Friday, January 31, 2014

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳ የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደላቸው ተሰማ

(-ሐበሻ) በጎንደር /ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ ነበሩ የተባለት የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደሉ ተሰማ። የአርበኞች ግንባር ለግድያው ሃላፊነቱን ወስዶግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 . ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 , ህይወቱ አልፏል።ብሏል።

(የአርበኞች ግንባር ወታደርፎቶ ፋይል)
እንደ አርበኞች ግንባር ገለጻ ከሆነይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።ብሏል።

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይፎቶ ከፋይል)

በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል። የሚለው የአርበኞች ግንባር ዜና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብሏል።


በዚህ ዜና ዙሪያ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

  http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12396

Thursday, January 30, 2014

በጎንደር የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች ታሰሩ

(-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ወጥቶ ለሱዳን በሚሰጠው መሪት ዙሪያ ድርጊቱን እንዲቃወም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ መታሰራቸው ተሰማ።
-ሐበሻ ከሰማያዊ ፓርቲ አካባቢ የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።
ፖሊስ የሰልፉን ቀስቃሶች ካሜራ እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን መውሰዱን የጠቆመው ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘው መረጃ ፖሊስ ዛሬ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትንእሁድ የሚደረገው ሰልፍ ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌለው መቀስቀስ አትችሉምያላቸው ሲሆን አስተባባሪዎችምበሕገመንግስቱ መሠረት ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀድ የለብንም። ቀድመን ማሳወቅ እንጂ። ይህን ደግሞ አድርገናልቢሉም ፖሊስ ማስተዋወቅ አትችሉም በሚለው አቋሙ ጸንቶ መደብደብ መጀምሩም ተሰምቷል።
የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎች ከድብደባው በኋላ ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውንና ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸውም ታውቋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12366