የአንደን ሰው ህይወት ማዳን የአጠቃላይ የሰው ልጅ ዘርን ማዳን ነው የሚለውን አሰተምሮትን በተግባር የፈጸመ ትክክለኛ ሙስሊም ነው ።” ብለውታል። ሰማእቱ ሳሊህ ስላደረገው ሃይማኖታዊ እና ሰብ አዊ ተጋድሎ በክርስቲያን ወገኖቹም በኩል ታላቅ አክብሮት እና አድናቆት አልተለየውም። የኬኔያ ባብቲስት ኮንቨንሽን ቤ/ክን አስተዳዳሪ የሆኑት ዊሊንግተን ሙቲሶ “ነፍሱን ሰለክርስቲያኖች ህይወት ሲል በመያዣነት ያቀረበ ታላቅ ሰማእት ፣በሞቱ የብዙዎችን የተዛባ ሃይማኖታዊ አመለካከትን የቀየረ(ሁሉም ሙስሊሞች አክራሪነትን ይደግፋሉ ተብሎ የሚወራው ፍጹም ሃሰት መሆኑን በተግባር ያሰመሰከረ) ወገናችን ፣ ክርሰቲያኖች ዘወትር የሚኮሩበት እና የሚዘክሩት ታላቅ ሰው ነው ።”ብለውታል ።



በማንዲራ አካባቢ የሮማን ካቶሊክ ቤ/ክ ሃላፊ የሆኑት ጆን ሞሶዮካ እንዲሁ” አሸባሪዎች ሃይማኖትን ሸፋን ማድረግ እንደማይችሉ ፣ሃይማኖትም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር መገናኛ እንጂ የሰዎች መከፋፈያ መሳሪያ ያለመሆኑን ወንድማችን ፋራህ በሚገባ አሰተምሮናል ።” በማለት ክርስቲያናዊ እና አባታዊ የሆነው ምስክረነታቸውን ሰጥተዋል። ራሺድ የተባለው የሳሊህ ወንድም በበኩሉ ለኬኒያው “ዘ ስታር “ጋዜጣ ሰለ ሟቹ ወንድሙ መሰዋትነት ሲገልጽ”የወንደሜ መሞት በኬኒያዎች መካከል የተለያዩ ሃይማኖተኞች እና የማህበረሰብ ክፍሎች እንዴት ተቻችለው እንደሚኖሩ መንገድ ጠራጊ ነው ብዩ ተሰፋ አደርጋለሁ።” ሲል ተናገሯል።

ሳሊህ ምንም እንኳን የጎረቤት ኬኒያ ተወላጅ ቢሆንም የከፈለው መሰዋትነት በየትኛውም ጠርዝ ይሁን በየትኛውም ስፍራ በጎሳ ፡በጽንፈኝነት እና በጠባብነት ለወደቁ ወገኖች ትልቅ ትምህርት አለው አርሱም ተቻችሎ እና ተፈቃቅሮ ለመኖር ዋንኛ መለኪያው የጎሳችን፣ የቋንቋችን፣ የሃይማኖታችን እና የእውቀታችን ግዝፈት እና ምጥቀት ወይም የውጫዊ አካላችን ልዩነት ሳይሆን ክቡር የሆነው ሰው መሆናችን ብቻውን ከበቂ በላይ መሆኑን ነው። ፈጣሪያችን እግዚአብሔር/አላህ የወንድማችን የሳሊህ ነፈሱን ይማረው !!!!።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50178

Thursday, January 21, 2016

የአጋዚ ሠራዊት የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን መኝታ ክፍል ሰባብሮ ገባ


በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ሰዓት ሕወሓት የሚመራው መንግስት አጋዚ ሰራዊት በነቀምት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን መኝታ ቤቶች ሰባብሮ በመግባት በንብረት ላይ ጉዳት ከማደርሱም በላይ የተማሪዎችን ውድ እቃዎች መዝረፉንም የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው አስታወቁ::

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በወታደሮች መከበቡን ያስታወቁት ምንጮቻችን የሴቶችም ሆነ የወንዶች መኝታ ክፍሎች ተሰባብረዋል:: ብዙ ዋጋ ያላቸው ንብረቶችም በነዚሁ ፖሊሶች ተወስዷል:: ከዚም በተጨማሪ ተማሪዎች ከመቀጥቀጣቸውም በላይ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል::

ፖሊሶቹ አሁንም ጊቢውን በመቆጣጠር ተማሪዎቹን በማሸበር ላይ ናቸው::

በኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ቁጣ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች የቀጠለ ሲሆን በዚህ ሳምንት ብቻ ከ6 የማያንሱ ተማሪዎች መገደላቸው ተዘግቧል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50148


የኖርዌይ ኢምባሲ ወደ ጋምቤላ የሚጓዙ ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳሰበ “ውጥረትና ግጭት አለ”


በአዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኢምባሲ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ:: ከዚህ ቀደም ወደ ጎንደር እና ወደ ኦሮሚያ የሚጓዙ ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳስቦ የነበረው ኢምባሲው ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያው በጋምቤላ ክልል ግጭትና ውጥረት በመኖሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል::

በጋምቤላ ክልል ከመሬት ቅርምት ጋር በተያያዘ በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እንደሚነሱ ይታወሳል::


የኖርዌይ ኢምባሲ ባወጣው ማሳሰቢያ ወደ ጋምቤላ መጓዝ ለደህንነት አስጊ በመሆኑና ውጥረቱም ግጭቱም ስላለ መጠንቀቅ ያስፈልጋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50141

Friday, January 15, 2016

በማዕከላዊ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ የደረሰበት ሙባረክ ይመር ቂሊንጦ ውስጥ ሞተ

(ቢቢኤን) የአላህ ውሳኔ ሁኖ ወደ አኪራ የሄደው ሙባረክ ይመር ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ እንደነበር አብረውት የታሰሩት በሀዘን ገለጹ::
ሙባረክ ቁሞ መራመድ እንደማይችል እንደደከመ እየተነገራቸው ከፈለገ ተንበርክኮ ይሂድ በማለት የማረሚያ ቤት ፖሊሶች መሳለቃቸውም ታውቋል
ከ2005 ጀምሮ በአህመድ ኢንዲሪስ የክስ መዝገብ የተከሰሰው እና ከደሴ ተይዞ በግፍ በቂሊንጦ ዞን3 ቁጥር 6 ታስሮ የነበረው ወጣት ሙባረክ ይመር ወደ አኬራ ሄደ

ኢና ሊላሂ ወኢነ ኢለይሂ ራጁዑን

በ2005 ሃምሌ 4 በብሄራዊ መረጃ እና በደህንነት ሰራተኞች ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ በቂሊጦ ማረሚያ ቤት ታስሮ የነበረው ወጣት ሙባረክ ይመር በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በህክምና እጦት ሳብያ በትላንትናው 
ለሊት ወደ አኬራ ሄደ::
ወጣት ሙባረክ ይመር በአባቱ አቶ ይመር አየነ እና ከእናቱ ወ/ሮ ወርቅነሽ ንጉሴ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ከተማ 04 ቀበሌ በ1974 ተወለደ እድሜው ለትምህርት ሲደረስ እውቀት ጮራ በሚባል ትምህርት ቤት እስከ 8ኛ ክፍል ተማረ ወጣቱ ሙባረክ ይመር 1996 መርየም መሃመድ ኑር ከተባለች እህት ጋር ትዳር መስርቶ 3 የልጆች አባት ነበር።

ትላንት ጥር 5 በአባሪዎቹ ተብለው ከታሰሩት ከነ አህመድ ኢንዲሪስ ጋር በልደታው ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ከምሽቱ 5 ሰዓት ታስሮበት በሚገኘው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ዞን 3 ቀጥር 6ተኛው ቤት የማጎሪያው አዳራሽ በር በከፍተኛው በመደብደብ ፓሊሶቹ ግን የመጡት ከረጅም ግዜ ቡሃላ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ሙባረክ ይመርን ታሳሪዎቹ ተሸክመው ሊወስዱ ሲሉ ፖሊሶቹ እናንተ አትወጥም ከፈለገ ራሱ በእግሩ ይሂድ በሚል ከልክለዋል፡፡ ሙባረክ ቁሞ መራመድ እንደማይችል እንደደከመ እየተነገራቸው ከፈለገ ተንበርክኮ ይሂድ በማለት መሳለቃቸውም ታውቋል፡፡ ከብዙ ጭቅጭቅ በሁላ ሙባረክ ሊሞት ገርገራ ላይ ሆኖ ነብስ ግቢ ውጪ በደረሰበት ሰአት ላይ ወደ ክሊኒክ እንደተወሰደ ህይዎቱ ማለፉን በሀዘንታ አብረውት የታሰሩ ይገልጻሉይገልፃሉ።ቢቢኤን በምሽት ፕሮግራማችን ወጣት ሙባራክ ይመር የመጨረሻዎቹ ሰዓታትን ጨምሮ ስለ ወጣት ሙባረክ ይመር የምናቀርብላቹህ ይሆናል::


የወጣት ሙባረክ ይመር ጀናዛ በአወሊያ ከታጠበ ቡሃላ ወደ ደሴ ተወስዱዋል፡፡ በነገው እለት የቀብር ስነስርአቱ የሚፈጸም ሲሆን የደሴ ሙስሊሞችም በነቂስ በመውጣት እንዲቀብሩ ጥሪ ቀርብዋል

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50013


በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል

 ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረውና ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በጭካኔ ለመገደላቸው መረጃ የሚቀርብበት ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎዋል። ኢህአዴግ በአፈቀላጤዎቹ አማካኝነትሰልፍ የወጣ የለም፣ ከተማችን ሰላም ነው፣ የተገደለ የለም፣ . . .” በማለት የማስተባበያ ሙከራው በራሱ ሹሞች ሲጨናገፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። በሌላ በኩል በፌዴራልና በአግአዚ መራር ሰቆቃ እየደረሰበት ያለው ሕዝብባርነት በቃን፣ ግድያው ይቁም፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ . . .” የሚሉ መፈክሮችን እያነገበ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባለፉት ሦስት ቀናት የተከሰተውን ያቀረበው ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል።

ባለፈው ሐምሌ ወር ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ታስሮ እንደነበርና ታሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው ተማሪ አብደታ ኦላንሳ ቀብር ዛሬ (ረቡዕ) አምቦ ከተማ ተፈጽሟል። በስልክ ያነጋግርናቸው ነዋሪ ትናንት ማታ የወጣቱን አስከሬን ለመቀበል በወጣ ህዝብ ላይ የጸጥታ ሃይሎች ድብደባ አድርሰዋል። ወደ ሰማይ ሲተኩሱም ነበር። አንድ ሰው በጥይት ተመትቶ ተገድሏል ብለዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአምቦው ነዋሪ አስከትለውም ዛሬ በቀብሩ ላይም እንዲሁ የከተማው ነዋሪ በብዛት ወጥቶ እንዳይቀብረው ለማስተጓጎል ወታደሮች በተለይ ወጣቶችን መኪና ላይ እየጫኑ ወስደዋቸዋል ብለዋል። ወደ ቀብሩ ጉዞ ላይ የነበረ ወጣት በጥይት መገደሉን ገልጸውልናል።

ትናንትና ደግሞ በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ አጠገብ የአንድ ወጣት አስከሬን ተገኝቷል ብለዋል።
የአምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ሂርኮ አምቦ ውስጥ ተገደሉ የተባለውን አስተባብለዋል።

ባልደረባችን ጃለኔ ገመዳ አነጋግራቸው ነበር ባለው መረጃ አምቦ ውስጥ የተገደለ ሰው የለም አዲስ አበባ ከተማ ታሞ የሞተ ሰው አአስከሬኑ አምቦ ገብቶ ዛሬ ተቀብሯል ለበለጠ መረጃ የአምቦ ከተማ ከንቲባውን አነጋግሩሲሉ ቢመሯትም ከንቲባ ዱጋሳ ኦሉማ በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ተደውሎ አላነሱትም።

አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሞቶ ዛሬ ተቀበረ ስለተባለው ወጣት አብደታ ኦላንሳ ጉዳይ ሆስፒታሉ መዝገቡን ተመልክቶ ነገ ማብራሪያ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ሶራ ሃለኬ ባገኘው መረጃ ደግሞ ፌደራል ፖሊሶች የተማሪዎች መኝታ ቤቶች እየገቡ ጭካኔ የተመላበት ድብደባ አካሂደዋል ብዙ መቶዎች አስረው ወስደዋል።

ስሜን አትግለጡ ያለው ተማሪ፣ ተማሪዎች ያሉትን ለማጣራት ወደ ከተማዋ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ደውሎ እንዳልተሳካለት ባልደረባችን ሶራ ሃላኬ በዘገባው አመልክቷል።

በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ደግሞ የከተማው መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎችየመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ” “ ግድያው ይቁምበማለት ትናንትናና ዛሬ ሰልፍ ወጥተዋል ሲሉስማችንን እንዳትገልጹብንያሉ ተማሪዎች ለባልደረባችን ቱጁቤ ሆራ ገልጸውላታል።

በሰላም ነበር ሰልፉ የሚካሄደው የመንግሥት ሃይሎች በተኑት፣ የተወሰኑ ተማሪዎች ተደበደቡ፣ የታሰሩም አሉ ያለው ተማሪ እኔም ራሴ ከተደበደቡት አንዱ ነኝ ብሏል።

የሃሮማያ እና የጅማ ተማሪዎች እንዲሁም በአምቦ ተማሪዎች መገደላቸውን በመቃወም፣ ድርጊቱ ይቁም ትግላችን ይቀጥላል ብለን ድምጻችንን ስናሰማ ነበርሲል ገልጿል።

የሻሸመኔ ከተማ የአስተዳደር እና ደህንነት ሐላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን ግን ሃሰት ነው ይላሉ

ሰልፍ የወጣ የለም። ሰልፍ ማካሄድ ተፈቅዷል፣ ግን የወጣም የለም የታሰረም የለም፣ ተማሪዎች እየተማሩ ናቸው። መማር የፈለገ ይማራል፣ የማይፈልገውን ግን አናስገድድም መብቱ ነውየሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ስንታየሁ አንዳንድ ጥያቄ ያነሳ ሊኖር ይችላል ብለው ነበርና ቱጁቤ ምን ጥያቄ ነው ያነሱት? ብትልማለት የጠየቁት እኮ ነገር የለም ቢሯችን የደረሰው መረጃ የለም ከተማውም ሰላም ነውእንዳሏት አክላ ጠቅሳለች።

በሌላ በኩል በምእራብ ሃረርጌ በአዳ ቡልቱም ወረዳ በዴሳ ከተማ ከትላንት በስቲያ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ሕብረተሰቡባርነት በቃንየሚል መፈክር አንግቦ ለተቃዉሞ እንደወጣ መንግስት ጥቃት እንዳያደርስብኝ ሰሜ አይገለጥ ያሉ የሰልፉ ተካፋይ ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል።

በቀለ ገርባና በቀለ ነጋ ይፈቱ፣ የታሰሩ ተማሪዎች  ሁሉ ይፈቱ ማስተር ፕላን ይሰረዝ የሚል በራሪ ወረቀቶች ይዘዉ ነዉ የወጡት። መንግድ ላይ የከተማዋ ካቤኒ አባል መሃመድ ሰይድ መጥቶ ወረቀቶችን ከእጃቸዉ ነጥቆ ሲበትን ሰልፈኞቹ ደበደቡት። ፌዴራል ፓሊሶችና አዳማ በታኝ ሃይሎች አሁን ያገኙትን ሁሉ እያወከቡና እያሰሩ ነዉ አግአዚዎችም ገብተዋል።

የባዴሳ ከተማ ካቢኔ አባል አቶ መሃመድ ሰይድ የበኩላቸዉን እንዲገልጹልን ሰልክ ደዉለንላቸዉ ነበር አያነሱም።

በምእራብ ሃረርጌ ሂርና ከተማ ለአንድ ሳምንት ያክል ሲካሄድ  የሰነበተዉ ተቃዉሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አድማ በታኞች በወሰዱት እርምጃ ወደ ለየለት ጦርነት ተቀይሯል ይላሉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ በመጠየቅ የኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍልን ያነጋገሩ የሰልፉ ተካፋይ።

ሰላማዊ ሰልፍ ነበር የተጀመረዉ። መከላከያ ሰራዊት አምጥተዉ በሰላም የጀመርነዉ ትግላችንን ወደ ጦርነት ቀየሩት። በጥይትና  በእንባ አስመጪ ጋዝ እየደበደቡን ነዉ። አጋአዚ ሁሉ አምጥተዉ ወንድ ሴት ሳይሉ በሒርና ከተማ ያለ ነዋሪ በር ሰብረዉ በመግባት እያሰሩ እየገረፉ ነዉብለዋል።

በዛሬዉ የጸጥታ ሃይሎች ጥቃት ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል  ብለዋል የሰልፉ ተካፋይ ነኝ ያሉት የዓይን እማኝ። ካሁን በፊት በጽኑ የቆሰሉ ሶስት ሰዎች  ጭሮ ሆስፒታል እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሂርና ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር አቦዶ በበኩላቸዉ ከተማዋ ሰላም ናት ይላሉ።

አይ እየታሰሩ ያሉ ሰዎች የሉም። ዉሸት ሊሆን ይችላል፣ እስካሁን የታሰረ ሰዉ የለም ከተማችን እስካሁን ሰላም ናት፥ ይህ ሁሉ ዉሸት ነዉብለዋል።

ትላንት በምእራብ ሃረርጌ የአሰቦት ከተማ ተማሪዎች የከተማዋ ባንክ ቤት ፊት ለፊት ቆመዉ የአዲስ አበባና የፊንኒኔ ዙሪ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረቦች ሰልፉን የተካፈትን በማነጋገር ዘግቧል።

የከተማዋ ፖሊሶችን ባለስልጣናት ተኩስ በማሰማት ሰልፉን መበተናቸዉም ታዉቋል፣ የቆሰለ ሰዉ ግን የለም። የአፋን ኦሮሞ ክፍልን ያነጋገረ አንዱ ተማሪ በአሰቦት ከሰዓት በሁዋላ 6 – 9 ሰዓት ሁለተኛ ዙር በተካሄደ ተቃዉሞ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች ለገበያ የወጡ አርሶ አደሮች መቀላቀላቸዉን ገልጿል።

ከዚያ በሁዋላ ሶስት መኪና ሙሉ የመከላከያ አባላት ወደ ከተማዋ ገብተዉ ተኩስ ከፈቱ፥ ተኩስን በመጋፈጥ ተማሪዎቹና ሕዝቡ ድንጋይ በመወርወር ተከላከል በተወረወሩ ድንጋዮች የተጎዱ የመከላከያ አባላት አሉበማለት በከተማዋ የነበረዉን ሁኔታ አብራርቷል። ተከትሎም የጸጥታ ሃይሎች ቤቶችን  ሰብረዉ ገብተዉ ተማሪዎችን ለቅመዉ አስራዋል ብሏል።

ትናንት  በዚሁ በምእራብ ሃረርጌ ጡጢሲ በሚባል ከተማና የዳሮ ገጠር ነዋሮዎች የተቃዉሞ ስልፍ ማከሃዳቸዉን ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የከተማዉ ነዋሪ ገልጿል። ጥያቄአቸዉምአቶ በቀለ ገርባ እና የታሰሩት ሁሉ ይፈቱልን ኦሮሞ የሃገር ባለቤት ነዉ በማለት ሴት ወንድ ሳይል ነዉ ሁሉም ለተቃዉሞ የወጣዉ። ተማራዎች አልተካፈሉም። አርሶ አደሮች የአገር ሽማግሌዎች ናቸዉ ልጆቻችንን አትሰሩብንበማለት ለተቃዉሞ የወጡት።

በጡጢሲ ተቃዉሞዉ በሰላም ቢጠናቀቅም፣ ፖሊሶች ብዙዎችን ቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ተገልጾል።
የምእራብ ሃረርጌ አስተዳዳሪ አቶ አልይ ኡመር የአሰቦት ከተማ ከንቲባ አቶ ቶፈቅ አልህ እና የከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ሃላፊ አቶ አደም ሲራጅን ለማነጋግር የተደረገዉ ሙከራ አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ በኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጀመረ፣ ተቃዋሚዎቹ የታጠቁና የመንግስት ባለስልጣናትን፣ መሳሪያ ያልያዙ የጸጥታ ሃይሎችን፣ ገበሬዎችንና፣ ሕዝብን የሚያሸብሩ ናቸዉ ማለታቸዉን ሮይተርስ ባለፈዉ ታህሳስ አራት ዘገባዉ ጠቅሷል።

http://www.goolgule.com/protest-in-oromia-region-continues/

Wednesday, January 13, 2016

ጸረ ሙስና ኮሚሽን በአባይ ጸሀዬ ሙስና ላይ መረጃ ቢደርሰውም ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ


አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ።
በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት / ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል።
ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬንየመሬት ከበርቴውየሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው።
የኮሚሽኑ የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል።
በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል።
ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል።
አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜለምንየሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤ መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ።ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከርየሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!!
ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽንበሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ።
ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር።
ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበትእንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነውበማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ።
መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል።
የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ።
ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱበየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነውሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለንበሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውምበአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷልሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስየስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስአቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድበሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪስርዓቱ በስብሷልባይ ናቸው።
ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነውበማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውምስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነውበማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ።
የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡

የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
(በጎልጉል ሪፖርተር)
http://www.satenaw.com/amharic/archives/11542