Thursday, October 31, 2013

ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እጅግ ልብ የሚነካ ደብዳቤ እስር ቤት ለሚገኘው እስክንድር ነጋ በድምጽ ላከች (ይዘነዋል)

(-ሐበሻ) ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጣች 3 ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እስር ቤት ለሚገኘው ባለቤቷ እስክንድር ነጋ እና ለሌሎችም እስረኞች በድምጽ በመተረክ መልዕክት አስተላለፈች። ሰርካለም በመልዕክቷስለ ሁለት ሰው ማሰብ እንዴት ይከብዳልብላለች። በትረካዋ ከኢትዮጵያ ልትወጣ ስትል የነበሩትን የመጨረሻ ቀናት ታስታውሳለች። መልዕክቱን ያድምጡት።

Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, October 30, 2013

አወጋን “ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳኖች እየተሸጠ ነው” አለ

(-ሐበሻ) ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው ሲል አወጋን (የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ) ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አመለከተ። ንቅናቄው በላከው መረጃከደቡብ ጎንደር፣ ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪዎቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ (የትግራይ ተወላጆች) ግፍ እየተሰራባቸው ነውሲል ከሷል።

(ሁመራ ከተማ)

ባለፉት 2 ወራት ብቻ 16 ሰዎች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ያለው የአወጋን መረጃ ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን ይሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት (የወሎ እና የጎጃም በሚል) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲያዎችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል:: ብሏል።
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም መሆኑን ያጋለጠው የአወጋን መረጃ በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬዎችን ኩላሊት ነው ይላል።እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤል በህገወጥ መልኩ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪፍ እና አጎራባች አካባቢዎች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ ዶላር በማስከፈል ይለቋቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላሊታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ::” በማለት አወጋን ለወገኖቻችን እንድረስላቸው ሲል ጥሪውን ከሰሜን ጎንደር አስተላልፏል።

ለአወጋንን ክስ የመንግስት አካላትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

 Posted By.Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8772

Monday, October 28, 2013

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?


fire


በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች እርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።
ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።
አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።
በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።
ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።
ጡረተኛው ፕሬዚዳንት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የተፈጥሮ ደኑ ከመጨፍጨፉ በፊት ውሳኔው እንዲመረመርና እንዲጠና ሚያዚያ 28 ቀን 2002 ዓ ም ለክልሉ ደብዳቤ ልኮ ነበር። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በወቅቱ የአፍሪካ የተፈጥሮ ጥበቃና የአየር ንብረት ተሟጋች ነኝ ያሉበት ወቅት መሆኑንን በማስታወስ፣ የፕሬዚዳንቱን መመሪያ በመጠቆም ባለስልጣኑ የጻፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ህዳር 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ደመሰሱት። ከላይ የተጠቀሰው ኩባንያ የ50 ዓመቱን ውል ቅድሚያ ክፍያ የአንድ ዓመት 19 ሺህ ዶላር ስለከፈለ ቦታውን እንዲረከብ ዞኑንን አዘዙ።
የበላይና የበታቹ በማይታወቅበት የመለስ አወቃቀር ጥብቅ ደኑ ያለበት መሬት ለህንዱ ኩባንያ ተላለፈ። ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ እስከ ፕሬዚዳንቱ ያደረሱት ሊቀመንበር እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ከሃላፊነታቸው ተባረሩ። ህዝብ የኑሮው መሰረትና የህይወቱ ያህል የሚንከባከበው ደን ተጨፈጨፈ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ደኑ ሲጨፈጨፍ የነበረው ሃዘን በቃል የሚገለጽ አልነበረም።timber log
ባገኘው ከፍተኛ የደን ምርት ጣውላ ማምረት የጀመረው ኩባንያ መጋዘን ገንብቶ የጣውላ ንግድ ውስጥ ገባ። አሁን ድረስ ንዴቱና የበደል ስሜቱ ያለቀቀቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደባቸውን ግፍ “ዝርፊያ” እያሉ ነው የሚጠሩት።
ህግን ጠብቀው ኢህአዴግን ያሳሰቡት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በእስርና በድብደባ በማሰቃየት ኢንቨስትመንትን /ነዋሪዎቹ ዝርፊያ ነው የሚሉት/ በክልሉ ቀጣይ ማድረግ አይቻልም። አስቀድሞ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢህአዴግና ኩባንያው ጆሮ ሰጥተዋቸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደማይችል አስተያየት ሰጡ አሉ።
92 ሚሊዮን ብር በላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዳ ያለበት የእርሻ ድርጅት፣ ንብረቱ በእሳት ከወደመ በኋላ የተሸከመው እዳ አጀንዳ ሆኗል። የደረሰበት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉንና ኢህአዴግን ካሳ እንደሚጠይቅም ከወዲሁ ተሰምቷል። ዜናውን ያቀበሉ ክፍሎች “ህዝብ ላልተቀበለው ኢንቨስትመንት ካሳና የልማት ባንክ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው” የሚል ጥያቄ መነሳቱን አመልክተዋል።
ለአበባ እርሻ ላስቲክና ኬሚካል በማስያዝ ልማት ባንክን እያለቡ የተሰወሩ በርካታ ድርጅቶችና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሸሪኮቻቸው መኖራቸውን በማስታወስ በጋምቤላ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል። ካራቱሪ በኪሳራ መንገዳገዱን፣ ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በ”ውክልና” ለሳዑዲ አረቢያ ቀለብ እንዲያመርት የተከሉት ሳዑዲ ስታርና ሌሎች የህወሃት ሰዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ መበደራቸውን ገልጸዋል።
“ህዝብን ያለፈቃዱ በማፈናቀልና መሬቱን በመቀማት የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሁሌም አደጋ ላይ መሆኑ አያጠራጥርም” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ገልጸዋል። “ኢንቨስትመንት እንኳን ደህና መጣህ በሚል ህዝብ ካልተቀበለው ዘረፋ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ጆሮ ያጣ ህዝብ ተቃውሞውን ገለጸ” በማለት በደረሰው ውድመት ባይደሰቱም ለውድመቱ ተጠያቂው ኢህአዴግና ከኢህአዴግ ጋር ተሻርኮ ዝርፊያ ያከናወነው ድርጅት እንደሆነ አመልክተዋል።
ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ግፍ ሃብት ለማፍራትና ለመበልጸግ የሚያስቡ ትልቅ ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ ዝርፊያና ኢንቨስትመንትን ለይቶ መሔድ ካልቻለ ስጋቱ እየጨመረ ይሄዳልና ከስህተት በመመለስ ህዝብ በሚፈቅደው መልኩ ማስተናገድ ግድ ነው” ሲሉ አሁንም ጆሮ የለውም ለሚባለው ኢህአዴግ ማሳሰቢያ አዘል ምክር ለግሰዋል። ባለሃብት የሚባሉትም ከዚህ ታላቅና አሳዛኝ ውድመት ሊማሩና ህዝብ “እንኳን ደህና መጣችሁ እንዲላቸው ህዝብ ከሚቃወመው ዝርፊያና አሰራር ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል” ብለዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት ቃጠሎውን ማመናቸውን ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ያስታወቀ ሲሆን አጣሪ ኮሚቴ ተቃቁሞ አደጋውን ያደረሱት እነማን ናቸው የሚለው እየተመረመረ እንደሆነ ጠቁሟል። የክልሉ የጎልጉል ምንጮች በርካታ ሰዎች እሳት አስነስታችኋል በሚል መታሰራቸውና በፌዴራል አንጋቾች እየተመረመሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። እሳት ያስነሱትን ለማጋለጥ በሚል በየመንደሩ በሚደረግ ማዋከብ ነዋሪዎቹ መማረራቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው የእስረኞች ቁጥር ባይታወቅም ወደ ማዕከል የተላኩ በርካታ እንደሆኑም ገልጸዋል። በማያያዝም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኢህአዴግም ሆነ ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ህዝብን ማዳመጥ ሊቀድም እንደሚገባው ጠቁመዋል።
   Posted By.Dawit Demelash

Friday, October 25, 2013

ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ

ህወሃትን ገልብጦ “ከየትኛው ክልል ድጋፍ ሊገኝ?”
sebhat nega


ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ።
አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት “አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል” በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት እንዳልሆነ አስመስለው አቶ ስብሃት የመለሱት የክልሎችን ስም በመጥራት ተቀባይት እንደማይኖረው ነው። ይህም አባባላቸው እኛን ገልብጦ አገር አንድ አድርጎ መምራት አይቻልም የሚል እንደምታ ያለው ቢመስልም፤ “ሪፑብሊክ” ለመመሥረት የተነሳውና እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን ህወሃት የመጨረሻ የመጥበብ ዓላማ በማስረጃ የገለጹበት ነው፡፡
ህወሃት “ኢህአዴግ” የሚባለውን ድርጅት ሲያበጀው የአገልግሎት ዘመን መድቦለት እንደሆነ ስለ ድርጅቱ የወደፊት መድረሻ ድንበሩ ከሚያወሱ የድርጅቱ የተለያዩ ማረጃዎችና ነባር አባሎቹ መጠቆሙ ይታወሳል። ህወሃት 40ና 50 ዓመት ኢትዮጵያን በብሔር ፖለቲካና በዘር እያጋጨ ለመግዛት የሳለው ስዕል እንዳሰበው ካላዘለቀው እንዴት ጠቦ እንደሚጠናቀቅ የጠቆሙት ስብሃት፣ አስተያየታቸው አካሄዱ የገባቸውን በሙሉ አበሳጭቷል።
በ1997 የምርጫ ወቅት ተፈጥሮ በነበረውና በራሱ በቅንጅት ሰዎች ሽኩቻ በተኮላሸው ህዝባዊ ድል ግለት ወቅት ኢንዲያን ኦሽን የተሰኘው ጋዜጣ “ህወሃት ወደ ትግራይ የማፈግፈግ እቅድ ይዟል” በማለት የዘገበውን ዘገባ በማስታወስ በአቶ ስብሃት መልስ ላይ አስተያየት የሰጡ፤ በቅድሚያ አቶ ስብሃትን “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም” በሚል ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ “የስብሃት ንግግር ህወሃት ታሪኩ ሲጠናቀቅ ጠቦ እንደሚቋጭ ነው። ለዚህ ሲል ነው ህዋሃት ከአንቀጽ 39 ጋር ቅበሩኝ የሚለውና የአማራ ክልል መሬትን እየዘረፈ የመውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ሌት ከቀን መሬት እየቆረሰ አዲስ ካርታ የሚያመርተው፤ ዓለምአቀፋዊ ድንበርም ለትግራይ እንዲኖራት ያደረገው” ብለዋል።
“ህወሃት ካለውና ከተፈጠረበት  ክፉ ዓላማ አንጻር በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ‘ቦታ አይኖረኝም’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ ሁልጊዜ ሲጨንቀው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስዕል ያሳያል። የስብሃትም ንግግር ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው” በማለት ምልከታቸውን የተናገሩት የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ውሳኔውና ህልሙ ስኬት የናፈቀው የቅጥረኞቹ የህወሃት ሰዎች ጭንግፍ ምኞት ቢሆንም መላው የትግራይ ህዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርት ያለ አቋም በመያዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚቆም መሆኑን ማሳየት እንደሚገባው” አመልክተዋል።azeb 3
ከህወሃት ሊቀመንበርነታቸውና ከስራ አስፈጻሚነታቸው አራት ጊዜ ማመልከቻ በመጻፍ በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያመለከቱት ስብሃት ነጋ በኤፈርት ጉዳይ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ስምምነት እንዳልነበረቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አያይዘውም ህወሃት የመከፋፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያወቅ፣ እንዲያውም በየጊዜው የሚነሱ የሃሳብ ልዩነቶች የድርጅቱ ልዩ ስጦታውና በረከቱ አንደሆነ ተናግረዋል። ልዩነትና በልዩነት ጥግ ድረስ ደርሶ መፋጨት የህወሃት የጥንካሬው መሰረት እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ስብሃት በድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ህወሃት ለሁለት ተከፍሎ አደጋ ላይ የወደቀበትን ጊዜ አስተባብለዋል። እነ አቶ ስዬንም “የተባረሩ” ሲሉ አቅመ ቢስ አድርገው ስለዋቸዋል።
ኤርትራ ራሷን በወጉ መከላከል እንኳ የማትችል አገር እንደሆነች የጠቆሙት ስብሃት ኤርትራን ተማምኖ የሚከናወን የተቃውሞ ትግል የጤና ነው ብለው እንደማያምኑ “እብደት ነው” በማለት ኢህአዴግም ሆነ እሳቸው በእንቅስቃሴው ላይ ስጋት እንደሌለባቸው ለመግለጽ ሞክረዋል። ስብሃት በአሜሪካ ከተለያዩ ወዳጅ ሚዲያዎች ጋር እየተወደሱ ጥያቄና መልስ ያካሄዱ ሲሆን በተለይም ስለ መለስ ቅንድብ ከዘፈነው ሰለሞን ተካልኝ ሲቀርቡላቸው የነበሩት ጥያቄዎች የሚያዝናኑ ነበሩ። ጥያቄና መልሱን የተከታተሉ “ጠያቂው መልሱን አስቀድሞ ጥያቄ ማስከተሉ ጥሩ ተማሪ መሆኑንን በማረጋገጥ የምስክር ወረቀት የፈለገ አስመስሎታል” ሲሉ የለበጣ አስተያየት በማህበራዊ ገጾች ላይ አስፍረውበታል። አቶ ስብሃት በአሜሪካ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን መደባደባቸውና በፖሊስ ይፈለጉ እንደነበርም መዘገቡ ይታወሳል። አቶ ስብሃት ከፖለቲካው ፈላጭ ቆራጭነት ወጥቻለሁ ቢሉም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንቢቶች አሁንም “የህወሃት የኋላ ዘዋሪ” እንደሆኑ አመላከች እንደሆነ ተጠቁሟል።
  Posted By.Dawit Demelash