Friday, July 5, 2013
ከድጡ ወደ ማጡ! የቀበሮ ባሕታዊ በሎንደን
July 4, 2013
ወንድሙ መኰንን፣ ሎንደን
መግቢያ
በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁ ወገኖቻችን በኛ ሎንደን በምንኖረው የኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ በሆንን ኢትዮጵያውያን ላይ በአንድ መነኵሴ ነኝ ባይ የቀበሮ ባሕታዊ ግለሰብ አማካኝነትና በወያኔ ቀጠረኞች የደረሰብንን ይቅር የማይባል በደል ዕለት በዕለት እንደምትከታተሉና መጨረሻችንን ለማየት በጉጉት እንደምትጠባበቁ እዚህ ያሉት ወንድሞችና እህቶች በሚገባ ያውቁታል። ያመሰግናሉም። ታዲያ ከዚያች ቀውጢ የሁዳዴ ጾም መያዢያ ማግስት፣ ጀምሮ የተዘጋብን ቤተክርስትያን ጉድይ እስካሁን እልባት ሳያገኝ፣ ቀርቶ ሕጻናቱም፣ አይቆርቡም፣ አዛውንቱም፣ ወይዛዝርቱም እግዚአብሔርን ማምለኪያ ቦታ አላገኙም። ይኸ በደል ባንድ ካኽን ንኝ ባይ ሲፈጸም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪአው መሆን አለበት። ብቻ በየሰንበቱ፣ “አንድ ሐሙስ የቀራችሁ፣ የእንጨት ሽበት፣ ሽሜ ጉጉ”እያተባሉ በወያኔ ሶልዲ በተገዙ ስድ ወጣቶች እየተሰደቡ፣ ሴቶችም ለጆሮ በሚቀፍ ስደብ እየተሸማቀቁ፣ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ገቢ እየገቡ ሕንጻዋን እየተሳለሙ፣ ከሕዝብ ጋር ከሚንከራተቱ አንድ ቄስ፣ አንድ መሪ ጌታ፣ እና በመምሕር ታሪኩን ጨምሮ በዛ ካሉ ዲያቆናት መሪነት ሜዳ ላይ እየጸለዩ፣ አራት ወራት አሳለፈዋል። ምን ላይ ደረሰ እያላችሁ የምትጠይቁ በዝታችኋል። ሁለቱ አዋጊ ጳጳሳትም፣ አቡነ ገብርኤልና አቡነ ቀውስቶስ፣ የትም ቦታመንቀሳቀስ በማይገባቸው የሱባኤ ሰሞን አገረ ስብከታቸውን ጥለው ሕንጻውን ሊቀሙን ቢመጡም፣ በተደረገው ርብርብ ሳይሳካላቸው ቀርቶ “አባ” ተባዩን የቀበሮ ባህታዊ፣ “በርታ” ብለው ወደመጡበት ተመልሰዋል። “በመነኵሴ ነኝ” ባዩ አመጸኛ ግለሰብ አዝማችነት፣ ተዝቆ፣ ተዝቆ በማያልቀው የወያኔ ገነዘብ ኪራይ ከፋይነት ተደለለው፣ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ረግጠው በማያውቁ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጋጠ-ወጦች (ጋንግስተሮች) እስከመገፋት መገፍተር፣ደርሷል። እና አባ ተባዩም ንብረት እስከመስረቅና ማጋዝ ጀምረው ነበር። እንዲያም ሁኖ፣ እስካሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተክስቲያኑን እየጠበቀና እየተከላከለ ይገኛል። ግፉ ግን በዝቷል። ሁለንተናው ዘቅጧል። ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ ተብሎ ቢደመደም ይበጃል። “አባባሱባት” ነበር ያልኳችሁ ባለፈው? እሱን እርሱት። ያሁኑ ይባስ።
የመዳን ንሰሐ ለጥቃት ሲያጋልጥ
ባለፈው ሳምንት የተፈጽመው አሳፋሪ ወንጀል፣ በታሪካችን ምንጊዜም “በምዕምን ላይ ደረሰ” ሲባል ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ ነው። ፈረንጆች “Abuse of Trust” ይሉታል። ያመኑት ፈረስ በደንደስ እንደሚሉት ነው። በመጨረሻው ጽሑፌ ከአንባቢዎቼ የተልያየሁት “ብጹዐን አባቶች ለታስታርቁን ወይስ ልታዋጉን መጣችሁ?” በማለት በሞነጫጨርኩት መጣጥፍ ነበር። አባዛኛው መልዕክቱ ቢገባውም፣ ሌሎች ሰዎች ነገሩን እያባባስኩ እንጂ እየረዳሁ አለመሆኔን ስላሳሰቡኝ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ላለመጻፍ አቅጄ ቆየሁ። የኔ ዝምታ ግን “ትሻልን ፈትቼ ትብስና አገባሁ” ቢጤ ሆኖብንና አሸንፈው ጭጭ ያሰኙኝ መሰላቸው። የኔ መተው ነገሩን አልከተተውም። ጳጳሳቱ ወደመጡበት በመመለሳቸው፣ የወያኔን ይሁንታ ተጨምሮበት፣ የቀበሮ ባህታዊው ባሰባቸው። በነጋ በጠባ ሕዝቡን “በምን ላቁስለው?” እያሉ ሲያልሙ የሚያድሩ ይመስላሉ። ፓትርያርኩ በሞቱላቸው ጊዜ፣ ይኸን ሕዝብ በምን ቆሽቱን ላድብን ብለው፣ ለታጋይ ጳውሎስ ፍትሀት አደርጋለሁ ብለው ተነስተው እንደአንጫጩን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሌላ አገኙ። የቤተክርስቲያናችንን መሠረት የናደ፣ እንኳን ከአንድ የአሀይምኖት አባት ነኝ ብሎ ከሚመጻደቅ ይቅርና፣ ከመርካቶ ዱሩየም የማይጠበቅ፣ በጣም የወረደ ተግባር ፈጸሙ። “ቤተክርስቲያናችንን ይጎዳል፣ ዝም በሉ” ለምትሉን፣ ዝምታ ለበጓም አልበጃት፣ ዝም አንልም። ዝም እማ ካልን ዲያብሎስ ይነግሳል። በዓለም ዙሪያ ያሉት ክርስቲያን ወንድሞችና እየቶቻችን የደረሰብንን በደል አውቀው፣ በጸሎታቸው እንዲተባበሩን፣ በደሉ ይታወቅ። የሎንደንማ ሕዝብ በተፈጽመው አስነዋሪ ነገር ተደናግጦ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ገብቶት ቁጭ ብሏል። አንዳንዱ፣ “ተው ከእግዚአብሔር ያግኙት”ይሉናል። ኤዲያ! እግዚአብሔር በአምሳያው የፈጠረን የምንችለውን አድርገን የማንችለውን ልንተውለት ነው። የምንችለውንም፣ የማንችለውንም ለሱ መተውማ ስንፍና ነው። የተጎዱት ያቃስታሉ። እንዴት ዝም እንላለን? ከመሀላችን አንዳችን ተጎዳን ማለት፣ ሁላችንም ተጎድተናል ማለት ነው። ነውሩን እራሱ ይደብቅ እንጂ እኔ ጫካ አይደለሁም የምደብቅለት። አልደብቅለትም። ያበጠው ይፈንዳ! ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።
Posted By.Dawit Demelash
Posted By.Dawit Demelash
Thursday, July 4, 2013
ወያኔ እያለ ሙሰኝነትን ማጥፋትም መዋጋትም አይቻልም!
የወየኔን ዘረኛ አምባገነን ስርዐት ከቀደሙት ስርአቶች ለየት የሚያደርገዉ ነገር ቢኖር ስርዐቱ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ፤ የትምህርት እድል እንዲሁም የስራና በኢኮኖሚ የመበልጸግ እድል የሚሰጠዉ “ወርቃማዉ ዘር” እያለ ለሚጠራዉ የራሱ ወገን መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ያለ የለለ ጥሪት ያለገደብ እንዲቦጠቡጡ የሙሰኝነቱን በር ወለል አድርጎ የከፈተዉም ለዚሁ “ወርቃማዉ ዘር” እያለ ለሚጠራዉ ወገን መሆኑም ጭምር ነዉ። ይህም ኢትዮጵያ ዉስጥ ሙሰኝነት የተፈቀደላቸዉና ያልተፈቀደላቸዉ ዜጎችና ተቋሞች እንዳሉ በግልጽ ያሳያል። በቅርቡ በዜና ማሰራጫዎች ሙሰኝነታቸዉ ተጋልጦ ታሰሩ እየተባለ የተነገረላቸዉ ግለሰቦች ወያኔ ከፈቀደላቸዉ በላይ በሙሰኝነት የከበሩ ወይም ከከፍተኛዎቹ የወያኔ ሹሞች ጋር የስልጣን ሽሚያ ዉስጥ የገቡ ግለሰቦች ዳውላዎች ናቸዉ።
ባለፈዉ ሳምንት ማብቃያ ላይ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች የሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በግልጽ እንደሚያሳየዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሙሰኝነት ላይ እንዲሰማራ ብቻ ሳይሆን የሙሰኝነቱን ዘርፍ እንዲመራ በህግ ያልተጻፈ ሀላፊነት ከተሰጠዉ ተቋም አንዱ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ነዉ። ባለፈዉ ሚያዚያ ወር የፌዴራሉ ዋና ኢዲተር መስሪያ ቤት ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኗል ብሎ በሪፖርቱ ካሰፈረዉ አምስት ቢሊዮን ብር ዉስጥ ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮኑ የመከላከያ ሚኒስትር መሆኑ የሚታወስ ነዉ። እዚህ ላይ አንድ የሚገርመን ነገር ቢኖር በቅርቡ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ አንደተናገሩት ከሆነ የኢትዮጵያ ፓርላማ “ሚስጥር ለመጠበቅ” በሚል ሽፋን በሙሰኝነት እንዳይጠየቅ ህግዊ ሽፋን የሚሰጥ አዋጅ በማርቀቅ ላይ የሚገኘዉ ይህንኑ በሙሰኝነት የተዘፈቀዉን የመከላከያ ሚኒስትርን ሆድ ለመደበቅ ነዉ።
ለመሆኑ ሀላፊነቱና የስራ ድርሻዉ አገርን ከዉጭ ጠላት መጠበቅ የሆነዉ የወያኔ መከላከያ ተቋም በንግድ፤ በእርሻ፤ በኮንስትራክሺንና በከባድ እንዱስትሪ ግንባታ የስራ መስኮች ዉስጥ ያለቦታዉ ተዘፍቆ እየታየ ለምን ይሆን የዚህ ተቋም የሂሳብ መዝገብ በኦዲትሮች እንዳይታይ የሚደነግግ አዋጅ እንዲወጣ ያስፈለገዉ? ለምንድነዉ ጠ/ሚኒስትር ተብዬዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት በኦዲተር አይመረመሩም ያሉት?
መልሱ ቀላልና ግልጽ ነዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዘናጋት ሙስናን አጠፋለሁ ብሎ የጀመረዉ የዉሸት ዘመቻ ያነጣጠረዉ የአገሪቱን የመከላከያ ተቋም ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩት የወያኔ ጄኔራሎች ላይ በመሆኑ ነዉ። ወያኔ የሾማቸዉ የራሱ ኦዲተሮች አመታዊ የሂሳብ ቁጥጥር ሪፖርት በግልጽ እንደሚያመለክተዉ ከፍተኛ የሂሳብ ጉድለትና የመዝገብ አያያዝ ዝርክርከነት የታየባቸዉ ወያኔያዊ ተቋሞች የመከላከያ ሚኒስቴር፤ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአገር ዉስጥ ደሀንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ ናቸዉ። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከህወሃት አለቆቹ በተሰጠዉ ቀጭን ትዕዛዝ መሠረት ወንጀላቸዉን ለመደበቅ ህጋዊ ድጋፋ እንዲያገኙ የሚጣጣረዉም ለእነዚሁ ሦስት ተቋሞች ነዉ። እነዚህ ህዝብን ሰላም የነሱ፤ የአገሪቱን ሀብት ሙልጭ አድርገዉ የዘረፉና ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ ስግብግበች የሞሉበትን ተቋም ጭራሽ ህግ ሽፋን ከተጠያቂነት ዉጭ ማድረግ የበለጠ እንዲዘርፉና በህዝብ ደም እንዲነግዱ ህገ መሰነግስታዊ እዉቅና መስጥት ነዉ።
ወያኔ ያሻዉን ያክል አስቀያሚ ገጽታዉን ሸፍኖ ለህዝብና ለአገር የሚያስብ መስሎ ለመታየት ቢሞክርም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንኳን ሙሰኝነትን የመሰለ በአይን የሚታይ ጉልህ የወያኔ መታወቂያ ቀርቶ ወያኔ ለወደፊት ለማድረግ በዕቅድ የያዘዉን ሁሉ ከወዲሁ የሚያዉቅ ህዝብ ስለሆነ ሙሰኝነትንና በስልጣን መባለግን ለማጥፋት የመጀመሪያዉ ትግል ከወያኔ ዘረኞች ጋር መሆኑን ተረድቶ ትግሉን ቀጥሏል። ይህ የተጀመረ ህዝባዊ ትግል ወያኔንና ሁለቱን መንታ ልጆቹን ማለትም ሙሰኝነትና ዘረኝነት ከአገራችን ምድር እስኪነቀሉ ድረስ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Tuesday, July 2, 2013
ኢትዮጵያውያኑ በአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ ለ30ኛ ዓመት እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል በአላሙዲ
ስፖንሰር የተደረገው በRFK ስታዲየም ዲሲ በተመሳሳይ ቀን ተጀምሯል። በሜሪላንዱ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ በሺዎች
የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የታደሙ ሲሆን አላሙዲ ስፖንሰር ባደረገው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ደግሞ ጥቂት የወያኔ/ኢሕ
አዴግን ሥርዓት የሚደግፉ ሰዎች ተገኝተዋል።
ይህን አላሙዲን ስፖንሰር ያደረገውን ዝግጅት በመቃወም በስታዲየሙ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ የዋሉት ኢትዮጵያውያን
“የአላሙዲ የደም ገንዘብ እይደልለንም” ሲሉ ተሰምተዋል።
አላሙዲ እጁን ከሰሜን አሜሪካው ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲያነሳ የጠየቁት ሰልፈኞቹ በተለይ አላሙዲ የስር ዓቱ ደጋፊ
በመሆኑ እርሱን ብቻ የሚጠቅም የኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ መዘርጋቱንም ሰልፈኞቹ በተቃውሟቸው አሰምተዋል።
ለ30 ዓመት የቆየውን ፌዴሬሽን ለመገንጠል አስበው ያልተሳካላቸውን አሁን በአላሙዲ ስፖንሰር የሚደረጉትን ግለሰቦች
ሰልፈኞቹ “ተጠያቂ ናችሁ” ሲሉ የተሰማ ሲሆን፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በኢትዮጵያ እየደረገ ያለውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት
በማስታወስ ከወያኔ ጋር ተባብረዋል ያሏቸውን ሰዎች ስም በመጥራት አውግዘዋቸዋል። አላሙዲ በኢትዮጵያ የወሰደውን የመሬት
ቅርሚትና በዚህም መሬት ላይ ያገኘውን ገንዘብ “የደም ገንዘብ” ሲሉ የገለጹት ሰልፈኞቹ በቀጣይም የተቃውሞ ሰልፍ
እንደሚያደርጉ ታውቋል።
በዋሽንግተን በአላሙዲ ስፖንሰርነት የተዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል በሰው እጥረት ድርቅ መመታቱን የታዘቡት አስተያየት
ሰጪዎች “አላሙዲ ከፍሎ ከሌላ ስቴት ያመጣቸው ሰዎች ሳይቀሩ የርሱን ፌስቲቫል በመተው ወደ ኢትዮጵያውያኑ የሜሪላንድ
ዝግጅት መምጣጣቸውን” ጠቁመዋል።
ከሲያትል በአላሙዲ ገንዘብ ሆቴልና የአየር ትኬት ተቆርጦልኝ ነው የመጣሁት ያለው አንድ አስተያየት ሰጪ “አላሙዲ
ከኢትዮጵያ የወሰደውን ገንዘብ በዚህ በኩል ላካክሰው በሚል ነው በነፃ ሲቆርጡልኝ እሺ ብዬ እዚህ ከመጣሁ በኋላ በሜሪላንዱ
የመክፈቻ ዝግጅት ላይ
የተገኘሁት” ሲል
ተናግሯል
Subscribe to:
Posts (Atom)
