Thursday, December 29, 2016

ኮሎኔል ደመቀን ለማፈን ወያኔ ግብግብ ላይ ነው !!! ጎንደር አንገረብ እስር ቤት ላይ ተኩስ አለ

ኮሎኔል ደመቀን በሃይል አውጥቶ ለመውሰድ ከሰባት ጊዜ በላይ የሞከረው ወያኔ አሁንም ተመሳሳይ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ ነው የተነገረው። እንደተለመደው የጎንደር ሕዝብ እርብርቡን እንዲያደርግ ጥሪ ይተላለፍ ተብሏል።

የይስሙላው የፌደራል ፍርድቤት ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረገው ችሎት በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትን ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ አይቶ ለሌላ ቀጠሮ አስተላልፏል። በዚሁ በሞት ፍርድ በሚያስቀጣ የክስ ፋይል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በሌሉበት እንደተከሳሽ መጠቀሳቸው ወያኔ ኮሎኔሉን በሃይል ለመውሰድ መወሰኑን ማሳያ ነው።


በሰላማዊ መልኩ የህዝብ ፊርማ ሰብስበው እራሱ ወያኔ በፃፈው ህገ መንግስትና በወያኔ ብቻ በታጨቀው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህጋዊ ጥያቄ ጠይቀው እውቅና የተሰጣቸውን የወልቃይት ኮሚቴ እመራሮች ወያኔ ወደ ጎንደር አፋኝ ሃይል ልኮ ማፈን ሲጀምር ሃምሌ 5 ቀን የፈነዳው የጎንደር ብሎም የተቀረው የአማራ ሕዝብ ቁጣ ንሮ የስርአት ለውጥ ወደ ማምጣት ተሸጋግሯል።

ኮሎኔል ደመቀ ብቻው እንድ ክፍል ውስጥ እግረ ሙቅ በብረት ታስሮ እንደሚገኝ ሰሞኑን ስንገልፅ ነበር። የነፃነት ጥያቄ በእስር አይመለስም። ህዝብ ሁሌም ያሸንፋል!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/70583

Wednesday, October 12, 2016

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሥጋቷን ገለፀች | VOA

የዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የውጥረት ሁኔታ ሥጋት ያደረባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ አስታውቀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የውጥረት ሁኔታ ሥጋት ያደረባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ላነሷቸው የመሬት መብትና የምርጫ ሕግን ማሻሻያ የመሳሰሉ ብሦቶች መልስ ለመስጠት መንግሥት ቃል መግባቱን ፕሬዚዳንት ሙላቱ መስከረም 20 ለፓርላማው ያደረጉትን ንግግር መንግሥታቸው እንዳጤነው ቃል አቀባዩ ገልፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረባቸውን ሃሣቦች ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲንቀሣቀስ እንደሚያበረታታ አመልክተዋል፡፡

ኪርቢ በማከልም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ላይ የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ በተለይም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎችን መያዝን፣ ነፃ ሃሣብን መገደብን፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ማገድን እና የሰዓት ዕላፊ ገደብ መጣልን የመሳሰሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልግበትን ሁኔታ ግልፅ እንዲያደርግ መንግሥታቸው እንደሚፈልግም አስረድተዋል፡፡

እነዚህ እርምጃዎች ሥርዓትን ለመመለስ የታሰቡ ቢሆኑ እንኳአሉ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢነፃ ድምፆችን ማፈንና በኢትዮጵያዊያን መብቶች ውስጥ እራስን የሚጎዳ ጣልቃ ገብነት ማድረግ ለብሦቶቹ መፍትኄ ከማግኘት ይልቅ ሁኔታዎችን የሚያባብሱ ነው የሚሆኑት፡፡

ምንጭ:-VOAዋሺንግተን .

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/67489

Monday, October 3, 2016

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ


 የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::

 የደረሱ መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::

በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::

በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::

በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/66893