Saturday, January 31, 2015

የገዢውን ፓርቲና መንግስትን ሽፍትነት ያጋለጠው አንድነትን የማፍረስ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!!! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ


ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል፡፡ በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው፡፡ ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል፡፡ በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን፡፡
ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል፡፡ በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17159

Friday, January 30, 2015

አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ

ትዕግስቱ አወሉ እንደ አየለ ጫሚሶ
tplfs election board
የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡
የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ ተግባሩን በዕቅድ ይዞ በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ግምባር ቀደም ተሰላፊው የተቋም ባንዳ “ምርጫ ቦርድን”፤ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ በተለይ ሁለት ግለሰቦችን አሰለፈ፡፡ ዘመቻ “ቅንጅትን መግደል” ተጀመረ፡፡
በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ምንም በማያሻማ ሁኔታ በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ያማሞቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ለሚገኙት አለቆቻቸው THE ETHIOPIAN GOVERNMENT CHEWS THE CUD” (የኢትዮጵያ መንግሥት ቅንጅትን አኘከው) በሚል ርዕስ የጻፉት እንዲህ ይነበባል፤
Over the course of the week of January 7, the National Electoral Board of Ethiopia (NEB) hammered what appear to be the final nails in the coffin of the opposition Coalition for Unity and Democracy (CUD) party. Since their surprise showing in the 2005 elections, gaining enough seats to become the second largest political party in Ethiopia, the CUD has virtually disintegrated as a result of internal power struggles and interference from the Ethiopian Government (GoE). In the latest setback, the NEB awarded the famous victory sign — the CUD symbol widely recognized by voters — to former ally turned foe, Lidetu Ayalew of the United Ethiopian Democratic Party-Medhin (UEDP-Medhin).  The NEB followed this later in the week by finally awarding registration of the reformed Coalition for Unity and Democracy Party (CUDP) party name to yet another former CUD ally turned foe Addis Ababa city council member-elect Ayele Chamisso.  Though Ayele, who is broadly viewed as having been co-opt by the GoE, has invited all faction of the former CUD to join his party, few will likely take his offer.
In a meeting with Ambassador on January 11, NEB board chairman Dr. Merga Bekana and vice-chairman Dr. Addisu Gebre-Egziabhier said that the Board still had not decided on the CUDP’s registration and would continue to consider the matter in coming weeks. Almost immediately following the meeting, however, the NEB publicly announced that it had decided that morning to award the party license to Ayele. This followed their controversial decision earlier in the week to give the CUD’s famous victory symbol to the CUD’s despised adversary Lidetu Ayalew (another person believed to have been co-opted by the GoE during the CUD’s post-2005 election struggles), and his UEDP-Medhin party.
The opposition fiercely accused the NEB of being under the influence of the GoE and of delivering votes to the ruling Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Forces (EPRDF) party after the opposition’s surprisingly strong showing. Since then, a new Board has been put in place, but the opposition have not altered their criticism. The NEB’s recent decisions to award the CUD party symbol and name to politicians, who are at best undeserved and at worst proxies of the GoE, has done much to reignite lingering suspicions regarding the NEB’s independence. As if to prove these suspicions, NEB vice-chairman Dr. Addisu (a Tigrayan political scientist widely believed to be the “enforcer” at the NEB) recently commented to USAID’s Senior Democracy Advisor — a former Stanford University Political Science Professor ) (strictly protect) that the NEB had decided to “kill the CUD.” The NEB decisions of the last week have effectively done exactly that.
በጃኑዋሪ 7 ሳምንት ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) ፓርቲ የሬሣ ሳጥን ላይ የመጨረሻ የሚባለውን ሚስማር መትቷል፡፡ በ2005 (1997) ምርጫ በአገሪቱ ሁለተኛው ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችለውን አስደናቂ ድልና በቂ መቀመጫ ካገኘ በኋላ ቅንጅት በውስጡ በነበረው የኃይል (የሥልጣን) ሽኩቻና ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ይደርስበት በነበረው ጣልቃ ገብነት ምክንያት አለሁ ቢልም እየተፈረካከሰ ነበር፡፡ በቅርቡ በተደቀነበት ሌላ ደንቃራ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ዝነኛውንና በብዙሃን መራጭ ዘንድ ዕውቅና የነበረውን የቅንጅትን (V) ምልክት ቀድሞ (የቅንጅት) ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ – ኢዴፓ-መድህን ልደቱ አያሌው ሸልሞታል፡፡ በመቀጠልም ምርጫ ቦርድ ይህንን ተከትሎ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የስም ምዝገባ ቀድሞ የቅንጅት ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የአዲስ አበባ ምክርቤት እጩ ተመራጭ አየለ ጫሚሶ ሸልሞታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅጥረኛ እንደሆነ በሰፊው የሚታመነው አየለ ጫሚሶ ከቀድሞው ቅንጅት ተሸራርፈው ለወጡት ሁሉ የእርሱን ፓርቲ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቢደርግም ጥቂቶች ብቻ ጥሪውን ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ . . .
addisu  g of neb
አዲሱ ገብረእግዚአብሔር
የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔርከአምባሳደሩ (ያማሞቶ) ጋር ጃኑዋሪ 11 ቀን ባደረጉት ስብሰባ የቅንጅትን ምዝገባ በተመለከተ ገና ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ እና በመጪዎቹ ሳምንታት ጉዳዩን እንደሚመለከቱት ነበር የተናገሩት፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ስብሰባው እንዳበቃ ማለት ይቻላል የዚያኑ ቀን ጠዋት የቅንጅትን የስም ምዝገባ ለአየለ ለመስጠት መወሰኑን ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ይፋ አደረገ፡፡ ይህ የቦርዱ ውሳኔ በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የቅንጅትን ዝነኛ (V) ምልክት በቅንጅቶች ለተናቀውና የፓርቲው ጠላት ለሆነው ልደቱ አያሌውና ለኢዴፓ-መድህን ፓርቲው ለመሸለም የተደረገውን አከራካሪ ውሳኔ ተከትሎ ነው፡፡ (ልደቱ አያሌው ከምርጫ 1997 በኋላ ቅንጅት ውስጥ በነበረው ትግል ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት የተመደበ ሌላው ቅጥረኛ እንደሆነ ይታመናል)፡፡ . . .
ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር እንደሆነ እና ተቃዋሚዎች አስገራሚ ውጤት በምርጫው ላይ ካሳዩ በኋላ (የመራጮችን) ድምጽ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዴግ) እንዳስረከበ ተቃዋሚ (ፓርቲዎች) አጥብቀው ይከስሳሉ፡፡ ከዚያ ወዲህ አዲስ ቦርድ የተሰየመ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን አሁንም ትችታቸውን አላቆሙም፡፡ የቅንጅትን ስም እና ምልክት ፍጹም ለማይገባቸውና ለኢትዮጵያ መንግሥት የቅርብ ወዳጆች ለሆኑት ፖለቲከኞች ማስረከቡ ምርጫ ቦርድ ከአድልዎ የነጻ አለመሆኑ ላይ ያሉትን ጥርጣሬዎች እንደገና እንዲቀጣጠል አድርጓል፡፡ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር አዲሱ በቅርቡ ለዩኤስኤይድ ከፍተኛ የዴሞክራሲ አማካሪና የቀድሞ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር (ስሙ እንዳይወጣ በጥብቅ የተከለከለ) ምርጫ ቦርድ “ቅንጅትን ለመግደል” ወስኖ እንደነበር መናገሩ እነዚህን ጥርጣሬዎች እርግጠኛ ያደርጋቸዋል፡፡ (የአዲግራት ተወላጅ የሆነው) (ዶ/ር አዲሱ የትግሬ የፖለቲካ ሳይቲስት ሲሆን የምርጫ ቦርድ “ፈጣሪና አድራጊ” እንደሆነ በሰፊው ይታመናል)፡፡ ባለፈው ሳምንት ምርጫ ቦርድ የወሰደው ውሳኔ (የቅንጅትን ስምና ምልክት ለቅጥረኞቹ መስጠቱ) ይህንኑ (ቅንጅትን የመግደሉን ዕቅድ) የሚያረጋግጥ ነው፡፡ . . . (ሹልክዓምድ (ዊኪሊክስ) ላይ የወጣውን ሙሉ መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
አሁንስ ማነው ባለሳምንት? በዚህኛው የምርጫ ድራማ አየለ ጫሚሶን የሚጫወተው ትዕግስቱ አወል እንደሆነ ይፋ ሆኗል፤ ልደቱንስ ማን ይተውነዋል?
ከዚህ በፊት በሰማያዊና በሌሎች ፓርቲዎች ላይ የደረሰውና አሁንም እየደረሰ ያለው እንዲሁም ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ የደረሰው ሰቆቃ የዘንድሮውን ሁኔታ የተለየ እያደረገው እንደሆነ ጎልጉል ከተለያዩ ምንጮች የሚደርሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህም ነው “ምርጫ ቦርድ” ቅንጅትን በዕቅድ እንደገደለው አሁንም አንድነትንና ሌሎቹን ተቀናቃኞች “አኝኮ ለመግደል” ውሳኔው የሆነው፡፡
ከሕዝብ በኩል የሚሰማው የሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት ግን የህወሃትን የልመና ኮሮጆ በሚሞሉት ምዕራባውያንም ዘንድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው እንደሆነ ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት በተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ ተሰራጭቶ ያገኘነውን መረጃ መጥቀሱ የቁርጠኝነቱን መጠን በተወሰነ መልኩ የሚያመለክት ነው፡፡ “በዕለቱ የደረሰበትን ጉዳት አስመልክቶ ለቢቢኤን ሬዲዮ የተናገረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ጉዳይ አንድነት ፓርቲ ኃላፊ ስንታየሁ ቁስሉ ሳይደርቅ በወኔ እንዲህ ነበር ያለው “ወያኔ ላጠፋው ጥፋት የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለ ማወቅ አለበት፡፡ ለትግላችን እንሰዋለን፤ በዋዛ አንላቀቅም”፡፡
http://www.goolgule.com/election-board-to-chew-and-kill-udj/

Thursday, January 29, 2015

“በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ባይ ሰው ነኝ” – የአርቲስት አስቴር በዳኔ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገፆች እና አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ላይ ስሟ በተደጋጋሚ የሚነሳው አርቲስት አስቴር በዳኔ የሀገራችንታዋቂአርቲስቶችን ባሳተፈውና ህወሃት የተመሰረተበትን 40 ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም በጠየቀቻቸው ጥያቄዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆና ሰንብታለች፡፡ አስቴር ለመከላከያ ሚኒስትር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ለሆኑት ለጄኔራል ሳሞራ የኑስ ባቀረበቻቸው ጥያቄዎች የደነገጡ አንዳንድ የሙያ ጓደኞቿ ሳይቀሩማግለልና መድልዎለመፍጠርም ሲሞክሩ ስለመታየታቸው ይነገራል፡፡ የራሷን አቋም በግልፅና በድፍረት በዚያ መድረክ ላይ ካቀረበችው አስቴር በዳኔ ጋር አዲስ አበባ ላይ አጠር ያለ ቆይታ ከቁምነገር መጽሄት ጋር አድርጋለችለግንዛቤ እንዲረዳዎ -ሐበሻ እንደወረደ አስተናግዳዋለች::


ቁም ነገር፡- ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስምሽ በስፋት እየተነሳ ነው፤ ምንድነው?
አስቴር፡- እንግዲህ ከሰሞኑ የደደቢት ጉዞ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በጉዞው ላይ ለየት ያሉ ጥያቄዎች
ጠይቃለች በሚል መሰለኝ የተለያየ ነገር እየተባለ ያለው፡፡

ቁም ነገር፡- አንቺስ የተለየ ጥያቄ ጠይቄያለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ?
አስቴር፡- ያሉና ሁሉም የሚያውቀውን ህዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን ነው የጠየቅሁት፤ አዲስ ነገር አለው ብዬ አላስብስም፡፡

ቁም ነገር፡- በመጀመሪያ እስኪ በጉዞው ላይ እንዴት እንድትሳተፊ እንደተጠራሽ ንገሪኝ?

አስቴር፡- እንደማንኛውም አርቲስት ነው የተጠራሁት፤ ጉዞው እንዳለ የነገረኝ አርቲስት መለሰ ወልዱ ነው፡፡ የህወሃትን 40 ዓመት ምክንያት በማድረግ አርቲስቶችን ወስደው ሊያስጎበኙ አስበዋል አንቺም ተጋብዘሻል ሲለኝ ደስ አለኝ፡፡ እንደ ፊልም ሰሪ ታሪካዊ ፊልም የመስራት ፍላጎት ልቤ ውስጥ ስላለኝ ለወደፊቱ የሚሰራ ነገር አይጠፋም ብዬ ሄድኩ፡፡ወደ እዛ ስንሄድ በቲቪ ብቻ የምታያቸው ባለስልጣኖች ከእኛ ጋር ጃኬት አድርገው መንገድ በመንገድ ሲሄዱ ሳይ ገረመኝ፡፡

ቁም ነገር፡-እነማን እነማን ነበሩ?

አስቴር፡- ዋና ዋናዎቹ ባለስልጣናት ነበሩ፤ እንግዲህ ሁሉንም ላላውቃቸው እችላለሁ፤ ግን የማውቀውን ያህል ጥሪ ካልከኝ፤ አቦይ ስብሃት፤አቶ በረከት ስምኦን፤አቶ አዲሱ ለገሰ፤ አቶ ስዩም መስፍን፤ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ፤ አቶ አባዱላ፤ / ካሱ ኢላላ ነበሩ፡፡

ቁም ነገር፡- ለጄኔራል ሳሞራ ያነሳሽው ጥያቄ ምን ነበር?

አስቴር፡- ከስብሰባው በፊት በአውቶብስ ስንሄድ አብረን ካለን አርቲስቶች ጋር ያው የተለመደ ወሬ እናወራለን፡፡ ሁሉም የመሰለውን ነው የሚናገረው፡፡ እኔ ደግሞ የምናገረው የማምንበትን ነው፡፡ የማስበውን እግዚአብሔር ያውቃል፤ ኑሮዬ ካሜራ ፊት ለፊቱ እንደተደቀነበት ሰው መሆን አለበት ብዬ ነው የማስበው ፡፡ ማስመሰል አልወድም፡፡እና እዛ አውቶብስ ውስጥ ስናወራ የምናወራውን የሰማ አንድ የኢህዴግ አባል የሆነ አርቱስትለምን ይህንን እዚህ የምታወሩትን መድረክ ተዘጋጅቶ አትናገሩም?› አለ፡፡ እኔ ደስ ይለኛል አልኩና በማግስቱ ነው መሰለኝ የደርግ 604 ክፍለ ጦር የተደመሰሰበትን ቦታ አስጎብኝተውን ስንመለስ ስብሰባ ተጀመረ፡፡አዳራሹ በሙሉ ሰው ሞልቷል፤ፖሊሶች ጠባቂዎች አሉ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም አሉ፡፡ እና ስብሰባው ተጀምሮ ጄኔራል ሳሞራ ገለፃ ሲያደርጉ አንዳንድ ማስታወሻዎችን እየፃፍኩ ነበር፡፡ ለምሳሌ እሳቸው ሲናገሩ ምን አሉለአስር ዓመታት ያህል ስንታገል ቆይተን ውጤት አልመጣ ሲል በአዲስ አስተሳሰብ ነው ለውጥ ያመጣነውብለው ነበር፡፡እንደውም ምንድነው ያሉትአሮጌ አስተሳሰብ አዲስ አስተሳሰብን ለመቀበል ይጎትታልብለው ነበር፡፡እንግዲህ እስከ እዛ ቀን ድረስ የተለያዩ የትግሉን ቦታዎች ተመልክተናል፡፡ እና ከእሳቸው ገለፃ በኋላ መድረኩ ለጥያቁ ክፍት ሲሆን አርቲስት አበበ ባልቻ መጀመሪያ ጠየቀ፤ ከዚያ ሳምሶን ማሞ ጥያቄ ጠየቀ/እናንተ እንደውም ባለፈው እትማችሁ ላይ አውጥታችሁታል/ ከዚያ ጥያቄ የሚጠይቅ ጠፋ፤ ቤቱ ፀጥ አለ፡፡ጠይቁ እየተባለ በየሻይ ቤቱና በየምግብ ቤቱ ባለስልጣናቱን በጀርባ ከማማት አሁን ነው መጠየቅ ያለብኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ግን ፈራሁ፤ከዚያ ለአቶ በረከት በትንሽ ወረቀት ላይጥያቄ መጠየቅ ፈልጌ ነበር፤ ግን ፈራሁብዬ ላኩላቸው፡፡

ቁም ነገር፡- እንዴት ለእሳቸው ለይተሽ ይህንን ጥያቄ ጠየቅሽ?

አስቴር፡- ምን ሆነ መሰለህ? ከዚያን ቀን ቀደም ብሎ፤ እዚህ አዲስ አበባ ኤፍኤም ላይ ተንሻፎ ስለእኔ የተወራ ወሬ ነበር፤ በጉዞው ላይ በነበርኩበት ጊዜ ትንሽ አሞኝ ነበር፤ መንገዱም ሙቀቱም በሰዓቱ ምግብም ስለማንበላ አንዳንዴ ከጉብኝት በኋላ 10 ሰዓት ነበር ምሳ የምንበላው በዚህ በዚህ የተነሳ ታምሜ በየቦታው እቀመጥ ነበር፡፡ የሆነ ቦታ ተቀምጬ ሳለ ከጀርባዬ አንድ ሰው ትከሻዬን መታ መታ አድርጎውሃ ጠጪ የእኔ እህትሲለኝ፤እሺ የኔ ወንድምብዬ ቀና ስል አቶ በረከት ናቸው፡፡ እንዴት እንደደነገጥኩ ልነግርህ አልችልም፡፡በስመ አብ ሁሉ ብዬ አማትቤ ነበር፡፡ ከዛ በየመንገዱ ላይ ሌሎቹም ባለስልጣናት ሲያገኙን ‹.አስቴር እንዴት ነው? በርቺይሉኝ ነበር፡፡ ስብሰባ የተካሄደው ከዛ በኋላ ስለነበር ለአቶ በረከት ወረቀቷን ስልክ አንብበውየፈለግሽውን ጠይቂብለው ምልክት ሰጡኝ፡፡ በወቅቱ ለሴቶች ዕድል ይሰጥ ሲባል ሌላ ሰው ስላልነበረ ለእኔ ተሰጠኝ፡፡ የተቀመጥኩት ከበስተኋላግራ ወንበር ላይ ነበር፡፡ የመጠየቅ ዕድሉ ሲሰጠን ግን ማይክ ስለማይደርስ ወደፊት ነይ ተብዬ ፊት ወንበር ላይ ተቀምጬ ነበር የጠየቅሁት፡፡ እንዴት እንደፈራሁ
ልነግርህ አልችልም፡፡ አንዳልኩህ ቤቱ በሙሉ በባለስልጣናት ተሞልቷል፡፡ግን እንደምንም ብዬ የፃፍኩትን ወረቀት እያየሁ ጠየቅሁ፡፡

ቁም ነገር፡-ምንድነው የጠየቅሽው?

አስቴር፡-ለምሳሌ ደርግን ለምን ጠላት ብለን እንጠራለን? ከደርግ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፤ በአይዲዮሎጂ ልዩነት ነው እንጂ በአብዛኛው ንፁህ የኢትዮጵያ ልጆች አሉበት፤ አሁንም ጠላት ማለት ተገቢ ነው ወይ? የሚለው የመጀመሪያ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ለሀገር ለመስራት ብለው የሚወዳደሩ በመሆናቸው ተፎካካሪ ፓርቲ ለምን አይባሉም? ተቃዋሚ የሚባለው ግን ከስሙ ጀምሮ የግድ መቃወም ያለበት ይመስለዋል፤ ግንቦት ሲመጣ 24 ዓመት ይሆናችኋል፤ እና ከዚህስ በኋላ በአዲስ አስተሳሰብና ፍልስፍና ሌላ የፖለቲካ ፖርቲ በምርጫ አሸንፎ ሀገሪቱን ሲመራ ልናይ እንችላለን ወይ? የሚልም አለ፡፡መንግስት ለመቀየር ከዚህ በኋላ የግድ ጦርነት አያስፈልግም፤ ስለዴሞክራሲ ስታስቡ ልባችሁ ምን ይላችኋል? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ነው የጠየቅሁት፡፡

ቁም ነገር፡- ምላሹስ?

አስቴር፡- ጄኔራል ሳሞራ የተቻላቸውን ያህል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ደርግን በተመለከተ ጠላት ያልኩትን ይቅርታ አድርጊልኝ ነው ያሉት፡፡ ትክክል ነው የደርግ ወታደር ተገዶ የሚዋጋ ነው፤ ነገር ግን ምን አለ መሰለሽ በወታደራዊ ውጊያ ውስጥ መጀመሪያ ላይ ተዋጊን ሞት ሞት እንዲሸተው ማድረግ ያስፈልጋልሲሉ አርቲስቱ ሁሉ አጨበጨበ፤ ተቃዋሚ ፓርቲን በተመለከተ ተፎካካሪ በሚለው ቢተካ እኔ ተቃውሞ የለኝም ግን አንዳንድ ተቃዋሚ የሀገሩን ጥቅም ለውጪ ሁሉ አሳልፎ የሚሰጥ አለ ብለዋል፡፡

አስቴር፡- ከጥያቄሽ በኋላ በአርቲስቶች በኩል የነበረው ስሜት ምን ይመስላል?

ቁም ነገር፡- ብዙዎቹ ሸሹኝ፤ከእኔ ጎን መሆን ራሱ የፈሩ ነበሩ፤ ትተውኝም የሄዱ አሉ፡፡ የሚገርምህ ግን ባለስልጣናቱም ሆነ የእነሱ ደጋፊዎች እኛ እኮ የታገልነው ማንም ሰው የመሰለውን እንዲናገር ነው፤ ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅሽው፤
ነበር ያሉኝ፡፡

አስቴር፡- ከዋናዎቹ ጥያቄውን ከተጠየቁት ሰዎች ሳይመጣ ከሙያ ጓደኞችሽ መምጣቱ ምን ስሜት ፈጠረብሽ?

ቁም ነገር፡-አላውቅም፤ እንግዲህ ምናልባት እንደዚህ ብላ ትጠይቃለች ብለው አስበው ላይሆን ይችላል፡፡ ግን ውስጤ አንድ ነገር ነግሮኛል፤ አንዳንዶቹ ደስተኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ፡፡ ምናልባትም ትንሽ ደፋር ሳልሆንባቸው አልቀረሁም/ ሳቅ/ አንድ አርቲስት እንደውም ማታ ራት ከበላን በኋላ አጠገቤ መጥቶ ምን አለኝ መሰለህ? አንቺ ምን ይሁን ነው የምትይው?› አለኝ፤ ምን ይሁን አልኩኝ? አልኩትኢህአዴግ ህዝብ እስከመረጠው ጊዜ ድረስ ዓመትስ ቢነግስ ምን አለበት?› አለኝ፡፡ እኔ ታዲያ ምን ቸገረኝ፤ እኔ እኮ ስለዲሞክራሲ ስለተነሳ ነው ጥያቄ የጠየቅሁት እንጂአንድ ሰው ተነስቶ እኔ ንጉስ ነኝቢለኝ ዓመት ንገስ ነው የምለውአልኩት፡፡ይሄ ግን የብዙዎቹን አስተሳሰብ የሚወክል አስተያየት እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡ በነገራችን ላይ እኔ የተለየ ነገር ፈጥሬ የተናገርኩ ሰው አይደለሁም፡፡ የተሰማኝን ነው የተናገርኩት፡፡እውነት ነው ብዬ የያዝኩት ነገር ካለ በድፍረት እናገራለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- በየማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስላንቺ እየተባሉ ያሉትን ነገሮች ተመልክተሻቸዋል?

አስቴር፡- እኔ ብዙ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ አይደለሁም፡፡ በሳምንት አንድና ሁለት ጊዜ ባይ ነው፡፡ ለምሳሌ የእኔን ፎቶና የባለስልጣናትን ፎቶ አድርገው ስድብ በመፃፍ የሚያሰራጩ አሉ፤ ይሄ ትክክል አይደልም፤ የእኔ አላማ መሳደብ አይደለም፤ በመሳደብም ሆነ የሰውን ክብር በመንካት የሚመጣ ለውጥ አለ ብዬ አላምንም፡፡ እነዚህ ሰዎች እኮ ከፋም ለማም ሀገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉ ሰዎች ናቸው፤ ያለፉበትንም የትግል ሂደት ሄደን ተመልክተናል፡ የሚካድ አይደለም፡፡ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች አጠንክሮ ችግሮቹንም መንገር ነው የሚያስፈልገው፡ ፡እኔ በአሁኑ ወቅት ጊዜ የለኝም፤ ብዙ ስራ አለኝ፤ አራት መፅሐፍ ላሳትም ያዘጋጀኋቸው አሉ፤ አንድ ግጥም ሲዲ ጨርሻለሁ፤ የቤተሰብ ሀላፊ ነኝ፡፡ የልጆች እናት ነኝ፡፡ ፌስቡክ በሚሰጠው አፍራሽ አስተያየት ላይ ምንም ልል አልችልም፤ አልሞቀኝም አልበረደኝም፡፡ ከዚህ ይልቅ ፊልም ሰርቼ ብታወቅ ነው የምመርጠው፡፡ የሚገርምህ ቤተመንግስት ሁሉ ተጠራች ብለው የሚያወሩ አሉ፡፡

ቁም ነገር፡- ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር መያያዙ አስጨንቆሻል?

አስቴር፡- ለምን ያስጨንቀኛል? የፖለቲካ ጥያቄ ስትጠይቅ ጉዳዩ ወደ ፖለቲካ እንደሚሄድ እገምታለሁ፡፡ግን እኔ የጠየቅሁት ጥያቄ ካየሁት ከሰማሁት፤ሰው ከሚያወራው ተነስቼ በመሆኑ ያን ያህል አነጋጋሪ መሆኑ አስገርሞኛል፡፡

ቁምነገር፡- አስቴር ፖለቲከኛ ናት?

አስቴር፡-አይደለሁም፤

ቁምነገር፡-ፖለቲካ ትወጃለሽ?

አስቴር፡- ማለት.. የሚያናድዱኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ በዚያ በኩል ያለውን ሁኔታ ለማወቅ የምቆፍር አይነት ሰው ነኝ፡፡ ግን የፖለቲካ ጋዜጣና መፅሔት የምከታተል ሰው አይደለሁም፡፡ እርግጥ ነው በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ባይ ሰው ነኝ ፡፡

ቁምነገር፡- አርቲስት ከፖለቲካ ነፃ መሆን ይችላል ብለሽ ታስቢያለሽ?


አስቴር፡- አርቲስት ፖለቲከኛ ሳይሆን መስታወት ነው፡፡ መስታወት ደግሞ ያለውን ነገር በግልፅ ነው የሚያሳየው ብዬ ነው የማምነው፡፡

ቁም ነገር፡- በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለችው አስቴር ምን አይነት ሴት ናት?
አስቴር፡- አስቴር በጣም ቆንጆ፤ በንጉሱ ፊት ሞገስ ያገኘች፤ ለህዝቧ ምህረትን ያመጣች ብልህ ሴት ናት፡፡እናትም አባትም ሆኖ መርዶኪዮስ ነው ያሳደጋት፡፡መርዶኪዮስ ከህንድ እስከ ኢትዮጵያ ነበር የሚያስተዳድርው፡፡ ንጉሱ ሲያገባት አይሁዳዊ መሆኗን አያውቅም፡፡ መርዶኪዮስ ሐማ ለሚባለው የንጉሱ ባለሟል አልሰግድም በማለቱ እንዲገደል ይወሰናል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን መላ ዘሩ ሁሉ እንዲጠፋ ይፈረድበታል፡፡ ይህን ጊዜ መርዶኪዮስ አስቴርን በዚህ ጊዜ ህዝብሽን ማዳን አለብሽ ይላታል፡፡ንጉሱ ብዙ ሚስቶች ስላሉት የሚፈልጋትን ካላስጠራ በቀር እሱ ጋር መቅረብ አይቻልም፡፡ አስቴር ግን ህዝቡ ለሶስት ቀን ፆም ፀሎት ይያዝ አለች፤ ከሶስት ቀን በኋላ ንጉሱ ሳያስጠራት ቢገድለኝም ይግደለኝ ብላ ንጉሱ ፊት ሄዳ ቆመች፡፡ ንጉሱ ዘንጉን ከዘረጋላት አለፈች ማለት ነው፤ ዝም ካለ ግን ያው ትገደል ነበር፡፡ ግን አስቴር በንጉሱ ፊት ሞገስ አገኘች፡፡ ምንድነው የምትፈልጊው? ሲላት ስለህዝቧ ተናገረች ስለህዝቧ የተጻፈው የሞት ደብዳቤ ለጠላቶቿ ሆነ፤ህዝቧንም አዳነች ማለት ነው፡፡ በጣም ነው አስቴርን የምወዳት፤
ቁም ነገር፡- በመጨረሻስ?


ቁም ነገር፡-ለሁሉም አስተያየት ለሰጡኝ ሰዎች ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡ አድናቆታቸውን ለሰጡን ብቻ ሳይሆን ለተቹኝም ለሰደቡኝም አመሰግናለሁ፡፡ ምክንያቱም ሰው ሁልጊዜ የሚናገረው በአዕምሮውና በአስተሳሰቡ በእውቀቱ ደረጃ ነው፡፡ ሁሉም ሰው እንደእኔ ያስብ ለማለት አይቻልም፡፡የተነገረውን ነገር የምትቀበልበት ልብ ነው አንተን የሚገልፅህ፡፡ ቀና አስተሳሰብ እንዲኖረን ነው የምፈልገው፡፡አንድ የሚያደርገን ነገር ላይ ብናተኩር ነው ደስ የሚለኝ፡ በፖለቲካ ልዩነት ሳቢያ እንደ ጠላት ባንተያይ እላለሁ፡፡ፖለቲከኛነትና እንጀራም ቢለያይ ጥሩ ነው፡ እኔ ለማንም ጥላቻ የለኝም፤ ማንንም አልቃወምም፡ ፡ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ እንፍጠራት ነው የምለው፡፡ እየተፈራራን የትም አንደርስም፡፡የመሪዎቻችንን ልብ በፍቅር መማረክ ይቻላል፤ፈሪ ህዝብ ለምንም አይጠቅምም ፡፡ መንግስትም ፈሪ ህዝብ ይዞ ልማቱን መቀጠል አይችልም፡፡ ከዚህ ፍርሃት እንደ ህዝብ ተላቀን በፍቅርና በሰላም ለሀገር ይጠቅማል የምንለውን አሳብ እየሰጠን እንድንኖር ነው የምምኘው፡፡
ቁም ነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38553