Sunday, October 2, 2016

ልጆቿን ያጣችው ቢሸፍቱም አለቀሰች !

* ተቃውሞን በጠመንጃ ለመግታት አይቻላችሁም
*
መግደል ይቁም !
ከረፋድ ጀምሮ የታዬ የተሰማው ሁሉ ሰቅጠጭ ግፍ ለማመን ያስቸገረኝ ግን የሆነ እውነት ነውለማመን ከቸገረኝ ካልኩት በተከታታይ ከደረሰኝ መረጃ እንዲህ የሚል ይገኝበታል ” …በዓሉ ከተጀመረበት ከጠዋት ጀምሮ የተቃዋሞ ድምጽ ነበር ፓሊስ አካባቢውን ከበበ ህዝብና ፖሊስ ገጠሙ አስለቃሽ ጭስ ወደኋላም ጥይት መተኮስ ጀመረ ህዝቡ ጭስና ጥይቱን ሲሸሽ በጥይት የተመታው ተመታ የሸሸው በግምት እስከ 10 ሜትር ድንጋያማ ገደል ውስጥ ከመውደቅ አላመለጠም …” በቦታው የነበሩ የአይን እማኝ ካካፈሉኝ መረጃ ቅንጫቢው ነው 

መንግሥት ላለፉት በርካታ አመታትና በተለይም በተከታታይ ወራት የህዝብን ድምጽ ለማፈንና ለማክሸፍ በወሰደው እርምጃ የታሰረ የቆሰለ የተሰደደውን ሳንቆጥር በሽህ የሚቆጠር የንጹሃን ዜጎች ነፍስ ተቀጥፏል ይህ ሁሉ እየሆነ ለእልቂቱ የሚሰጠው ስምየአሸባሪዎችሴራ የሚል ነው ዳሩ ግን በከባቢው እያሸበረ ያለው ጠመንጃ የታጠቀ የመንግስት ኃይል እንጅ ጣት የሚቀሰርባች አሸባሪዎች በከበቢው የሉም !

ከሁሉም የሚያሳዝነው እንዲህ እየገደሉ እስከ መቸ ሊገዙ እንደሚፈልጉ አለማወቃቸው ነው ! ከሁሉም የሚያሳዝነው የሚገድሉት ንጹህ ዜጋ ሚኒሶታ ሆኖ የተቃውሞውን መረጃ የሚያቀብለው የፖለቲካ ተንታኙ ጆሃር መሀመድ ጦር አድርጎ መገመታቸውና ማስነገራቸው ነው ከሁሉም የሚያስገርመው ከብርሃን ፍጥነት መረጃው እውነትን እያሳዬ መዋሸት መቅጠፋቸው ነው ! ከሁሉም የሚያሳዝነውየአስተዳደር በደል ፈጽመዋልእየተባለ የበደሉት ተቃወመ ብለው እያሳደዱ ያሳሰሩ የገደሉት በክበር ከስልጣን ገለል ሲደረጉ በእነሱ ጫማ እየተረገጠ የከረመው ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ማየት እጅግ ያማል  ጥይት ተቃውሞን አይገተውምና ዜጋው በመላ ሀገሪቱ በሚባል ሰፊ ይዞታ ተቃውሞውን እያጋጋለው መገኘቱ የሚያሳየው እውነታ በኃይል ድምጽን ማፈን አለማስቻሉን ግን ገዥዎች መማር አልቻሉም !

የንጹህ ዜጋን ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄ በጠመንጃ መመከት የመንግስትን ጭፍን አንባገነንነት ከማሳየትና ተቃውሞን ከማጎልበት ባለፈ ፋይዳ የለውም ! ዛሬ የቢሸፍቱ ተራ ሆኖ ቢሸፍቱ ልጆቿ በግፍ ተገድለው አልቅሳለች ትግሉን ግን ጭፍጨፋው እንደማያስቆመው ሳስብ በክፉ አንባገነን መሪዎቿ ሰርክ የምታነባዋ ሀገረ ኢትዮጵያ ታሰዝነኛለች እኛም ልጆችዋ እናሳዝናለን 🙁 ደሩ ግን የዚህ ሁሉ ንጹህ ደም ዋጋ የትንሳኤው ቀን ያቀርበው እንደሁ እንጅ አያርቀውም ! ፈጣሪ ሁሉንም ያያል ! ይፈርዳልም !

እጅግ በጣም ያሳዝናል ልብ ይሰብራል 🙁 በቢሸፍቱ ላለቁት ወገኖቸ የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው የሞቱትን ነፍስ ይማር 

http://www.satenaw.com/amharic/archives/22323


No comments:

Post a Comment