Tuesday, June 7, 2016

ይቺ ቆራጥ ኢትዮጵያዊት ነጻ ናት… ፍቷት!

ይቺ ቆፍጣና ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው በመባል ትታወቃለች። እርሷ ፍቅረማሪያም አስማማው እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ሆነው በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር በማበር፤ የኢህ አዴግን ብልግና ለማረቅ ከዛም አልፎ ከስልጣኑ በማውረድ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት በማሰብ፤ ሰላማዊ ትግል ሲያደርጉ ነበር።

ነገር ግን የመንግስታችን ነገር ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭብለው እንዲተርቱ እና በአለት ላይ ውሃ ማፍሰስ ብለው እንዲጨምሩ አይነት ሰላማዊ ትግል የሚገባው አልሆነም። እንኳንስ ሊገባው ሰላማዊ ታጋዮቹን በሙሉ ወደ እስር ቤት እያስገባ አሸባሪ ብሎ በመሰየም እያሸማቀቀ የትግል ምህዳሩን አጠበበው።

ይሄ ነገር ተስፋ ያስቆረጣቸው እነ እየሩሳሌም ኢህ አዴግን በሚገባት ቋንቋ ሊያነጋግሯት ወደ ጫካ ሲወርዱ ተያዙእኔ ብሆን ወደ ቻካ ልገባ ስል ብያዝአዎ ልዋጋ ነው ብዬ የማምን አይመስለኝም፤ በጣም ከተቸገርኩ እና የምለው ካታሁ…. ‘’እንጨት ልልቀም ነው…’’ የምል የሚመስለኝ።
እነ እየሩሳሌም ግን ለፖሊሶችም ለፍርድ ቤት ዳኞችም አዎን ትጥቅ ወዳነገቡት ታጋዮች እየሄድን ነበር። ኢህ አዴግ ሰላማዊ ትግሉ ሊገባት ስላልቻለ በሚገባት ቋንቋ ልናነጋግራት ነበር። ብለው ተናገሩ!

እነ ኢየሩሳሌም ግንቦት ሰባት አርበኖችን ለመቀላቀል ማሰባቸን ወንጀል አይደለም። ብለው እየተከራከሩ ነው። ይሄንን ለማስረዳት በርካታ የቀድሞ ታጋዮችን ምስክርነት ጠርተዋል። ነገር ግን የሃገሬ ፍርድ የጭቦ ነውና፤ ልጆቹ ምስክር ማሰማት እንኳ እንዳይችሉ ተከልክለው ለምን ሆድ ባሳችሁለምን ተከፋችሁ ለምንስ ዱር ቤቴ አላችሁ በሚል ብይን ሊሰጥባቸው ሃምሌ አስራ ሶስት ተቀጥረዋል።

ፍርድ ቤቱ ቀና ቢሆን ኖሮ እነ እየሩሳሌም የሰሩት ስራ ምንም ወንጀል እንዳልሆነ ለመረዳት አንድ ሁለት የግንቦት ሃያ ዶክመንተሪ ፊልሞችን ማየት ይበቃው ነበር።

እነ ህውሃት ለዛምን ምንም አይነት ሰላማዊ ትግል ሙከራ ሳያደርጉ ጫካ ሲገቡ ጀግና ተብለው እነ እየሩስ ሰላማዊ ትግሉን አይተውት መንገዱ ሲዘጋባቸው ሌላ መንገድ መምርጣቸው በምንም መስፈርት ወንጀል ሊሆን አይችልም!!!

እየሩሳሌም ዛሬ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ሙሉ ጥቁር ለብሳ እጇ ላይ የሃገሯን ሰንደቅ አላማ አድርጋ ነበር።


እነ ኢህ አዴግ ሆይ ለሴቶች እኩልነት ቆመናል የምትሉ ከሆነ (ካልሆነም)  ይቺ ቆራጥ ኢትዮጵያዊት ነጻ ናትፍቷት!

http://www.abetokichaw.com/?p=91