Thursday, October 1, 2015

ወያኔዎች ሂሳብ የምታወራርዱበት ግዜ መጣ!!!

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ
አንድ ድርጅት በአመት 2 ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ የድርጅቱን ጠቅላላ ሂሳብ ይፈትሻል ። ወጪው ምን ያህል ነው? ገቢውስ ምን ያህል ነው? ከወጪ ቀሪ  ምን ያህል አስገባ? እያለ ድርጅቱ ማትረፉን እና  ማክሰሩን ያውቅበታል። እንዲሁም ሃላፊ ቦታ ያሉትም ሰወች የሚገመገሙበት ነው። የታማኝነት ስራ፤የታማኝነት እድገት፤ የታማኝነት አገልግሎት፤ ለአገራችንም ይገባል።

ወያኔወች አገሪቱን ከተቆጣጠራቹሁበት  ግዜ ጀምሮ እንደፈለጋቹ ስትዘርፉ እንዳሻቹሁ ስታዙ ከርማቹሃል። ባንኮችን የሃገሪቷ ህግ ከሚያዘው ውጪ ቢሮአቹሁ ቁጭ ብላቹሁ በቀጭን ትእዛዝ ብቻ ወደ ውጪ አገር በምትሄዱበት ግዜ የፈለጋቹሁን  ያህል ዶላር በማን አለብኝነት  እየዘረፋቹ እንደሆነ  እናውቃለን። የህዝብ ንብረት የሆነውን ሁሉ  በመዝረፍ ለራሳቹሁ በጣም ብዙ ድርጅቶች እንደከፈታቹ  እናውቃለን። የህዝብ  ሃብት በመንጠቅ ትልልቅ ፎቆችንም እንደገነባቹ እናውቃለን።  በህዝብ ስም ከውጪ እርዳት በመለመን  እንዲሁም ለጋስ አገሮች ለህዝብ እንዲደርስ የሚሰጡትን የእርዳታ ገንዘብ   በልጆቻቹህ ስምና በተለያዩ  ስሞች በተለያዪ አለም አቀፍ ባንኮች እንደምታከማቹ እናውቃለን። አሁን ግን ግዜው ሂሳብ የምታወራርዱበት ግዜ ነውና ተዘጋጁ።

በዘረፋቹሁት የህዝብ ንብረት የተለያዩ  ድርጅቶችን  በስማቹሁ ከፍታቹሁ   የወያኔ  መንግስት ስልጣን ከያዘ በሃላ እንዚህን ሁሉ ድርጅቶች ተከፍቷል ብላቹ  ለኢትዮጵያ ለህዝብ እንደምትሰሩ ለማስመሰል የምትሞክሩትን እና የምትቀልዱትን ቀልድ መለወጥ አልተቻላቹሁም። ብዙ ህንጻወች ተሰርተው ከተሞች አድገዋል ብላቹ በናንተ ስምና በልጆቻቹ ስም እንዲሁም  ለሆዳቸው ሲሉ በሰገዱ ጥቅመኞች የተገነባ እንደሆነ  ስለምናውቅ ከተማዋ  ፎቅ በፎቅ ሆነች የምትሉትን ቀልድ  ሰሚ ጆሮ የለም። አሁን ግን እንዲዚህ አይነት የድናቁርት ወሬ የምንሰማበት ግዜው አልቋል እና ሂሳባቹሁን ልናወራርድላቹ ከዳር እስከዳር ተነስተን እየመጣንላቹሁ ነው ።

ልማት ላይ ነን እድገት ላይ ነን እያላቹሁ  በሕዝብ ስም የምታሾፉ ልማት ማለት እህል እንደማያውቅ አንበጣ በሁሉም የኢትዮጵያ ወሳኝ ቦታወች ላይ ሰፍራቹሁ መብላታቹሁን ነው ልማት የምትሉን ? ልማት ላይ ነን የምትሉን ብቃት ያላቸውን ሰራተኞች በማባረር የራሳቹሁን ደናቁርት  ካድሬን መሰግሰግ ነው ?  ልማት የምትሉን  አየር መንገዱን 90%፤ መከላከያ 95%  ፤ሚኒስትሮች 85%፤ ጉምሩክ 90% ፤ኢምግሬሽን 90% ፤አየር ሃይል 90% ፤የአገር ውስጥ ተቆጣጣሪ 90% ፤የውጪ  ንግድን ተቆጣጣሪ 90%፤ የስልጣኑን  ቦታ ይዛችሁት  አውቃቹሁ ወይም ቦታው መጥናቹህ ቢሆን መልካም ነበር  ነገር ግን ደናቁርቶች እራሳቹሁ ተደናቁረው ሌላውን የሚደናቁሩትን  ሰብስባቹ በበላይ መቀመጣቹሁን ነው ልማት የምትሉን ?  የትምህርት ውጤታቹህም  እንደዚሁ በ 90% ቢሆን ኖር ምነኛ ባማረ ነበረ ። እኛም የቀልድ ጊዜው  ማብቃቱን የወያኔ ደናቁርቶች የሚናገሩትን የምንሰማበት ሰዓት ማብቃቱን ነግረናቸሁ ሂሳባቹሁን ለማወራረድ ሰለመጣን ለዛ ተዘጋጁ።

ጊዜው ለወያኔዎች የምጥ ግዜ እንደሆነ እናውቃለን። ውስጣቸው በከፍተኛ  ሁኔታ መባላት ውስጥ እንዳሉም እናውቃለን። የዘረፉትን  የሕዝብ ሃብት ኪሳቸውን ሞልቶ  አስጨንቆአቸዋል። እንደዚህ እየዘረፉ እና ህዝቡን እየገደሉ ለሁል ግዜ ስልጣናቸው ላይ ተቀምጠው መኖርን ቢመኙም ይህንን ምኞታቸውን አጨልሞ ለኢትዮጵያን የብርሃን ጊዜ ሊያመጣ የሚችል እራይ ይዘው በአርበኞች ግንቦት ሰባት በሌሎችም የኢትዮጵያ  ታጋዮች በመዋህድ ከኤርትራ ምድር አልፎ  ከጫፍ እስከጫፍ  ባለችው ኢትዮጵያ  የትግሉ አላማ እና ትግሉን የማቀጣጠሉ ስራ  በሚገባ ተሰርቶ  ህዝባችን በሚገርም  ፍጥነት ወደ ትግሉ በመቀላቀል የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ የተነጠቀውንም ሰላም ለመመለስ  ወያኔ ላይ የሰላ ብረት ደግኖ ሂሳቡን ሊያወራርድ መጥቷል።

ይሄኔ ነው ወያኔ በሻንጣ ብር ይዘው መሰወር የጀመሩት። ያላቸውን ንብረት ወደተለያዩ የውጪ ባንኮች ማስገባት ልጆቻቸውንና የቅርብ ዘመዶቻቸውን በማሸሽ  እውን እነሱ እንዳሰቡት የኢትዮጵያንን  ሃብትና ንብረት ማሸሽ ይችላሉን ?

ትግሉ የተቀጣጠለው በአገር ቤትም በውጪም ነው ለውያኔዎች ውስጡም  እሳት ውጪውም እሳት ሆኖ ነው የሚጠብቃቸው።  የኢትዮጵያንን ሃብት ዘርፈው  የኢትዮጵያን ህዝብ ገድለው ወዴት ሊሰወሩ ወድዬትም መሰወር አይችሉም። በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ  ዘርፌ እና ገድዬ አመልጣለው  ብሎ ያሰበውን የወያኔ ሰወችን ነቅቶ  በመጠበቅ ላይ ነው። አሁን ሂሳብ የምታወራርዱበት  ስለሆነ በአለም ላይ ያሉት ባንኮች በሙሉ ከኢትዮጵያን  ህዝብ የተዘረፉ ንብረት መሆኑን በማሳወቅ አገርን ለማጥፋት ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ የሰራቹሁት ስራ ለአለም በማሳወቅ በይፋ የሚነገርበት  ግዜ ከፊታቹ በቆረጦቹ የኢትዮጵያ ልጆች ስለመጣ ሂሳባቹሁን  እናወራርዳለን።

1 የዘር ማጥፋት ወንጀል የሰራቹሁ ወንጀለኞች

2 አገሪቷን ለባእዳን ቆርሳቹሁ የሸጣቹሁ ወንጀለኞች

3 ዘርን ከዘር ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጠፋፋት የተነሳቹ ወንጀለኞች

4 ንጹሃንን በማሰር በማሰቃየት እስርና መከራ በማብዛት ወንጀል

5 የአገሪቷን ሃብት ያለአግባብ ለግል ጥቅማቹሁ በማዋል ወንጀል

6 ስልጣንን ለአፈና  ስራ በመጠቀም ወንጀል.

7 ስልጣንን አለአግባብ በማን አለብኝነት በቦታው ለማይመጥን ሰው በመስጠት ወንጀል
ኢትዮጵያኑን በማግለል  በመስሪያቤቱ የአንድ ብሄር ተናጋሪ ሰዎችን  ብቻ  በመቅጠር ወንጀል…… እያሉ የሰራቹሁትን ወንጀሎቻቹሁን የምናወራርድበት  ሰዓት አሁን ነው። የትም ማምለጥ የለም። የትም መደበቅም የለም። በሁላቹሁም በራፍ አንኳኩተን እንመጣለን። ያኔ ሂሳባቹሁን ታወራርዳላቹሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47069

No comments:

Post a Comment