Wednesday, August 31, 2016

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ጎንደርና ጎጃምን እንደሶሪያ ሊጠፋ ተዘጋጅቷል – ታንኮች ጭምር ከነቀምት ቡሬ ጎጃም እየተጓዙ ነው

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አማራውን በተለይም ጎጃም እና ጎንደርን እንደ ሶሪያና ሕዝቧ ሊያወድማት እየተዘጋጀ ነው:: ዛሬ የሕወሃት ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመከላከያ ሰራዊቱ አማራውን እንዲያጠፋ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ በደሴ መስመር ብረት ለበስ መኪናዎችና የጦር መሳሪያዎች ወደ ጎጃም እና ጎንደር እየተጓዙ መሆናቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::

እንደ ምንጮች ዘገባ ጨጨሆ ላይ እነዚህን በደሴ መንገድ እየተጋዙ ያሉትን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮችን ህዝብ እንዲያስቆማቸው ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ምን ላይ እንደደረሰ ግን -ሐበሻ ለማወቅ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በሌላ በኩልም ከነቀምት ወደ ቡሬ ጎጃም የጦር ታንኮች እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:: የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ በጎጃም እና ጎንደር ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ እልቂት ለማድረስ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ቆርጦ በመነሳቱ ታንኮችን ጭምር እያጋጋዘ ነው::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/65064

Sunday, August 21, 2016

“ኢትዮጵያ አገሬን እወዳታለሁ” አትሌት ፈይሳ ለሌሳ

ትላንታን ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን ማን ያወቃቸው ነበር ? ሆኖም ኮሎኔሎ እሥር ቤት ሆነው የትግል ምልክት ሆነዋል። አንድ ግለሰብ ናቸው። ግን በአሁኑንወሳኝ ወቅት ታሪክን እየሰሩ ያለኡ ግለሰብ።

በተመሳሳይ ሁኔታ ፈይሳ ለሌሳን ማን ነበር የሚያውቀው ? ይህ ወጣት ዛሬ ግን አሰደናቂ ታሪክ ሰራ። አንድ ጦማሪ እንደ ጻፈው ወርቅ አላገኝም፤ ሁለተኛ ነው የወጣው፣ ግን የአልማዝ ሜድሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

ኢትዮጵያ አገሬን እወዳለሁ፣ ግን የሕዝብ ስቃይ ይሰማኛልያለው አትሌንት ፈይሳ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በአጋዚዎች እጅ እየደረሰ ያለውን ግፍ በአደባባይ፣ በኦሎምፒክ መዝጊያ ቀን ለአለም በሙሉ አጋልቷል። ይህ ወጣት የፈጸፈው ገድል ልቤን በደስታ አቅልጦታል። ይህ ወጣት አኮኩሩቶኛል””

I am Athlete Feyisa Lilesa, clocked 2nd and took Silver in this year’s Rio2016 Olympic in men’s Marathon, crossed the finishing line with my hands crossed, a sign that is now widely recognized as a symbol of civil resistance in Ethiopia, a country gripped by successive anti-government protests which began in Nov. 2015. I love my country Ethiopia!


ከህዝብ ስለተገኘሁ የህዝብ ስቃይ ይሰማኛል ይህንንም ለአለም ህዝብ በሚዲያ ለጠየቀኝ ተናግሬአለሁ ጀግና ነኝ ባልልም የአቅሜን ሞክሬአለሁ! ባላችሁበት በርቱ!

🗣ሩጫ ለሀገር ነፃነትም ይውላል ድሉ በወያኔ ህወሓት እየተረገጠ ላለው ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም ነፃነት ለሚናፍቀው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን ድሉ የኢትዮጵያዊያን ነው። ጎንደሬዎችና ኦሮሞዎች ባህርዳሮች ነፃነት ናፋቂዎች ሁላቹ በርቱ። ነፃነት ናፍቆኛል አፈናው በዝቶብኛል!
አንደኛ ባለመውጣቴ ባዝንም አላማዪን አሳክቻለሁ።አይቆጨኝም

http://www.satenaw.com/amharic/archives/19850

Thursday, August 18, 2016

ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው


 “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪክፉኛ ናፍቋል!
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል።ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላልበሚሉናአንመልስምሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።

አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።

ህወሃት በግድያው ከገፋበት ከአሜሪካ በኩል የሚሰጠው ምላሽ እንደ ወትሮው በኤምባሲ ወይም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንደተለመደውጉዳዩ አሳስቦናልየሚል ተራ መግለጫ እንደማይሆን ማረጋገጫ መሰጠቱን ጎልጉል የሚያምናቸው የዲፕሎማት ምንጮች ከአሜሪካ ተናግረዋል። እንድ መረጃ አቅራቢዎቹ ቀጣዩ የአሜሪካ አቋም በውጭ ጉዳይ /ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) ዋና ኃላፊ ወይም ከፕሬዚዳንቱ /ቤት (ኋይት ሃውስ) በኩል የሚተላለፍ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፉት ሳምንታት ግማሽ ያህል የህወሃት ባለስልጣናት አሜሪካ ደርሰው መመለሳቸውን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሌላ ዜናን ለማስተባበል ሲሞክሩ ሳያስቡት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

በሌላ ዜና በህወሃት ውስጥወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነውበሚሉናሊመለስ አይገባምበሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።

ወልቃይትን እንመልስባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ።ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል? ውርደት ነውበሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።

እንደ ዘጋቢያችን መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩትአንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።

ወልቃይት የኖሩት ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።

በዚህ ሁለት ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።


ህወሃት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡

http://www.goolgule.com/tplf-discussing-to-give-back-wolkait/