Monday, December 2, 2013

በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በዝዋይ እና በአ.አ ማዕከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የ528 ፖለቲካ እስረኞችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ

Tuesday December 3rd 2013

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በዝዋይ እና በአዲስ አበባ ማ ዕከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ። ግንባሩ ባሰራጨው መረጃው በአሁኑ ወቅት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን አጋልጦ የ528ቱን ስም ይፋ አድርጓል። እነዚህ የፖለቲካ እስረኞች የተፈረደባቸውን ዓ.ም፣ አሁን በክስ ሂደት ላይ እንዳሉ፣ እንዲሁም ከየትኛው ብሔር ብሔረሰብ እንደመጡ ያሳወቀ ሲሆን የሕወሓት መንግስት እነዚህን የፖለቲካ እስረኞች በሽብርተኝነት መክሰሱን ተቃውሟል። የፖለቲካ እስረኞቹን ስም ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፦
PDF

   Posted By.Dawit Demelash





ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት የተደረገ ጽናታዊ ጉዞ፣ በሺዎች የሚቆጥሩ ተሳትፈዉበታል

December 2, 2013
የህወሃትን ማስፈራራትና ማፈራራት ችላ በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬ ገና ጎሕ ሳይቀድ ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተመሙ። የታሰሩትን የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችንና ሌሎችን የሕሊና እስረኞችን በመጠየቅ ህዝባዊ እንቢተኝነትንም አሳዩ።
Ethiopian Muslims on the way to Kilinto prison
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ሊፈርድባቸዉ እያቅማማ ቢሆንም ዛሬ በነቂስ የወጣው ህዝብ “ዋ!.. በነርሱ ላይ መፍረድ በኛ ላይ መፍረድ ማለት ነዉ” በማለት ሰላማዊ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል።
ህወሃት በነዚህ የሰላም አንባሳደሮች ላይ የረከሰ ፖለቲካዊ ፍርዱን በይኖ ለተለመደዉ የይቅርታ ፍጆታዉ ከዲያስፖራ ሰዎችን በመመልመል ቢኳትንም እራሱ በድሎ በስዉር ሽምግልና ይቅርታ ለማስጠይቅ የሚያደርገዉ ሙከራ በገሃድ ሲከሽፍበት ተስተዉሏል በሺዎች የሚቆጠሩ ዛሬ የድምጻችን ይሰማን ትእዛዝ ተከትለዉ “ዋ” ብለዉታልና!
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ምን ይላሉ?
“ጽናት ከደማችን የተቀላቀለ የማንነታችን ምስክር ነው!…ጽናት እኮ የማነነታችን ነጸብራቅ እንደሆነ ላለፉት ሁለት አመታት አሳይተናል።ለበደል ለጭቆናዉ ናዳ ናዳ በህብረ ድምጽ በቃልኪዳናዊ ቅላፄ በአንድ አምላካዊ ጎዳና ወደ ነፃነት እየተጓዝን “አሃዱን አሃድ” እንላለን ።ስቃይንም መከራንም ልክ እንደ ዉዱ የሐበሻ ልጅ ቢላል እንችላለን! ከስቃይንና መከራም በሗላም በስኬት ተምሳሊትነት እንደተዘከሩት የብርቅ ስብእና ባለቤቶች እንዘከራለን።
እናንት ከንቱ አንባገነናዉያን ሆይ!…ግድ የለም…አንባገነናዊ ክንዳቹ እስኪዝለፈለፍ ድረስ አሰቃዩን…መግረፍ፣መደብደብ፣ማሰርና መግደል ሲያቅታቹ እዉር ድንብራዊ መፈርጠጥን ትፈረጥጣላቹ። ዛሬ በቂልንጦ የጽናት ድምጽን አስተዉላችሗልን?ጽናታዊ ጉዞአችን ይቀጥላል…ልክ እንደቢላል ሁሉ “አሃዱን አሃድ!” የሚል ድምጽ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እያስተጋባ ነዉ እኮ!..ዋ!” ይላሉ ሚሊዮኖች ይህ የናንተዉ የኛዉ ድምጽ የሆነዉ ቢቢኤን ነዉ ሊንኩን በመጫን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ።ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
 Posted By.Dawit Demelash

Sunday, December 1, 2013

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ( የዕለቱ ዜና ዘገባ ) 01.12.2013


Posted By.Dawit Demelash

ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ  http://www.finote.org/Finot01_12_2013.mp3

የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ከሰራዊቱ ሊቀነሱ መሆኑ ታወቀ

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል፤ የሕወሃት ጄኔራሎች ፈርተዋል

ምንሊክሳልሳዊ-

በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳውን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የቀድሞ የኢሕዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንደሚቀነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየቀኑ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድን ተጠንቷል ባለው እና የተወያየበት ሰነድ እንደሚያመለክተው በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እና ከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆን ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊት ውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል ተነጋግሮበታል::
እነዚሁ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት የሰራዊቱ መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በመገናኘት የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲው እና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችን በማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት የቀረበው ሰነድ ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅ በመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተ በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል::በሙስና ከአስተዳደርዊ ባለስልጣናት በበለጠ የተዘፈቁት የሕወሓት ጄኔራሎች በስብሰባ እና አብዛኛው ንብረቶቻቸን በተዘዋዋሪ በመሸጥ ስራ ላይ እየተንቀሳቀሱ ሲገኝ በሱዳን በኢምሬት እና በአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በአሜሪካ በቤተሰቦቻቸው ስም የተለያዩ ንብረቶችን በመግዛት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮሽ ጨምረው ገልጼዋል::

  Posted By.Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10271