ኮሎኔል ደመቀን በሃይል አውጥቶ ለመውሰድ ከሰባት ጊዜ በላይ የሞከረው ወያኔ አሁንም ተመሳሳይ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ ነው የተነገረው። እንደተለመደው የጎንደር ሕዝብ እርብርቡን እንዲያደርግ ጥሪ ይተላለፍ ተብሏል።
የይስሙላው የፌደራል ፍርድቤት ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረገው ችሎት በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትን ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ አይቶ ለሌላ ቀጠሮ አስተላልፏል። በዚሁ በሞት ፍርድ በሚያስቀጣ የክስ ፋይል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በሌሉበት እንደተከሳሽ መጠቀሳቸው ወያኔ ኮሎኔሉን በሃይል ለመውሰድ መወሰኑን ማሳያ ነው።
በሰላማዊ መልኩ የህዝብ ፊርማ ሰብስበው እራሱ ወያኔ በፃፈው ህገ መንግስትና በወያኔ ብቻ በታጨቀው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህጋዊ ጥያቄ ጠይቀው እውቅና የተሰጣቸውን የወልቃይት ኮሚቴ እመራሮች ወያኔ ወደ ጎንደር አፋኝ ሃይል ልኮ ማፈን ሲጀምር ሃምሌ 5 ቀን የፈነዳው የጎንደር ብሎም የተቀረው የአማራ ሕዝብ ቁጣ ንሮ የስርአት ለውጥ ወደ ማምጣት ተሸጋግሯል።
ኮሎኔል ደመቀ ብቻው እንድ ክፍል ውስጥ እግረ ሙቅ በብረት ታስሮ እንደሚገኝ ሰሞኑን ስንገልፅ ነበር። የነፃነት ጥያቄ በእስር አይመለስም። ህዝብ ሁሌም ያሸንፋል!
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/70583