Saturday, August 31, 2013

ነገ በመስቀል አደባባይ ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች ሊካሄዱ ነው



በነገው እለት ሰማያዊ ፓርቲና የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ህገወጥ ነው ብሏል
ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚመለከተውን አካል አሳውቄአለሁ ያለው ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ፤ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በፊት ማሳወቁን ገልፆ፤ በሁለት ሰልፎች ምክንያት ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂው መንግሥት ነው ብሏል፡፡
“ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉ አልተፈቀደለትም ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ ፓርቲው ይህንን ተላልፎ በሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሀላፊነቱን ይወስዳል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚፈልግ አካል ሰልፉን ያደራጀውን ሰው፣የሰልፉን አላማ ይዘት፣ የሚወጣውን የሰው መጠን ግምት፣የሚካሄድበትን ጊዜና ቦታ መግለፅ እንዳለበት የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ማስፈቀድም እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ “ማሳወቅ ማለት ማስፈቀድ አይደለም” ያሉት አቶ ሽመልስ፤ ካሳወቁም በኋላ ፍቃድ መጠየቅ የግድ ነው ብለዋል፡፡ “በበኩሌ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅህፈት ቤት እሁድ የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀዱን አውቃለሁ” ያሉት አቶ ሽመልስ፤ በየትኛውም አገር በአንድ ቀንና በአንድ ቦታ ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች ማካሄድ ስለማይፈቀድ፣ ፈቃድ ሰጭው አካል ይህን እያወቀ ለሰማያዊ ፓርቲ ፈቃድ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም ብለዋል፡፡ “በመሆኑም ሰልፉን የሚያካሂደው የተፈቀደለት አካል ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ሽመልስ አክለውም፤ “በየትኛውም አገር ፍቃድ ሳይገኝ ሰላማዊ ሰልፍ አይወጣም፣ማሳወቅ ብቻ በቂ ነው ብሎ ህግን በመናቅ የትም አይደረስም፣ይህን ተላልፎ ቢገኝ ለሚፈጠረው ችግር ፓርቲው ሀላፊነት እንደሚወስድ ራሱም ያውቀዋል” ብለዋል፡፡ “በአንድ ቀን ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች የማይፈቀዱት የተለያዩ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠርና የፀጥታ ሀይሎች ወደተለያዩ ስራዎች ሊሰማሩ ስለሚችሉ የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ነው” ሲሉ አቶ ሽመልስ ገልፀዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው ከሶስት ወር በፊት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ያነሳቸው የህዝብ ጥያቄዎች ካልተመለሱ፣ ከሶስት ወር በኋላ ሁለተኛውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በተደጋጋሚ መግለፃቸውን አስታውሰው፤ ይህም ጊዜ ነገ መሆኑንና አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸውን ተናግረዋል፡፡ “እኛ የማሳወቂያ ደብዳቤውን ያስገባነው ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅ/ቤት በፊት ነው” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ መንግስት በእኛ ላይ የተደረበውን ሰላማዊ ሰልፍ መሰረዝ እንዳለበት በመግለጫ ማሳወቃቸውንና ሰልፉን ከማካሄድ የሚገታቸው እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ “ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት የማሳወቂያ ደብዳቤውን ካስገቡ በኋላ ፅ/ቤቱ የስብሰባውን አላማ፣የትና መቼ እንደሚያካሂዱ፣የሰው ብዛት ምን ያህል እንደሚገመት ፓርቲው እንዲያሳውቀው በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ለጥያቄዎቹ ሁሉ በደብዳቤ ምላሽ መስጠታቸውን ኢ/ር ይልቃል አስታውሰው፤ ነገር ግን ማሳወቂያ ፅ/ቤቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ባለመስጠቱ እንደተፈቀደ ቆጥረን ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከሰማያዊ ፓርቲ በኋላ መጥቶ ሰልፍ የሚያካሂደውን አካል በማስቆም፣ መንግስት ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል - የፓርቲው ሊቀመንበር፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፤ “እኔ የማውቀው አንድ ሰላማዊ ሰልፍ ነው፤ የሰማያዊ ፓርቲ ህገወጥ ነው” በማለት መልሰዋል፡፡ ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ በዕለቱ ስለመካሄዱ ለፓርቲው አሳውቀው እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ማርቆስ፤ “ደብዳቤ ፅፈን ስንሰጣቸው የፓርቲው ሰዎች አንቀበልም በሚል ወርውረውት ሄደዋል” ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የጠየቅናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል፤ “ፅ/ቤቱ በቃልም በደብዳቤም ያሳወቀን ነገር የለም፤ እኛም በነገው ዕለት ሰልፉን እናካሂዳለን” በማለት የፅ/ቤቱን ምላሽ አጣጥለውታል፡፡ ትናንትና ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠርቶ እንዳነጋገራቸው የገለፁት ኢ/ር ይልቃል፤ “ሰላማዊ ሰልፍ እንደምታካሂዱ የደረሰን መረጃ የለም” መባላቸውን ጠቁመው፤ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት እንዳሟሉ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ አሳውቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ከሚመለከተው አካል ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ገልፀው፣ ሰማያዊ ፓርቲም ሰልፉ የተፈቀደበትን ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡ “በመሆኑም የነገው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ህገ ወጥ ነው” ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

   Posted By.Dawit Demelash

Friday, August 30, 2013

ነሐሴ 26 በአዲስ አበባ መንግስት በጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።


ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።
መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።
ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
 Posted By.Dawit Demelash

Sunday, August 25, 2013

በሀይማኖት ሽፋን የወያኔ የፖለቲካ አጀንዳን ማራመድ ይቁም!

August 25, 2013

አምባገነኑ የህውሃት ኢህአዲግ አገዛዝ አገራችን ኢትዮጵያን ላለፉት ሀያ ሁለት አመታት በጎሳ በቋንቋና በሃይማኖት ለመከፋፈል ሆድ አደር ተላላኪዎቹን አስርጎ በማስገባት ዜጎችን እርስ በርስ በመከፋፈል ሰይጣናዊ እኩይ አላማውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጉዳይ አስፈጻሚው የሆኑትን ሆድ አደር ግለሰቦች በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር አስርጎ በማስገባት ይቅር የማይባል ከፍተኛ በደል በመፈጸም ላይ ይገኛል።
እነዚህን ሆድ አደር ወገኖች የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ጠንቅቆ ሊያውቃቸው ይገባል። ወያኔ በዋልድባ ገዳም እና በመነኮሳቱ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘግናኝና አላፊነት የጎደለውን ተግባር ለማውገዝና ከአድራጎታቸውም እንዲታቀቡ የሚጠይቁ ምእማናን የተቃውሞና የተማጽንኦ ጥሪያቸው እንዳይሳካ ለማድረግ ሆድ አደሮቹ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፤ አሁን ደግሞ ከአሳዳሪዎቻቸው በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት፦ ጠንካራ እንቅስቃሴና የተቀናጀ የአንድነት ሕዝባዊ ትግል አሁን በጋራ በማድረግ ላይ የሚገኙትን የእስልምና እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ምእመናንን አንድነት ለማጥፋት በግራኝ መሀመድ ዘመን የፈረሱ ቤተክርስቲያኖችን ለማሳደስ ገንዘብ አዋጡ በሚል ሰበብ፤ የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበና ባደፈ ቃላት የተደረተ መሰሪ በራሪ ወረቀት ሰሞኑን እየበተኑ መሆኑን ተረድተናል።
ይህ አፍራሽና ከፋፋይ ተልእኳቸው በቃ መባል ያለበት ጉዳይ ሲሆን፤ በዲሲና አካባቢው የምትገኙ ምእመናንም የነዚህን የወያኔ መራሽ አፍራሽ ተላላኪዎችን ከፋፋይ ሴራ ለማስወገድ በቆራጥነት እንድትታገሉአቸው በልዑል እግዚአብሄር ስም እናሳስባለን። አገራችን ኢትዮጵያን ከበግ ለምድ ለባሽ የቀበሮ ባህታዊያን አምላክ ይጠብቅ።
አገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን አምላክ ይባርክ!!!
ከአገር ወዳድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ምእመናን
ዋሽንግተን ዲሲ

Thursday, August 22, 2013

ድብደባ የተፈፀመባቸው ከ 16 የሚበልጡ የአንድነት አመራርና አባል ህክምና ላይ ይገኛሉ ግን ለምን ?

ትናንትናው እለት ሁለት የአንድነት ፓርቲ የእስቀሳ ቡድን አባላት ፍቼ ከተማውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተተፈፀመባቸው መግለጻችን ይታወሳል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሶስት ከተሞች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለቅስቀሳ ወደ ፍቼ ካቀኑት የፓርቲው አመራሮችና አባላት መካከል ትላንት ነሃሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በከተማው የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ሃይለየሱስ በየነ በሚመሩ ሲቪል ለባሾች ከፍተኛ ድብደባና ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ድባደባውን የፈፀሙት ከ16 የሚበልጡ ግለሰቦች ሲሆኑ የተደበደቡት ሁለት የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የሆነው አቶ ነብዩ ባዘዘው እና አቶ መሳይ ተኬ ዛሬ ጠዋት የህክምና እርዳታ አግኝተዋል፡፡ የደረሰባቸውን ጉዳት የተመለከቱት ዶክተሮች የተሸለ ህክምና እንዲያገኙ ሪፈር ፅፈውላቸዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በፍቼ የተፈፀመውን መንግስታዊ ውንብድና አውግዞ የተጠናከረ ቡድን ልኳል፡፡

Wednesday, August 21, 2013

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ

August 21, 2013


ካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግል፤Ginbot 7 movement chairman Dr. Berhanu Nega በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሊሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንድን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት? የሚለውን ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሀይማኖቱ ተከታዮች አልፎ ያጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የሀገሩ) ትልቅ የመወያያ አርዕስት እየሆነ ነው:: ይህ ጉዳይ ግን ጥቅል ከሆነ ያመለካከትና የንድፈ ሀሳብ ጥያቄ በተጨማሪ ጥልቅና አስቸኳይ የሆነ የተግባር ፖለቲካ ጥያቄም ነው ይዞ የመጣው::
ሙሉውን  ለማንበብ  እዚህ  ይጫኑ  http://ecadforum.com/Amharic/archives/9524/
  Posted By.Dawit  Demelash
   

Monday, August 19, 2013

ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

recon-e


እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ።
“አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም” የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ። በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው መንግሥትም ችግሩን ከመፍታትና አገሪቱን ከስጋት ከማላቀቅ “ጥሪ አይቀበልም” በሚል የሃይል ርምጃ መምረጡ ነገሮችን ይበልጥ እንዳወሳሰበ ይናገራሉ።
በየአቅጣጫው ያሉ ወገኖች ቆም ብለው ሊደበቁት ከማይችሉት ከህሊናቸው ጋር ሊነጋገሩ እንደሚገባ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ግብጾች ግብጾችን ገደሉ፣ ገና ቀውሱ ይቀጥላል። ይህ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ቀውስ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ወደ እርቅ እናምራ። ለእውነተኛ እርቅ ጊዜው አሁን ነው” በማለት አንገብጋቢ ያሉትን ጥሪ ያስተላልፋሉ።
“ላለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያ ላይ ከየአቅጣጫው የተረጨው መርዛማ ፖለቲካና፣ ሰብአዊነት የጎደለው አስተዳደራዊ መዋቅር የፈጠረው ውጥረት ወደ መፈረካከስ እየነዳን ነው” በማለት የስጋቱን መጠን የሚጠቁሙት አቶ ኦባንግ ፣ በግብጽ የተፈጠረው ቀውስ በሃይል ሊቆም የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ምዕራባዊያንም ሆኑ አሜሪካ የሃዘን መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ስራ አለመስራታቸው ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ትምህርት ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል።
በሩዋንዳ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሰዎች አልቀዋል። በኮሶቮ ህዝብ ተጨፍጭፏል። ዳርፉር ንጹሃን የጥይት ራት ሆነዋል። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሃያላን መንግስታትና “ድርጅቶቻቸው” በእነዚህ አገራት ውስጥ ነበሩ። እያወቁት ነው የሆነው። ግን ጉዳዩ የጥቅም ችግር ስለማይፈጥርባቸው አገራቱ በደም ጎርፍ ሲታጠቡ በዝምታ ተመልክተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦባንግ፣ “ሶሪያ ስትፈርስ፣ ከ100 ሺህ ሰው በላይ ሲያልቅና አሁንም እያለቀ ባለበት ሁኔታ እልቂቱን ማስቆም እየቻሉ ዝምታን መርጠዋል” በማለት አቶ ኦባንግ ከነዚህ አገሮች፣ በተለይም “አሁን ግብጽ ላይ በተፈጠረው ችግር ካልደነገጥንና ለሚቀርበው የእርቅ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የማንዘጋጅ ከሆነ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጥያቄው የስልጣን ሳይሆን አገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሞት አደጋ የመግፈፍ አንደሆነ፣ ይህ አሁን ያንዣበበው የቀውስ ደመና ባስቸኳይ ካልተገፈፈ መከራው የሁሉም ወገን እንደሚሆን ጥርጥር እንደማያሻው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ “ንጹህ ልብናና ንጹህ ህሊና ያላችሁ ውጡ፣ ለእውነተኛ እርቅ እንስራ፣ አገሪቱንም እናድን፣ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና እኛው አገራችንን በማስቀደም እንታደጋት” ሲሉ ከወትሮው በተለየ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው በዓመጽ መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው ፕሬዚዳንት ሙርሲን የሚደግፉ የሙስሊም egyptወንድማማች ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ የሃይል ርምጃ ከመወሰዱ በፊት በግብጽ ይህ ችግር ሊደርስ እንደሚችል የወተወቱ ነበሩ። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከስልጣን የተወገዱበት አግባብ ቀውስ ሊያስነሳ እንደሚችል ቢነገርም ሰሚ ባለማግኘቱ ቀውሱ ግብጻዊያንን እርስ በርስ አጋደለ። ግብጾች ግብጾችን ጨፈጨፉ። እስከ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ቀውስ እንዴት ሊቆም እንደሚችል ፍንጭ የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የሰዓት እላፊ፣ ግድያና እስር ዓመጹን ሊገታው አልቻለም። ይልቁኑም መሳሪያ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ግብጽን በጥይት እያመሷት ነው። እየገደሉም ነው።
በኢትዮጵያም በተለያዩ ወቅት የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በጸረ ሽብር ህግ፣ በእስር፣ በድብደባ፣ በግድያ፣ በማስፈራሪያና በጡንቻ የማስተናገዱ አዝማሚያ ከእለት እለት መጠናከሩ የሚከፋቸውን ሰዎችና ቡድኖች እያበራከተ ነው። የተፈናቀሉ ወገኖች ተበራክተዋል። በተፈናቀሉና መሬታቸው እየተቸበቸበ ያሉ ወገኖች ምሬት የከፋ ደረጃ ደርሷል። ሚዛናዊ ያልሆነው የአስተዳደር መዋቅርና የኢኮኖሚ ልዩነት የፈጠረው ቅሬታ በቃላት የሚገለጽ አልሆነም። እንደ አቶ ኦባንግ ሁሉ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ በማመን እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩትና ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ታዋቂ ምሁር ለጎልጉል እንደተናገሩት “በአሁኑ ወቅት ጥላቻው ከርሮ ህዝብ በገሃድ ስምና ብሔር እየለየ ፊት ለፊት መናገር ጀምሯል፤ የኑሮው ውድነት፣ የመብት ረገጣው፣ ዕንግልቱ፣ … የጥላቻውን መጠን አደባባይ ላይ እንዲታይ እያደረገው መጥቷል። አገራችን ያለችበት መንገድ አደጋ አለው። እርቅ የግድ ነው” ብለዋል፡፡
እኚህ ምሁር “ኢህአዴግ ውስጥ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑና አሁን በየአቅጣጫው ያለው ችግር የሚያሳስባቸው ወገኖች ስላሉ እነዚህን ወገኖች በመቅረብ ለእውነተኛ እርቅ ለመስራት ጊዜው አሁን፣ ለዚያውም ሳይረፍድ በቶሎ ሊሆን ይገባል። ይህንን ካላደረግን ሁላችንም እናዝናለን። ይቆጨናል። በቀላሉ ልናልፈው ወደ ማንችልው ጣጣ ውስጥ ሳንገባ እንረባረብ” በማለት ተናግረዋል። አስተያየት ሰጪው በቅርቡ ራሳቸውን ገልጸው አስተያየት እንደሚሰጡ፣ ለጊዜው የተጀመሩ ስራዎችን በነጻነት ለመስራት ሲሉ  ራሳቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡበትን ምክንያት ተናግረዋል።
“አገር እንደ ሰው አካል ነው። አንድ ቦታ ሲታመም ስሜቱ የሙሉው አካሉ እንጂ የተጎዳው አንድ ክፍል ብቻ አይደለም” በማለት የማጠቃለያ አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሲቋቋም ዓላማው ሁሉም ነጻ የማውጣት ታላቅ ዓላማ አንግቦ በመሆኑ በዚህ ረገድ በቅርቡ የእርቅ ተግባሩን ሊከውን የሚያስችለውን እቅዱንና የድርጊት መርሃ ግብሩን ይፋ እንደሚያደርግ፣ ለዚሁም ተግባራዊነት ኮንፍራንስ እንደሚያዘጋጅ አመልክተዋል።
በነጻ አውጪ ስም መደራጀትና መታገል ሙሉውን አካል /አገር/ ሊያድን እንደማይችል ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ከንባታ፣ ሲዳማ፣ ከፊቾ … እያልን በተበጣጠሰ አመለካከት ከማነከስ የአገራችንን ህልውና በአንድ ትልቅ አጀንዳ ውስጥ በማካተት ለመስራት ድርጅታችን ለሚያቀርበው ጥሪ ህዝብና ጥሪ የሚደረግላቸው ወገኖች ሁሉ ቀና ምላሽ ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሙስሊም፣ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ ወዘተ በማለት ከብሄርና ጎሳው ልዩነት በተጨማሪ መለያየት መፈጠሩ የአገሪቱን እጣ ፈንታ አሳዛኝና አደጋ እንኳ ቢፈጠር ለተግሳጽ የሚፈራ ሰው እንዳይኖር ማድረጉ አሳሳቢ የሆነባቸው በርካታ ዜጎች አሉ። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት ግን ሁሉም ቦታ የፖለቲካ ኮተት የሌለባቸው፣ ንጹህ ልብና ያላቸውና ህሊናቸውን የሚያከብሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች ብቸኛ አማራጭ በሆነው እርቅ ላይ አበክረው መስራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል። እሳቸው የሚመሩት አኢጋንም ለእንደዚህ አይነቶቹ ንጹሃን በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም “አሁን ችግር በተባባሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ‘እርቅ’ እንደ መፍትሄ የሚቀርበው፣ ዓለም አሁን ከመቻቻል ሌላ አማራጭ ስለሌላት ስለሆነ እኛም እርቅ ላይ ያለአንዳች ማቅማማት መስራት ይገባናል፤ ይህ ዕርቅ ግን በደፈናው ምህረት የሚያሰጥ ሳይሆን በፍትህ ላይ የተመሠረተ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “ድርጅታችን እርቅ ላይ ያለው ሃሳብ ከሌሎች በተለየ የተቋቋምንበት፣ የሰፋና የተፈጠርንበት መሰረት በመሆኑ ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ እስካሁን የሰራናቸውን ስራዎች ውጤት ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፤ ይህም እንደወቅቱ ሁኔታ ተለዋዋጭ ሳይሆን የጋራ ንቅናቄው ገና ከጅምሩ የወጠነውና እስካሁን ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ጉዳይ ነው። ኢህአዴግም ሰላም ስለሚያስፈልገው፣ ባለስልጣኖቹም መኖር ስለሚፈልጉ፣ ደጋፊዎቹም ዋስትና ስለሚያሻቸው የተቃዋሚ ወገኖችም አገራቸውን ስለሚያስቀድሙ፣ ሁሉም ወገኖች ቀና ምላሽ ይሰጣሉ ብለን እናምናለን” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
   Posted By.Dawit Demelash

Friday, August 16, 2013

የሙስሊሞችን ጥያቄና የሸኽ ኑሩን ግድያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ማያያዝ ወንጀል ነው አንድነት ፓርቲ: !!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

August 16, 2013
ነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም
እንደተለመደው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተሰናዳ ያለውን ‹‹ሸህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ አዘጋጅቶ አስተላልፏል፡፡ ይህ ዶክመንተሪ የገዥውን ፓርቲ ብፅእና ከመተረክም በላይ ጉልበተኝነትንና ፍረጃን ማእከል አድርጎ ከአኬልዳማ እና ከጃሀዳዊ ሀረካት የቀጠለ በፓርቲያችን እና በዜጎች ላይ የተቃጣ ህገ ወጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ የመንግስትነት ስልጣን የያዘ አካል ሀገራዊ ችግሮችን ለምን በዶክመንተሪ ፊልም ለመፍታትና ለማዳፈን እንደሚጥር እንቆቅልሽ ቢሆንብንም አሁንም ከዜጎች የሚነሱ ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት እንዳለባቸው ፓርቲያችን በፅኑ ያምናል፡፡ የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄም በውይይትና በመግባባት ላይ ተመስርቶ ሊመለስ እንደሚገባና የሀይል እርምጃው መቆም እንዳለበት ያለንን ጽኑ እምነትና አቋም ደግመን እናረጋግጣለን፡፡Unity for Democracy and Justice (UDJ) party
መንግስት ህዝቡን በዶክመንተሪ ፊልም በማስፈራራት ለማሳመን ከመድከም ባሻገር ዴሞክራሲያዊ ባህሪን መላበስ አልተቻለውም፡፡ ዶክመንታሪ ፊልሙም እንደተለመደው የኢህአዴግ የፍረጃ ፖለቲካ የተንፀባረቀበት፤ የተለየ ሀሳብና ጥያቄ ያቀረቡ ግለሰቦችንና ተቋማትን ማሸማቀቅ ብሎም የማጥፋት እኩይ ተግባር ማሳያ ነው፡፡ ይሄ የጉልበት አካሄድ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ረገጣውን አባብሶ ከመቀጠል ውጭ መፍትሄ የማያመጣ ሲሆን የፓርቲያችንን ሰላማዊ ትግልም ሊቀለብሰው አይችልም፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለፅነውም ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ አድርጎ ውሳኔ ሳያሳልፍ በቴሌቪዥን ፍርድ መስጠቱ ገዢው ፓርቲ በህግ የማይገዛ አምባገነን ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ሲሆን የፍትህ ስርዓቱ ልዕልናም በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተገፏል፡፡
‹‹ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› በሚል ርዕስ የቀረበው ፊልም በህጋዊ መንገድ ተቋቁሞ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን የፓርቲያችንን ስም ለማጥፋት፤ ለመፈረጅና በህዝቡ ዘንድ እየገነባን ያለነውን ተቀባይነት ለመሸርሸር ሆን ተብሎ የተከናወነ የፈራጁን አካል ህገ-ወጥነትም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ የሙስሊም ወንድሞቻችንን ለሁለት ዓመት የዘለቀ ጥያቄና የሼህ ኑሩን ግድያ ከፓርቲያችን ጋር በማያያዝ ፖለቲካዊ ጥያቄ ለማስመሰል መሞከር ጥፋትም ወንጀልም ነው፡፡
ፓርቲያችን አንድነት አሁንም ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም ሳይለይ ዜጎች የሚያነሱት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፤ የመንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ገብነትም እንዲቆም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያረጋግጣል፡፡ የኢትዮጵያ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የፓርቲያችን አመራሮች በየግዜው የሚያደርጉትን ንግግሮች ሞያንና ንጹህ ህሊናን በሚያጎድፍ መልኩ እየቆራረጠ ሙሉ ትርጉሙን እንዳይዝ አድርጎ በማስተላለፍ እየፈጸመ ያለው አሳፋሪ ተግባር እንዲታረም ተቋሙን እናሳስባለን፡፡ በሼህ ኑሩ ላይ የተፈጸመው ግድያ በየትኛውም አካል የተፈጸመ ቢሆንም ህገ ወጥ እና ኢሰባአዊ መሆኑን ፓርቲያችን የሚያምን ሲሆን ድርጊቱም በሀገራችን ህግ እንዲዳኝ በድጋሚ እንጠይቃለን፡፡ መንግስትም በፓርቲያችን ላይ እያደረገ ካለው ፍረጃ እንዲታቀብና ወደ ውይይት እንዲመጣ እንዲሁም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያነሱትን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዲመልስ በድጋሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
  Posted By,Dawit Demelash

Thursday, August 15, 2013

ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ!

August 15, 2013

የሐገሬ ጉዳይ ያገባኛል፤ ይመለከተኛል ብላችሁ በሲቪክ፤ በፖለቲካ፤ በብሄር፤ በህብረ ብሄር የተደራጃችሁና እንዲሁም በግላችሁም የምትንቀሳቀሱ ታዋቂ ግልሰቦች በሙሉ፡ እሳት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ድርጅቶችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ለፊት ለፊት ውይይት እ. አ. አቆጣጠር ኦገስት 17 2013 በቨርጂኒያ ሸራተን ሆቴል ጥሪ ማድረጉን በአለም ዙሪያ ተበትነን የምንገኝ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ታዳሚዎችና አስተዳዳሪዎች ጥሪውን በታላቅ ስሜት የምንደግፍና እሳት ሚዲያ ይህንን መድረክ በማዘጋጀቱ ያለንን ከፍተኛ አድናቆት እንገልጻለን።Ethiopian Flag
ኢትዮጵያ ሃገራችን በታሪኳ በህዝብ የተመረጠ መሪ ሳይኖራት ነገስታትና አምባ ገነኖች ሲፈራረቁባት ኖራለች፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንኑ በደነደነ ትከሻው ሲሸከም ኖሯል።
ባለፉት 22 አመታት ሃገራችንን የገጠማት አገዛዝ ግን በአለም ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ የሰየመ፤ ለተቀረው ህዝብ ታላቅ ጥላቻና ንቀት ያለው ቡድን ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል። የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን፤ የግፍ አገዛዙን የሚቃወሙትን የተለያየ ስያሜ እየሰጠ ከማሰር፤ ሰቆቃ ከመፈጸምም በላይ ዘር እስከ ማጥፋት የሚደርስ ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል።
ዝርዝሩ ከናንተ የተሰወረ በይሆንም ለዋቤ ያህል፡ የወያኔ ስርዓት
1. በተፈጥሮ ሃብታችን እኛም ተጋሪ እንሁን ያሉትን የአኝዋክ ተወላጆች ፈጅቷል፡ ከሞት የተረፉትን ከቤታቸው፤ ከንብረታቸው፤ ከተወለዱበት መንደር አፈናቅሎ የአውሬ ሲሳይ አርጓቸዋል። መሬታቸውን ለባእዳን ሸጦታል፡ ስንቶቹ ሃገር ጥለው እንደተሰደዱ ስንቶቹ በህይውት እንደተረፉ እንኳ በውል አይታወቅም
2. በትረ ስልጣን ከመያዙም በፊት ሆነ ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ በመነሳት በጎንደርና በሰሜን ወሎ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅሎና ገሎ መሬታቸውን ቀምቶ የትግራይ ታጣቂዎችን አስፈሮበታል፡ ያም አልበቃ ብሎ ዘር እንዳይተካ የማምከኛ መርፌ እየወጋ የአማራን ዘር በማጥፋት ላይ ይገኛል፡
3. የሶማሌ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ከአለም እይታ ጋርዶ ፈጅቷቸዋል አየፈጀም ነው፡ በመሆኑም ምን ያህሉ በህይወት እንዳሉ ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
4. የኦሮሚፋ ተናጋሪ ህዝባችንን የተለያየ ስም እየሰጠ በየአደባባዩ አየፈጃቸው፤ እና በገፍ እስር ቤት እያጎራቸው ነው፡ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ያለው በመሆኑ ሊጨርሳቸው አልቻልም እንጂ የወያኔ እቅድ ለመጨረስ ነበር። ከዚህ እኩይ ተግባሩ፡ ይታቀባል ተብሎ አይጠበቅም።
5. አማርኛና ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን አጋጭቶ እንዲተላለቁ ታላቅ ሴራ ቢያሴርም በሁለቱ ህዝቦች በሳልነት ያቀደውን ያህል እንዲሳካ እድል አልሰጡትም።
6. የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የሃይማኖት መሪዎቻችንን ራሳችን እንምረጥ፤ መንግስት ራሱ ያወጣውን ህገ መንግስት ጥሶ በእምነታችን ጣልቃ አይግባ በማለት ላለፉት 18 ወራት ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ ቢቆዩም ጋጠ ወጡ የወያኔ ቡድን ግን አኔ የመረጥኩላችሁን ሃይማኖትም ሆነ የሃይማኖት መሪዎች ተቀበሉ በሚል መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘረባቸው ነው። ይህም ሳያንሰው ከክርስትና እምነት ተከታይ ወገነኖቻቸው ጋር ለማቃቃርና ለማፋጀት ከፍተኛ በጀት መድቦ ፍፁም ሃላፊነት የጎደለው ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛል።
የወያኔ ወንጀል ለቀናት ቢዘረዘር አያልቅም፡ ለተነሳንበት መልዕክት ግን በቂ ነው ብለን እናምናለን፡
ወያኔ ይህን ሁሉ ወንጀል ሲፈጽም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈናል፡ ሰብአዊ መብት በዛች ሃገር እንዲከበር እንታገላለን፤ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እንፈልጋለን ከሚሉ ድርጅቶች ግን ሚዛን የደፋ እንቅስቃሴ ሲደረግ አልታየም። ለምን ለሚለው ጥያቄ አንድ መቶ አንድ ምክንያቶች ሊሰጡ ይችላሉ። ግን እነዚህ የሚሰጡት ምክንያቶች ወያኔ ህዝቡ ላይ ከሚያደርሰው ግፍ የበለጡ ነበሩን? ናቸውን? ይህንን ለያንዳንዳችሁ ህሊና እንተወዋለን።
ሀ) የጋምቤላ እልቂት ብቻ በቂ መነሻ በሆነ ነበር፡ http://www.youtube.com/watch?v=BMAbsbAWyks&feature=player_embedded#at=14
ለ) ኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ሰቆቃ ብቻ ልዩነትን ፈቶ በጋራ ለመታገል በቂ በሆነ ነበርhttp://www.youtube.com/watch?v=UeR3AmFOzOc
ሐ) በእንደዚህ አይነት ደስታና ተስፋ የተጀመረው የ1997 ምርጫ https://www.youtube.com/watch?v=VMgdDe3ACtI ይህን በመሰለ አሰቃቂና አስደንጋጭ ሁኔታhttps://www.youtube.com/watch?v=oIOHPaqC6OI መጠናቀቁ ምንም አይነት የግል ፍላጎትና አላማን ወደጎን ሊያሰተውና ሊያስተባብር በተገባ ነበር፡
መ) በቅርቡ ለ3 አመት ያለምንም ፍርድ ታስረው ለመፈታት ፊርማ በማሰባሰባቸው ብቻ ቂሊንጦ
http://www.youtube.com/watch?v=Rq8ml5h8TwY ተወስደው የተደበደቡትና ለሞት የተዳረጉት የኦሮሞ ወገኖቻችን የሰቆቃ ጥሪ ብቻ ሊያናድደንና በቃ ሊያስብለን በተገባ ነበር
ሰ) ሰሞኑን በእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጅምላ ጭፍጨፋhttp://ecadforum.com/ethiopianvideo/2013/08/08/ethiopian-muslims-protest-august-07-2013/ ብቻ ወደ አንድ ሊያመጣ ይገባ ነበር፡
ረ) በወያኔ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተጠቂ መሆናቸውን እንኳ በውል ያላወቁ ልጅ ወልዶ ራሳቸውን ለመተካት በየጸበሉ የሚነከራተቱ ወገኖች እንባ http://www.youtube.com/watch?v=0tJ0VmilVmQ ብቻ በአንድ ጎራ ሊያሰልፈን ይገባ ነበር፡
ይህ ሁሉ አልፏል፤ ካለፈው መማር እንጂ መማረር የትም አያደርስምና ከዚህ በሗላ ግን ያለፈው ስህተት እንዳይደገም ብርቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ አደራችን የጠበቀ ነው።
የሐገሬ ጉዳይ፤ የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የእንሰሳ መብት በሚከበርበት ወቅት ባንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ ሰቆቃ መፈጸም የለበትም፤ ከትግራይ የተውጣጡ የወንጀለኛ ቡድኖች ባሪያ ሆነን መኖር አንችልም አይገባንምም ብላችሁ በተናጠልም ይሁን በቡድን በማህበረ ሰብ (ሲቪክ)ም ይሁን በፖለቲካ፤ በብሄርም ይሁን በህብረ ብሄር ድርጅት ስም የምትንቀሳቀሱ ሁሉ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝታችሁ ሃሳባችሁን በግልጽ ተነጋግራችሁ፤ ጊዜያዊ መፍትሄ (short term solution) ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳብ (Roadmap) መክራችሁና ዘክራችሁ አገርን ከመፍረስ ህዝብን ከጥፋት ትታደጉት ዘንድ የዜግነት ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ (ECADF)
 Posted By,Dawit Demelash

Tuesday, August 13, 2013

ታላቅ ሃገራዊ መልዕክት ለሁሉም በማዳረስ ሃሰትን ለማንገስ የሚደረገውን ሩጫ ያጋልጡ !!!

ታላቅ ሃገራዊ መልዕክት ለክርስቲያን ወገኖቻችን


እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በሃገራችን ኢትዬጲያ ለረጅም ዘመናት ከክርስትና እምነት ተከታዬች እና ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር ተከባብረን እና ተደጋግፈን ስንኖር መቆየታችን ይታወሳል፡፡

ይህም የመቻቻል እና የመደጋገፍ ባህላችን ዛሬም መልኩን ሳይቀይር አለምን በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ሆኖም ይህንን ተቻችሎ እና ተከባብሮ በሰላም የመኖር ባህላችንን ለማደፍረስ የኢህአዴግ መንግስት በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ በመግባት ከሊባኖስ አህባሽ የተሰኘ ከእስልምና አስተምህሮ ያፈነገጠ ባዕድ እምነት በማስመጣት በሙስሊም ወገኖቻችሁ ላይ በግዳጅ እምነታችንን ለማስቀየር እየሞከረ ይገኛል።
እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በሃገራችን ኢትዬጲያ ለረጅም ዘመናት ከክርስትና እምነት ተከታዬች እና ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር ተከባብረን እና ተደጋግፈን ስንኖር መቆየታችን ይታወሳል፡፡
For Ethiopian muslims and chrstians
እኛም ሙስሊሞች መንግስት በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ አትግባብን ከጥንት ጀምሮ በሃገራችን የነበረውን አስልምና መንግስት ባስመጣው አህባሽ በተሰኘ አዲስ ሃይማኖት አንቀይርም በማለታችን አክራሪዎች፣አሸባሪዎች ናችሁ በማለት በመንግስት እየተደበደብን እየተገደልን እና እየታሰርን እንገኛለን፡፡
መንግስት በሃማኖታችን ላይ ጣልቃ አይግባብን በማለት በሰላማዊ መንገድ መቃወም ከጀመርን ድፍን ሁለት አመት ሊሞላን ጥቂት ጊዜያት ብቻ ይቀሩታል፡፡ በሁለት አመት የሰላማዊ ትግላችን ሂደት ውስጥ ከጅማሮ አንስቶ አስካሁን ድረስ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርበን ምላሽ እስኪሰጠን እየጠበቅን ብንገኝም መንግስት እንደመንግስት በሚሊዬን የሚቆጠረውን የሃገሪቷን ሙስሊሞች ድምፅ ከመስማት ይልቅ ጥያቄዎቻችንን በማድበስበስ እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የጠየቅናቸውን 3 ቀላል ጥያቄዎችንን በማጣመም በሃሰት ፐሮፖጋንዳ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፤


ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ ሦስቱ መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን የሚከተሉት ነበሩ
1ኛ:- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች በህዝብ ያልተመረጡ በመሆናቸው በመስጂድ ውስጥ በሚደረግ ምርጫ በህዝብ በሚመጡ አመራሮች ይተኩ።
2ኛ:- አወሊያ ብቸኛው የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም በመሆኑ ከህዝብ በሚመረጥ ቦርድ ይተዳደር።
3ኛ:- በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በአስገዳጅነት እየተካሔደ ያለው የአህባሽ እምነት ጠመቃ ይቁም፣ እንደማንኛውም እምነት ግን በራሱ ተቋማት እምነቱን የመስበክ እና የማስፋፋት መብት አለው። መንግስት ከላይ ለተጠየቁት ጥያቄዎች አስፈላጊውን ትብብር ያድርግልንየሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ|፡፡
እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸው እጅግ በጣም ቀላል ጥያቄዎች ከላይ ያስቀመጥናቸውን ይመስላሉ።ዛሬ ግን መንግስት እነዚህን ተራ እና ቀላል ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ የስልጣን ቆይታን ለማራዘም ሙስሊሞችን እና ክርስቲያኖችን ለማጫረስ ሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት እንመስርት እያሉ ነው በማለት መርዙን እየረጨ ይገኛል፡፡
ከላይ እንዳነበባችሁት ሶስቱን ጥያቄዎቻችንን ለመንግስት እንዲያደርሱልን ከመላው ሃገሪቱ በፊርማ ተደግፎ የመረጥናቸውን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እስር ቤት በማስገባት በኢትዬጲያ መንግስት የተለመደችዋን አሸባሪ የሚለውን ክስ በመለጠፍ ወደ ወህኒ ወርውሮብናል፡፡
ይህም ሳይበቃ ከቀናት በፊት የረመዳን ፆም ፍቺ በኢድ አልፈጥር በአላችን ላይም ጸሎታችንን አድርሰን በመመለስ ላይ በነበርንበት ወቅት ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስቱን ቀላል ጥያቄዎች እና ወደ ወህኒ በመንግስት በሃሰት ተወንጅለው የተወረወሩብንን ኮሚቴዎቻችንን እንዲፈቱል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የሃገራችንን ሰንደቅ አላማ በመያዝ ጥያቄዎቻችንን አቅርበን በሰላም ወደየቤታችን በአላችንን ለማክበር በመመለስ ላይ በነበርንበት ወቅት የመንግስት ወታደሮች መንገድ በመዝጋት ሴት ወንድ ህፃን አረጋዊያን ሳይሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ደበደቡን፡፡ በድብደባውም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወገናችሁ ጉዳት ደረሰበት፡፡ነፍሰጡር ሴትን ጨመሮ ሌሎች 5 ሙስሊሞች ፖሊስ በፈጸመው አረመኒያዊ ድብደባ ሂወታቸውን አጥተዋል፡፤በሺዎች |የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወደ አስር ቤት ተግዘዋል፡፡
ይህም ኢሰብአዊ ድብደባ በአዲስ አበባ፣በደሴ ፣በወልቂጤ እና በአዳማ በሚኖሩ ሙስሊም ወገኖቻችሁ ላይ ተፍፅሟል፡፤ ይህንን እውነታ ከጎረቤታችሁ፣ከስራ ባልደረባችሁ ከሆኑ ሙስሊሞች ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡
መንግስት ግን በውሸት በሚያሰራጭበት ጣቢያው ጥቂት አክራሪዎች ኢስላማዊ መንግስት ካልተመሰረት በማለት ሁከት ቀስቅሰው በቁጥጥር ስር አውያቸዋለው በማለት በደስታችን በኢድ በአላችን ቀን የፈፀመብንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት በመካድ የህፃናት እና የሴት እህቶቻችንን እንዲሁም የአሮጊት እናቶቻችንን እና ሽማግሌ አባቶቻችንን እንባ፣ለቅሶ እና ደም የጥቂቶች ሲል አሾፈብን፡፤
በኢድ በአላችን ቀን መንግስት የፈፀመብን አሰቃቂ ድብደባ መሸከም ያልቻሉ እናቶች ህፃናት፣ሴቶች እና አባቶች ተክለ ሃይሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን በመግባት ሂወታቸውን በማትረፍ ቤተክርስቲያኗ ለታሪክ የማይረሳ አጋርነቷን አሳይታለች፡፤ድብደባው በሚፈፀምበት በነበረው በሁሉም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች ቤታቸውን በመክፈት የተጎዱትን ሙስሊሞች እንክብካቤ በማድረግ እና ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ለረጅም አመታት በአንድነት እና በፍቅር የመኖር ተምሳሌትነታቸውን እና አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፤
ውድ ወገኖቻችን ሆይ እኛ ኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላለፉት ሁለት አመታት በሰላማዊ መንገድ የጠየቅነው ፍፁም ሃይማኖታዊ ጥያቄ እንጂ መንግስት ከናነተ ጋር እኛን ለማጋጨት እንዳሰበው የሸሪአ መንግስት ይመስረትልን በሚል አይደለም፡፡
እኛ ሙስሊሞች አይደለም የሸሪአ መንግስት ይታወጅልን ብለን ልንጠይቅ ይቅርና በኢትዬጲያ የሚገኙ መስጂዶችን እንኳን ሙስሊሙ ያስተዳርራቸው፣የሙስሊሙ መሪ ተቋም የሆነው መጅሊስ ህዝብ በመስጂድ ውስጥ በሚመርጣቸው የሃይማኖት አባቶች ይተኩልን ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎን እተደበደብን እየተገደልን እና እየታሰርን እንገኛለን፡፤
በመሆኑም ሁሉም የኢትዬጲያ ህዝብ መንግስት ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅሙ ሲል ሙስሊሙን ከክርስቲያን ወገኑጋር ለማጋጨት በተለያዩ ሚዲያዎቹ አክራሪዎች፣ጥቂቶች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱባችሁ ነው በማለት በሚያደርገው ሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ እንዳትሸወዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
በኢ.ቲ.ቪ የሚቀርቡት ጥምጣም የጠመጠሙ ሙስሊም መሳዬች በሙሉ የአዲሱ አህበሽ እምነት ተከታዬች ሲሆኑ በተጨማሪም የመንግስት ካድሬዎች እና በገንዘብ የተሸነገሉ ግለሰቦች በመሆናቸው ሙስሊሙን እንደማይወክሉ በዚህ አጋጣሚ እንገልፅላቹሃለን፡፡
በመንግስት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አጠገባችሁ የሚገኙትን ሙስሊሞች በመጠየቅ ተጨማሪ እውነታዎችን መረዳት የምትችሉ መሆኑን እንገልፅላቹሃለን፡፡
ሰላም፣ ፍቅር እና ብልፅግና ለኢትዬጲያ ይሁን!!!
ይህን መልዕክት ላልደረሳቸው በማዳረስ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ!!!!
  Posted By.Dawit Demelash

ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?

lelissie


ላለፉት 5 ዓመታት ያህል ከልጆቿና ባለቤቷ ተለይታ በእስር ስትማቅቅ የነበረችው ሌሊሴ ወዳጆ መፈታቷ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስደሰቱ ተጠቆመ፡፡
የጋዜጠኛ ሌሊሴን መፈታት አስመልክቶ Ayyaantuu News Online ለንባብ ባበቃው ዜና እንዳመለከተው በስደት አውስትራሊያ ከሚኖረው ከባለቤቷና ከልጆቿ ጋር ተቀላቅላለች፤ ድረገጹ ዜናውን በምስል በማስደገፍም አቅርቦታል፡፡
በጋዜጠኝነት ሲያገለግል የነበረው ባለቤቷ ዳቢሣ ዋቅጂራ አገር ጥሎ መሰደዱን ተከትሎ በማታውቀው ምክንያት የኦነግ አባል ነሽ በማለት ኢህአዴግ 10ዓመት ያለ አመክሮ ፈርዶ ወኽኒ እንዳወረዳት ይታወሳል፡፡ ይህንን ህዝብን ያበሳጨና ያስቆጣ ጉዳይ ሌሊሴ ከታሰረችበት ጊዜ ጀምሮ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ጥበቃ ድርጅት (CPJ) ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲያወግዙትና እንድትፈታ ሲሟገቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም” በማለት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተናገሩትን ተከትሎ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ታህሳስ 24፤2005ዓም (January 2, 2013) በዘገበበት ወቅት፤ ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆን የሰው ልጆችን ኅሊና ከሚፈታተኑት የማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር በማያያዝ የግምባር ዜና አድርጓት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከአብራኳ የወጡትን ልጆቿን የማሳደግ ወግ የተነፈገችው እናት ከ3 ልጆቿ ጋር ሆና የሚያሳየውን ምስሏ አስደግፎ ጎልጉል በወቅቱ ሲዘግብ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለተናገሩት ቅጥፈት ማጣፊያ በማድረግ ነበር፡፡
ከኦነግ ጋር ግንኙንት አለሽ ተብላ ከ3 ለጆችዋ ተነጥላ 10 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባት ሌሊሴ ወዳጆ
ከኦነግ ጋር ግንኙንት አለሽ ተብላ ከ3 ለጆችዋ ተነጥላ 10 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባት ሌሊሴ ወዳጆ
በእስር ቤት ታጉረው ከሚገኙት በርካታ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች መካከል አንዷ ስለሆነችውና ስለአጠቃላይ የግፍ ቀንበር የተጫነባቸው ወገኖች በወቅቱ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የአቶ ሃይለማርያምን ንግግር “በእውነቱ ይህ ፍጹም ቅጥፈት የተሞላበትና አጸያፊ ነው፤ እነዚህ እስረኞች እኮ በቁጥር የሚታወቁ ብቻ ሳይሆኑ ስም፣ ቤተሰብ፣ ልጅ፣ ዘመድ፣ ወዘተ አላቸው፡፡ እናውቃቸዋለን፤ ዓለም ያውቃቸዋል፤ እንግዲህ ጠ/ሚ/ሩ ለእነዚህ ልጆችና ቤተዘመዶች ነው አባታችሁ/እናታችሁ/ዘመዳችሁ ወንጀለኛ አሸባሪ ነው እንጂ የፖለቲካ እስረኛ አይደለም እያሉ ነው ያሉት፤ … ይህ ሥነምግባር የጎደለው ንግግር ነው” በማለት ዕርቃኑን አስቀርተውት ነበር፡፡
“ሌሊሴ ከዚህ ቀጥሎስ?” በሚል በህይወት የተፈተነችበትን የእስርቤት ቆይታዋና በተመሳሳይ ሁኔታ በእስር የሚማቅቁትን ኢትዮጵያዊ ወገኖቿን አስመልክቶ የሚደርስባቸውን ከአንደበቷ ለመስማት የሚጠብቁ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ “ሌሊሴ ጭንቀቷን ለተጨነቀላት የኢትዮጵያ ህዝብ የመፈታቷን ዜናና የእስር ቤት ቆይታዋን ከራሷ አንደበት እንሰማለን” ብለው እንደሚጠብቁ ይናገራሉ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለባለቤቷ፣ ለልጆቿ፣ ለቤተሰቦቿና ከእስር እንድትፈታ እንደየእምነታቸው ለጸለዩና ለተጨነቁ በሙሉ በጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆ መፈታት እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በየእስርቤቱ የሚማቅቁትን የቤተሰብ አውራና የአገር ተረካቢዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች እና ሌሎች ንጹሃን ዜጎች መንግሥት እስርቤት አጉሮ ዕርምና ቂም ራሱ ላይ ከሚከምር ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ችግሩን ቢያስተነፍስና ወደ ዕርቅ ቢመጣ የተሻለ እንደሆነ የአገር ጉዳይ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋቾች ምክራቸው ይሰጣሉ፡፡ (ፎቶዎቹ የተወሰዱተ ከAyyaantuu News Online)
  Posted By.Dawit Demelash

Monday, August 12, 2013

ኢሕአፓ ወክንድ አራተኛ ጉባኤውን አካሔደ ( ቪዲዬ ም) አካተናል




ኢሕአፓ ወክንድ ሰኔ ፪፯ እና ፪፰ ባካሄደው በዚህ አራተኛ ጉባዬው ሐገራችን የምትገኝበትን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ፣ የውስጥና የውጭ ሀይሎች የሕዝቧን አንድነትና አይበገሬነት ለማዳከም ብሎም ሉዓላዊነቷን ለመድፈር የሚሸርቡትን ሴራ በጥንቃቄ መርምሯል። ከዚህም በማያያዝ ኢሕአፓ ወክንድ በሰማያዊ ፓርቲ በር ከፋችነት በሐገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ከቅርብ ቀን ወዲህ የወያኔን አፈና ሰብረው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው ሕዝባችን በተለይ በወያኔ የግፍ አገዛዝ ላይ ያለውን ተቃውሞ እና ለለውጥ ያለውን ተነሳሽነት አደባባይ ወጥቶ በተቃውሞ ሰልፍ እንዲያሳይ በመጥራታቸው እና የተቃውሞ ሰልፉቹም በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቃቸው ለበለጠ የተቀናጀ ትግል የሚያነሳሳ ነውና ሁለገብ ጸረ ወያኔው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያልተገደበ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁነቱን አረጋግጧል።
የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ ድርጅት ከተቋቋመበት ወቅት ጀምሮ ቀደምት አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን እና እናቶቻችን ለተሰውለት ሐገራቸንን ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ትግል ሳያሰልስ አስተዋፅዖ ሲያደርግ ቆይቷል። ይህ ቀጣይነት ያለው ትግል ብዙ መሰዋዕትነትን የጠየቀ ቢሆንም ወደፊትም ለሚከፈለው መስዋዕትነት ኢሕአፓ ወክንድ ከመቼውም ግዜ ይበልጥ ዝግጁ ነው። ኢትዮጵያችን አድጋና በልጽጋ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት መብቱ ተከብሮ የሚኖርባት ሐገር ስትሆን የማየት ራዕይ ሰንቀው እኛ ብናልፍም ጓዶቻችን ዳር ያደርሱታል፣ ታጋይ ይሞታል አንጂ ትግል አይሞትም፣ ኢሕአፓ ያቸንፋል!! እያሉ መተክያ የሌለውን ሕይወታቸውን የሰዉትን ብርቅዬ የሕዝብ ልጆች የትግል አርማቸውን ከፍ አድርጎ፣ በደምና በአጥንት የተገነባ አኩሪ ታሪካቸውን ጠብቆ ትግሉን ለማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለበት በማመን የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ ድርጅት አራተኛውን ጉባኤውን ባጠናቀቀብት እለት የትግል ቃል ኪዳኑን አድሷል።
ኢሕአፓ ወክንድ በዚህ ጉባኤው በውጭ የሚገኙ ጸረ ወያኔ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሙሉ ሀይላቸውን በማስተባበር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ዴሞክራሲያዊ አደረጃጀት ሁሉንም ዜጋ አሳትፎ የሕዝብ የስልጣን ባለቤትነት እንዲከበር፣ የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የሕዝቧ አንድነት ተጠብቆ የእምነት ነጻነት አንዲረጋገጥና በአጠቃላይ የወያኔ ስርአት ተወግዶ በሕዝባዊ ሥርዓት እንዲተካ በሐገር ቤት ከሚገኙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ መታገል አማራጭ የማይገኝለት አግባብ መሆኑን በአጽንኦት የሚቀበለውና ለተግባራዊነቱም በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፍ መሆኑን አረጋግጧል።
ኢሕአፓ ወክንድ ዛሬም አንደትላንት እራሱን አንደ አንድ አማራጭ ኃይል ለስልጣን ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ እያቀረበ ለሕዝብና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ከሚታገሉ ሀይሎች ጋር ከድርጅት አጥር ይበልጥ ኢትዮጵያዊነትን በማጥበቅ በውጪ የምንገኝ ሁሉ እንዴት በሐገር ቤት ካሉት ወገኖቻችን ጋር በመተባበር የጋራ መድረክ ፈጥረን፣ ለምን ነገ ዛሬ ሳንል በአንድነት መነሳት አንደሚገባን በስፋት ተወያይቶ የሚከተሉትን ነጥቦች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ በጽሞና ሊመለከቷቸው ይገባል ይላል።
፩. ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ምሁራን በወያኔ ጣልቃ ገብነት በነፃነት መስራት ባለመቻላቸው ሐገር ጥለው እየተሰደዱ መሆኑን።
፪. የአንድ ሐገር የኢኮኖሚ ምሶሶ የሆነው ሐገር በቀል የንግድ ማህበረሰብ በኢንቨስተር ስም የሚመጡ ባዕዳንና የወያኔን የንግድ ኩባንያዎች ገደብ ያጣ አድሎአዊ ተጽእኖ የተነሳ ስራ መስራት ባለመቻሉ ሐገር ጥሎ እየተሰደደ መሆኑን።
፫. ለአንድ አገር የጀርባ አጥንት የሆነው ወጣት ሐገሩን ጥሎ እየወጣ መሆኑን፣ ያልቻለ ደግሞ የሱስ ተገዥ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑን። 
፬. ጋዜጠኞችን ወያኔ ሆን ብሎ እያዋከበ፣ እያሰረ፣ እየገደለ የተረፉትንም ከሐገር እንዲወጡ እያደረገ መሆኑን።
፭. የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር፣ የሰራተኛ ማህበር፣ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ በሐገሪቱ እድገት፣ ሉዓላዊነት፣ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉልህ ሚና ሊኖረው የሚችለው ዜጋ ሁሉ ከሐገሩ እየወጣ በምትኩ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ለአንድነት አስጊ የሆኑ ባእዳውያንና የአንድ ዘር ምርጥ ቡድን አባላት የበላይነት በኢትዮጵያ ሐገራችን ተንሠራፍቶ መገኘቱ ሐገራችንን መስቀለኛ መንገድ ላይ ያደረሳት መሆኑ ኢሕአፓ ወክንድን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳስቦታል። በመሆኑም ኢሕአፓ ወክንድ ከዚህ በመነሳት የተቃዋሚ ድርጅቶችንም አሰላለፍ አጽንኦት ሰጥቶ ተመልክቷል።

፮. ሕዝባችንን ሆን ብሎ ለመከፋፈልና ለማዳከም ብሎም ለወያኔ መሰል ጎጠኛ ጠባብ ቡድን አባላትና ለባእዳን ጠላቶቻችን የዘመናት ተገዥና ባርያ ለማድረግና ሕዝባችን በግፍና በመከራ እየማቀቀ መብቱ ተረግጦ እንዲቀጥል የሚደረጉ ስውርና ግልጽ ሴራዎችን ነቅቶ ማጋለጥና መታገል የሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነትና የታሪክ ግዴታ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የማይገባ መሆኑን።
ኢሕአፓ ወክንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነታቸውን አቻችለው እራሳቸውን አንደ አማራጭ በማቅረብ አላማቸውን ለሕዝብ ቀርበው በግልጽነት በማስረዳት ሕዝባዊ ውሳኔን በጸጋ የሚቀበሉበትን ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት በወያኔ እየተገፋ ከሐገሩ የወጣውን ወገን እንደየእውቀቱና እንደየተሰጥዖው ለሐገሩ እና ለሕዝቡ ማበርከት የሚጠበቅበትን የዜግነት ግዴታውን ሊወጣበት የሚችልበት መድረክ እስካልፈጠሩና እስካልከፈቱ ድረስ ለሐገራችን ችግር ፈጣሪ ባይሆኑም ለችግሩ መፍትሄ ሰጪ ሊሆኑ ባለመቻላቸው ከታሪክ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ማስገንዘብ ይወዳል።
ስለዚህ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ወያኔን በማንኛውም መንገድ መታገል የሚፈልገውን ወገን ዛሬ እንደችሎታውና እንደተሰጥኦው አሰልፈው ማታገል ይጠበቅባቸዋል። ኢሕአፓ ወክንድም ይህን ትልቅ አቅምና እውቀት ያለውን ሐገር ወዳድ ሀይል አሰባስቦ ለማታገል ቆርጦ ከተነሳ ወገን ጋር በሐገር ቤትም ይሁን በውጭ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የተላበሰ ሁሉንም ሐገር ወዳድ የሚያሳትፍ ሥራ በመስራት ከአሁን ቀደም በተግባር ያሳየውን አንቅስቃሴ ከመቼውም ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ውሳኔዎችን አሳልፎአል። 
የሐይማኖት ነጻነት አንዲከበር፣ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ፣ በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የሚደረገው የይዞታ ማፈናቀል፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግፍና ሰቆቃ እንዲያበቃ፣ የወያኔ ወንጀለኞች ካባቸውን በመቀየር የተቃዋሚ ድርጅት መሪ መስለው መቅረብ ሲሞክሩና የሐይማኖት ቤቶቻችንን በታጣቂዎችና የበግ ለምድ በለበሱ ተኩላዎች መውረር ሲቃጡ በግንባር ተሰልፎ በማጋለጥና በመመከት፣ ዘንድሮ ፴ኛ ዓመቱን ያከበረውን የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን ከወያኔ ስውርና ግልጽ ደባ ጥቃት ለመመከት ከህዝብ ጎን በመሰለፍ ያደረገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለወገኖቻችን እያበሰረ ይህን ኃላፊነት ወስደው በብቃት ታግለው ላታገሉን አመራሮቻችን አይበገሬነትና ውድ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይህ ጉባኤ ስራችሁ ምስክራችሁ ሆኗልና ለአሉባልተኞች ቦታ ሳትሰጡ በያዛችሁት የድል ጎዳና ግፉበት ይላል።
ከኛ በፊት በክብር ባለፉ ጀግኖች ስጋ፣ ደምና አጥንት እንዲሁም መተኪያ በሌለው የሕይወት መሰዋትነት ተከብራና ታፍራ የኖረች ውድ ሐገራችንን፣ በሰላም በፍቅርና በመተሳሰብ አንድነቱን ጠብቆ፣ ተዋዶ፣ ተጋብቶ፣ ተዋልዶ፣ ተሳስሮ፣ ለብዙ ሺ አመታት የኖረው ሕዝባችንን፣ ወያኔና የውጭ ጠላቶቻችን እንዲሁም ዘመን አፈራሽ በታኝ ባንዳዎች “የፖለቲካ ተንታኞች” የሚያካሂዱት ግልጽም ሆነ ስውር ሴራና ገደብ ያጣ ግፍ ከአቸናፊነት እንደማይገቱት አለመገንዘብ ታሪክ አራሷን አንድምትደገም መዝንጋት ወይም እብድነት መሆኑን ልብ በሉ ይላል::
ኢሕአፓ ወክንድ ደርሶ በሕዝባችን ደም መነገድ ለሚሹ፣ “ዘመናዊ” ባንዳዎች ከሕዝብና ከታሪክ ተማሩ ይላል። ታሪክ እራሷን ትደግማለችና፣ ዛሬም ኢትዮጵያ የአልፍ አእላፍ ጀግኖች ሐገር ናትና! ዛሬም ለጸረ ኢትዮጵያዊነት ማርከሻው ኢትዮጵያዊ አንድነት ነውና! በባእዳን፣በወያኔና በዘመናዊ ባንዳዎች በተቀደደልን ቦይ እንደውሃ በመፍሰስ በዘር በሐይማኖት ወዘተ ተከፋፍለን የመከራ ዘመናችንን ለማራዘም የማንመች የባንዳ ሳይሆን የጀግኖች ልጆች ነን የሚሉትን አይበገሬ አንበሶች ካላቸው የትግል ተመክሮ የሕዝብ ወሳኝነትን አስቀድመው ለወገንና ለሀገር የመስራት ብቃት አንጻር በአሁኑ ወቅት በሕቡእ አና በግልጽ እየሰሩ ያሉ አመራሮቻችንን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት በአመራርነት እንዲቀጥሉ ጉባኤዬው ከመወሰኑም በላይ በሀገር ቤት በሕቡዕ ከሚንቀሳቀሱ አመራሮቻችን በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካም ትግሉን ለማቀላጠፍ የጋራ አመራር አካል ተመስርቷል። ይህንንም አካል እንዲመራ በዚህ የወክንድ ፬ኛ ጉባኤ ጎድ ይማም ተመርጧል።
ትግሉን ለማስቀጠል በጉባኤው የተመረጡት አመራሮች፥
፩. ይማም
፪. በላይ 
፪. ድሪባ 
፫. ፍሬ ጽድቅ
፬. ታዘበው 
፭. ብሩክ 
ለነዚህ የአመራር አካላት በሐገርቤት በህቡዕ፣ በውጪ በይፋ የኢትዮጵያን አንድነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ እስካላሰገቡ ድረስ ማንኛውንም ፀረ ወያኔ ትግል በጋራ ለማስቀጠል ከሚፈልጉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውይይት ምክክር ሊያደርጉ የሚያስችል ኃላፊነት ኢሕአፓ ወክንድ ሰጥቶአቸዋል።
ኢሕአፓ ወክንድ በቀጣዩ የትግል ጊዜ፣ በኢትዮያዊነት የሚያምን ዜጋ ሁሉ ሐገራችንንና ሕዝባችንን የዲሞክራሲ የፍትህ የሰው ልጅ በዘሩ ሳይሆን በሥራውና በእውቀቱ የሚከበርበት፣ ሁሉም በነፃነት የሚኖርበት ሐገር እንድትኖረን ለምናደርገው ትግል ዛሬ ያለንን ቅራኔና ልዩነት አቻችለን የሕዝብን ውሳኔ ሰጭነትና የስልጣን ባለቤትነት አምነን ተቀብለን ወያኔንን ማስወገድ ካልቻልን ነገ ከነገ ወዲያ የምናደርገው ትግል ከዘረኛው ወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት እየዘረፈ ገበሬውን ከመሬቱ በኢስቨስተር ስም እያፈናቀሉ ኢትዮጵያ ሐገራችንን የሸቀጣቸው ማራገፍያ ካደረጎት ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከሳውዲ ጋር ይሆናል። ትግሉም ከዴሞክራሲ ትግል መርሕ በተጨማሪ የሐገር ባለቤትነት ትግል ይሆናል። አንድ ዘረኛና ጠባብተኛን የሕዝብ መሰረት የሌለውን ወያኔን በጊዜ ተቻችለን ማስወገድ ሳንችል ቀርተን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ከእኛ ለሚቀጥሉት ትውልዶች እኛ ከወያኔ ነፃ ያላወጣናትን ሐገር በማስረከብ እነሱ ከቻይና ከህንድና ከአረብም ነፃ እንዲያወጧት ውስብስብ ትግል ትተንላቸው እንዳናልፍ ደግመን ደጋግመን ልናስብበት ይገባል እንላለን።
በዚህ ወሳኝ ትግል፣ በዚህ የታሪክ አጋጣሚ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከኛ በፊት በነበረው ትውልድ መስዋአትነትና ጀግንነት የቆየችንን ሐገር ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ የማስረከብ ግዴታችንን መወጣት ከተሳነን፣ ልጆቻችን በኛነታችን የሚያፍሩ፣ የተናቁ፣ ሐገር አልባ ዜጎች ከመሆን አያልፉም። ግና የታሪክ አደራችንን ከመወጣትም አልፈን አንድ እርምጃ ወደፊት በመሄድ የአንባገነኖችን በሕዝባችን ጫንቃ ላይ መፈራረቅን ለማስቆም፣ የሕዝብን የነቃ ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ በማረጋገጥ የድርጅት መሪዎችን፣ ፖለቲከኞችን፣ የመንግሥት ባለስልጣኖችን፣ የሐይማኖት መሪዎችን፣ ምድራዊ ሲኦልን በህዝባችን ላይ የሚያውጁ ጠያቂ የሌላቸው አምባገነኖች ከመሆን ለመግታት የሚያስችል መሰረት ጥለን ብናልፍ ታሪክ ለዘለዓለም አንደሚዘክረን ጥርጥር የለውም። ሕዝብ የስልጣን ባለቤት በመሆን ያሻውንና የሚበጀውን የሚመርጥበት ስርአት ተመስርቶ ግልጽነት ተጠያቂነትና የጋራ አመራር ዘይቤ ነግሶ የሚታይባት ኢትዮጵያን ለመመስረት በአንድነት እንነሣ።
ስልጣን የሕዝብ ነው!! አንድነት ሀይል ነው!! 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ሕዝባችን ያቸንፋል!!


   Posted By.Dawit Demelash

40 Ethiopian professionals seek asylum in S. Korea


When South Korea came under communist invasion in 1950, Ethiopia was part of a UN multinational force that sided with South Korea and fought against the northern invaders. Almost 65 years later today, an affluent South Korea remembers the camaraderie, and pays tribute with a solemn gesture.

Forty young Ethiopian professionals some of whom are the children and grand children of the Ethiopian soldiers who took part in the 1950-53 war, have asked for a political asylum and their host country has handled their request without a hitch.


Nineteen others have decided to return to Ethiopia, though a few more from their ranks may have second thoughts and remain behind.


The Ethiopians wrapped up their eight-month-old training season before they decided not to return to their country on grounds of "gross human rights violations."


Speaking on the phone, Sisay Woldegabriel, he himself the son of an Ethiopian soldier who took part in the Korean War, said his colleagues have committed themselves to struggle against the repression regime.


"It is suffice to mention how Ethiopian Moslems are being brutalized by police and government forces because they asked that their basic rights be respected," Sisay told Ethiomedia with a tone of resentment and anger.


He said political repression in Ethiopia has hit rock bottom that the only solution is for all Ethiopians to join
 hands in the fight against the brutal regime in power.


"We have all decided to join pro-democracy Ethiopian groups around the world," Thomas Ashame said, speaking on behalf of his compatriots at the Henan Refugee Camp.


Asked how life has been in the midst of the Korean people, both Ethiopians expressed enormous gratitude 
to the Korean people and government.

Ethiopia sent one infantry battalion to help South Korea repel invading communists from North Korea during the 1950-53 Korean War and 122 of them were killed in action, according to a 2006 AP report.

    Posted. Dawit Demelash


Saturday, August 10, 2013

ከፖለቲከኞች በላይ ገኖ የወጣው “ድምጻችን ይሰማ” ኢህአዴግ አክራሪነትን እየጋበዘ ነው!!

1


”የሰላማዊ ትግል ምንነት ለማይረዱ ትልቅ ትምህርት የሰጠ፣ ኢህአዴግ ፍጹም የሆነ ልምድ ባካበተበትና ኤክስፐርት በሆነባቸው የትግል ስልቶች ብልጫ ወስዶ ለማንበርከክ እንደሚያስቸግር፣ ሰላማዊ ትግል ከራስና ከስሜት ጋር የሚደረግ ታላቅ አስተምህሮት መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። የድምጻችን ይሰማ ትግል በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆኖ ይቆያል” በግል አድራሻ ከተላከ አስተያየት የተወሰደ።
በአሃዝ፣ ጉዳቱ በሚገለጽበት መጠን፣ ጉዳቱ የሚገለጽበት ደረጃና የቋንቋው አቅም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወገኖች፣ የውጪ ታዛቢዎች፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ራሱ ኢህአዴግ፣ ህወሃትና መላው ወዳጆቹ በአንድ እውነት ይስማማሉ። እሱም ህወሃት ራሱ ባመጣው ጣጣ፣ ራሱ ትዕዛዝ ሰጪ ሆኖ ያደረሰው ሰብአዊና በቀላሉ ሊበርድ የማይችል መከራ እንደሆነ በየአቅጣጫው አስተያየት እየተሰጠ ነው።
ያለ ምንም ማጋነን ኢህአዴግ ደም አፍሷል፣ ህይወት ቀጥፏል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ፈንክቷል፣ ጣጣው ለሌሎች የሚተርፍ አካሄድ በመከተሉ ችግሩን አወሳስቦታል። ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ርምጃ የሚወስደው “ከብዙ ትዕግስት” በኋላ መሆኑን “በመንግሥት ወግ” ቢገልጽም “የሚያምነው ያገኘ አይመስልም” የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል። እንደውም “ለየትኛዋ የሚወዳት አገር” በሚል ለፕሮፓጋንዳ አፉን በከፈተ ቁጥር ዘለፋ እየወረደበት ነው።

“ኢህአዴግ ጉልበት አልባ ተደረገ!”

ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ገለጻቸው ለሌላው ግራ የሚያጋባ አባባል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ግን በነሱ እምነት ኢህአዴግ አቅም አልባ ሆኗል። አቅም አልባ ያደረገው “የድምጻችን ይሰማ” የትግል ስልት ነው። ኢህአዴግ ያለውና 4የሚታወቅበት መለያው የታጠቀው መሳሪያ፣ ወታደሩ፣ የፌደራል ሃይሉ፣ የክልል ፖሊስ፣ ፈጥኖ ደራሹ፣ የሰላምና መረጋጋቱ ፣ የስለላ ሃይሉ፣ የአጋዚ ጦሩ፣ የአንድ ለአምስት አወቃቀሩ … ከሁሉም በላይ ደግሞ ጉልበተኛነቱን የሚቆጣጠሩለት የአንድ ብሔር “ታማኝ” ሃይሎች መሆናቸው እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ።3
“ኢህአዴግ አለኝ የሚለውን ጉልበቱን መጠቀም ቢፈልግም መድረኩን ‘በተጠና’ የትግል ስልት በሚፈልገው ደረጃ ሊጠቀም አለመቻሉ በደጋፊዎቹና በራሱ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ የዕዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚያካሂዱት ትግል ኢህአዴግ ጉልበቱን እንዳይጠቀም ከልክሎታል። አሁን እየወሰደ ያለውና የወሰደው የሃይል ጥቃት ሊወስድ ከሚፈልገው ጋር ሲነጻጸር ሃይሉ ሽባ መደረጉን ያሳያል፤ ይህ ደግሞ የሰላማዊ ትግል ውበት ነው” ሲሉ ኢህአዴግ በገባው ጭንቅ መጠን ርምጃ ባለመውሰዱ እንደሚቆጭ ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር የሽብር፣ የማሸበርና የመግደል “ጠቢብ” ለሆነው ኢህአዴግ አሁንም ችግሩ የሚፈታው በሃይል፣ በባሰ ሃይል እንደሆነ ከማመን አላፈገፈገም ሲሉ ያብራራሉ።
ኢህአዴግ ነገሮችን እያባባሰ የሰላማዊ ትግሉን ወደ አመጽ ለማስቀየር ሃሳብ ቢኖረውም “የድምጻችን ይሰማ ህብረት አስቀድሞ መረጃ የማግኘትና በሰላማዊ ትግል ተክኖ መገኘት ኢህአዴግ ያሰበውን እንዳይፈጽም አድርጎታል” በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢህአዴግ “አክራሪነትን የሚሰብኩና የሚያቀነቅኑ አሉ” በማለት ለሚለፍፈው “እስካሁን የአክራሪ ሙስሊም እንቅስቃሴ ስለመታየቱ መረጃ የለም። ከተፈጠረም አክራሪነት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ራሱ ኢህአዴግ ነው። ደም ማፍሰሱን አጠናክሮ በቀጠለና ዜጎችን ማሰሩ በገፋበት ቁጥር ለመሞት የሚዘጋጁ ዜጎች አገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል የወንድሞቻቸውን ጭፍጨፋ በመመልከት የመስዋዕትነቱ ተካፋይ ለመሆን ዓለምአቀፋዊ የሙስሊም ኅብረተሰብ ቁጣ ያስተባብርና ራሱን ችግር ላይ ይጥላል፤ ለአገርም መከራ ይሆናል፡፡”
በተቃራኒው አክራሪነት እየተስተዋለ የመጣው አሁን እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “በአሁኑ ሰዓት አገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ውህደት ቀደም ሲል እናቶቻችንና አባቶቻችን በየዋህነት ሲያደርጉት እንደነበር አይነት ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማያያዝም እንዲህ ያለው ስጋት በሰላማዊ ትግል ጉልበት አልባ የሆነውን ኢህአዴግ ሃይል እንዲያገኝና ይህንን ሃይል እንዲተማመን አድርጎታል ሲሉ ይከራከራሉ።

“ኢህአዴግ ሰክሯል”

ኢህአዴግ መስከሩን፣ አንጎሉ መዞሩንና የሚያደርገው እንደጠፋው የሚናገሩ ክፍሎች እንደሚሉት የኢድ ቀን ኢቲቪ ያሰራጨውን ዜና ቀላል ምሳሌ አድርገው ያቀርባሉ። የድምጻችን ይሰማ መነሻ ምክንያት የሆኑትን አዲሱን የመጅሊስ መሪ በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ 2“ሙስሊሞች ላይ የወሰዳችሁትና የምትወስዱት ርምጃ የሚደገፍ ነው፣ ትክክል ነው” በማለት ያቀረበው ቃለ ምልልስ “ከስካርም በላይ አዙሪት ነው” ሲሉ የኢህአዴግን የበሽታ መጠን ይገልጻሉ። ሙስሊሙን አንኳን አሰራችሁት፣ ደበደባችሁት፣ ገደላችሁት በሚል ደረጃ “ደግ አደረጋችሁ፣ ርምጃችሁ ትክከል ነው” በማለት ዜና ማሰራጨቱ ኢህአዴግ በራሱ ሚዲያ በችግሩ ላይ እሳት ማርከፉን የሚያመላክት  ስለመሆኑ በማሳያነት ያቀርባሉ።
አንድ ጤና ያለው መንግስት የህዝብ ቁጣ ሳይለሳለስ፣ የቁጣውን መንስዔ አደባባይ በማቅረብ “ተጎዳን በሚሉ የህብረተሰብ፣ በተለይም የአንድ እምነት ተከታዮች ፊት ማዘፈን ኢህአዴግን የያዘውን የስካር የዞረ ድምር  (ሃንግኦቨር) የማሽተት ያህል ነው” የሚሉት ክፍሎች ኢህአዴግ ቢያንስ ለራሱ፣ ህወሃትና ቁንጮው ላይ ሆነው ሃብት ለሰበሰቡት ሲል እርቅ ሊወርድ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብበት ይመክራሉ። ጉዳዩንም በጥበብ እንዲይዘው ይመክራሉ።

መተማመን ድሮ ቀረ!!

በሙስሊም ወገኖች አወሊያ የተጀመረው የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ፣ የኢህአዴግ የጥያቄው አያያዝ ችግር ተዳምሮበት የእምነቱ ተከታዮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተቃውሞው እየተዳረሰ ይገኛል። የአገሪቱን ሙስሊሞች ከጫፍ እስከጫፍ በሚያስገርም የግንኙነት መረብ እያስተባበረ የሚነደው ሰላማዊ ቁጣ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ድጋፍ አለማግኘቱን ለኢህአዴግ ሃይል እንደሆነው የሚናገሩ ወገኖች “ይህንን አስመልክቶ በሚቀርበው መረጃ ግራ ተጋብተናል” ይላሉ።
“እንኳን የሌላውን ሃይማኖት የራሳቸውን ሃይማኖትና ስርዓት ማስጠበቅ ያቃታቸው የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮች፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ደገፉ ተብሎ ሲዘገብ ዘገባው ሚዛን የሚደፋ አይሆንም” በማለት የሚከራከሩ ክፍሎች “የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእምነታቸው ሊሰጡ የሚገባውን ክብር ከድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ መማር ከቻሉ ይህ ብቻ በራሱ ይበቃል” በማለት በተቃራኒ ወቀሳ ይሰነዝራሉ። እንደውም የራሳቸውን የእምነት ቤት ማጽዳት ባለመቻላቸው ሊወቀሱ እንደሚገባ መረጃ በማጣቀስ ይከራከራሉ።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ካለው የረዥም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራና የምንገኝበት የጂኦ ፖለቲካ ካሸከመን ጣጣ ጋር በማዳመር “ሜዳዎች ሁሉ ሸራተን ሆነው አይዋቡም” የሚል አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች “መተማመን ድሮ ቀረ” ሲሉ የሌሎች እምነት ተከታዮችን ዝምታ ይገልጹታል።
“ሙስሊሞች አብዛኞች በሆኑበት ቦታ ያለ ችግር ቢፈልጉ አክርረው፣ ቢፈልጉ አለዝበው እምነታቸውን ያራምዳሉ። አነስተኛ በሆኑባቸው አገራት ደግሞ ያለውን የአስተዳደር መሰረት የመጋራት ፈተና ይፈጥራሉ”  የሚሉት እነዚህ ክፍሎች “እነዚህ በሌሎች አገሮች የታዩ ተሞክሮዎች ከምዕራቡ መገናኛ ውስወሳ ጋር ተዳምረው በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ያስቀመጡት ጠባሳ ቀላል አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ ችግር አለ” ባይ ናቸው። በሌላም በኩል በማህበራዊ ድረገጾች አርሲ አርባ ጉጉና ጅማ የተከናወነውን በማንሳት ሰሞኑንን ለመከራከር የሞከሩትን በመጥቀስ የፍርሃቻው ማሳይ አድርገው ያስቀምጡታል።

ፍጹም ሰላማዊ ትግል – ፍጹም የሚያስቀና ህብረት!!

መሰረታዊ የእምነትና አመራር ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን በተጠና መንገድ የሚያካሂዱት የ”ድምጻችን ይሰማ” የትግል መስመር አስገራሚ እየተባለ ነው። ህብረታቸውና በተዋረድ የሚያካሂዱት መናበብ አስደማሚ ሆኗል። አልፎ አልፎ ከሚሰራጩ ወፍ ዘራሽ5 መልዕክቶች በስተቀር መሪዎችን በመከተል የሚያሳዩት ትብብር የሚያስቀና እንደሆነ እየተነገረ ነው። ተመሳሳይ ዓላማ ይዘው እርስ በርስ የሚቧቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ከድምጻችን ይሰማ “የሰላማዊ ትግል” ቀመር ሊማሩና ይሁንታ ካገኙ ስልጠናም ሊወስዱ እንደሚገባ የሚናገሩ ተበራክተዋል።
እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የሙስሊም ወገኖች ጥያቄና ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ወደኋላ እንደማይሉ በመደጋገም ይፋ እያደረጉ ነው። ኢህአዴግ ከተካነበት ድርጅቶችን የመሰንጠቅና “የእባቡን አንገት ቁረጥ” ከሚለው የአምባገነኖች መርሁ አንጻር ድምጻችን ይሰማ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለመቻሉ አስገራሚ የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። ቅንጅት እንደ ሰደድ እሳት አገር አዳርሶ ኢህአዴግን ባስጨነቀ ማግስት “ሳሎኑ ተበርግዶ ኢህአዴግ ሲንቦጫረቅበት” የተመለከቱ፤ ዓመት ከመንፈቅ ያህል የዘለቀውንና ከዕለት ወደ ዕለት በብቃትም ሆነ የኢህአዴግን መሠሪነት በመመከት እንዲሁም የተጠና የትግል ችሎታ በማሳየት ወደር ያልተገኘለትን የድምጻችን ይሰማ ትግል ከማድነቅ ወደኋላ አይሉም። ለሌሎች ሲመክሩም የመስመርና የትግል አስተላለፍ ለውጥ ለማድረግ አሁንም ጊዜው እንዳላለፈ ሊገነዘቡት ይገባል በማለት ለሌሎች የሰላማዊ ትግል ምንነት ላልገባቸውና የገባቸው መስሏቸው ተስፋ ለቆረጡ ይመክራሉ፡፡

http://www.goolgule.com/a-non-violence-beyond-politics/