Thursday, February 28, 2013

የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ እና ትርጉሙ

FEB.28.2013
ለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፈለ ከተማዎች የወያኔ መንግስት ፓሊሶችና ደህንነቶች በሙስሊሙ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር ዝርፊያ የተቀላቀለበት አሸባሪ ብርበራና ፍተሻ ሲያካሄዱ ሰንብተዋል። ይህ ብርበራ በአይነቱ ፍጹም ከሆነ የወሮባላ ተግባር የተለየ እንዳልሆነ የደረሰባቸው፣ ያዩና የሰሙ ሁሉ የሚመሰክሩት ነው።
የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለይስሙላ እንኳን ያልያዙ ጭንብል ያጠለቁ ፓሊሶችና ደህነነቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በር እየበረገዱ በመግባት ቅዱሳን መጸሃፍትን፣ ሞባይልን፣ ቴሌፎኖን እና ወርቅ በግፍ መዘረፋቸውን ሰለባዎቹ አረጋግጠዋል። ይህ በእነዚህ ንጹሃን ሙስሊም ወገኖች ላይ ከተፈጸመው ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ ተጨማሪ መሆኑ ነው።
የእነዚህን አሳዛኝ ግፈኛ ተግባር የሰማው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዜናውን በየካቲት 14 ቀን 2005 አ.ም ምሽት ዘግቦ ነበር። በዚህ ዘገባ ላይ የቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ የሰለባዎቹን ምስክርነትና አስተያየት ብቻ ማቅረብ ተገቢ ያልመሰለው ፕሮፌሽናሉ ጋዜጠኛ፣ ሚዛናዊ ዘገባ ለማቅረብ ድርጊቱ ተፈጸመባቸው ወደተባሉት ክፍለ ከተማዎች የፓሊስ አዛዦች መደወል ነበረበት። ይኼኔ ነበር ጋዜጠኛው ሳጅን ዘመድኩንን ያገኘው። ይህን የመንግስት ወንጀል እንዲያስተባብሉ እድል የተሰጣቸው ሳጅን ዘመድኩን የሰጡት መልስ ሰዋዊ ሳይሆን አውሬያአዊ ነው ማለት ይቻላል።
የተሰራውን ግፍ መዘገቡ ያናደዳቸው የፖሊስ አዛዦች ጭራሹኑ ጋዜጠኛውን ራሱን አሁን መጥቼ አስርሃለሁ የሚል መልስ ነበር የሰጡት። እብሪተኛው ሳጅን ጋዜጠኛው እንኳን ዋሽንግተን መንግስተ ሰማያትም ገብቶ እንደማያመልጠው ካዛቱ በኋላ ቃለ ምልልሱ አለቀ።
ይህን ቃለ ምልልስና የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ ስንሰማ ቅጽበታዊ ምላሻችን ሳቅና መገረም ሊሆን ይችላል። ከዚህ የደንቆሮ ሃሳብ ከሚመስል አስቂኝና አስገራሚ አነጋገር በስተጀርባ ግን በእጅጉ የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስና የሚያስቆጭ ትርጉም አለው። የሳጅን ዘመድኩን ጥያቄ አመላለስ የልዩ አጋጣሚ ጉዳይ (Isolated Event) አይደለም። እንደዚያ ከመሰለን ክፉኛ ተሳስተናል። በሳጅን አንደበት የሰማነው አውሬ ወይም የህወሃት ድምጽ ህዝባችን በእየለቱ ቁም ስቅሉን የሚያሳየውን የወያኔ የየእለቱን ዘረኛ ቋንቋ እና ተግባር ነው። ሳጅን ዘመድኩን የተናገረው የሰለጠነበትንና ወያኔ የወሰነውን ነው በእሱ ልሳን የሚናገረው።
ወያኔዎች የፈለገንን አድርገን አዋርደን እንገዛችኋለን፤ ምን አባታችሁ ትሆናላችሁ ነው የሚሉን በወያኔኛ ቋንቋ። ሳጅን ዘመድኩን እንደምንገምተው ደንቆሮ አይደለም። ወያኔ ውስጥ ያደገ ወያኔኛ የተማረና የሰለጠነ፣ ሁሉንም ጣቢያዎች ከሚያዙት ሰዎች አንዱ ነው። ትእዛዝ ፈጻሚ ወያኔ ነው። ህዝብ ደሞዝ የሚከፍለው የህዝብ ተቀጣሪ ነኝ ብሎ አያምንም። እንደሁሉም ወያኔዎች እየዘረፈ የሚኖር ሽፍታ ነው። ህግና ህገ-መንግስት ለጌጥ የተቀመጠ መሆኑን ወያኔዎች ሁሉ ያውቃሉ። ተናግረውታልም።
በሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊ አነጋገር ስቀን ከሆነ የሳቅነው በራሳችንና በህዝባችን ሰቆቃ ነው። በራሳችን ውርደት ለመሳለቅ አይተናነስም።ሀገራችን በእንደ እነ ሳጅን ዘመድኩን ያሉ ሰዎች ነው የምትመራው። ትልቅ ውርደት ላይ ነን። ሀገራችን ከውረደት፣ ህዝባችንን ከሰቆቃ የማዳን ግዜው አሁን ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ምርጫችን ሁለት ነው። ወይ “ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል እያልን የቁም ሞት ኑሮአችንን መኖር” አሊያም ወያኔን አስገድደንም ሆነ አስወግደን የሚገባንን የኩሩ ህዝብና ሀገር ስብእናችንን ማስመለስ እና ሀገርን ከማዳን ከሞራላዊ ግዴታ ተጠያቂነት ነጻ የመሆን።
እንዳንሳሳት! የሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊና እብሪታዊ ቋንቋ ወያኔያው የእለት ተእለት ዘይቤ ነው። ስለዚህ ጀንበር ቁልቁል ሳትጠልቅብን ወያኔን አስገድዶ ለመጣል ከሚንቀሳቀሰው ህዝባዊ ሃይል ጋር በመሆን የመታገያ ጊዜው አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, February 27, 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል « አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው » እነ ስብሃት « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን » እነ አባይና አዜብ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

    Posted By.Dawit Demelash



ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ
tigist gebre

“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …
በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።
በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።
“ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛል” በማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት ወ/ሮ ሰብለ አስተያየታቸውንና ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።
የካቲት 3፤2005 (2/10/2013) የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ያሰማው እረፍት የሚነሳ ዜና እስካሁን አልተቋጨም። ሱዳን ሸገራብ በሚባለው ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ጥር 22 ቀን 2005 ዓ ም ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ከቤታቸው ይወጣሉ። በካምፕ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በግምት ሰላሳ ሜትር ሳይርቁ ታፈኑ።
ባለቤታቸው አቶ መልካሙ ባዬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አፋኞቹ ራሻይዳዎች ናቸው። ራሻይዳ የቆዳቸው ቀለም ጠየም ያለ የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ቀደም ሲል ከሶስት እስከ አራት ሺህ ዶላር እየተቀበሉ በደላላ አማካይነት ስደተኞችን በሲና በረሃ ወደ ግብጽ ያሻግሩ ነበር። እስራኤል በሲና በረሃ ወደ ድንበሯን ዘልቀው የሚገቡበትን የስውር መንገድ ስትዘጋው ራሻይዳዎቹ የገቢ ምንጫቸው ተዘጋ። ገንዘብ የለመዱት ወንበዴዎች የንግዱ ስልት ቀየሩና ሰው ማፈን ጀመሩ። አፈናውንም ከሚያካሂዱባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙትን አድፍጠው በመያዝ፣ ስደተኞችን ከስደተኛ ካምፕ አፍኖ በመውሰድ፣ ከሌሎች አፋኞች ስደተኞችን በአነስተኛ ገንዘብ በመግዛት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ሜሮን እስጢፋኖስ ይናገራሉ፡፡
ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ይህንን ዜና ሲሰሙ ደነገጡ። ዜናውን ካሰራጨው የቪኦኤ ዝግጅት ክፍል አድራሻ በመጠየቅ አቶ መልካሙን አገኟቸው። አቶ መልካሙ በቃለምላልሳቸው ወቅት እንደተናገሩት ሁሉ ለወ/ሮ ሰብለ የደረሰባቸውን ሁሉ አጫወቱ። ወ/ሮ ሰብለ “የሰማሁት ሁሉ እረፍት ነሳኝ። የማውቃቸውን ሰዎች ማስቸገር ጀመርኩ። ጊዚያዊ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመርኩ። ህይወት ለማትረፍ እየጣርኩ ነው” ሲሉ ጥሪ ያካተተ አስተያየት ሰነዘሩ።
ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው። አፋኞቹ 35 ሺህ ዶላር ካልቀረበላቸው የሰውነት አካል ክፍል ለሚዘርፉት አራጆች ያስረክቧቸዋል። እዚያ ከደረሱ ድርድር የለም። የሰውነት ክፍላቸው የበለጠ ዋጋ ስለሚያወጣ ሌሎች ወገኖች ላይ እንደተፈጸመው እርሳቸውም ላይ ይከናወናል።
የ12 እና የ 1 ዓመት ከስምንት ወር ልጅ ያላቸው ወ/ሮ ትዕግስት ባለቤታቸውን በስልክ እንዲያነጋግሩ ይደረጋሉ። ባለቤታቸውም ይሰቃያሉ። እግራቸውና እግራቸው መካከል ብረት ተደርጎባቸዋል። ይደበደባሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገው ባለቤታቸው የተጠየቁትን ገንዘብ ባስቸኳይ እንዲከፍሉላቸው ለማስጨነቅ ነው። ባለቤታቸው እንደተናገሩት “ምንም አማራጭ የለኝም። የተጠየቀውን ገንዘብ ማግኘት አልችልም። ልጆቼ ወደፊት ሲጠይቁኝ ለምኜ አቃተኝ ለማለት እየለመንኩ ነው። ባለቤቴ ግን ምንም ማድረግ እንደማልችል ታውቃለች፤ … ” ብለዋል።
የ 12 ዓመቷ ልጃቸው ሱፊ “እኛንም እንዳይወስዱን ስለምንፈራ ከቤት አንወጣም” በማለት ልብ የሚነካ መልስ ከቪኦኤ ለቀረበላት ጥያቄ መልስ ሰጥታለች፡፡ “እናቴን አፈኗት” ያለችው ህጻን የበርካታዎችን ልብ እረፍት ነስታለች። ወ/ሮ ሰብለ “እንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሲቃ ተሞላበት ጉዳይ እየሰማን በውጪ ያለን ወገኖች እንዴት 30 ሺህ ዶላር ማዋጣት አቃተን” ሲሉ ይጠይቃሉ። ወ/ሮ ትዕግስት ጸሃይ ቢተርፉ ለሌሎች በማስተማር ተመሳሳይ ችግር በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እንዳይደርስ የማድረግ ስራ ይሰራል የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
በሰብአዊ ተግባርም ሆነ በየትኛውም ዓይነት ማህበር ተመሳሳይ ስራ ተሳትፎ እንደሌላቸው ያስታወቁት ወ/ሮ ገነት፣ ይህን ጉዳይ የሳቸውን ልብና አእምሮ ዕረፍት ነስቶት ለዚህ ተግባር ራሳቸውን እንደሰጡ ሁሉ፣ ሌሎችም ይህንን ልብ ሰባሪ አደጋ ሌሎች ወገኖችም ሰምተው ተባባሪ እንዲሆኑ በሚል ለጎልጉል አስተያየት መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ለመንግስት ስለማሳወቃቸው ተጠይቀው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጸሐፊ ስልካቸውን በማፈላለግ ካገኙ በኋላ ማነጋገራቸውን ይገልጻሉ። በምላሹም “ይልቁኑ አፋኞቹ ስልካችሁን እንዳያውቁ ተጠንቀቁ። እየደወሉ ይጨቀጭቋችሁዋል” የሚል የማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
ቴዲ አፍሮ በፑንት ላንድ ሞት የተፈረደበትን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ በመድረስ ህይወቱን እንደታደገው አቶ መልካሙ አስታውሰው በተመሳሳይ የባለቤታቸውን ህይወት ሊታደግ የሚችል ወገን ሊኖር እንደሚችል ተቁመው ለማንኛውም “መፍትሔው እግዚአብሔር ዘንድ ነው” የሚል መልዕክት በቪኦኤ በኩል አስተላልፈዋል።
ወ/ሮ ሰብለ በበኩላቸው “ፈቃደኛነቱ ካለ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን” በማለት የጀመሩት የነብስ ማዳን ስራ በቅርብ ወዳጆቻቸው መደገፉን አስታውቀዋል። አያይዘውም ሩጫው ከጊዜ ጋር መሆኑንን አመልክተዋል።
ገንዘቡ ከተገኘ ለአፋኞቹ እንዴት ይደርሳል? ወ/ሮ ትዕግስትስ እንዴት ነጻ ይሆናሉ? በሚል ወ/ሮ ሰብለ የሰሙት ነገር እንዳለ ለተጠየቁት፣ ሰዎቹ እስራኤል አገር ወኪል አንዳላቸውና፣ ገንዘቡ ለወኪሎቻቸው ሲገባ ግብጽ ወስደው እንደሚለቋቸው፣ ይህንን ለማከናወን የሚችሉ ሴት አቶ መልካሙ ማዘጋጀታቸውን እንደነገሯቸው የሴትየዋን ስም በመጥቀስ ተናግረዋል።
“በድብደባና በስቃይ ደክሜያለሁ። አሁን ገንዘቡ ተከፍሎ ቢለቁኝም በረሃውን አቋርጬ ግብጽ የምደርስበት አቅም የለኝም። እሞታለሁ። አትክሰሩ። እኔ አልተርፍም። የምትችሉ ከሆነ ህይወቴን ይወስዳት ዘንድ ለፈጣሪ ጸልዩ” ይህ ሲና በረሃ ታፍኖ የቆየ ኤርትራዊ ወጣት ለወንድሞቹ የተናገረው የመጨረሻ ንግግር ነበር። ወንድሞቹ እስራኤል አገር በስደት ሃዘን ተቀመጡ። ከዚያ በኋላ ስልካቸውን ቀየሩ። ወንድማቸውን በስልክ ድምጽ ነፍሱ ሳይወጣ ሞቱን ተቀበሉ” ሲሉ የሰሙትን ወ/ሮ ሰብለ አጫውተውናል። በሌላም በኩል በተመሳሳይ ታፍና የነበረች አንድ ወጣት የሚከፈለው ተከፍሎ በቅርቡ ከግብጽ አዲስ አበባ እንደገባች አመልክተዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሙት የሲና በረሃ አሰቃቂ ስቃይ ሳቢያ የወ/ሮ ትዕግስት ገብሬን ህይወት ለማትረፍ ራሳቸውን ከፊትለፊት ያቆሙት ወ/ሮ ሰብለ ሊያነጋግራቸው ለሚፈልግ ሁሉ የኢሜል አድራሻቸውን አስታውቀዋል። yegetasew@yahoo.com
ዝግጅት ክፍሉ፦ በተመሳሳይ፣ በተለያዩ ስፍራዎች የሚፈጸሙትን የወገኖቻችንን ስቃይ አስመልክቶ ላልሰሙ ትምህርት ይሆን ዘንድ ጽሁፍ ለምትልኩልና ወገኖች ሁሉ ቅድሚያ እንደምንሰጥ ለመግለጽ እንወዳለን። በተለይም በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ከ30- 40 ዓመት የኖሩ ስደተኛ ወገኖች ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያዊን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ብትጠቁሙን ጉዳዩን እንደምናጣራው ከወዲሁ እንገልጻለን።
ወ/ሮ ሰብለና ለተመሳሳይ አላማ የተነሱት እህቶች የሚከተለውን ደብዳቤ ለእምነት ባልደረቦቻቸውና ለቤተክርስቲያን ያቀረቡትን የተማጽኖና እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።


  Posted By.Dawit Demelash

Tuesday, February 26, 2013

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል። የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን “ጸረ-ልማት ሃይሎች” (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት “እህት ድርጂቶች” ይወስዳል፡፡ በህወሃት “የማይበገር ጀግንነት” ውስጥ ያለው እውነታ (‘ሪያሊቲ’) ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር) አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር “የምን እደረገህ” ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ። ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው። ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም። ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።
Eskinderኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል። ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ “ጥፋተኞች ሆንን።” የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ “ምክንያታዊ” በሚመስል ሁኔታ ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ’ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት’ ወስጃለሁ፡፡
ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ”ፍትህ አካላት” እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር። ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው አወጣ ብሎ የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው። የዳኤል ፓስት
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡ በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ “ዓለማቀፉ” ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ”የዲፕሎማሲ” ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? “የመለስ” ራዕይን ጨምሮ?

   Posted By.Dawit Demelash

Sunday, February 24, 2013


Ethiopian Minister Junedin seeks Asylum in Kenya

Junedin Sado
EthioChannel, a pro regime “private” Saturday Newspaper has today reported that top ruling party official and “the Minister of Civil Service” has sought asylum in neighboring Kenya.
Junedin Sado’s wife, Habiba Mohammed, is one of 29 people facing terrorism charges related to protests by Muslims. Junedin last year published a letter in the same newspaper defending his wife and criticizing the federal prosecutor’s charges. In the letter, Mr. Junedin said that he had approached the Saudi Arabian Embassy in his personal capacity to raise money to build a mosque to fulfil the wishes expressed in the will of his late mother. The money recovered from his wife, Mr. Junedin said, was meant for the mosque and not to fund terrorist activities.
Habiba was charged  in October 2012 with funneling money from the Embassy of Saudi Arabia to Islamist terror groups, at a hearing at the Ethiopian Federal High Court. The Paper today also reported that although Junedin had asked for a medical leave to Thailand  he was refused by Ethiopian authorities.
Jundein was president of the Oromia Region from 28 October 2001 until 6 October 2005. He subsequently was appointed Transport and Communication Minister, which is the office he was holding when Prime Minister Meles Zenawi moved him to the Science and Technology Ministry October 2008. Following the 2010 general election, Junedin was appointed Minister of Civil Service until November 2012 Prime Minister Hailemariam replaced him with another Minister in his Ministerial reshuffle. The Oromo People’s Democratic Organisation (OPDO), a constituent of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, the ruling coalition had also expelled him from the Organisation. It was reported that after “self criticism he was readmitted and secured his posts”.  He previously served as the president of the OPDO. Although the Ethiopian Parliament had the plan of “removing Junedin’s immunity” it in its agenda, it was not implemented to that effect. Junedin has also been the Board Chairman of Addis Abeba University (AAU).
Junedin was one of the “most powerful” ruling Party officials who represented the regime in various international and local duties. He was also one of the few Ministers that represented the ruling Party in the Ethiopian General election debates. A close confident and loyal of the late Prime Minister Meles Zenawi, Junedin was one of the ardent critics of Ethiopian opposition and Muslim critics/protesters, sources who knows the Minister closely at the Oromia regional  Council recount.
EthioChannel’s cover story on Junedin
The paper also stated that it was not established how Junedin left for Kenya, so far.  Some sources close to De Birhan had informed us that Junedin had absconded to Kenya with eight senior members of OPDO and colleagues. There are no details on the whereabouts of his three underage children
Posted By.Dawit Demelash



Saturday, February 23, 2013

በዘንድሮዉ ምርጫ ወያኔ የረጂም ግዜ አጃቢዎቹም ሊከዱት አንደሚችሉ በመነገር ላይ ነዉ ተባለ

በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚደረገዉ የከተማና የወረዳ ምርጫ የወያኔ አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ከዚህ ቀደም ወያኔን አጅበዉ ምርጫዉን የብዙዎች ምርጫ ያስመሰሉ እንደ ራዕይ፤ ኢፍዴሃግ፤ መኢብንና ቅንጅትን የመሳሰሉ ፓርዎች ዘንድሮ ጭራሽ በምርጫዉ ላይ ላይሳተፉ ይችላሉ የሚል ወሬ አዲስ አበባ ዉስጥ እየነፈሰ መሆኑን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ። እነዚህና ሌሎችም የጋራ መድረክ እየተባለ በሚጠራው የፖለቲካ ስብስብ ዉስጥ ተሳታፊ የሆኑ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ ዝግጅት ማድረግ እንዲችሉ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቀድሞዉንም ቢሆን ከአጃቢነት ዉጭ ምንም ማድረግ ከማይችሉበት የይስሙላ ምርጫ ሊወጡ እንደሚችሉ የየፓርቲዎቹ መሪዎችና በመናገር ላይ ናቸዉ፡፡
እነዚህ ህዝባዊ ድጋፍና ተቀባይነት የሌላቸዉ ፓርቲዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዕጩዎችን ማቅረብ የግድ በሆነበት በዚህ የአካባቢ ምርጫ የአገሪቱን ሀብት እንደራሱ ንብረት ከሚቆጣጠረዉ ወያኔ ጋር መወዳደር ቀርቶ ለምርጫዉ ከሚያስፈልጋቸዉ የዕጩዎች ቁጥር ዉስጥ ከመቶ አምስቱን እንኳን ማቅረብ አለመቻላቸዉ ታዉቋል። ፓርቲዎቹም ይህንን በሚገባ ስለሚረዱ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ እርዳታ
እንዲያደርግላቸዉ ለገዢዉ ፓርቲ ለኢህአዴግ አቤቱታ ቢያቀርቡም ኢህኣዴግ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ጥያቄያቸዉን ሳይሰማ ቀርቷል።
በዚህ የተነሳ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች በምርጫዉ ተሳትፈናል ለማለት ብቻ አንዳንድ ቦታ ላይ በጣት የሚቆጠሩ ዕጩዎች ቢያቅርቡም በከፍተኛ የገንዘብ ችግር የተነሳ በምርጫዉ ለመሳተፍ የሚችሉ ባለመሆናቸው የዘንድሮዉን ምርጫ የሚያዘጋጀዉ፤ የሚወዳደረዉና ከራሱ ጋር ተወዳድሮ የሚያሸንፈዉም ወያኔ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት ከ65 በላይ ፓርቲዎች ውስጥ ሃያ ስምንቱ ከምርጫ በፊት ውይይት ይቅደም ብለዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እራሳቸዉን ከምርጫው ማግለላቸው የሚታወቅ ሲሆን ዉሸት የማይሰለቸዉና በኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የተሞላው ምርጫ ቦርድ ግን 15 ፓርቲዎች በተወዳዳሪነት ተመዘግብዋል እያለ ህዝብን በማጣለል ላይ መሆን ታዉቋል።


   Posted By.Dawit Demelash

Friday, February 22, 2013

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል

ethiopia

በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
(Photo: mesfinwoldemariam.wordpress.com)
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡፡
በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹ክርስቲያኖች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡
በሥልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ አንድ ዓይነት የፖሊቲካ እምነት ብቻ ይዞ ሌላውን መደፍጠጥ፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የኦርቶዶከስ ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን ልማድና የአሠራር ባህል እየሆነ ሲሄድ ሁሉንም ነገር አንድ ዓይነት ብቻ ለማድረግ የሚታየው ጥረት የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ባሕርይ የሚቃረን በመሆኑ ስር አይኖረውም፤ ይህ ሁሉም ሰው ሊያስብበት የሚገባው አንዱ ነገር ነው፤ ሁለተኛው አንድ ወይም ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ቢሉ አገር የሚሸበርበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አገር ለማድረግ የሚመኙም አሉ፤ ኢትዮጵያን ሃይማኖት-አልባ የጉግማንጉግ አገር ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ኢትዮጵያ በአንድ አጋጣሚ ወንበሩ ላይ የወጣ ጉልበተኛ የሚያትምባትን እምነትም ሆነ ሃይማኖት የማትቀበል አገር መሆንዋ ተደጋግሞ የታየ ነው፤ ኢትዮጵያን የይሁዲ አገር ለማድረግ ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የክርስቲያን አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የእስላም አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ሁሉም አልሆነም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና ዘልቃለች፤ ይህንን በማክሸፍ ለማንም ምንም ጥቅም አይገኝም፤ በአንጻሩ ደግሞ የሥልጣን ወንበሩ ላይ የወጡ ጉልበተኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የነጻነት ጮራ እያዳፈኑ የነጻነትን፣ የእኩልነትንና የሕግ የበላይነትን ዓላማ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፡፡
የነጻነትና የሕጋዊነት መክሸፍ የሰላም ጠንቅ ነው፤ የሰላም መክሸፍ የልማት ጠንቅ ነው፤ የልማት መክሸፍ ደሀነት ነው፤ ደሀነት የሞት አፋፍ ነው፤ ይህንን ለመገንዘብ የሚያዳግተው ሃያ አንድ ዓመት የሞላው ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለመምራት የሚደናበሩት ሰዎች ሁሉ ሃያ አንድ ዓመት አልፎአቸዋል፤ ነገር ግን ከላይ የተገለጸው የመክሸፍ ጉዞ ጭራሽ አይታያቸውም፤የሚታየውም ሲነግራቸው የተበለጡ ስለሚመስላቸው አይሰሙትም፤ ስለዚህም የሚታየውን ሳያዩ፣ የሚሰማውን ሳይሰሙ ጊዜ የሚበላውን ጉልበታቸውን ብቻ ተማምነው በጭፍን እንምራችሁ የሚሉትን ተከትለን ለእኛ በሚታየንና ለእነሱ በተሰወረባቸው ገደል ውስጥ ለምን አብረን እንግባ? አብረን ገደል በመግባት አንድነታችንን የምንጠብቅ የሚመስላቸው ሰዎች በሁለት በኩል ይሳሳታሉ፤ አንደኛ ከአገዛዙ መሪዎች ዘንድ የሎሌ ተከታይነትን እንጂ የአኩልነት አንድነትን አያገኙም፤ እኩልነት በሌለበት አንድነት አይፈጠርም፤ ሁለተኛ ወደገደል የሚጨምር አንድነትን መምረጥ ሕይወትን ትቶ ሞትን መምረጥ ነው፡፡
በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ መክተፍ-መከታተፍ ሙያ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ሠለጠኑበት፤ መክተፍ-መከታተፍ አብሮ የመኖር ጸር ነው፤ አብሮ የመኖር ጸር የሚሆነው በፍቅር ፋንታ ጥላቻን፣ በሰላም ፋንታ ጠብን፣ በመረዳዳት ፋንታ መጋጨትን፣ በልማት ፋንታ ጦርነትን በመንዛት ነው፤ አንዳንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግልጽም ሆነ በስውር እንደጠላት መቁጠርና በእነሱ ላይ ቂምን እንዲቋጥሩ ማድረጉ የማንንም የፖሊቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ይጎዳል እንጂ አይረዳም፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ በኩል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በየገዳማቱና ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በሊቀ ጳጳሳት ምርጫው ላይ አገዛዙ እያሳየ ያለው ጣልቃ-ገብነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እያስቀየመና እያስኮረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በእስልምና ሃይማኖት ላይም የሚታየውን ጣልቃ-ገብነት ተከታዮቹ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በርትተው በመቋቋማቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ለጆሮ እየቀፈፈና በጣም አሳፋሪ እየሆነ ነው፡፡
ይህ በሃይማኖቶች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ውጤት ይኖረዋል፤ ውጤቱ በአገዛዙ የውስጥም ሆነ የውጭ አመራሩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖረዋል፤ የሃይማኖቶቹ ጉዳይ እንደጎሣዎች መከታተፍ በኑሮ ላይ ብቻ ጫናውን የሚያሳርፍና በምድር የሚንከላወስ አይደለም፤ ወደሰማይ ያርጋል፤ የሰማይ ሠራዊትን ይጠራል፤ ያንን ኃይል እንኳን የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአሜሪካውም አይችለውም፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ ልብ ያለው ያስተውላል፤ ዶላር ነፍስን አይገዛም፤ ክብርን አይገዛም፤ ወዳጅንም አይገዛም፡፡

     Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, February 20, 2013

በወያኔ ኢትዮጵያ: ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ፣ ቆርጦ ቀጥል ኢኮኖሚ

ዶ/ር ዘላለም ተክሉ
02/19/2013
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየተላለፈ ያለውን አሳፋሪ “ የጀሃዳዊ ሃረካት” ድራማ በአግራሞት ስመለከትና በቅርቡም ይለቀቃል ተብሉ ስለሚጠበቀው “ ነውጥን ናፋቂ የሩቅ አገር ሰዎች” የፕሮፖጋንዳ ቪዲዮ እያሰብኩ ሳለሁ ነው ሌላ ኢኮኖሚያዊ ድራማ በ Addis Fortune ድህረ ገጽ ላይ የተመለከትኩት:: ይህ እኔ ልጽፍ የተነሳሁበት ድራማ በፊት ከጠቀስኳቸው ድራማዎች ለየት የሚያደርገው ፊልሞቹ በሙስሊምና ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ ፍርሃት፣ አለመተማመንና ጥላቻን ለማባባስና የሃማኖት መብት ጥያቄያቸውን ለማፈን በስፋት እየተካሄደ ያለ ዘመቻ ሲሆን በጽሁፍ መልክ የወጣው ድራማ ግን መንግሥት ላለፉት 7 እና 8 ዓማታት አስመዘገብኩ እያለ በሚላላጥበት የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የተከሰተውን የቀመር መዛባት ቅሌት ተድበስብሶ እንዲታለፍ እያደረገው ያለ ሴራ መሆኑ ነው::
ሁላችንን እንደምናውቀው ወያኔ በሃገሪቱ ከ 11 እስከ 12 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አመጣሁ እያለ ከበሮ መደለቀና ማስደለቅ ከጀመረ ዓማታት አስቆጥሯል:: ይህ በሃገሪቷም ሆነ በአፍሪካ “ታይቶ ያልታወቀ” ብጽግና ሊገኝ የቻለው ባለ “ራዕዩ” እና “ብልሁ” መሪ መለስ ዜናዊ በቀረጹት “ልማታዊ መንግሥት” አመራር ብቃት እንደሆነም እስኪሰለቸን ሲነገረን ቆይቷል:: ይህ ፉከራ በጣም የተጋነነ መሆኑን የዓለም ባንክ (World Bank) እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (International Monetary Fund) በተደጋጋሚ ቢያስረዱም በተለይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በሰላ ምላሳቸው እነዚህን ድርጅቶች ከምዕራባውያን ኒዮ-ሊብራሊስት (Neo- liberalist) እና የኒዎ-ኮሎኒያሊት (Neo- Colonialist) አፍራሽ ተልዕኮ ጋር በማመሳሰል አፋቸውን ዘግተው እንዲቀመጡ አድርገዋቸዋል:: የሃገራችን ህዝብም በነዚህ ዓመታት ተገኘ የሚባለው ዕድገት የቁጥር ቅዥት (Numerical Myth) እንጂ የሚዳሰስ ጥቅም ያላመጣ እልቁንስ ለበለጠ የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት፣ ድህነት፣ረሃብና ስደት የተዳረገበት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሲሞግት በጠባብ ብሄረተኝነት፣ ትምክተኝነት፣ ነፍጠኝነትና ሽብርተኝነት በመፈረጅ አርፎ እንዲገዛ ተደርጎ ይገኛል: ይህንኑ ዕብደትም የተቃወሙና በጽሁፍ ያጋለጡ ጋዜጠኞች፣ የሰባዊ መብት ተከራከሪዎች፣ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ተንታኞች ወይ በአገር ውስጥ እስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ ወይ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል::
እውነታው በዚህ ሁኔታ ባለበት አንጻር ነው እንግዲህ አዲስ የዕድገት ቀመር ትንበያ በገዢው መንግሥት ጓሮ በር እየወጣ ያለው:: በ Addis Fortune ድህረ ገጽ ላይ እንደቀላል ነገር (as low profile issue) እዲወጣ የተደረገው ጽሁፍ እንደሚያሳየው የሃገሪቱን አጠቃላይ ምርት (Gross Domestic Product) ለማስላት እስካሁን ድረስ በማነጻጸሪያነት (Base Year) ሲወሰድ የነበረው 1999/ 2000 በ 2010/11 በመቀየሩ የዓመታዊ ዕድገቱ ትንበያ ከ 11 በመቶ ወደ 8.5 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተዘግቧል:: ይህ ድንገተኛ ክለሳ IMF/ World Bank ለዓመታት ከሚከራከሩበት የ 7-8 በመቶ ዕድገት ጋር ተቀራራቢ ሆኖ ቢገኝም መንግስት ይህንን ያደረገው ውጥረትና ጥርጣሬ ለማርገብ ሳይሆን ተጨማሪ ምርትና አገልግሎት በስሌቱ ሂደት በመጨመራቸው እንደሆነ ያስተባብላል:: የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማም እስካሁን እየተሰራበት ያለው ቀመር ምን ያህል በተሳሳተ ግምት ላይ ተመስርቶ የተቀሸበ ተራ አሃዝ ብቻ እንደሆነና በአጠቃላይም የወያኔ ፖለቲካው ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውም ቆርጦ ቀጥል (Cut & Paste) የሆነ የቁጭ በሉ ውጤት እንደሆነ ለማሳየት ነው::
የዕድገት ቀመሩ በተሳሳተ መሰረት ላይ እንደተቀሸበ የሚያመለክተው መነሻ የ 1999/ 2000 አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርትን (GDP) እስካሁን ድረስ ላሉት ዓመታት ዕድገት ማነጻጸሪያ ተደርጎ መወሰዱ ነው:: ከ 1998–2000 የሃገሪቱን ኢኮኖሚና ከ 70 እስከ 80 ሺህ ዜጎች ነፍስ እምሽክ አድርጎ የበላው የኢትዮጵያ–ኤርትራ ጦርነት የተካሄደበትና ሃገሪቷም በከፍተኛ ድርቅና የምግብ እጥራት የተመታችበት ጊዜ መሆኑ እየታወቀ እንደ ኖርማል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዘመን ተወስዶ ለዕድገት መለኪያነት ጥቅም ላይ መዋሉ በጣም የተሳሳተ አካሄድ ነበር:: ይህ እኮ ማለት የቀነኒሳን የረጅም ርቀት ሩጫ ውጤት መሻሻል ለመለካት ከሞ ኢብራሂም (ሶማሊ እንግሊዛዊው) ወይም ከስለሺ ስህን ወይም ከኃይሌ ገብረስላሴ ጋር ሳይሆን ምንም ችሎታ ከሌለኝ ከኔ ጋር እንደማነጻጸር ማለት ነው:: እንኳንስ አንፃራዊ ሰላም የሰፈነበትና ከ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ዕርዳታ በዓመት የሚጎርፍለት መንግሥት ይቅርና ያለማንም ምዕራባውያን ዕርዳታ ሲንገታገት የነበረው የደርግ ዘመን እንኳን ከ 1999/ 2000 ጋር ቢነጻጸር የተሻለ ዕድገት ሊያሳይ እንደሚችል ምንም ጥርጥር አይኖረኝም:: ወያኔ መቼስ ይህ እውነታ ጠፍቶ ነው ማለት ዘበት ነው:: እልቁንስ “የአኬልዳማ” እና “ የጀሃዳዊ ሃረካት”ን ቆርጦ በመቀጠል በሰራው ድራማ ሊመታው እንዳሳበው የህዝብ እንቅስቃሴ የሚመቸውን መለኪያ ቆርጦ በመቀጠል ከሚያሰላው ቀመር ከፍተኛ ዕድገት እንዳመጣ የሚያሳይ ድራማ ለመስራት አልሞ እንጂ::
በተለቀቀው ጽሁፍ እንደተመለከተው የዕድገት ማነፃፀሪያው (Base Year) መቀየሩ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ እውነታ ላይ ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌለው ምንም ለውጥ አያመጣም ብሎ መንግስት እንደሚያምን ተገልጿል:: ይህ መከራከሪያ ነጥብ ግን ምንም ውሃ እንደማይቋጥር እንደሚከተለው ማሳየት ይቻላላል:: በመጀመሪያ ደረጃ የአገሪቱ አጠቃላይ ምርትን (GDP) አደገ ሲባል የአገሪቱ አመታዊ ገቢ አደገ ማለት ነው:: ይህም ያደገ አጠቃላይ ገቢ ለጠቅላላው ህዝብ ሲካፈል ነው የነፍስ ወከፍ ገቢ አደገ የሚባለው:: የነፍስ ወከፍ ገቢ የሚያድገውም የስራ ዕድልና የግል ንግድ ሲስፋፋ ነው:: የነፍስ ወከፍ ገቢ ሲያድግ ነው በቀን ሦስት ጊዜ የመመገብ፣ የተሻለ የመልበስና መጠለያ የማግኘት ዕድሉ የሚጨምረው:: እነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶቹ እየተሟሉ ሲሄዱ ነው ዜጎች ከድህነት ወጡ የምንለው:: ወገኖች ከድህነት እየወጡ ሲሄዱ ነው የፍጆታ ፍላጎቱ እያደገ የሚሄደው እንዲሁም የተረፈውንም ገቢ መቆጠብ የሚጀመረው:: እንግዲህ ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት በእውነቱ ኢኮኖሚው እንደተባለው አድጎ ቢሆን ኖሮ ከላይ የጠቀስናቸው ቀጥተኛ ተያዥዥነት ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በህዝባችንና በሃገራችን ላይ በታዩ ነበር:: በየዓመቱ ተገኘ የተባለው የ 11 በመቶ ስሌት የላሸቀ አጠቃላይ ምርት (GDP) ከተገኘበት ዓመት ጋር ተነጻጽሮ የተቀሸበ ዕድገት በመሆኑ ህረተሰባችን ተጨባጭ (Tangible) የሆነ የገቢ መሻሻል እንዳመጣ አላሳየም፣ የሥራ ዕድሉም አልተስፋፋም፣ ፍጆታና ቁጠባውም አልተጠናከረም፣ የዕለት ኑሮም አልተሻሻለም፣ ድህነቱም አልቀነሰም፣ ስደቱም አልተገታም። እልቁንስ የተሳሳተው የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ በተዘዋዋሪ መንገድ ለኑሮ ውድነቱ (Inflation) የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል:: ገቢው ያደገለት ብዙ ተጠቃሚ (Consumer) እናገኛለን ከሚል የተሳሳተ ግምት በመነሳት ነው ጥቂት ጥቅመኞች በአጭር ጊዜ ትርፍ በሚያስገኝ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ብዙ ኢንቨስት ያደረጉት:: ለነዚህ ዘርፎች ልማት በጥሬ ዕቃነት (Intermediate Good) በብዛት በመዋላቸው ነው የኢንዱስትሪ ምርቶች እጥረትና ዋጋ መናር የተከሰተው:: የጠበቁትን ያህል ገዢ አጥተው ተንቀዋለው ቀሩ እንጂ ኢኮኖሚው ያደገ ህብረተሰብ ይገዘናል ብለው ነበር ብዙ መኖሪያ ቪላዎችና ኮንዶዎች የተገነቡት:: የነዚህ ግንባታዎች የጥሬ ዕቃ ፍላጎት መጨመር ነው ለተራው ቤት ሰሪ ህዝብ የሲሚንቶ፣ ቆርቆሮና ሌሎች የሕንጻ ግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ መናር አስተዋጽኦ ያደረገው:: በአጭር ጊዜ ትርፋማ ዘርፎች ላይ የተለየ ትኩረት በመደረጉና የግብርና ዘርፉ የግል ኢንቨስትመንት በመዘንጋቱ ነው የምግብ አቅርቦቱ የቀነሰውና ከፍተኛ የዋጋ መናር የታየው::
የዕድገት ማነፃፀሪያው (Base Year) መቀየሩ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተጽዕኖው ላለፉት ዓመታት ብቻ ሳይሆን በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ (Growth and Transformation Plan)ተአማኒነትና ተግባራዊነትም ጭምር ነው:: እንደሚታወቀው ይህ ዕቅድ የተዘጋጀው ከ2005/06–2009/10 ተከሂዶ የተጠናቀቀውን የተፋጠነ፣ ዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ ዕቅድን (Plan for Acceperated and Sustainable Development to End Poverty) መሰረት አድርጎ ነው:: በዚህ የመካከለኛ የልማት ዕቅድ (Medium Term Plan) ወቅት ተገኘ የተባለውን የ 11 በመቶ ዕድገት ነው እንግዲህ የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መነሻና መነጻጸሪያ የሆነው:: የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የ 2010/11–2014/15 ሲጠናቀቅ ቢያንስ የማነጸሪያውን 11 በመቶ ማስጠበቅ (Base Case) አለዚያም 14 በመቶ ዕድገት (High Case) የማግኘት፣ የሃገሪቱን ግብርና ምርት በእጥፍ ማሳደግና ድህነትን ከ 22 በመቶ በታች ማውረድ ነው:: ይህንንም ትልም በማሳካት በአጭር አመታት ውስጥ አገሪዋቷን አሁን ካለችበት ዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ሃገሮች (Low Income Countries (<$996)) ተርታ ወደ መካከለኛ ሃገሮች መደብ (Middle Income Countries($996-$3945)) ማሸጋገር ነው ረጅም ዕቅዱ:: እንግዲህ ችግሩ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው:: በ 2005/06–2009/10 ተገኘ የተባለው 11 በመቶ ዕድገት ከላይ እንደተረዳነው በተሳሳተ ስሌት የተገኘ ጠቁዋሚ ቀመር ነው:: የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱም ይህንን የተሳሳተ ስሌት መሰረት ካደረገ ሊሰሩ የታቀዱት የግብርና፣የኢንዱስትሪና የአገልግሎች ዝርዝር ሥራዎች በእብቧይ ላይ እንደተካቡ ግንቦች ናቸው ማለት ነው:: ቀድሞውንም በሌለ የ 11 በመቶ ዕድገት እንዴ ተብሎ ነው ከዚያ በላይ ለውጥ ለማምጣት ተጨማሪ የሰውና የፋይናንስ ሃብት እየፈሰሰና በቀሪውም ጊዜ ማፍሰስ የሚቻለው:: በዚህ ሁኔታ ተአማኒነቱ ያጠራጥራል እንጂ አሁን ይገኛል ተብሎ የተገመተው 8.5 በመቶ ዕድገት እንደማነጻጸሪያነት ቢወሰድ እንኳን እንዴት ተደርጎ ነው መሰረቱ የተናጋውን ግንባታ እንዳይፈርስ አድርጎ ማስቀጠል የሚቻለው? እንዴትስ ተደርጎ ነው ካለፉት ግማሽ የዕቅዱ ዓመታት አፈጻጸም ጋር ማስማማት(reconcile) የሚቻለው?
ለነገሩ ፖለቲካው ቆርጦ በመቀጠል ህግና የመገናኛ ብዙሃን ሥርዓት ላይ ለተገነባ መንግሥት ቆርጦ የተቀጠለ የልማት ዕቅድና የልማት ዕድገት መረጃ ማዘጋጀት ምን ይሳነዋል ተብሎ ይታማል:: ወያኔ እስካለ ድረስ የዚህ ዓይነት ቁጭ በሉ ሥራዎች ወደፊትም በስፋት እንደምናይ ምንም ጥርጥር የለኝም:: ቁም ነገሩ ይህን ለአምባገነነዊ አገዛዙ ማራዘሚ ይጠቅመኛል ብሎ የተያያዘውን አካሄድ ድክመቶች መልሰን በግብአትነት በማጎልበት ሥርዓቱን በአፋጣኝ ለማስወገድ ለሚደረገው ትግል እንደመሳሪያነት የመጠቀም አቅም ማሳደግ መቻላችን ነው::
ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰላምና በክብር ለዘላለም ትኑር::

   Posted By.Dawit Demelash

  

  ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ

Abebe Gellaw's legal fundኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጭቆና፣ አድልኦ፣ ግፍና በደል አንገሽግሿቸው ተሰደው በሚኖሩበት ምድር ሁሉ ክብራቸውና ነጻነታቸው ተጠብቆ መኖር እንደሚገባቸው ፈጽሞ አጠያያቂ አይደለም። የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮችም ይህንን መሰረታው መብት ለማስጠበቅ ከህግ በላይ ምንም ሀይልና ጉልበት ያለው መሰሪያ የለም።
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “አሰረን አሳደደን” በማለት በአውሮፓና በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ በስደተኛ ስም በተለያየ የማምታቻ ሽፋን ተደብቀው ኢትዮጵያዊያን ያለስጋት የነጻነት አየር እየተነፈሱ እንዳይኖሩ ለማድረግ የሚጥሩ ሰላዮችና የጨቋኙ ስርአት አቀንቃኞች መኖራቸው በተለያየ ጊዜ የተረጋገጠ ሃቅ ነው።
ምንም እንዃን በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የነዚህ ወንጀለኛና አሸባሪ ግለሰቦች ሰለባ ቢሆኑም እስካሁን ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በቂ ጥረት አልተደረገም።
ባለፈው ግንቦት 10 2004 (May 18, 2012) ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው አበበ ገላው የቀድሞው አንባገነን መለስ ዜናዊን ወንጀሎች በአለም መሪዎች ፊት ስላወገዘ እና ስላጋለጠ እንዲሁም የታፈነ የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ጩኸት ስላሰማ በተለያዩ የህወሃት ጀሌዎች የሽብር ፈጠራ ወንጀል ሰለባ ሆኗል። በቅርቡ ከነዚህ በህገወጥ የወንጀልና የስለላ ተግባር ከተሰማሩ የህወሃት ጀሌዎች መሃል ጥቂቶቹን ያጋለጠው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ጠበቃ ይዞ በህግ ለመፋረድ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ይሄንኑ አላማ ለማሳካት እና ወያኔዎች የፈጠሩትን የጸጥታ ስጋት አቅም በፈቀደ መንገድ ለመቅረፍ ጥቂት የECADF የፓልቶክ መድረክ አባላት በራሳቸው አነሳሽነት ባዋጡት ገንዘብ ለዚሁ አላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ልዩ የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል::
ነጻነትና የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮች ከህግ በላይ ወንጀለኞችን የመፋለሚያ መሳሪያ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህንን ጥረት አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል እንዲያግዙ ወገናዊ ጥሪ ቀርቧል።
ህግን ተጠቅሞ ህገወጦችን መፋረድ አንድ የትግል ስልት በመሆኑ ለአንድ ሰው ብቻ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። እርስዎም ለዚሁ እንቅስቃሴ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊነቱን ካመኑበት ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች በአንዱ መንገድ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ:::

    Posted By.Dawit Demelash

Monday, February 18, 2013

መሪ አልባዉ የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በስንዴ ግዢ ጉዳይ ሲጨቃጨቅ መክረሙ ተሰማ

ከዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ መሪ የሌለበት የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተብየው መፈራራትና መከባበር የሚባል ነገር ርቆት አባላቱ “ፕሮፓጋንዳ ይሻለናል” ወይስ “ሀቁን ተጋፍጠን መፍትሔ እንፈልግ” በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተከፍሎ በየቀኑ ሲጨቃጨቅ እንደሚዉል ለካቢኔዉ ቅርበት ያለቸዉ የታመኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። የስንዴው ፖለቲካ በሚል አርዕስት ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰዉ ዜና መሰረት የወያኔ አገዛዝ አገሪቱ ዉስጥ በኤኮኖሚዉና በማህበራዊ ዘርፎች እየደረሰ ያለዉን ቀዉስ መቆጣጠር አቅቶት አሁን ስራዬ ተብሎ የተያያዘዉ የእህል ውድነት በህዝቡ ላይ በተለይ ወያኔ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብሎ በሚፈራዉ በከተማዉ ህዝብ ላይ ያስከተለውን ቀውስ በአስቸኳይ “ለማረጋጋት” ምን ያህል ስንዴ ከውጭ እንግዛ በሚል ጭቅጭቅ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አክልዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል ።
በዚህ ሳምንት ከወያኔ ጓዳ በደረሰን ዜና መሰረት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሚል በያዝነዉ ወር 850 ሺህ ኩንታል ስንዴ አገር ውስጥ ገብቷል። የዚህ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ወጥቶበት የተገዛዉ ስንዴ ጉዳይ ቀድሞዉንም በቋፍ የነበረዉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭራሽ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ዉስጥ እንዲዘፈቅ አደርጎታል። በአንድ በኩል ግዢዉ የሚፈጥረዉ የዉጭ ምንዛሬ ጉድለት የባሰዉኑ የዋጋ ግሽበቱን ያባብሰዋል የሚሉ የካቢኔዉ አባላት ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ “ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከውጭ አምጥተን አከፋፍለናል ሆኖም ምንም አይነት ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት አልቻልንም ብለዉ የሚከራከሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም ከእነዚህ ሁለት ቡድኖች ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለቸዉና የአገሪቱ ችግር የገባቸዉ አንዳንድ የካቢኔዉ አባላት ደግሞ ችግራችን ስንዴ መግዘት ወይም ማምረት ሳይሆን የገዛነዉን ወይም ያመረትነዉን ስንዴ ለተጠቃሚዉ ህዝብ በሚገባ ማከፋፈል አለመቻላችን ነዉ የሚሉም አልታጡም። ለምሳሌ የወያኔ አገዛዝ እራሱ በሰጣቸዉ መግለጫዎች “በ1.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ከ3 ሚሊየን ቶን በላይ ስንዴ ኢትዮጵያን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ያደርጋታል፤ ችግሩ ግን ይህ ብዛት ያለዉ ስንዴም ሆነ ከዉጭ አገር ተገዝቶ የሚመጣዉ ስንዴ ዬት እንደሚገባ አይታወቀም።
ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን በተገኘዉ መረጃ መሰረት ገበያ ለማረጋጋት በሚል ሰበብ ስንዴ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ አየር በአየር ወደ ሌላ አገር እየተዛወረ በመሸጥ ላይ ሲሆን ግዢውን የሚፈቅዱት፣የሚያስፈጽሙት፤ የሚያጓጉዙትና ብሎም ወደ ደቡብ ሱዳንና አረብ አገሮች እያወጡ የሚሸጡት፣ በዘርና በስጋ ዝምድና የተሳሰሩ የህወሀት ሰዎች መሆናቸው በገልጽ ይታወቃል።
መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረባቸዉ ግዜ ማንም ሰዉ ደፍሮ የማያነሳቸዉ ይንንና ይህንን የመሳሰሉ ጉዳዮች ዛሬ የመወያያ አርዕስቶች እየሆኑ በመምጣታቸዉ ስልጣን ከእጃችን ሊወጣ ይችላል በሚል ፍራቻ ብዙ የወያኔ ባለስልጣኖች አገሪቱን ባዶዋን እያስቀሯት መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ፤ በተለይ ከአገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የሚኮበልለዉ የዉጭ ምንዛሬ ብዛት ያሰጋቸዉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ አዳራ ያሉን የገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የህወሀት አባላት ዝርፍያ በዚህ ከቀጠለ በቅርብ ግዜ ዉስጥ የኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛ ካዝና ባዶ ይሆናል ብለዋል።
 
 Posted By.Dawit Demelash

 

Saturday, February 16, 2013

በአዲስ አበባ ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ በእጩነት የተመዘገቡት ኢህአዴግ ናቸው

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወኪል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች= በመዘዋወር ያጠናቀረው ዘገባ እንደሚያመለክተው በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ፣ ተወዳዳሪ ሆነው በእጩነት የቀረቡት 99 በመቶ የሚሆኑት የኢህአዴግ አባላት ናቸው።
አብዛኞቹ ተመራጮች የመንግስት ሰራተኞችና በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ተመድበው የሚሰሩ ናቸው። በእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ እንደሚታየው ከ40 በመቶ በላይ ተመራጮች ከ3ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚሸፍን የትምህርት ደረጃ አላቸው። 40 በመቶ የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች ደግሞ ከ10ኛ ክፍል እስከ ዲፕሎማ የሚደርስ የትምህርት ደረጃ አላቸው። ከ20 በመቶ በላይ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያ ደግሪ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሎአል።
ከ99 በመቶ በላይ በሆኑት ጣቢያዎች በእጩነት የቀረቡት ኢህአዴጎች ሲሆኑ፣
የተቃዋሚ አባላትን ፈልጎ ማግኘት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው።

  Posted By.Dawit Demelash
33 የተቃዋሚ ድርጅቶች በምርጫው ላለመወዳደር የያዙት ጠንካራ አቋም ገዢው ፓርቲ የዘንድሮውን የአካባቢና አዲስ አበባ ምርጫ ብቻውን እንዲሮጥ አስገድዶታል።
በ1997 ዓም ምርጫ ቅንጅት በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ካሸነፈ በሁዋላና ገዢው ፓርቲ ውጤቱን በጉልበት ከቀማ በሁዋላ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በመላ አገሪቱ በቂ ፉክክር የታየበት ምርጫ አልተካሄደም።
የገዢው ፓርቲ አባላት እስካሁን ድረስ ምርጫ ካርድ ላልወሰዱት ሰዎች ካርድ እያደሉ እንደሚገኙ በተለያዩ

አባት ያቆየውን በማፍረሱ የሚመፃደቅ ሰራዊት!

ጌታቸው, ከኦስሎ
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
የሰሞኑ የአዲስ አበባ ከራሞት እና የቴሌቭዥን ጣቢያዋ የዜና ርዕስ ”የመከላከያ ሰራዊት ሳምንት” ተከበረ የሚል ነበር። በ አዲስ አበባም የኢትዮጵያ ሰራዊት” የደረሰበት የእድገት ድረጃ”
Ancient Ethiopian army
ጥንታዊው የኢትዮጵያ ወታደር
ተብሎ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተሰሩ፣ የተገጠሙ፣ እየተባሉ የተነገሩ አውደ ርዕዮች ከመታየታቸውም በላይ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታድዮም ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም በተገኙበት ኢህአዲግ ለመጀመርያ ጊዜ ወታደራዊ ትርኢት አሳይቷል። መቸም ማንም ዜጋ የሀገሩ ሰራዊት ጠንካራ መሆኑን እና ሃገርን የመጠበቅ አቅም እንዲኖረው ይመኛል። ይህ ሁሉንም የሚያስማማ ጉዳይ ነው።
አሁን ባለንበት አለም ውስጥ የወታደራዊ ጥበብ የጉልበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ውስብስብ እውቀትን እና ግንዛቤን የሚጠይቅ ሳይንስ ነው። ወደሚፈለገው የእውቀት ደረጃ ለመድረስ ግን አንድ ሰራዊት ማሟላት የሚገባው ብዙ ነገሮች አሉ። በኢህአዲግ የተደራጀው የኢትዮጵያ ሰራዊትን ሳስበው ብዙ ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች አሉ። ከእነኝህ ጥያቄዎች ውስጥ -
  • ሰራዊቱ የቆመው ለስልጣን መጠበቅያነት ነው ወይንስ ለሕግ እና ለስርዓት ብቻ?
  • ሀገር የመከላከል ሥራ እግረመንገድ የሚስራ ሥራ ነው ወይንስ ቅድምያ የሚሰጠው?
  • ሉአላዊነት (soverginity) የሚለውን ቁልፍ ቃል ሰራዊቱ ከከፍተኛ መኮንኖች እስከ የመስመር መኮንኖች ብሎም እስከ ተራው ወታደር ድረስ በምን ያህል የዲግሪ ደረጃ ይረዳዋል?
  • ሰራዊቱ ኢትዮጵያን እንዴት ነው የሚገልፃት?
  • ሰራዊቱ በምን ያህል ደረጃ ከአካባቢያዊ የወንዝ ስሜት እርቆ በብሔራዊ ስሜት ውስጥ ነው? መኮንኖቹ ምን ይህል አለምአቀፋዊ ስልታዊ (strategic) የኃይል አስላለፎችን ይረዳሉ? የመተንተን አቅማቸውስ? ወዘተ ከብዙ በጥቂቱ የምነሱብኝ ጥያቄዎች ናቸው።
ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው ታሪኮች ውስጥ ነፃነት እና ሉአላውነቷን አስከብራ የኖረችው በእየዘመኑ የነበሩት መሪዎቿ ለሁለት ነገሮች ተገዢ ስለነበሩ ነው። ይሄውም አንዱ ለእግዚአብሔር ሁለተኛው ለሀገራቸው ፍቅር። ዛሬ ላይ ሆነን አፄ ምኒልክን ”ለምን ማይክሮሶፍት ኮምፕዩተር አልተጠቀሙም? አፄ ዮሐንስ ለምን በዶዘር የሊማሊሞን አቀበት አላፈረሱም? ”መሰል ጥያቄ ካልጠየቅን በስተቀር በዘመናቸው መስራት የሚገባቸውን በነበረው ቴክኖሎጂ፣የአቅም ውሱንነት፣ብድር እና እርዳታ ከመላው አለም እየጎረፈላቸው ሳይሆን በባዶ እግሩ የሚሄድ ሰራዊት ይዘው ይችን ሀገር እንደ ሀገር ከሙሉ ክብር እና ማዕረግ ጋር አስረክበውናል።
መደነቅ ከተገባን ከየትኛውም የወታደራዊ የትምህርት ተቁዋም ሳይመረቁ አለምን ባስደነቀ የወታደራዊ ስልት አድዋ ላይ ድል ያደረጉትን፣ ዶጋሊ ላይ ያንቀጠቀጡትን፣ ምፅዋ ላይ የተናነቁትን ማሰብ እና መዘከር ተገቢ ነው። ኢህአዲግ የኢትዮጵያ ሰራዊት በዓል ብሎ ለማክበር ብቻ ሳይሆን ለማሰብ እራሱ ሃያ አንድ አመት ስለፈጀበት የሚያዝኑ የመኖራቸውን ያህል። ለምን አሁን? የሚሉ ጥያቄዎች ግን በብዛት የሚነሱ ናቸው።
ወንድምን ገድሎ ሃውልት መስራት
TPLF statue in Mekele Ethiopia
መቀሌ የሚገኘው ወንድማማቾች ደም መፋሰስ ተምሳሌት (የኢህአዲግ የ ”ድል” ሃውልት)
ኢትዮጵያ በዘመናዊ መልክ የመጀመርያውን ወታደር (ወጥቶ አደር) በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን መመስረቷ እና በኃላ በፋሺሽት ጣልያን ላይ ከአርበኞች ጋር የተፋለመው የጥቁር አንበሳ ጦር ቀጥሎም በቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ በምድር ጦር፣በ አየር ኃይል እና በ ባህር ኃይል ደረጃ መዋቀሩ ይታወቅል። ኢህአዲግ እንግዲህ ይህንን ለዘመናት የተገነባውን ሰራዊት በ1983 ዓም አዲስ አበባን ሲቆጣጠር መበተን የመጀመርያ ስራው ነበር። ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ አውጥታ ያስተማረቻቸው ምርጥ መኮንኖችን ”የታገሉት ለህዝብና ለ ሃገር ነው” ብሎ በሥራ ገበታቸው እንዲገኙ ከማድረግ ይልቅ በእየእስርበቱ ‘ጉዳያችሁ እስኪጣራ’ እያለ አጎራቸው። የተቀሩት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሀገር ትተው እንዲሄዱ ተደርጉ የተረፉት ደግሞ በሀገርቤት ከግል ንግድ እስከ በመንገድ ላይ ወጥቶ እስከመለመን ደረሱ። በሽምቅ ውግያ እና በቆረጣ የሚታወቁት የኢህአዲግ ሰራዊት በተቀረው አለም ከሃያ አምስት እስከ ሰላሳ አመት የሚፈጀውን የከፍተኛ መኮንነት ማአረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጎናፀፉ ተደረጉ። ጀነራሎች፣ ኮለኔሎች ሆኑ።
ይህ ብቻ አይደለም የሰራዊቱ ቤተሰቦች ከሁለት እና ከእዛም በላይ ትውልድ ይኖሩበት የነበሩትን ቤቶች በተለይ በካምፕ አካባቢ የነበሩትን በሙሉ በአንዲት ጀንበር እንዲለቁ ተደረጉ። ቤተሰብ ተበተነ ልጆች ለጎዳና ተዳዳሪነት ተጋለጡ። የቀድሞ ሰራዊት አባላት የነበሩት ምንም አይነት የዘር እና የወንዝ ስሜት የሌላቸው የሀገር ፍቅር እና ሉአላዊነት በሚል ፍቅር የተቃጠሉ ዜጎች በሜዳ ተበተኑ። ከኢህአዲግ ባለስልጣናት አንድም እነኚህ እኮ የሀገር ሰራዊት ናቸው። ዛሬ እንድንቆም ያደረጉን ከሱማሌ ጋር ተናንቀው ሀገር ያዳኑ ናቸው ያለ አልነበረም።
በእዚህ ብቻ አልተገታም ኢትዮጵያ ሃውልት የምትሰራው ከባእዳን ጋር ላደረገችው ጦርነት እንዳልነበር ኢህአዲግ ወንድም ከወንድሙ ጋር ለተጋደለበት አሳፋሪ ታሪካችን እንደ ትልቅ ገድል ሃውልት አቆመ። ሃውልቱንም ”ድላችን” አለው። ሆኖም ግን ከወንድምህ ጋር ላደረከው ጦርነት ሃውልት ማቆም መጪው ትውልድ እንዲቆስል ነው? ቀድሞ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ጊዜም ሆነ ከእዛ በኃላ ብዙ የእርስ በርስ ጦርነት ነበሩ። ግን ነገሥታቱ ወንድሜን ገድልኩ ብለው ሃውልት ሰርተዋል? ብሎ ለሚጠይቀው ኢህአዲግ መልስ የለውም። እውነት ግን የትኛው ንጉስ የቱን ደጃዝማች ገደልኩ ድል አደረግሁ ብሎ ሃውልት ሰራ? ኢህአዲግ ግን ከወገኑ ጋር ላደረገው ደም መፋሰስ አድርጎታል።
እንግዲህ የኢትዮጵያ የሰራዊት ቀን ሲከበር ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ሁሉ መታሰብ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው። ኢትዮጵያ ብለን ስንጠራ ከሙሉ አካሏ እና ታሪክዋ ጋር መሆን አለበት። አንዲትን ሴት እጇን ትተን ወይንም እራሷን ቆርጠን ሌላ አካሏን እያነሳን ሴት ብለን መጥራት እንደማንችል ሁሉ ኢትዮጵያንም መነሻዋን ያወቀ ሰራዊት መድረሻውን የሚረዳ መኮንን ሲኖራት ነው ሰራዊቱ የሕዝብ ስሜትን የተጋራ አብሮት ሊሞት የቆመ ልብ ማግኘት የሚቻለው። ከ እዚህ ውጭ እንዴት ነው ገና በሀገሪቱ ያለፈ ታሪክ ላይ ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ብቻ ሳይሆን መተማመን ላይ ያልደረሱ መኮንኖች የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚያስከብሩት?
አባት ያቆየውን በማፍረሱ የሚመፃደቅ ሰራዊት
የኢትዮጵያ ሰራዊትን ከጅቡቲ እና ሱዳን ጋር እያወዳደርን አድገናል ተመድገናል ማለት ተገቢ አይደለም። በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ የነበሩ እና ነፃነታቸውን ካገኙ ገና አመታት ያስቆጠሩ ሃገራት የኢትዮጵያ መለክያ እና ማነፃፅርያ ሊሆኑ አይችሉም። በመጀመርያ እኛ ማን ነን? የት ነበርን? አሁን የለንበት መድረስ የሚገባን እና ልካችን ነው ወይ? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው።
አንድ ብርጭቆ ውሃ ያለውም ሆነ አንድ ባልዲ ውሃ ያገኘ ሁለቱም ብዙ ውሃ አለኝ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ግን ባለ ብርጭቆው ብዙ ውሃ አላኝ ያለው አቅሙን እና ሊኖር የሚገባውን
Ethiopian National Defense Force - Ethiopian navy
የኢትዮጵያ የባህር ኃይልን አፄ ኃይለ ስላሴ ሲጎበኙ
ካለመረዳት ከሆነ ችግር ነው።ኢትዮጵያ በአየር ኃይልም ሆነ በባህር ኃይል አቅሟ ሌላው ቀርቶ ስጋት ብላ ታስብ የነበረው ከ መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የሚሰነዘረውን ጥቃት እንጂ በጎረቤት ደረጃ አልነበረም። በ1969 ዓ.ም ሱማልያ በኢትዮጵያ ላይ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ያነሳችው በወቅቱ የነበረው የሀገሪቱ ውስጣዊ ችግር የልብ ልብ መስጠቱ እንጂ የ ኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም ከሚገባው በታች ወርዶ አይደለም። እርግጥ ነው በወቅቱ የአሜሪካ መንግስት እስካፍንጫው በቀድሞዋ ሶቭየት የታጠቀውን የሶማልያ ጦር ኢትዮጵያ እንዳትዋጋ የጦር መሳርያ ግዢ ማዘግየት መፈፀሙ በወቅቱ ቶሎ ወደውግያው ላለመግባት የቀረቡ ምክንያቶች ነበሩ። ሆኖም ግን በአየር ኃይሉም ሆነ በምድር ጦር ደረጃዋ ጥሩ ነበር። ለእዚህም ነው ኢትዮጵያ ሱማልያን ባብዛኛው የተዋጋችው በሚሊሻ ጦር የሆነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከአነሳሷ ጀምሮ ኢህአዲግ ሰራዊቱን በትኖ ወደኃላ ባይወስዳት ኖሮ ዛሬ መወዳደር ያለብን ከደቡብ አፍሪካ እና እንደ ቱርክ ከመሰሉ ሀገሮች ጋር ይሆን ነበር ብዬ አስባለሁ።
ለእዚህ ማስረጃ የሚሆነው የባህር ኃይላችን የነበረበት ደረጃ ነው። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አቅም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ጋር የሚወዳደር እንደነበር ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በተደጋጋሚ ከሻብያ ጋር በተደረገው ውጊያ በሰው ኃይልም ሆነ በማቴርያል እያገዘ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል ያዘጋው ኢህአዲግ ዛሬ የኢትዮጵያ የሰራዊት ቀን ብሎ ሲያከብር አያምርበትም።
ኢትዮጵያ በዘር በጎሳ የሚያስብ ሰራዊት ኖሯት አያውቅም። ዘራይ ድረስ እና አብዲሳ አጋ ጣልያንን በሀገሯ ያንቀጠቀጧት፣ አድዋ ላይ ኢትዮጵያውያን የተዋጉት፣ ምፅዋ ላይ በ1980ዎቹ መጀመርያ ላይ የረገፉት የኢትዮጵያ ወታደሮች ከምንም በላይ ክልላዊ ስሜት ሳይሆን ክብርት ለሆነች ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ መሆኑ መጀመርያ ማመን ከሁሉ በፊት ይቅደም። ወደድንም ጠላንም ዛሬ ላለንበት እኛነት መሰረቶቻችንን ማክበር ካልቻልን የሚያከብረን አለመኖሩን ማሰብ አለብን።
በመጨረሻም ከኢህአዲግ በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከመኮንን እስከ ተራ ወታደር የሀገር ፍቅርን ቅድምያ የሚሰጥ የወንዝ ስሜት ያልገዛው መሆኑን ለመረዳት የ1953ዓም የ መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ በአፄ ሃይለስላሴ ላይ ያደረጉት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና በ1981ዓም በኮለኔል መንግስቱ ላይ የተሞከረው የመፈንቅል ሙከራ መጥቀስ ተገቢ ይመስለኛል። ይሄውም ሰራዊቱ ምን ያህል የህዝብን እና የሀገርን ጉዳይ ከንጉሡ እና ከኮለኔል መንግስቱ በላይ እንደሚመለከት አመላካች ነው።
ለእዚህ ማሳያ የሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቶን ታሪክ በትንሹ የሚያሳይ ቪድዮ ማየቱ ጠቃሚ ነው። ሜጀር ጀነራል ደምሴ የኢትዮጵያን አየር ወለድ ከመሰረቱት አንዱ ናቸው። በሱማሌም ሆነ በኤርትራ ጦርነት ላይ ሲዋጉ የኖሩ በኃላ ግን በኮሎኔል መንግስቱ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሲያደርጉ በእራሳቸው በመሰረቱት የ አየር ወለድ የተገደሉ የጦር መኮንን ነበሩ።
ዛሬ የኢትዮጵያ የሰራዊት ቀን የሚከበረው እንዲህ አይነት ለሀገር የሞቱ ደርግን እራሱን ሲዋጉ የነበሩ ጀግኖች ተረስተው ነው። ባጭሩ ግን ኢህአዲግ የአትዮጵያን የሰራዊት ቀን ሲያከብር አላማረበትም።


     posted By.Dawit Demelash

Friday, February 15, 2013

“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል
inspection panel and world bank

/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል።
ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል።
በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለውና ይፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። የምርመራ ዘገባውን ስላጠናውና ስላቀረበው የኢንስፔክሽን ተቋምና የስራ ተሞክሮ በቂ ግንዛቤ ያላቸው እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የዓለም ባንክ ቦርድ ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ላለመቀበል አንገራግሮ እንደማያውቅ ያስረዳሉ።
በሚመሩት ህዝብ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትና በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያካሂዱ አገራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፍራው በመገኘትና መረጃዎችን ከመሠረታቸው ዘልቆ በመመርመር  አጥንቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) የሚባለው ተቋም ከኢትዮጵያውያኑ ሰለባዎች ውክልና በመውሰድ ስራውን ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ጎልጉል ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆ ነበር።
ኢህአዴግ በርዳታና በብድር የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ፣ ለአፈና፣ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ ለተለያዩ የአፈና ተቋም ሰራተኞቹ ደሞዝና ህዝብን በመርገጥ ስርዓቱን ለሚንከባከቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ገንዘቡን ለመጠቀም ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንደሚያውለው በበርካታ መረጃዎች ያረጋገጠው የኢንስፔክሽን ቡድን ለዚሁ ስራው ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በቅርቡ አቅንቶ ነበር።
ምርመራው ያስደነገጠው ኢህአዴግ በተለያየ መልኩ ሰለባዎች በደላቸውን እንዳይናገሩ፣ በጥቅም የተደለሉ ሰዎችን በየቦታዎቹ በማዘጋጀትና በማስፈራራት አፈና ማካሄዱን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች በወቅቱ ቢያስታውቁም ጎልጉል መረጃውን ለስራው መሳካት ሲባል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።
ከቀናት በፊት ሪፖርቱን አጠናቆ ለዓለም ባንክ ቦርድ ያቀረበው የኢንስፔክሽን ቡድን (ፓናል) በማያወላዳ መንገድ ተጽኖ ፈጣሪ ተቋም መሆኑንን ያስረዱት ለስራውና ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች፣ ሪፖርቱን ከቦርዱ አባላት አንዱ እንኳ አልቀበልም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችልም አብራርተዋል።
“አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቦርድ አባላት የፓናሉን ሪፖርት ውይይት እንዲደረግበት እስካልጠየቁ ድረስ ፓናሉ ባቀረበው መሠረት እንዳለ ይጸድቃል። ከጸደቀም በኋላ ሪፖርቱ በዓለም ባንክ ስም ይፋ ይሆናል። ሪፖርቱ ታምኖበት ይፋ ከሆነ በሪፖርቱ የቀረቡት የመፍትሄ ጭብጦች ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እስካሁን ባለው አሰራር የፓናሉ ሪፖርት ተቃውሞ አጋጥሞት አያውቅም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
“ይህ ታላቅ ውጤት የተገኘው በእቅድና አስተውሎ በመራመድ ነው። ወደፊትም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች አሉ። የአገዛዙን ትምክህትና ማን አለብኝነት የሚያረግቡ፣ ብሎም የሚያተኑ ስራዎች ለመስራት ለተጀመረው ስራ ይህ ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ይሆናል” ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እዚህ ያበቁት ክፍሎች አስረድተዋል።
ጉዳዩ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሰ? ለሚሉት ጥያቄዎችና ኢህአዴግ ስለተከሰሰባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ October 12, 2012 አስቀድሞ የዘገበውን ማጣቀስ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል።

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!

ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

 Posted By.Dawit Demelash