Friday, January 3, 2014

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች


ኢሳት ቲቪ በዛሬ ስርጭቱ እንደዘገበው በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች። ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎችን ከመኪና ላይ በማስወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል
“
እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።

ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

     https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11540

Thursday, January 2, 2014

የመቀለ ወጣቶች ከህወሓት መሪዎች ጋር ተጋጩ


የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)

አብርሃ ደስታ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው፦
ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 24, 2006 ዓም በኮብልስቶን ስራ የተሰማሩና (ለመሰማራት በማህበራት የተደራጁ) የመቀለ ወጣቶች በመቀለ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ተሰብስበው ነበር። የተሰበሰቡበት ምክንያት በጨረታ የተወዳደሩበት የኮብልስቶን ግንባታ መሰረዙ ሊነገራቸው ተብሎ ነበር።
ባለፈው ዓመት በኮብልስቶን ስራ የተሰማሩ ወጣቶች አብዛኞቹ መክሰራቸው ይታወሳል። የከሰሩበት ምክንያት ደግሞ ለኮብልስቶን ስራ ተብሎ ከዓለም ባንክ የተከኘ ገንዘብ በሐላፊዎች አለ አግባብ መመዝበሩ ነበር። የኮብልስቶን ገንዘብ የሰረቁ ባለስልጣናት መታሰራቸው ይታወሳል።
አሁን በወጣው ጨረታ መሰረት ግን ለስርቅ የሚሆን የሚተርፍ የኮብልስቶን ገንዘብ አይኖርም። በዚህ ምክንያት የህወሓት መሪዎች ጨረታው ለመሰረዝና ሌላ አዲስ ጨረታ ለመክፈት ወስነዋል። ወጣቶቹም የህወሓት መሪዎች የወሰዱት እርምጃ ክፉኛ ተቃውሞውታል። ወጣቶቹ ለጠየቁት ጥያቄ ተገቢ መልስ ባለመግኘታቸው ስብሰባው ረግጠው ወጥተዋል። የአደራሹ በር በመዝጋት ስብሰባው ረግጠው እንዳይወጡ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አልተሳካም።
ወጣቶቹ ነገ ጠዋት (ዓርብ) ወደ ክልል ቢሮ ተሰባስበው ይሄዳሉ። የክልል መንግስት መፍትሔ ካልሰጣቸው የተቃውሞ ሰልፍ እስከማድረግ ይደርሳሉ።
ይህ የኮብልስቶን ጉዳይ ባብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች ትልቅ አጀንዳ ሁኗል።

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11503

Wednesday, January 1, 2014

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ( የዕለቱ ዜና ዘገባ ) 01.01.2014

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ሊቀ ጳጳስ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ከአሜሪካ ሲመለሱ በደህንነት ቢሮ ለ 72 ሰዓት ታስረው ተፈቱ
አዜብ መስፍን ቁልቢ ክብረ በዓል ላይ ወጣቶችን አስደበደበች ሞባይል ቴሌፎናቸውንም አስነጠቀች
የወያኔ ካድሬ ጋዜጠኞች በ CPJ ላይ ዘመቱ የታሰሩትንም ጋዜጠኞች ወንጀለኞች አሉ
በደቡብ ኢትዬጵያ ዜጐችን በጅምላ ማሰሩ ደርቷል
ለደቡብ ሱዳን ውዝግብ ንግግር ሊጀመር ነው የሚሉ ናቸው ዝርዝር ዜናውን ሊንኩን  በመጫን ያዳምጡት http://www.finote.org/Finot01_01_2014.mp3 http://www.finote.org/Finot01_01_2014.mp3

    በማስከተልም ታሪክን የረሳ ስህተቱን ይደግማል በሚል የቀረበ  ፅሁፍ አስደምጠን  በመቀጠል  ድህረ መስከረም 1969 በሚል የቀረበ ፅሁፍ አስከትለን በመጨረሻም  አዕምሮ በለጠ ከአዲስ አበባ አንጃ ምንድን ነው የሚለውን አስደምጠን የፕሮግራማችን ፍፃሜ ይሆናል

   

የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል ፍትሃዊ ነው።


የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል ፍትሃዊ ነው። ትግላችን ስለጥንቱ ዘመን ሳይሆን ስለዛሬ እና ስለነገ ነው። ምንም እንኳን በታሪካችን ውስጥ ያለፉትን ሰቆቃዎች ተምረንባቸው ብናልፍም ወሳኙ ትግል ስለጥንት አባቶቻችን ታሪክ ሳይሆን ስለኛ ታሪክ ነው። ዋናው እና ወሳኙ ትግል ለልጆቿ እስር ቤት ስለሆነችው የዛሬዋ ኢትዮጵያና ለተተኪው ትውልድ በነጻነት እና በኩራት ልናወርስ ስለሚገባን የነገዋ አገራችን ጉዳይ ነው። ለመለውጥ የተነሳነው ያለፈውን ዘመን ሳይሆን የዛሬውን እና የወደፊቱን ታሪካችንን ነው። ኢትዮጵያ ዜጎቿ ሁሉ በሰላም፣ በኩልነት፣ በመከባበር እና በአንድነት የነጻነት አየር እየተነፈሱ የሚኖሩባት ምድር መሆን እንዳለባት ለነጻነት ሲሉ መስዋእት የሆኑት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፣ የታሰሩት፣ የተሰቃዩት የተሰደዱት ወገኖቻችን ሁሉ የሚያምኑት እውነታ ነው። ዋጋቢስ ጭቅጭቅና የዘር መከፋፈል በዋነኝነት የሚያሰራጩት ወያኔዎችና ቡችሎቻቸው መሆናቸውን በመገንዘብ አንድነታችንን አጠናክረን የበለጠ ተደራጅተን እና ተቀናጅተን ትግላችንን እናፋፍም። ድል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ!

  አበበ ገላው