Monday, April 2, 2018

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ፣ የጀግኖች አርበኞች ገድልና የሃገራችን ታሪክ ሲነሳ ለምን ወያኔን ያመዋል

ታላቋ ብሪታኒያ በድንበር የሚዋሰኑትን ሱዳንን እና ግብፅን በቅኝ ግዛት እና በበላይ ጠባቂነት (Colony and de facto protectorate 1882 _ 1956) ታስተዳድር ነበር። በወቅቱ እንግሊዝ ትከተለው የነበረው የአገዛዝ ስልት ግብፅን በቀጥታ እራሷ እያስተዳደረች ነገር ግን በሱዳን ውስጥ ለእሷ ታማኝ የሆኑ ግብፃውያንን በመሾም ሃገራቱን ትገዛ ነበር። ጣሊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በቆየበት በ5ቱ ዓመት የአርበኞች ትግል ወቅት በየወረዳውና አውራጃው ለእሱ ታማኝ የሆኑ ባንዳዎችን ይሾም ነበር። በጣም የሚገርመው ቀኝ አዝማች፣ ግራ አዝማች ወዘተ እያለ ባንዳዎቹን እንደ ኢትዮጵያ ባህል ግራዚያኒ ሹመት መስጠቱ ነበር። በመሆኑም እውነተኛዎቹን ከሃሰተኞቹ ለመለየት ለጊዜውም ቢሆን አደናጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል። የመለስ ዜናዊ፣ የስዩም መስፍን፣ የአርከበ እቁባይ እና የስብሃት አባቶችና አያቶች የጣሊያን ባንዳ ሹመኞች እንጂ በኢትዮጵያ መንግስት የተሾሙ አለመሆናቸው ይነገራል። በመሆኑም በወቅቱ በርካታ ለጣሊያን ያደሩ ባንዳዎች ከፋሽስት ጣሊያን ጎን በመቆም በሰላይነት፣ በቅጥረኛ ወታደርነት፣ በዳኛነት፣ በቢሮ የጽህፈት ስራና በመሳሰሉት ይሰማሩ ነበር። በወቅቱ በጠላት የተሾሙ ባንዳዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ለፋሽስት አለቆቻቸው ከሚያቀርቧቸው ክሶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦
  • ቀን ቀን ገበሬ፣ ሌሊት ደግሞ አርበኛ ነህ፣
  • አርበኛ ቤትህ ታሳድራለህ፣ ስንቅና መረጃም ታቀብላለህ፣
  • ከአርበኞች ጋር ግንኙነት አለህ፣ ጥይትና መሳሪያ ገዝተህ ልከህላቸዋል፣
  • የኢትዮጵያን ባንዲራ በሰርግ ወይም በሃዘን ጊዜ ተጠቅመሃል (ሰቅለሃል)፣
  • ኢትዮጵያን ለማሰልጠን ለመጣው ለታላቁና ለገናናውን የጣሊያን መንግስት አልገዛም ብለሃል ተቃውመሃል፣ ሌሎችንም ቀስቅሰሃል ወዘተ የሚሉ ነበሩ።

ለሃገራቸው ሰምአት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል ህዝቡን ለጣሊያን አትገዙ ብለው አውግዘዋል በማለት መረጃውን ለጣሊያን ሹማምንት ያቀበሉት ጣሊያን በህዝቡ ውስጥ ለስለላ የሰገሰጋቸው ባንዳዎች ነበሩ። የፍርድ ሂደቱንና ቅጣቱን ብንመለከት አቡነ ጴጥሮስ ላይ ለፍርድ ከተቀመጡት ከሶስቱ በጣሊያን ከተሾሙ ዳኞች ውስጥ አንዱ ትግሬ ባንዳ ሲሆን በመጨረሻም  ጥፋተኛ ናቸው በማለት በሞት እንዲቀጡ ብይን ከሰጡ በኋላ አቡነ ጴጥሮስን ህዝብ በተሰበሰበት ዓደባባይ ላይ ግምባና ደረታቸውን በጥይት ተኩሰው ከገደሏቸው የጣሊያን ወታደሮች ውስጥ አንዱ ለፋሺስት ያደረ የትግሬ ባንዳ ወታደር ነበር። ህዝቡንም ቢሆን የኢትዮጵያን ባንዲራ በመኖሪያ ቤታችሁ አጥር (ምሰሶ) ላይ አውለብልባችኋል በማለት የእስርና የግድያ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር። በመሆኑም ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያውለበለቡ ጀግኖችን ማንገላታት ከጌቶቹ ከፋሽስት ጣሊያኖች  የወረሰው ነው። እንደሚታወሰው በትግሉ ወቅት በየገባበት ከተማ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እያወረደ የህወሃትን አርማ በመስቀል የኢትዮጵያን ባንዲራ ግን ከክብሯ አውርደው እህልና ቅራቅምቧቸውን መቋጠሪያ ከረጢት ያደርጉት ነበር። በአንድ ወቅት ሟቹ መለስ ዜናዊ ሰራዊትህ ለምን እንደዚህ ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠየቅ፣ ባንዲራ ጨርቅ ነው በማለት እንደተሳለቀ ይታወሳል። ነገር ግን ወያኔ ሲያጣጥለው የነበረውን ባንዲራ እነ እስክንድር እና ተመስገን በክብር ሲያውለበልቡ በመታየታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ዛሬ በወያኔ አገዛዝ ዘመን ትናንትና በአድዋ፣ በማይጨውና በ5ቱ ዓመታት የኢትዮጵያ አርበኞች ትግል ወቅት ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሰሱለትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ መውለብለቡ ወንጀል ነው መባሉ በህወሃትና በወራሪው በፋሽስት ጣሊያን መሃል ከቆዳ ቀለም ውጪ ሌላ ልዩነት ያለ አይመስልም። ለህሊናህ ፍረድ ብባል እንደኔ በህግ መጠየቅ አለበት ብዬ የማምነው “ባንዲራ ጨርቅ ነው” ብሎ የተሳለቀ እንጂ የአባቶቹን ሰንደቅ አላማን በክብር ያውለበለበ አይደለም።

ታሪክን ወደ ኋላ ሄደን ለማየት ብንሞክር የጣሊያን ጦር በ1988ዓ.ም አድዋ ላይ በአፄ ምኒልክ ብልህ አመራርና በጀግኖች አባቶቻችን ድል ተመቶና ተዋርዶ ከሃገራችን ከተባረረ በኋላ ቂም ቋጥሮ አርባ አመት ኢትዮጵያን ለመበቀል ተዘጋጅቶ በታንክ በአውሮፕላንና በዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ቀኝ ግዛት ለማድረግ በሃገራችን ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት ከፈተ። የኢትዮጵያ አርበኞች ከመሃል ሃገር ተነስተው ወደ ማይጨው በእግር በፈረስ በመጓዝ ጦርነቱ ወደሚደረግበት ትግራይ ተመሙ። ይሁንና ጣሊያኖች የራሳቸውን መደበኛ ወታደር ብቻ ሳይሆን ባንዳዎችን መሳሪያ አስታጥቀው ጠበቋቸው። በመሆኑም ባንዳ ሽፍቶች ወገናቸው የሆኑት ኢትዮጵያውያኖችን መንገድ እየጠበቁ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም እየገደሉ መሳሪያቸውን ይነጥቁ፣ በአጋሰስ ተጭኖ ይላክ የነበረ ስንቅና ትጥቅ ይዘርፉ ነበር። በተለይ ከዋናው ሰራዊት መንገድ በመሳት ተነጥለው በምግብና በውሃ ጥም እጦት የሚንከራተቱትን አርበኞች መሳሪያቸውንና ንብረታቸውን ለመዝረፍ አድፍጠው ያጠቋቸው ነበር። በመሆኑም አርበኞቻችን ያደርጉት የነበረው ትግል ከወራሪው የጣሊያን ወታደር ጋር ብቻ ሳይሆን ከትግሬ ባንዳ ሽፍቶችም ጭምር ነበር። ጊዜው ስለራቀ አሁን ሲያስቡት ቀላል ሊመስል ይችል ይሆናል እንጂ አባቶቻችን ስንት ውጣ ውረድ አሳልፈውና ተንከራተው፣ ከውጭ ወራሪ ጠላት እና ከውስጥ ባንዳ ጋር ታግለው ነው ሃገራችንን በነፃነቷና በአንድነቷ ጠብቀው ያቆዩዋት። (የሃበሻ ጀብዱ የተባለውን በአዶልፍ ፓርለሳክ የተጻፈውንና በተጫነ ጆብሬ የተተረጎመውን የ1989 ዓ/ም እትም መጽሐፍ የባንዳን ክህደትና ሸፍጥ በተመለከተ ብዙ መረጃ ይሰጣል)።
ፋሺስት ጣሊያን ሰዎችን በባንዳነት ሲመለምል ከሚከተለው መስፈርት ውስጥ ዋናው ግለሰቦቹ ከሌላ ሰውም ሆነ ከሃገራቸው በፊት እራሳቸውን የሚያስቀድሙ፣ ለጥቅም ያደሩ እራስ ወዳድ መሆናቸው ነው። በመሆኑም ንግስና ይገባናለ የሚሉ ያኮረፉ የትግሬ ባላባቶች የነበራቸው የስልጣን ጥማትና ራስ ወዳድነት በቀላሉ ለጣሊያን ፕሮፓጋንዳ ሰለባነት አጋልጧቸዋል። ይህ ለጥቅም ሲባል ሌላውን ሰው ለጠላት አሳልፎ የመስጠት ባህሪ በቆይታ ከግለሰብ ወደ ማህበረሰብ እያደገ (እየተዛመተ) በመሄድ ትግራይ ብቻ ትጠቀም ወይም (Tigray First) ወደሚል የቡድን ዝርፊያና ወደ ዘረኝነት አደገ። በዚህ የስግብግብነት ባህሪያቸው ላይ የፋሺስት ያልተቋረጠ የጸረ አማራና የጸረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ፣ ከደርግ ጋር ሲዋጉ ይከተሉት የነበረው ማህበረሰብን ሁሌም በጨቋኝና በተጨቋኝ መደቦች የሚከፍለው የኮሚኒስት ፍልስፍና፣ የአረብ ሃገራት በእርዳታ ስም ያደርጉት የነበረው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፣ የወያኔ አመራሮች ከላይ እስከታች የነበራቸው የትምህርት እጦት፣ የግንዛቤና የባህሪ ችግሮች ሲጨማመሩበት ምን ያህል ሰዎቹን፣ ስግብግብ፣ እራስ ወዳድና ደም የጠማው ክፉ አውሬ (Beast) ሊያደርጋቸው እንደሚችል መገመት ይቻላል።
ወራሪው ፋሽስት ጣሊያን በአምስቱ ዓመታት ቆይታው የገነባውን መንገድና ሕንፃ በመመልከት የኢትዮጵያ አርበኞች ጣሊያንን ተዋግተው ማባረራቸውን ለጣሊያን ያደሩ ባንዶች ሲኮንኑና ሲቃወሙ መስማት የተለመደ ነበር፡፡ ይህ አባባላቸው መነሻው ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ላሰለጥን ነው የመጣሁት የሚለው ፕሮፓጋንዳ ነው። እነዚህ በቀኝ መገዛትን ይደግፉ የነበሩ ባንዶች ፋሽስት ጣሊያን በኢትዮጵያ በመቆየቱ ለሚያገኙት ጥቅም እንጂ የህዝቡ ሞትና ስቃይ፣ የሃገር ክብርና ነጻነት መጓደል አይቆረቁራቸውም ነበር። ፋሽስት ጣሊያን ቢቆይ(በቀኝ ቢገዛን)መንገድና ሕንፃ ይገነባልን ነበር የሚለው ደካማ አስተሳሰብ እኛ ኢትዮጵያኖች እራሳችን ሠርተን ሀገራችንን መለወጥ፣ መገንባት፣ ማሳደግ እንችላለን የሚል በራስ የመተማመን ስሜት የሌለው የአባቶቹን ታሪክ ወደኋላ ሄዶ መመልከት ያልቻለ ነው። የአክሱም፣ የላሊበላና የጎንደር ስልጣኔን ማየት የተሳናቸው፣ አፄ ምኒሊክ መንገዱን፣ ስልኩን፣ ባቡሩን፣ መኪናውን፣ ዘመናዊ የመንግስት መዋቅርና ስልጣኔና የመሳሰለውን እንዳልጀመሩ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የመርዝ ቦንብ እያዘነበ የገባውንና 30ሺህ የአዲስ አበባን ህዝብ የጨፈጨፈውን ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማሳደግ (ለማሰልጠን) ነው የመጣው በማለት ባንዶች ማናፈሳቸው፣  የፋሽስት አስተሳሰብ እራስን ዝቅ የማድረግን፣ እኛ ብንማር፣ ብንሰራ በራሳችን እውቀትና ልፋት ብንጥር ሃገራችንን እናሳድጋለን የሚልን አስተሳሰብ የሚፃረርና የሚያቀጭጭ፣ የበታችነትን ስሜት ውጤት ነው። ባንዳ ክብርም ሆነ ፍቅርና ወንድማማችነት አያቅም። የባንዳ አልፋና ኦሜጋ ጥቅም እንጂ የሃገር ነጻነት፣ የወገን ፍቅር፣ ያባቶች ታሪክና ተጋድሎ አይደለም። ለእነሱ ሴረኛነት እንጂ እውነተኛነት ቦታ የለውም። ሉዓላዊነት፣ ነጻነት፣ ኩራት የሚባሉ የመንፈስ ልእልና የላቸውም። ብርሃንና ጨለማ ህብረት እንደሌላቸው ሁሉ አርበኝነትና ባንዳነት ፈጽሞ አንድነት የላቸውም። እኛና እነሱ የተለያየ ፍላጎትና ማንነት ያሉን የሁለት ዓለም ሰዎች ነን። ምናልባት በቆዳችን (በመልክ) ልንመሳሰል እንችል ይሆናል እንጂ ሊታረቁ የማይችሉ የተለያዩ ስነልቦና ያለን ሰዎች ነን።
ጣሊያን ሃገር ውስጥ እያለ በሹመኝነት ቢሮክራሲው ውስጥ ተሰግስገው የነበሩት ሹምባሽ ባንዶች ልክ ጣሊያን በአርበኞች ትግል ከሃገር እንደተባረረ ሁኔታዎች አስገድዶን እንጂ ንጉሳችንንና ሃገራቸንን ጠልተን አይደለም በማለት በተገለባባጭ የእባብ ፀበያቸው ንጉሱን ተማፀኑ። ቀ/ኃ/ስላሴ የፈራረሰችና በፋሽስት ዝብርቅርቋ የወጣን ሃገርን ለማስተካከል ብዙ ስራ እንደሚጠብቃቸው ግምት ውስጥ በማስገባት ሃገሪቷን ለማረጋጋት ሲሉ ለባንዳዎቹ ይቅርታ በማድረግ ቀጥታ ሃገርን በማደራጀትና በማቅናት ስራ ተጠመዱ። ይሁን እንጂ ሹምባሽ ባንዶች በጣልያን ጉያ ስር ሆነው አርበኛውንና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊውን እየሰለሉ እንዳላስፈጁ፣ ከድል በኋላም ሴረኛነታቸውን ባለመተው ከንጉሱ ስር እየተልከሰከሱ በአርበኛው ላይ የእባብ መርዛቸውን ይረጩ ነበር። ሃገርን ሲያደሙ የነበሩ ባንዶች በቢሮክራሲው (በመንግስትን ስልጣን) ውስጥ ተሰገሰጉ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ያየውንና የታዘበውን በስነ ቃል እንዲህ ብሎ ገለፀ።
“እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፣”

ተምረናል የሚሉ የዘመናችን የባንዳ ልጆች ይህ እንደ ጥላ ሁሌም የሚከተላቸው አሳፋሪ የክህደት ታሪካቸውን ለመሸሽ እንደ መጀመሪያ አማራጭ ያስቀመጡት ከእውነት የራቀ ለእነሱ የሚያመቻቸውን የሃሰት ትርክት በመፃፍ ያችኑ ተረት ተረታቸውን እንደ ዳዊት እያነበነቡ እራሳቸውን ማጽናናት ነው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገድልና ታሪካቸው፣ የጦርነት ውሏቸው በተነሳ ቁጥር ቁስላቸውን እየነካካ ስለሚያሰቃያቸው ኢትዮጵያን ከነታሪኳ አንድ ላይ ለማጥፋት ይከጅላቸዋል። የአክሱም ስልጣኔ ለትግሬው ምኑ እንደሆነ ቢጠየቁ ታሪክ አጣቅሰው በመረጃ መናገር የማይችሉ ደናቁርት በባዶ እብሪት ተወጥረው አክሱም ለወላይታው ምኑ ነው እያሉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያላቸውን ንቀት በአደባባይ ይገልጻሉ። እንደ እብደትም ሲያደርጋቸው ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ነው ያላት፣ አርበኞች የተዋደቁለትን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ ነው እያሉ ይሳደባሉ። የባንዳ ክህደት በባንዲራ ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ጀግኖቿንም በማዋረድና የሰሩትን አኩሪ ገድል ጥላሸት በመቀባትም ነው። ለምሳሌ በአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያን ህዝብ አስተባብረውና ጦሩን መርተው ለድል ያበቁትን የጦሩን መሃንዲስ የዳግማዊ አፄ ምኒሊክንና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት በአድዋ እንዳይቆም በወያኔ መከልከሉና በተቃራኒው ደግሞ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ደም ላፈሰሰው ለጣሊያን የጦር አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዳቦርሚዳ ሃውልት እንዲቆምለት መፍቀዳቸው ህወሃቶች ለአማራ ያላቸውን ስር የሰደደ ጥላቻ ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ከፋሺስት ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ዝምድና ይመሰክርባቸዋል።

ወያኔ  ከደርግ ጋር ስዋጋ ወደ 50 ሺህ ሰው አልቆብኛል ይላል። ነገር ግን ወያኔ የመንግስት ስልጣን ከያዘበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በየማጎሪያው የሰራቸውን ለጊዜው ትተን በአጋዚ ጦሩና በፌዴራል ፓሊስ የተጨፈጨፈው የሰላማዊው ህዝብ ብዛት ወያኔ  ከደርግ ጋር ስዋጋ ሞተብኝ ከሚለው በብዙ ጊዜ እጥፍ የሚበልጥ ነው። ለምሳሌ ለህዝቡ ሃላፊነት የማይሰማው የወያኔ አገዛዝ ትርጉም በሌለው በባድሜ ጦርነት ወደ 75 ሺህ ህዝብ በላይ ማግዷል፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር የወልቃይት አማራ ህዝብን ህወሃት ገድሏል፣ በጎንደር፣ በደብረ ታቦር፣ በባህር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልዲያ፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ (በረራ)፣ በቢሾፍቱ ደብረዘይት፣ በአንቦ፣ በጨለንቆ፣ በጋምቤላ፣ በኮንሶና በመሳሰሉት ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች የጨፈጨፋቸው ዜጎች በብዙ መቶ ሺህዎች ወይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ናቸው። እዚህ ላይ መገንዘብ የሚያስፈልገው ህወሃት ሞቱብኝ የሚላቸው ታጋዮቹ ጦር ሜዳ ላይ ነው፣ ነገር ግን እነሱ እየገደሉት ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በጦር ሜዳ ላይ ሳይሆን ሰላማዊ ህይወቱን በሚመራበት በመሃል ሃገር ላይ ነው።
ያን ሁሉ ብልግናቸውንና የፈጸሙትን ወንጀል ከኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወረ ይመስል “ለማያቅሽ ታጠኚ” እንደሚባለው ዓይነት ዛሬ ደግሞ ለኢትዮጵያ ባንዲራ ተቆርቋሪ መስለው ህዝብ ያተራምሳሉ። በሽታቸው የሚድነው ጥፋታቸውን አምነው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ብሔራዊ እርቅ ማውረድ እንጂ ህዝብን በማተራመስ ወይም ታሪክ በመደለዝ አይደለም። መቼስ ባለጌ ሁሌም ባለጌ በመሆኑ ውለታም ሆነ ይሉኝታ አያቅምና ይህንን ሁሉ አንገት የሚያስደፋ አሳፋሪ ታሪክ ና በደም የተጨማለቀ እጅ ይዘው ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይጸየፋቸው ገበናቸውን ሸፍኖና ይቅር ብሎ እንደ ባዳ ሳይሆን እንደ ወንድም ባኖራቸው በእነሱም ብሶ የኢትዮጵያን ህዝብ ምክንያት እየፈለጉ ጭንቅ ጭንቅላቱን ይቀጠቅጡታል። —//—

ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን
ደረጀ ተፈራ
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89509