Monday, July 11, 2016

ዜጎችን የመኖር ሕልውና እያሳጡ ልማት የለም። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን መበቀል ይቁም

ከዘጠና ሰባት ምርጫ በኋላ በኣዲስ ኣበባ ሕዝብ ላይ የበቀል ጎራዴውን የመዘዘው የሕወሓት ኣገዛዝ በኦሮሚያ ክልል የተነሳበት ተቃውሞ ለበለጠ በቀል ኣነሳስቶታል። ዜጎችን ሲፈናቀሉ ተለዋጭ ቤት ከመስጠት ይልቅ ከትግራይ ክልል ለሚመጡ የሕወሓት ኣባላት ኮንዶሚኒየም ቤት ከጦር መሳሪያ ምርቃት ጋር ይሰጣቸውል።የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በማለት የገበሬዎችን መሬት በመንጠቅ በኢኮኖሚ የበለጸጉ ጥቂት የሕወሓት ዘረኛ ጎጠኛ ቡድኖችን በኢንቨስትመት ስም ለማስፈር ያሰበው ኣላማ በኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ከሽፎ የተበተነበት ጎጠኛው ስርዓት አዲስ አበባን አለማለሁ በሚል ሰበብ የከተማውን ነዋሪ በማንገላታት በመግደል እና ሜዳ ላይ በማፍሰስ እያፈናቀለ መሆኑ በነዋሪው ዘንድ ከፍተና ቅሬታ ከመፍጠሩም ኣልፎ ስልታን ጠባቂ የሆኑ የኣገዛዙ ኣገልጋዮች በተፈጠሩ ግርግሮች መሃል መሞታቸው ይታወቃል። ይህ ለሕዝብ ያልቆመ ፖሊሲ ኣጽድቆ ለማስፈጸም መስራት ያመጣው ኣደገኛ ውጤት ነው።

የወያኔው ኣገዛዝ የኣዲስ ኣበባን ከተማ ሙሉ በሙሉ በሕወሓት ኣባላት እና ዘመዶቻቸው ቁጥጥር ስር በማዋል የኢኮኖሚ የበላይነት ለማግኘት እና ስልጣን ላይ ለመቆየት በሚያደርገው እያንዳንዱ እኩይ ተግባር ዜጎች የመኖር ሕልውና እንዲያጡ ከማድረጉም በላይ ለሕዝብ ያለን ንቀት በተደጋጋሚ እያሳየ ነው። ሰብዓዊነት በጎደለው እና በሕገወጥ መንገድ የኣገዛዙ ኣካላት ነዋሪዎች ከ30 እና 40 ኣመታት በላይ ከኖሩበት መኖሪያቸው ካለምንም ምትክ መኖሪያ ቤት በማፈናቀል የጎዳና ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ላይ ይገኛል። ተቆጣጣሪ ባሌላቸው የኣገዛዙ መስተዳደር ኣባላት እና ኣመራሮቻቸው ደካማ እና ያልበሰለ ኣመራር ችግር ፈጣሪነት በሕዝብ ላይ ከባድ ችግሮች መፈጠር ቀጥሏል።ለረዥም ኣመታቶች ከኖሩበት ቦታ ሕጋዊ ማስረጃ እና ሰነዶች እንዳላቸው ተረጋግጦ እያለ ተለዋጭ ቤት ለመስጠት ዛሬ ነገ እየተባለ ዜጎች እየተጉላሉ ሲሆን ከትግራይ ክልል ለሚመጡ የሕወሓት ኣባላት ግን የኮንዶምኒየም ቤቶች ከጦር መሳሪያ ምርቃት ጋር እየተከፋፈሉ እንደሚገኙ በየክፍለከተማው የሚገኙ ምንጮች ይገልጻሉ።


ከዘጠና ሰባት ምርጫ በኋላ በኣዲስ ኣበባ ሕዝብ ላይ የበቀል ጎራዴውን የመዘዘው የሕወሓት ኣገዛዝ በኦሮሚያ ክልል የተነሳበት ተቃውሞ የበለጠ በቀሉን እንዳጋለበት በተግባር የሚሰራው ክፋት ይመሰክራል።ዜጎችን የመኖር ሕልውና ኣሳጥቶ በላስኪት ቤት ያውም በክረምት ለበሽታና ሞት መዳረግ ልማት ኣይደለም፤የዜጎችን ሕልውና ያለገናዘበ ያልመዘነ ልማት በቀል እና ዘረፋ ነው።ይህ ሕዝብን የማያከብር ኣገዛዝ በተደጋጋሚ ያስመሰከረው ነገር ቢኖር የግፍ ብትሩን በዜጎች ላይ ማሳረፉን ማሳየቱ ብቻ ነው።የዜጎች ብሶት ኣሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የሕወሓት ኣገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ ዜጎች የመኖር ሕልውና ስለማያገኙ ሕዝብን በማደራጀት እና በማስተባበር ኣገዛዙን ማስወገድ ቀዳሚ ስራችን ሊሆን ይገባል።

http://www.satenaw.com/amharic/archives/17612

No comments:

Post a Comment