Monday, June 30, 2014

ይሉኝታ ቢሱ ወያኔ በሚኒሶታ ቅሌቱን ተከናነበ



ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአላሙዲ የሚደገፈው የወያኔ ቡድን የሚኒሶታን ሕዝብና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለማደናገር በሚኒሶታ ጠቅላይ ግዛት በሴይንት ፓውል ከተማ በሚገኘው ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲት እስፖርት ሜዳ ላይ ባዶ  እስታድየሙን በመያዝ ቅሌቱን ተከናንቧል። ሕዝብን በመፍረት የስታድየሙን ዙሪያ በአረንጓዴ፣ ብጫ ፣ ቀይ ባንድራ  ሰቅለው ነበር። ለተቃውሞ የወጣውም ሕዝብ በአገር ቤትና በወያኔ ቤተክርስቲያኖች የሚጠቀሙበትን ወያኔ በባንድራችን  ላይ የለጠፈውን የሴይጣን ምልክት ያለበትን ባንድራ አለመጠቀማቸውን በማየት በኢትዮጵያ ባንድራ መቀለድ አይቻልም፤ በባንድራ ማታለል አትችሉም። 

ወያኔ ይህ ባንድራ አያውቅም፣ ይህን የኢትዮጵያን ባንድራ(አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ቀለማት  ብቻ ያለበትን ሳንደቅዓላማ) ለሁሌም ተጠቀሙ በማለት ተቃውሞና ማሳሳቢያ ሰጥቷል። በመኪና ማቆሚያ ከዚያም በሽቦ  አጥር እንዲሁም በለመዱበት የፍራቻቸው መከለከያ በሆነው ፖሊስ በውጭና በውስጥ የተከበበውና የተጀበው የኮንኮርዲያ  ዩንቭርሲቲ ስታድየም ወያኔዎች ይበልጥ ከሕዝብ ወለፈን እንዲርቁ ረድቷል።  ወያኔ በኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ላይ ያደረገውን የክፍፍልና በስፖርት ስም በሚኒሶታ ለማካሔድ  ያሰባውን ድርጊት የሚቃወመው ሕዝብ የወያኔና የአላሙዲ ገንዘብ ተቀባዮች ወደሚጫወቱበት ሜዳ ድረስ በመሄድ  ተቃውሙን በመፈክር ፣ በዝማሬና በጩሃት አሳምቷል። በወቅቱ ሕዝቡ ካሰማቸውና ከያዛቸው መፈክሮች ጥቂቶቹ ፡-

  • ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
  • Long Live Ethiopia !!!
  • ዘረኝነት ይቁም !
  • Stop Tribalism!
  • Free Tsegaye Debteraw
  • Free Eskender Nega
  • Free Andoalem Arage
  • Free Rhiot Alemu
  • Free Aberash Berta
  • Free all political prisoners in Ethiopia
  • Stop Killing Ethiopians
  • Stop Arresting Journalists
  • Stop Genocide in Ethiopia
  • We oppose recent killings of Oromo students in Ethiopia
  • Stop selling Ethiopia’ s land for Arabs and others
  • ሕዝብ ማፈናቀሉ ይቁም
  • በደም ገንዘብ ስፖርት ማካሄድ አይቻልም
  • በእስፖርት ስም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይታለልም
  • ሚኒሶታ ለሕዝብ ጠላት መሸሸጊያ አትሆንም
  • አንድ ነን አንከፋፈልም
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል
  • በባዶ ስታደየም ጫወታ የለም። ወያኔን ሕዝብ እንደማይወደው ከዚህ ተማሩ
  • እናንት ተጫዋቾች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ተሰለፋ
  • የደም ገንዘብ ይቅርባችሁ
ከመዝሙሮቹ ውስጥ፡-
  • አትነሰም ወይ አትነሰም ወይ ይሕ ባንድራ ያንተ አይደለም ወይ
  • እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም
ሰልፈኛው በ4፡30 ፕም ላይ በሱተር ታርጌት ተሰብስቦ ወደፊት እቅድ ወጥቶ ተከታታይ ሰልፎች እንዲካሄዱ ወሰኖ  የሚኒሶታ ህዝብ የወያኔን ስታድየም ባዶ በማደረጉ ምስጋና አቅርቧል። በስብሰባው የተገኘው ሰልፈኛ በሚኒሶታ የሚገኙት  ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ከእነዚህ የወያኔ ከፋፈይ ቡድኖች ጋር በማንኛውም ጉዳይ ትብብር እንዳይደርግ  በአክብሮትና በወያኔ እየተበደለ ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ጠይቋል። ዘረኞቹ መገለል ይኖርባቸዋል።ወደፊት  በሚካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች የሚኒሶታ ሕዝብ እንዲገኝ በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረ ኃይል

ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።
በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረኃይል













http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31807



Sunday, June 29, 2014

የዞን 9 ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – ‹‹ያለ ፈቃድ መሬቱንም ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ፖሊስ


ጌታቸው ሽፈራው ከአዲስ አበባ

የጦማሪያኑን የፍርድ ውሎ የሚከታተለው ሰው ዛሬም እንደወትሮው በጠዋት ነው የተገኘው፡፡ አራት ሰዓት ካለፈ በኋላ የጦማሪያኑ ጠበቃ ‹‹መዝገብ ቤቷ ስለሌለች ነገ ከሰዓት ተብሏል›› ብለው ሲነግሩን በርካታ ህዝብ በተገኘበት አንዲት መዝገብ ቤት በመቅረቷ ብቻ የፍርድ ውሎው እንዲራዘም መደረጉ ገርሞን ስለጉዳዩ እያወራን ለጥቂት ደቂቃዎች ግቢው ውስጥ ቆየን፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እየመጡ ነው ተባለ፡፡

የውሎው ትዕይንት እዚህ ላይ ነው የተጀመረው፡፡

ሶስቱም ጦማሪያን ሲመጡ ህዝቡ በጭብጨባ ተቀበላቸው፡፡ በድንገት እዚህ እዚያ የሚራወጡት ፖሊሶች ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ በመምጣት የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አባል የሆነችውን ምኞት መኮንንን ‹‹ፎቶ ግራፍ አንስተሻል፡፡›› በሚል ማንገላላት ጀመሩ፡፡ በኃይል እየጎተቱ ሲወስዷትም ዮናታን ተስፋዬ ‹‹እኔን ውሰዱኝ›› ብሎ ምኞትን በኃይል እየገፈተሩ የሚወስዱት ፖሊሶች መሃል ገባ፡፡ ፖሊስ ግን እሱንም ማንገላላት ጀመረ፡፡ እሱንም አብረው ወሰዱት፡፡ ምኞትና ዮናታን ጦማሪያኑን ተከትለው ችሎቱ ወደሚገኝበት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ ፖሊሶቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስፈራራት ጀመሩ፡፡


ፖሊሶቹ ከሚመጡበት በኩል የርዕዮት ዓለሙ አባት ጠበቃ አለሙ፣ እህቷ እስከዳር አለሙ፣ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ፣ 6 ያህል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት አባላትና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ‹‹ወዴት ነው የምንሄደው?›› በሚል እንደማይወጡ አሳወቁ፡፡ ፖሊሶቹ ‹‹ታዘነ ነው፡፡ ትወጡ እንደሆነ ውጡ!›› እያሉ ማስፈራራት ጀመሩ፡፡ ከፊት ያሉት ሰዎች ‹‹ችሎት መከታተል መብታችን ነው!›› ብለው አንወጣም ሲሏቸው እነ ምኞት ላይ የተወሰደውን እርምጃ ትክክለኛነት ለመግለጽ ፎቶ ማንሳት ክልክል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ማስፈራራት ቀጠሉ፡፡ በተለይ አንዱ ፖሊስ ‹‹ያለ ፈቃድ ፎቶ ማንሳት አይቻልም፡፡ ሳይፈቀድ መሬቱንም ቢሆን ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ያለበት ሁሉንም ያስገረመ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ አባባል የተሰበሰበው ሁሉ እያረረም ቢሆን ፈገግ ብሎበታል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31764

ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ



አማራዎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን አሉ

ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም።

ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል
የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።

በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።
በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።

ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።


በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31736

Thursday, June 26, 2014

በመቀሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

june 26th,2014
ሰኔ ቅዳሜ 21 ቀን ፣ በመቀሌ ከተማ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠራ፣ የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ ገለጹ። ሰልፉ በከተማዋ አስተዳደር እውቅና እንዳገኘ የገለጹት አቶ አብርሃ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከተሞች እንደታየው የመቀሌ ሕዝብ የሕወሃት ደጋፊ እንዳልሆነ የሚያሳይበት አጋጣሚ እንደሚሆን አስረድተዋል።
«የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው» ያሉት አቶ አብርሃ ለሰላማዊ ሰልፍ አስተዳደሩ እውቅና መስጠቱ በራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ገልጸዋል።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ በ 6፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ዉስጡን ዉስጡን ቅስቀሳ የተጀመረ ሲሆን፣ የአደባባይ ቅስቀሳ ነገ አርብ ቀን ሰኔ 20፣ ፖሊሶች ካላስተጓጎሉ እንደሚደረግም ታወቋል።
ከአንድ አመት በፊት በሚሊዮኖች ድምጽ፡ለነጻነት መርህ ሥር በመቀሌ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረ ይታወቃል። በወቅቱ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና ሰጥቶ ፣ በመቀሌ የአንድነት አባላት በአደባባይ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ፣ ሰልፉ ነገ ሊደረግ ዛሬ ማታ፣ የአመራር አባላትን በሙሉ እንዲታሰሩና ለሰልፉ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች/መኪናዎች እንዲታገቱ በመደረጋቸው፣ ሰልፉ መስተጓገሉ ይታወቃል።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15043

Wednesday, June 25, 2014

በዓለም አቀፉ የሠላም ደረጃ ኢትዮጵያ ከ162 ሀገራት 139ኛ ደረጃን ያዘች



በየዓመቱ የየሀገራትን የሠላም ይዞታ በማጥናት ደረጃን የሚያወጣው ኢኒስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም የ2014 የዓለም ሀገራት የሰላም ደረጃ ከሰሞኑ የለቀቀ ሲሆን በዚህም ጥናቱ ከ162 ሀገራት ኢትዮጵያን በ139ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል። ተቋሙ የአንድን ሀገር የሠላም ደረጃ ለማውጣት በርካታ የስኬት ማሳያዎች (Indicators) ግምት ውስጥ ያስገባል። ለዚሁ ልኬት ግብዓትነት ከሚውሉት መመዘኛዎች መካከል የውስጥና የውጭ ግጭቶች፣ አንድ ሀገር ከጎሬበቶቹ ጋር ያለው የግንኙነት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የሽብር ተጋላጭነት፣ የወንጀል መስፋፋት እንዲሁም በእያንዳንድ አንድ መቶ ሺ ሰው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለውን የእስረኛ ብዛትንም በመውሰድ ደረጃውን ለማውጣት በልኬትነት ይጠቀማል። ከዚህም በተጨማሪ ከአጠቃላይ ብሄራዊው ምርት አንፃር ለሚሊተሪው ዘርፍ የሚወጣውንም የገንዘብ መጠን ታሳቢ ያደርጋል። እነዚህንና ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ነው መረጃዎቹ ተተንትነው ደረጃ ወደ ማውጣቱ ስራ የሚካሄደው።

የየሀገራቱ ደረጃ ወጥቶ በድርጅቱ ድረገፅ እንዲሁም በዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት ለህትመት የሚበቃ ሲሆን የዘንድሮውም ሪፖርት የ162 ሀገራትን መረጃ በመውሰድ ሰፊ ትንታኔ ከሰጠ በኋላ ኢትዮጵያ በ139ኛ ደረጃ አስቀምጧል። ተቋሙ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምም ሆነ ጦርነት የሌለበት ሁኔታ በመግለፅም በይደር የተቀመጠ ጉዳይ መሆኑንም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከፀጥታ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አመልክቷል። በዚህ የሀገራት የሰላም ደረጃ አይስላንድ የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ በዓለም እጅግ ሰላም የሰፈነባት ሀገር ተብላለች። ዴንማርክ ሁለተኛ ስትሆን ኦስትሪያ የሶስተኝነትን ደረጃን ይዛለች።

ከ162ቱ ሀገራት 162ኛን ደረጃ በመያዝ በደረጃው ግርጌ ላይ የተቀመጠችው ሶርያ ናት። አፍጋስታን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም በደረጃው የመጨረሻ ግርጌ ላይ የተቀመጡ ሀገራት ናቸው። ግብፅ 148ኛ ደረጃን ይዛለች።

ዓለም አቀፍ የሀገራት የሠላም ስኬት ደረጃ (Global peace Index) በኢንስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ ተቋም በየዓመቱ ይፋ የሚሆን ሲሆን መረጃውን በማሰባሰቡ በኩል በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰፊ ትብብርና ተሳትፎን ያደርጋሉ። ከዓለም አቀፍ ተቋማቱ መካከል የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት አካላትም ይገኙበታል። እንደ ኮፊ አናን እና ሊቀጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱን የመሳሰሉና በተለያዩ ጊዜያት ሀገራትን ከመሩ በኋላ የስልጣን ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሪዎችም የሙያ አስተዋፅዖችን የሚያበረክቱበት ተቋም ነው። ተቋሙ የሀገራትን የሠላም ደረጃ የሚያወጣው 22 መስፈርቶችን አስቀምጦ በዚያ ልኬት መሰረት ነው።


ምንጭ – ሰንደቅ ጋዜጣ (በአዲስ አበባ የሚታተም)

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31634

Monday, June 23, 2014

በሐዋሳ በ3 ጣቢያዎች የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም



(ፖሊስ ትናንት የአንድነትን ሰልፍ እንዲበተን ያደረገው እንዲህ ከተማዋን በመውረር ነበር)

ከሐሙስ ሰኔ 12 ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሰኔ 14 ማታ ድረስ በከተማው በሚገኙ የተለያዩ ጣቢያዎች ከ37 በላይ የፓርቲው አባላት እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከታሰሩት አባላት መካከል አቶ በየነ መረባ የተባሉ የሐዋሳ የአንድነት ፓርቲ ፀሐፊ አንተን ፍ/ቤት አናቀርብህም ከጓደኞችህ ጋር ነው የምንቀላቅልህ በማለት ሲያስፈራሩዋቸው፣ የትኞችን ጓደኞቼን ብለው ሲጠይቁ እሱን ታየዋለህ በሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ገልጸዋል፡፡ የሰመጉ የአዋሳ ተጠሪዎች ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት እንዲያቀርቧቸው ቢጠይቁም አይቀርቡም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡


ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31568

Saturday, June 21, 2014

ፖሊስ በሐዋሳ ከተማ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አሰረ- የታሰሩትንም ደህንነት ማወቅ አልተቻለም


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በራሪ ወረቀት በማደል ፤ ፖስተር በመለጠፍና በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አስሯል፡፡ በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)በነገው እለት በሀዋሳ ሀተማ ለሚያደርገውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ፖስተር በመለጠፍ፡በራሪ ወረቀት በማደልና በሞንታርቦ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተይዘው በተለያዩ በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዊች የሚገኙ ቢሆንም ማንም እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም፡፡የሀዋሳ ከተማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ስማቸውን መግለፅ እንደማይፈልጉና ማንም መጠየቅ እንደማይችል እንዲሁም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርን ስለሁኔታው ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡


በእስር ላይ የሚገኙት አባላት የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ በፖሊስ ተይዘው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም በባህል አዳራሽ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ የአንድነት አባላት ከማንም ጋር እንዳይገናኙ የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ፡፡ከስልካቸው በተጨማሪም በራሪ ወረቀቶቻቸውን ፖሊስ በሀይል ቀምተዋል፡፡





http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31478




Monday, June 16, 2014

አሸባሪው አቃቤህግ በአሜሪካ !! ሊያዳምጡት የሚገባ ( ቪዲዬ )



ህወሃቶች የፈጠራና የሐሰት ክስ እየፈበረኩ በርካታ ለወገንና ለአገር የሚቆረቆሩ ኢትዮጵያውያንን በአገር መክዳት፣ ዘር ማጥፋት እና ሽብር ፈጠራ ወንጀሎች በመክሰስ እና በማሰር ለከፍተኛ ፍዳና መከራ ዳርገዋቸዋል።

የእነ ሽመልስ ከማልን አርአያ እንዲከተሉ ተመልመለው እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣በቀለ ገርባ፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለእስርና ለሰቆቃ ከዳረጉት አቀብያነ ሕግ መሃል ቴዎድሮስ በሃሩ፣ ዘርሰናይ ምስጋናው፣ብርሃኑ ወንድምአገኝ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።



ቴዎድሮስ በሃሩ በአሁኑ ግዜ በአሜሪካን አገር በሰላም የተረጋጋ ኑሮ ለመመስረት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ይሁናና በሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ፣ የሚኖረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ስላቀረበው መረጃ የሐሰት ክስ ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

ይህ ቪዲዮ ቴዎድሮስና ተባባሪዎቹ የህወሃቶችን ግፍ በፍርድ ቤት ሽፋን ለማስፈጸም የሰሩትን ወንጀል፣ በንጹሃን ዜጎች ያደረሱትን መከራና ፍዳ ለማሳየት ይሞክራል። ህወሃቶች እና ሎሌዎቻቸው በጸረ ሽብር ሕግ ሽፋን በሐሰት ክስ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ሽብርና ግፍ መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች መኖራቸውን ግን በቀላሉ መካድ አይቻልም።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31296

Saturday, June 14, 2014

የጦማርያኑ በፍርድ ቤት ውሎ

June 14, 2014
ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ‹‹ቅዳሜ›› ትርጉም አላት፡፡ የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ‹‹ቅዳሜ››ን ደግሞ እንደየ ምድቡ ይውልባታል፡፡ እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፡፡ ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየ ቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ፡፡
አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣የታመመን ያጽናናሉ፣በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ፡፡ ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ፡፡ አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡ በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛEthiopia bloggers in court አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው፡፡እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል፡፡ አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል፡፡ ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ፡፡መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል፡፡በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም፡፡‹‹የት ነህ? የት ነሽ?›› የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው፡፡
የተስፋዓለም ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ነበረች፡፡ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን አርቦች ከእነ ለሊታቸው በሥራ ያጠፋቸዋል፡፡ቅዳሜንም ረፈድ አድርጎ ይነሳል፡፡ እናም የመጀመሪያ ሥራው ለሕትመት የበቁ ጋዜጣና መጽሔቶችን አበጥሮ ማንበብ ነው፡፡ በማንበብ ብቻም አያቆምም፤ ከዘገባዎቹ አብዛኖቹ የተሠሩት በጓደኞቹ አሊያም በሚያውቃቸው ጋዜጠኞች ስለሚኾን ስልክ ይደውላል፡፡ ከዘገባዎች ውስጥ ተስፋዓለምን የሚያስደስቱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ሊኾኑ ስለሚችሉ የስልክ ልውውጦቹ ‹‹እንዲህ ብታደርግ/ብታደርጊ ኖሮ፣እንትናን ብታናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰጥህ ነበር፣እዚህ ቦታ እኮ እንዲህ ዓይነት መረጃ ነበር፣ይሄ እኮ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሕትመት ላይ ወጥቷል፣እውነቱን ለመናገር ይሄ ለሕትመት የሚበቃ ዘገባ ነው ብዬ አላምንም›› በሚሉ አስተያየቶች የተሞሉJailed Ethiopian bloggers appeared in court ነበሩ፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ የሚያስደስተውን ዘገባ ሲያነብ ወይም ፕሮግራም ሲሰማ አዘጋጁን አወቀው አላወቀው ስልክ አፈላልጎ በመደወል ያበረታታል፡፡ የተስፋዓለም ግማሽ ቅዳሜ የምታልቀው ይህን ሲያደርግ ነው፡፡
አኹን እነዚህ ወጣቶች ቅዳሜያቸውን በፌደራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ (ማዕከላዊ) ፖሊስ ተነጥቀዋል፡፡ ሃምሳ ቀናት ታስረው ዘጠኝ ቅዳሜን አጥተዋል፡፡ እንዳሻቸው የሚያደርጓትን ቅዳሜ አኹን እነርሱ አያዙባትም፡፡ ከጠዋቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ሲል ከእንቅልፋቸው ይቀሰቀሳሉ፡፡ ለቁርስ ዳቦ በሻይ ይሰጣቸዋል፡፡ (ቤተሰብ የሚያወስድላቸው ምግብ ቁርስ ከበሉ በኋላ ነው የሚደርሳቸው) እናም ተመልሰው ገብተው ይዘጋባቸዋል፡፡አብዛኞቹ ለየብቻ ከሌሎች እስረኛ ጋር የታሰሩ ሲኾን ሁለት፣ ሁለት ተደርገው የታሰሩም አሉ፡፡እናም ከምርመራ የተረፈ ቀናቸውን በዝጉና በጨለምተኛው ክፍል ያሳልፋሉ፡፡ በአንዷ ቅዳሜ ደግሞ እንደዛሬው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
አንዷን ቅዳሜ- በፍርድ ቤት
ሦስቱ ወጣቶቹ እነርሱ በማያዙባት ቅዳሜ እጆቻቸውን በካቴና ታስረው ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው በዐይን ግምት ሦስት መቶ የሚደርስ ችሎት ተከታታይ በግቢ ውስጥ ተገኝቶ ነበር፡፡ የዛሬዎቹ ጠባቂ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ ከነበሩት ሻል ያሉ ስለነበሩ ቤተሰቦች ችሎት ውስጥ ገብተው እንዲታደሙ ባይፈቀድላቸውም ግቢ ውስጥ ከመቆም የከለከላቸው ወይም ያመናጨቃቸው አልነበረም፡፡ bloggers in court Addis Ababa, Ethiopia
ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ አካባቢ ሲኾን ችሎቱ በሴት ዳኛ በመሰየሙ፤ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ እጃቸውን በሰንሰለት እንደታሰሩ ወደ ግቢው ገቡ፡፡ ዛሬ ወጣቶቹ በስስ ፈገግታ ‹‹አይዞአችሁ ደህና ነን›› የሚል የተስፋ ምልክት ለቤሰተቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው አሳይተዋል፡፡ ከእነርሱ ቀጥለው በፖሊስ ታጅበው የገቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት እጆቻቸው በካቴና እንደታሰረ ለቤተሰቦቻው ሰላምታን ሰጥተዋል፡፡ የእነርሱ ፈገግተኛ መኾን ለቤተሰቦቻቸው፣ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጥቂትም ቢኾን እፎይታን ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት እንደወትሮው ኹሉ በሁለት መዝገብ ተከፍለው ቢኾንም ፖሊስ ያቀረበው ምክንያትና መከራከሪያ አንድ ዓይነት ነበር፡፡ ችሎቱ ከተሰየመ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ በርካታ ጉዳዮችን ሲመረምር መቆየቱንና አሁንም ያልተጠናቀቀ ምርመራ ስለሚቀረው ተጨማሪ ሃያ ስምንት ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ጠበቃው አቶ አመሐ፤‹‹ፖሊስ ከዚህ ቀደም በወሰደው ጊዜ ቀጠሮ ሰንድ ለማስተርጎም፣ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ኢሜሎቻቸውን ለመፈተሽ እንዲሁም ያልተያዙEthiopian Jailed bloggers ግብረአበሮቻቸውን ለመያዝ ብሎ እንደነበርና አሁን ዝም ብሎ በጥቅሉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቼያለሁ እንደገና ይጨመርልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም›› ሲሉ አመልክተው ነበር፡፡ ዳኛው ፖሊስ የሠራውን ሥራና የሚቀረውን ምርምራ እንዲያስረዳ በማዘዛቸው፣‹‹ከሠራናቸው በርካታ የምርመራ ሥራዎች መካከል የተባባሪዎቻቸውን ቤት ፈትሸናል፣ለተለያዩ ባንኮች የተጠርጣሪዎቹን ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ከተወሰኑት ምላሽ አግኝተናል፣የተወሱ ምስክሮችንን ቃል ተቀብለናል፣ ከትርጉም ሥራውም የተወሰነውን ሠርተናል፡፡ ግብረአበሮቻቸው ወደ ክፍለ ሃገርና ወደ ተለያዩ አገራት እየሸሹ መያዝ ስለተቸገርን የፖሊስ ኃይል አሰማርተን እያፈለግናቸው ነው እነርሱንም መያዝ ይቀረናል፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡
አቶ አመሐ በበኩላቸው፤‹‹ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ ሃምሳ ቀናት ሞልቶታል፡፡ እነዚህ የሚላቸውን ነገሮች አጠናቆ ለመጨረስ የነበረው ጊዜ ከበቂ በላይ ነው፡፡አሁንም ቢኾን እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የደንበኞቼን አስሮ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም ስለዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቻውን ሊያከብርላቸው ይገባል፡፡ ይህን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባይቀበለው እንኳን ከዚህ በኋላ ፖሊስ በሚሰጠው ሃያ ስምንት ቀናት ጊዜ ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣ፤አጠናቆ ባይመጣ ደግሞ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተደርጎ ይመዝገብልን›› በማለት ጠይቀዋል፡፡
ዳኛዋ አቤቱታውን ካደመጡ በኋላ፤ፖሊስ ከዚህ በኋላ ሲቀርብ ለተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ መጠየቂያ አሁን የጠቀሳቸውን ምክንያቶች በምክንያትነት ይዞ እንዳይቀርብ በማሳሰብ የጠየቀውን የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል፡፡zone9 bloggers in court
በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ ፤ከፍተኛ የኾነ የጀርባ ሕመም ስላለበት ወንበር እንዲገባለት መጠየቁንና እስካኹን ሊገባለት እንዳልቻለ ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል፡፡ ዳኛዋ ከምንም ነገር በላይ የጤና ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ የጠየቀው ወንበር እንዲገባለት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በችሎት የተገኘው መርማሪ ፖሊስ፤‹‹በአጋጣሚ የእርሱ መርማሪ እኔ ነኝ የጀርባ ሕመም እንዳለበት ነግሮኛል፡፡ ወንበር እንዲገባለት ግን አልጠየቀኝም፡፡ አሁን ቢኾን ይህ በጣም ቀላልና እዛው እኛው ጋር ሊያልቅ የሚችል ነገር ነው፡፡ ችግር የለም እናስገባለታለን›› ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
እስረኞቹ ከችሎት ሲወጡ እንደ አገባባቸው በፈገግታ ሰላምታ እየሰጡ ሲኾን ችሎቱን ለመከታተል መጥቶ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ቆመው ሰውም እጁን በማውለብለብ ተሰናብቷቸዋል፡፡ (ፎቶ አዲስ ስታንዳርድ)
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12531/

ህወሓት አስተዳዳሪዎች ማሳሰሯን ቀጥላለች!

June 12th, 2014

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ነው። ህዝብ ማዳበርያ አንገዛም፣ ገንዘብ የለንም በሚል አቋሙ ፀንቷል። የህወሓት ባለስልጣናትም የወረዳና የጣብያ (ቀበሌ) አስተዳዳሪዎችን ህዝብ ማዳበርያ እንዲገዛ እንዲስያገድዱ ያስፈራራሉ። አንዳንድ ካድሬዎች አለቆቻቸውን ለማስደሰት ህዝብን ያስፈራራሉ፣ ያስገድዳሉ። አብዛኞቹ ደግሞ የህዝብን ችግር፣ ጭቆናና በደል ተረድተው ከህዝብ ጎን ይሰለፋሉ።
በራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ ለማሳመን (ለማስፈራራት) ማስፈራርያ የሚደርስባቸው አስተዳዳሪዎች ህዝብን ማስፈራራቱ ሰልችቷቸው ህዝብን አናስገድድም ብለው ከህወሓት ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝብን ችግር መረዳትን መርጠዋል። በዚህ ምክንያት ከአለቆቻቸው ጋር ተጣልተዋል። በመጣላታቸው ምክንያት ዓረና ገብቶብናል በሚል ምክንያት አስሯቸዋል።
ዓረና ናቸው ተብለው ዛሬ ሓሙስ ሰኔ 6, 2006 ዓም ከቀኑ 4:00 የታሰሩ የወረዳው 13 አስተዳዳሪዎች (የተወሰኑ የጣብያና የቁሸት ይገኙባቸዋል) የሚከተሉት ናቸው።
1) አቶ ኢያሱ ሞላ
2) አቶ ጥዑማይ ሻምበል
3) አቶ አሰፋ ገብረየሱስ
4) አቶ ወልዱ ተስፋይ
5) አቶ አወል መሓመድ
6) አቶ ሓዲስ ጣሰው
7) አቶ በየነ ተበጀ
8) አቶ ፈረደ ሞላ
9) አቶ ኪሮስ ስዩም
10) አቶ ተስፋይ ካሳዬ
11) አቶ ሞገስ ቸኮለ
12) አቶ ሻረው አጠና
13) አቶ አሸናፊ ቀሺ ናቸው።
እነዚህ አስተዳዳሪዎች በሓዱሽ ቅኚ ጣብያ ባንደራ በተባለ የገጠር ከተማ ታስረው ይገኛሉ። አስተዳዳሪዎቹ የታሰሩት ዓረና ስለሆኑ ነው ከህዝብ ጋር ወግነው ህዝብን ማዳበርያ እንዲገዛ አናስገድድም ብለው አሻፈረን ያሉ በሚል ምክንያት ነው።
ድሮ የህወሓት አባል መሆን የሚያሳስር ወንጀል ነበረ። አሁንም የዓረና አባል መሆን ያው የሚያሳስር ወንጀል ሆነ። ልዩነቱ ግን ህወሓት ሕገወጥ ዓማፂ ድርጅት ነበር፤ ዓረና ግን ሕጋዊ ሰለማዊ ድርጅት ነው።
የነፃነት ትግሉ ይቀጥላል። ታጋዮችን በማሳሰር ትግላችን አይደናቀፍም። ህዝብ ሙሉ ሊታሰር አይችልምና።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/14871

Thursday, June 12, 2014

ህወሓት የቤተክርስያን ገንዘብ ዘረፈ

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳአይናለምየተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደንየመለስ ፓርክተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹየመለስ ፓርክመባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል።
ባለፈው ወር ነው።ከመለስ ፓርክየተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነ ይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ታሰረ፤ ቅጣት መሆኑ ነው። ህዝቡ የታሰረው ፖሊስ ጣብያ አልነበረም፤ ፖሊስ ጣብያ አይበቃውማ። በብዙ የሚቆጠር ህዝብ (ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ እናቶች በቃ ሁሉም) በረኻ ላይ በፖሊሶች ተከቦ ታስሮ ይውላል። ዝናብ ይደበደባል፤ ፀሓይ ይመታል። ህዝቡ ግን ይህን ሁሉ ስቃይ ችሎ በቃሉ ፀና። ካድሬዎቹ ከስምንት ቀናት በኋላ ተስፋ ቆርጠው ተውት። ህዝቡ ግን ተቀይሟል።

ከተወሰነ ግዜ በኋላ የማዳበርያ ጉዳይ መጣ። መዳበርያ ዉሰዱ ተባሉ። አንወስድም አሉ፤ በአንድ ቃል። ህዝቡ ያቀረበው ምክንያት መዳበርያ ለመግዛት ገንዘቡም ፍላጎቱም የለንም የሚል ነው። ካድሬዎች ህዝቡን ለማስፈራራት ሞከሩ፣ አሰሩ፣ አዋረዱ። አልተሳካላቸውም። የካድሬዎች የመጨረሻ ሓሳብ ህዝቡ ለማዳበርያ የሚሆን ገንዘብ ከሌለው ከቤተክርስያን ታቦት እንዲበደር ጠየቁት። ህዝቡ አሻፈረኝ አለ። ከታቦት ተበድረን ማዳበርያ አንገዛም፣ ከእግዚአብሄር ቤት ተበድረን ለመንግስት አንሰጥም አሉ።

ካድሬዎችም ማዳበርያው በተሽከርካሪ ጭነው ጣብያው (ቀበሌው) ላይ አራገፉት። ህዝቡም የምንከፍለው ገንዘብ የለንም አለ። ካድሬዎቹ ደግሞ የአይናለም ህዝብ ታቦት የሚገኝበትመድሃኔዓለም ቤተክርስትያን በመሄድ ለማዳበርያው ዋጋ የሚሆን ገንዘብ ይወስዳሉ። የታቦቱ ቄሶች ዝርፍያ ተፈፅሞብናል በሚል ተግባሩን ይቃወማሉ። ቄሶቹ አርፈው እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። አሁን ለማዳበርያው የሚሆን ገንዘብ በቤተክርስትያኑ ተወስዷል። ህዝቡም ተቃውሟል። አሁን የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ህወሓትም እያስፈራራቸው ነው። ቤተክርስትያን ተዘርፏል ብለው ተቃውሞ ያሰሙ ቄሶች ግን ታስረው ይገኛሉ።

እንዲህ ነው ዝርፍያ። ህወሓት የዝርፍያ ባህሏን እስካሁን ድረስ አጠናክራ ቀጥላለች ማለት ነው።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31200