Thursday, February 25, 2016

የአባይ ወልዱ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የህይወት ዋጋ ያስከፍላል! | ጎንደር ህብረት

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራዉ ድርጅት መሪ አቶ አባ ወልዱ እና የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሐድስ ዘነበ ከዘራፊ ካድሬወቻቸው ጋር በመሰባሰብ፤ በወልቃይት፤ በጠገዴ እና በጠለምት ህዝብ ላይ የማያዳግም ጦርነት ለማካሄድ የጦር ነጋሪት እየደለቁ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ። ጦርነቱን በሚፈልጉት መንገድ በድል ለመወጣት እየተጠቀሙበት ያለው የሞራል መምቻ ደግሞ፤ ህብረተሰቡን፤ በገብያ፤ በቤተክርስቲያን እና ቤት ለቤት በማደን እያስፈራሩ ወደፖሊስ ጣቢ እየወሰዱ፤ ወልቃይት የትግራይ ክልል እንደሆነች እንድትቀጥል እንደሚፈልጉ በማሥመሰል በማሥገደድ እያስፈረሙ ናቸው።

ሌላ የዚህ ሳምንት አስገራሚዉ የወያኔ ቲያትር ደግሞ፤ ከስህተት ላይ ሥተት በመደራረብ ህዝብና ህዝብን ለማጋጨት የትግራይ ተወላጆችን ስልፍ አሰልፎ በጉልበት ይዞት የቆየዉን መሬት የትግራ ነዉ እያለ ማስጨፈሩ ነዉ። ወያኔ በመላዉ ኢትዮጵያ ሰልፍ ከልክሎ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በታንክና መትረየስ እዬጨፈጨፈ፤ ጎንድር መሪ የሌለዉ መሆኑን የተረዳዉ ወያኔ ወገራ አዉራጃ ላይ የትግራይ ተወላጆችን ከጎንደር ህዝብ ጋር ቂም ለመትከል የዉሸት ሰልፉን አቀነባብሮ ያስጨፍራል። የተቃዉሞ ስሜትን በአደባባይ መግለጽ ከሆነማ ይህ አይነቱ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ብሎም ለመላዉ ጎንደር/ አማራ ህዝብ መፈቀድ የግድ ይላል።

ጦረኛ ቡድን በአሁኑ ሰዓት ሌላ ወንጀል እና ደባ ከመፈጸም ይልቅ፤ መደረግ የነበረበት፤ የወልቃይት፤ የጠገዴ እና የጠለምትን ህዝብ ባለፉት 25 ዓመታት በተፈጸመበት ግፍና በደል ይቅርታ መጠየቅ ነበር እንጂ አድሮ ጥጃ የሆነዉ የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር የአማራን መሬት በሰፊዉ ለመቆጣጠር የጦርነት ክተት አዋጅ ነጋሪት መደለቅ እና በቴለቭዥን መስኮት ውሸት መርጨት አልነበረበትም። ይህ ድርጊት ታሪክ ይቅር የማይለው አሳዛኝ ተግባር ነው። ለዚህ ሰይጣናዊ ስራው የሚገጥመዉ ምላሽም በጣም የከፋ ሊሆን ስለሚችል ለጥፋት ብቻ ትግራይ መሬት ላይ የተቀመጠዉ አቶ አባይ ወልዱ በጊዜው የያዘውን ሥልጣን እና ያስታጠቀውን ሚሊሺያ ሌላ ሊበግረው የሚችል ሃይል መሥሎት በትቢት ወይም በድንቁርና ከአንድ ጥፋት ወደ ሌላ ጥፋት መሸጋገሩ ትልቅ አደጋ ነዉ። በመላው አገሪቱ በዜግነታቸው ኮርተው፤ የሚኖሩበትን ህብረተሰብ አምነው እና ተዋደው የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት ጠገዴ የግፍ እሳት ላለማቃጠል ቆም ብሎ እንዲያስብ እጅግ እናሳስባለን።

ላለፉት 30 ዓመታት የቃፍቲያ ሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ/ጠለምት ህዝብ የአማራ ምንነቱን ተነጥቆ፤ አማራም ጎንደሬም አይደለህም ተብሎ፤ የዘር ማጽዳት ድርጊት ተፈጽሞበታል። ለዘመናት ከኖረበት መሬት ተፈናቅሎ ብዙ ትዉልድ ለስደት ተዳርጓል። ላለመሰደድ በቀየው መሞትን የመረጠ ተወላጅ፤ እጣ ፈንታው ለዘመናት ፀሐይን እንዳያይ ተወስኖበት እስር የሚማቅቀዉን ብዛት፤ የትግራ እስር ቤቶች ይቁጥሩት። በጀምላ የተቀበረዉን ደግሞ፤ ጊዜ እያወጣዉ ነዉ፤ ክቡር ገረመድን አራያ ይናገራሉ።

የዚህን አካባቢ ህዝብ ከገደለ እና ካፈናቀለ በኋላ፤ ብዛት ያላቸውን የትግራይ ተወላጅ የወያኔ ደጋፊዎቹን ተከዜን አሻግሮ አስፍሯል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ይህን ሁሉ ግፍ እና በደል ከፈጸመ በኃላ፤ በአካባቢው ለህዝበ ውሳኔ ለማቅረብ የማጥቂያ ስልት ነድፎ ተነስቷል። በቂ የወልቃይት ተወላጆች የሉምና እኔ ያሰፈርኳቸውና አንዳንድ ሆዳሞች በድምጽ ብልጫ ለኔ ድምጽ ሊሰጡ ይችላሉ ብሎ በማመን፤ የዘወትር ዉሸትና ብልጥነቱን በማጠናከር እራሱ ፌደራል ብሎ በሰየመዉ ምክር ቤት ህዝቡ ተጠይቆ ምክር ቤት ይወስናል የሚል አጀንዳ ይዞ ብቅ ለማለት እየተዘጋጀ ነዉ። ከአሁን በኋላ፤ የወልቃይት አማራም፤ ጎንደሬም የመሆን ውሳኔ የሚጸናው፤ በወልቃይት መሬት በሰፈሩ ተከዜ ተሻጋሪ የትግራይ ተወላጆች ሳይሆን፤ የመላው ጎንደር ሕዝብ ውሳኔ ነው።

ይህ የማንነት ውሳኔ ደግሞ፤ በወያኔ መሪዎች በነ አባይ ወልዱ ችሮታ የሚለገስ ሳይሆን፤ በቆራጥነት፤ እነሱ የረገጡትን ጀግንነታችን አሥመስክረን በምንጎናፀፈው ነፃነት ብቻ ነዉ።። በዚህ መልክ ቆርጠን ስንነሳ ነው፤ የጎንደር ታሪካዊ መሬት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደነበረዉ ወደጥንቱ ጎንደር ክፍለ ሃገር በአስቸኳይ ሊመለስ የሚችለው ብሎ የጎንደር ሕብረት አጥብቆ ያምናል። ይህ እንደሚመጣ ወያኔ አስቀድሞ በማወቁ፤ መላ የትግራይን ወንድ ልጅ ከመንግሥት ካዝና እየዘረፈ ሙሉ በሙሉ አስታጥቋል። ይን ለመመከት፤ ካሁን በፊት ደግመን ደጋግመን እንዳስጠነቀቅነው፤ ዛሬም እንዳለፈው፤ ለአቅመ አዳም የደረሰ ጎንደሬ በሙሉ መታጠቅ አለበት። የወልቃይት ጉዳይ፤ ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን በላይ በዜጎች ማንነት ላይ እዬተፈጸመ ያለ አስከፊ በደል ነው። በመሆኑም በቆራጥነት መስዋዕትነትን መክፈል፤ የማንነትም፤ የተወላጅ ባለቤትነትም፤ የዜግነት ግዴታ ነው።

ከዚያም በላይ! በጎንደር ህብረት አቋም እና እምነት ደግሞ፤ ይህ በጎንደር ህዝብ ላይ፤ ብሎም በሰፊዉ አማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የወያኔ ቱባ መሪ አባይ ወልዱ የክተት አዋጅ ወያኔ እራሱን እንደማነቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖ የሚመራዉ ስርዓትም የመጨረሻዉ የሞት ጣር እና ኑዛዜ ከመሆን እንደማያልፍ እርግጠኛ ሁነን እንናገራለን። ታላቁን የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ለማዳማት በፈጸሙት የአርባ አመታት የጭፈጨፋ እና የጥላቻ ዘመቻ በኪሳራ ስሌት እየገፋ የሁለቱ ማህበረሰብ እስከ አሁኑ ድረስ ችግርም ሆነ ደስታዉን የወያኔን ከፋፋይ መርዝ ተቋቁሞ በጋራ ህይወቱን እየገፋ ይገኛል። ይህ እንዳይደፈረስ ከታሰበ፤ “የትግራይ ህዝብ የጎንደርን መሬት በጉልበት እንድንገዛ ድጋፍ ሰቶናል” እያሉ የሥራዓቱ ሙስና እጃቸዉ የነካ ግለሰቦችን በማናገር በቴሌቢዥን መስኮት የሚያካሂዱት ቅስቀሳ በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብም የአቶ አባይ ወልዱን የእርስ በእርስ ጦርነት አዋጅን በመቃወም በጎንደር ሕዝብ ላይ የተቃጣዉን ጥቃት ለመጋፈጥ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። እንዲሁም የብሔረ አማራ ዲሞክራሲ ንቅናቄ (ብአዴን)ብሎ የሚጠራዉ፤ የአማራን ህዝ እወክላለሁ የሚለዉ የወያኔ አጋር ድርጅት፤ የወያኔ መጠቀሚያ መሳሪያ የመሆን የባዶ ጨዋታ ዘመን አክትሞ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የሚያካሂደዉን የመስፋፋት ዘመቻ እንቅስቃሴ ህዝቡ ተቃዉሞዉን በመግለጽ ምላሽ ለመስጠት በሚዘጋጅበት ሁኔታ ሁሉ ጣልቃ ገብቶ ተጽዕኖ ከማድረግ እንዲቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም፤ ከህዝብ አብራክ የወጣዉ ሰራዊትም የአገሩን ዳር ድንበር ከማስከበር ዉጭ የወያኔ ታዛዥ ሁኖ በዘረኛ መንግስት የተበደለ ወገኑን ተኩሶ ከመግድል እንዲቆጠብ እናሳስባለን።፤ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን አረመኒያዊ የግፍ ሥራዓት ሊሸከም ባለመቻሉ፤ በእምቢተኝነት እየተነሳሳ ያለውን ወገንህን፤ በተለይም በሽዋ፤ በወለጋ፤ በአርሲ፤ በሃረር በጋምቤላ፤ የሚያካሄደዉን ጭፍጨፋ በአስቸኳይ እንዲቆም ወገናዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። እንዲሁም፤ የወያኔ መንግስትም ብዙ ደም ሳይፈስ ስልጣን ለቆ አገሪቱን የሚያድን፤ ህዝቡን የሚያረጋጋ፤ ሁሉን ያካተተ በሕዝብ የተመረጥ መንግስት በአስቸኳይ እንዲቋቋም በጥብቅ እናሳስባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ጎንደር ህብረት።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51415

Tuesday, February 23, 2016

በኦሮሚያ ክልል ከ20 በላይ ዜጎች ትናንትና ዛሬ ተገደሉ

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የአጋዚ ጦር በወሰደው የሃይል እርምጃ ከእሁድ ምሽት ጀምሮ 20 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና 42 በላይ መቁሰላቸው ታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል በሃረርጌ መቻራ፣ በደኖ፣ ጨለንቆ፣ አወዳይ፣ ሜጨታ፣ አብሮራና፣ ሃሮማያ በወለጋ ደምቢደሎ፣ ቄለም፣ ሳሲዶ፣ ወረዳ ባሎ ከተማ በአርሲ በቆጂ፣ በቡሌ ሆራ በገናሌ፣ በምስራቅ ሸዋ አዳሚቱሉ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን ከባድ መሳሪያ ታንክና መትረየስ የታጠቁ የአጋዚ ጦር በተማሪዎችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ በመተኮስ 20 በላይ ኢትዮጵያውያንን መግደሉ ታውቋል።

በወለጋ ቄለምና ባሎ ከተማ አመኑ ተረፈ፣ ገለታ ነገሮ፣ ቢሉሱማ አብዲሳ፣ ቶሌራ መርጋ እና አርገኔ የተባለች ሴት በሰቃቂ ሁኔታ በመግስት ሃይሎች ተገድለዋል።

በሃረርጌ በመቻራ በበደኖና፣ ጨለንቆ ሃሰን አብደላ፣ አሳድ ኢብራሂም እና ሮባ ማሞ የተባሉ ወጣቶች በጥይት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

በመቻራ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ደረቱ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ ሌላ ወጣት አስከሬን ተሸክመው ጎዳና ላይ ሲወጡ ታይተዋል።

በዚሁ ከተማ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ 20 በላይ ሰዎች ወደገለምሶ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ታውቋል።
ተቃውሞ ከተነሳበት ህዳር 1, 2008 ጀምሮ ተቃውሞው የጸረ-ሰላም ሃይሎች ነው ከዚያም የመልካም አስተዳደር ቸግር ያመጣው ነው ሲል የተለያዩ መግለጫዎችን ያወጣው የመንግስት፣ በአርሲ-ሸሸማኔ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ጉዳዩ የጸረ-ሰላም ሃይሎችና አክራሪዎች ነው በማለት ንብረቶችን መውደማቸውን ገልጿል።ይሁን እንጂ የመከላከያ ሰራዊትና ፊዴራል ፖሊስ በወሰዱት የሃይል እርምጃ፣ ስለሞቱት ዜጎች ቁጥር እስካሁን አልተገለጸም።

ባለፉት 3 ወራት በተካሄደው ተቃውሞ 300 በላይ ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ፣ ቁጥሩ በውል ያልተገመቱ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ 5000 በላይ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል


ኢሳት (የካቲት 22 2008)

http://www.satenaw.com/amharic/archives/13320

Friday, February 19, 2016

በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና በጉደር ዛሬ ብቻ 16 ሰዎች ተገደሉ በምስራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ ዛሬም ሕዝብ ከአጋዚ ጦር ጋር ተፋጧል

        የአጋዚ ጦር በነቀምት (Photo)

(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ አካባቢ በምትገኘው አባሮ መንደር የአጋዚ ጦር 4 ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደሉ ተሰማ:: የሕዝቡ ተቃውሞ በምስራቅ ሐረርጌ የተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች እንደቀጠለ ነው::

በምስራቅ ሐረርጌ በጉራዋ ወረዳ በጨፌ ጃናታ መንደር በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ የአጋዚ ጦር በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ማቁሰሉን ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል::

በምስራቅ ወለጋ ነቀምት በተነሳ የህዝብ ቁጣም የአጋዚ ሠራዊት እንዲሁ በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ያጠቃ ሲሆን ወጣት ሴቶች ሳይቀሩ የአጋዚ ጥይት ሰለባዎች መሆናቸውን ምንጮች ዘግበዋል:: የነቀምት ከተማ ሄልሜት በለበሱና ሙሉ የጦር መሳሪያ በታጠቁ የአጋዚ ሠራዊት የተከበበች ሲሆን በከተማዋ ለሚነሱ ጥቃቅን ጥያቄዎች ሁሉ ጥይት ምላሽ እንደሆነ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ዛሬ ሻሸመኔ አቅራቢያ በምትገኘ አባሮ መንደር በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ ፌደራሎች 4 ወታቶችን መግደላቸው ሲገለጽ በኮፋሌ እና አካባቢዋ ደግሞ 12 ሰዎች መገደላቸውና ከ20 በላይስ ሰዎች በጥይት ክፉኛ መቁሰላቸው ተዘግቧል::


በተለይ ዛሬ በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና በጉደር አካባቢዎች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን የሚገልጹት ምንጮች የሕዝቡም ቁጣም በዚያው ልክ እንደቀጠለ ገልጸዋል:: በተለይ በነቀምት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት የሆኑ ወታደሮች ሳይቀሩ በአጋዚ ሰራዊት በጥይት መቁሰላቸው ተሰምቷል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51251

Wednesday, February 17, 2016

ቤልጂየም ከግዛቷ ያባረረቻቸው ኤርትራዊው ሰደተኛ በ አ/አው የ ቦሌ አርፖርት ውስጥ “እየተሰቃዩ” ነው

እባካችሁ ወላጅ አባቴን ከመከራ እና ሰቃይ ታደጉልኝ ሴት ልጃቸው የተማጽኖ ጥሪ ከኖሮዊይ    በውርሃ ጥቅምት 2015  ጎረቢት  ደቡብ ሱዳን ወደ ምእራብ አውሮፓዊቷ ቤልጂየም በመጓዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁት ኤርትራዊው አቶ ተስፋ ገብር ሃይሌ ደስታ የጠበቁት እና የሰነቁት የጥገኝነት ጥያቄ መልካም ዜና ይዞ አልመጣም ነበር።

ኤሪ ጋዜትየተባለ ድህረ ገጽ ሰሞኑን እንደ ዘገበው ከሆነ ቤልጂየም/ብራስልስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነባቸው 52 አመቱ አቶ ተስፋ ገብር ይዘውት የነበረው መጠኑ ለጊዜው ያልተገለጸ ገንዘብ እና ንብረት በቤልጂየም የኢምግሬሽን እና የደህነነት ሃላፊዎች ከመነጠቅ አልፎ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸውወደ መጣህበት ወደ /ሱዳን እንባርሃለንበሚል ስሜት ያለ ውዴታ በግዴታ በየካቲት 2 /2016 እጃቸው በካቲና ተጠፍሮ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነ አውሮፕላን ከተጫኑ በሁዋላ / ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደረሱ ወደ ቤልጂየም ከማቅናታቸው በፊት የነበሩባት አገር (/ሱዳን ) ለመመለስ ሀጋዊ የጉዞ ሰነድ አልባ በመሆናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግለሰቡን ወደ ሌላ አገር ለማሸጋገር ውክልና ስለ ሌለው ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ኤርትራም እንዳይመለሱ ቤልጂየም ከምእራባዊያን ጎረቤቶቿ ሊደረሰባት የሚችለው ብርቱ የሰበዊ መብት ጥሰት ተቃውሞን በመሰጋት አና ዋስትና ባለማግኘታቸው በአ/ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ከብረት ከተሰራ ወንበር ላይ ያለ ብርድ ልብስ በብርድ እና በሙቀት እየተቀጡ መሆናቸው ተገልጿል።

በኖሮዊይ የሚገኙ የአቶ ተስፋ ገብር ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ ያደረገው ዜና ዘገባው አቶ ተስፋ ግብር በቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ቆይታቸው ለየተለያዩ የሰነልቦና ችግሮች ከመጋለጣቸው ባሻገር ወደ ኤርትራ ወይም ወደ /ሱዳን ካለሆነ ደግሞ ወደ ኡጋንዳ ሊባረሩ እንደሚችሉ የሚገልጹ ማሰፈራሪያዎችም እንደገጠሟቸው ተነግሯል የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቢሆን የቤልጄየም መንግስትን ፍላጎት ለማርካት ሲል ብቻ የሰብ አዊ መብት ረገጣን ሸሽተው አውሮፓን መዳረሻ በማድረግ የተሰደዱት የአቶ ተስፋ ገብር እና መሰል ሰደተኞችን የምርጫ እና የጥገኝነት ፍላጎትን በመጣረስ የተፈጸመ በመሆኑ አየር መንገዱም ቢሆን ለከፋ ትችት የተዳረገ ሲሆን የወላጅ አባቷ የሰብእዊ መብት መጣስ ያሰጋት በኖሮዊይ አገር የምትኖረው የአቶ ተሰፋገብር ሴት ልጅ ኢትዮጵያ መንገድ የፈጸማቸው ድርጊቶችን በመኮነን ወላጅ አባቷ ቢቻል የፖለቲካ ጥገኝነት ወደ ጠየቁባት ወደ ቤልጂየም እንዲመለሱላት አሊያም / ለሚገኘው ለአለማቀፉ የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)ተላልፈው እንዲሰጡላት ተማጽናለች። አለም አቀፍ ዝና እና ክብር ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግለሰቡ ላይ ስርቶታል ሰለ ተባለው የሰበዊ መብት ጥሰት ሆነ በአሁኑ ወቅት በርካታ አለማቀፍ አየርመንገዶች ከምእራብ አውሮፓ በገፍ የሚባረሩትን ሕገ ወጥ ሰደተኞችንለመንገደኞቻችን ደህንነት ሲባል እንጭንምየሚል አቋሟቸውን በሚያሰሙበት በአሁኑ ወቅት የኛው አየር መንገድ ለምን ይህንን መሰሉን አደጋ በራሱ እና በደምበኞቹ ላይ ለመጋበዝ እነደ ፈለገ እሰከ አሁን ድረስ የሰጠው ማብራሪያ ማስተባበያም ሆነ ይሁንታዊ ምላሽ አለተገኘም።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ቤልጂየም ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ የደህንነት አባል ላይ ተመሳሳያ ኢሰብ አዊ የመብት ረገጣ ያደረገች መሆኑ የሚታውስ ሲሆን ፍሬ ሃሳቡም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው። አለም ሰገድ ተካ የተባለ አገዛዙን በመቃወም በወረሃ ጥር 27 / 2001 በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ በመደበቅ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ሲጥር አውሮፕላኑ ግብጽ ላይ ነዳጅ ለመሙላት ሲቆም አለምሰገድም አውሮፓ የደርሰ መስሎት ከአውሮፕላኑ ጉያ ብቅ ይላል። 28 አመቱ የደህንነት ሰራተኛው አቶ አለም ሰገድ ሁኔታን በድንጋጤ የተመለከቱት ፕይለቶቹ ለራሳቸውም ደህነነት በመፍራታቸው አቶ አለም ሰገድ ካይሮ ላይ እጁን ለግብጽ ኢሚግሬሽን ባለሰልጣናት እንዲሰጥ ለማግባባት ቢሞክሩም የግብጽ የደህንነት ባለሰልጣናት ግን ኢትዮጵያዊው የደህንነት ሰራተኛው ካይሮ ላይ እጁን መሰጠት አይችልም (አሻፈረን )በማለታቸው ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶቹም የአየር መንገዱ የደህንነት ክፍል አባሉ አቶ አለም ስገድን ሳይወዱ በግድ ወደ ቤልጂየም ይዘውት ይጓዛሉ።

ቤልጂየም/ብራስለስ አንደ ደረሱም በዘመኑ የኢ አዲጋዊ አጠራር የክልል ሶስት ተወላጅ በመሆኑ ብቻ በአገዛዙ ሹማምንቶች የተለያዩ በደሎች አንደሚደርሱበት ለህይወቱም እንደሚሰጋ ፣የደህነነት ሰራተኛ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ በማሳየት በብራስልስ/ቤልጂም የፖለቲካ ጥገኝነት ያቀርባል። የአቶ አለምሰገድ ጉዳይን በግርድፉ የተመለከቱት የቤልጂየም የኢሚግሬሽን ሃላፊዎች የጥገኛ ጠያቂዎን ጉዳይ በአንክሮ ሳይመለከቱ የአቶ አለም ሰገድ መታወቂያ በመያዝበደል አደርሱብኝወደ አላቸው የኢሕ አዲግ ደህንነት ሹማምንቶች ፋክስ በማድረግ የማብራሪያ ጥያቄ ያቀርባሉ። / ገዢዎች በኩልየምትሉት ግለሰብ የእኛ አባል አይደለም፣ አሸባሪ ሊሆን ይችላልወዘተየሚል ምላሽ በማግኘታቸው አቶ አለምሰገድ ተደብቆ ወደ ቤልጂየም ለመኮብለል በሞከረበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሬሽን ሰራተኞች በግዴታ ተጭኖ ወደ / ለመመለስ ይገደዳል።

አቶ አለምሰገድ ከቦሌው አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስም የጠበቁት ዘወትር የሚወዱት ቤተሰቦቹ ሳይሆኑ በደል አደርሱብኝበማለት ጥሏቸው የሄደው የኢ ዲግ የደህነነት ሹማምንቶች ነበሩ። አቶ አለም ሰገድ ቦሌ እንደደረሰ ብዙም ሳይቆይ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የወሰዳል። በዚህ ወቅት ነበር የቀድሞ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ (ኢነጋማ ) የስራ አስፈጻሚ ኮሜተ አባላት ፣መብረቅ/መብሩክ ለተባሉት ጋዜጦች እና ለተለያዩ የነጻ ፕሬስ ውጤቶች ይሰሩ የነበሩት ፣በአሁኑ ወቅት ደግሞ በስድት አለም ከምድረ አሜሪካ ከላስ ቬጋስ ከተማ ዘውትር እሁድ በአካባቢው ሰአት አቆጣጠር 630 pm (በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 1230) በአማሪኛ ቋንቋ የሚተላለፈው እና በራሱ ድህረ ገጽ hiber radio .com እንዲሁም በመላው አለም ተደራሽነት እና ታዋቂነት ባላት ሃበሻ ድህረ ገጽ አማካኝነት መረጃ ለሚናፍቀው ህዝባችን የወቅታዊ መረጃዎች ምንጭ የሆነው የሕብር ራዲዮ መሰራቾች እና ዋና አዘጋጆች ለሁኔታው ልዩ ትኩረት በመስጠት የምርመራ ጋዜጠኝነት ክህሎታቸውን (ኢንቨስቲጊቲቭ ጆርናሊዝም ሪፖርቲንግ ) በመጠቀም ፣ጉዳዩንም ከሰብ አዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዘ መሆኑን በመገንዘብ እና ጉዳዩን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይ ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ በፍጥነት ያሳውቃሉ

የቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሪሽን ሃላፊዎች ከኢሕ አዲግ የደህንነት ሹማምንቶች ጋር በመሆን በአቶ አለምሰገድ ላይ የፈጸሙት የሰበዊ መብት ረገጣዎችን የተመለከቱት በፓሪስ/ፈረንሳይ እና በጀርመን/በርሊን የሚገኙ የአውሮፓ የዲፕሎማቲክ አባላት በቤልጂየም ሕገወጥ እርምጃ በመደናገጥ ቤልጄየም የወሰደችው የተቻኮለ የተሳሳታ እና ግዴለሽነት የተላበሰው እርምጃዋን በአጽነኦት በመኮነናቸው የተነሳ የብራስልስ ባለሰልጣናት በሰሩት ሰህተተ በመጸጸት ሁኔታውን ለኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና የደህነነት ሹማምንቶች አበከረው በማስጠንቀቅ እና በመማጸን በአቶ አለምሰገድ ላይ ምንም አይነት የአካላዊ እና የስነልቦናዊ ተጽኖ እንዳይደርስበት በማሰገንዘባቸው አቶ አልምሰገድ ከታሰረበት የማእከላዊ እስር ቤት ብዙም ሳይቆይ እንዲፈታ፣ ቤልጂየምም በሰራቸው ትልቅ ስህተት አቶ አለምሰገድን በግልጽ ይቅርታ በመጠየቅ ለአቶ አለም ሰገድምም የሞራል ማካካሻ የሚሆን መጠነኛ የገንዘብ ጉርሻ መሰጠቱን የቀደሞዎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላቱ እና የአሁኖቹ የህብር ራዲዮን አዘጋጆቹ ኢህአዲግ ዘውትር ነጻው ፕሬስንየተቃዋሚዎች ልሳናትአደርጎ ለመፈረጅ ቢሞክርም ነጻ ፕሬስ መኖር ለአገዛዙ ሰዎች ሳይቀር በጭንቀት ቀን እንደሚጠቅማቸው የአቶ አለም ሰገድ ገጠመኝን በናሙናነት በመጥቀስ በትውስታ መነጽራቸው. ይመለከቱታል

http://www.satenaw.com/amharic/archives/13007