Sunday, August 10, 2014

የወያኔ መንግስት ገድሎ ደብዛቸውን ላጠፋቸው ከፍተኛ የኢህአፓ አመራሮች የተዘጋጀ የፎቶ ኢግዚቪሽን። EPRPYL, Norway

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ


ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ

አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው


እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር

አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።


በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ

አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ


ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።


እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።

በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ


ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣


በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33334

Thursday, August 7, 2014

ታዋቂው ፖለቲከኛና መምህር ወጣት አብርሃ ደስታ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ አለ

Aug.7.2014
በአራዳ መጀመሪያ ፍ/ቤት ችሎት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይቀርባል ቢባልም ዘግይቶ 10 ሰዓት ከ25 ላይ ቀርቧል፡፡ ፖሊስ ሀምሌ 3 ቀን ፍ/ቤት ቀርቦ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በሽፋን ትሰራለህ በሚል በቁጥጥር ስር አድርጎ ለምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት የነበረ ሲሆን በ28 ቀን ውስጥም ምንም ማስረጃ ለችሎቱ አላቀረበም፡፡ በችሎቱ ላይ የአረና አመራር አቶ ካህሳይ፣የአብርሃ እህት በችሎቱ እንዲታደሙ ተፈቅዶላቸው ገብተዋል፡፡ አብርሃ ደስታ በእስርቤት የደረሰበትን ለችሎቱ ሲያስረዳ እያስገደዱ ቃል ተቀብለውኛል፣ ተደብድቤያለሁ፣ ከውጪ የመጡ የደህንነት ኃይሎች ምርመራ አድርገውብኛል፣ ጨለማ ቤት ለቀናቶች ነበርኩ፣ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ፣ የጨጓራ በሽተኛ ሆኜ በግድ እንጀራ እንድበላ ተደርጌያለሁ በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል ፡፡ ፖሊስ እነዚህ ድርጊቶች በፖሊስ ጣቢያው እንደማይደረጉና ማስረጃ የሌላቸው ውንጀላዎች ናቸው በማለት ያስተባበለ ሲሆን፣ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ደንበኛቸውን የሚመረምረውን መርማሪ ስም እንዲገለጽ ቢጠይቁም የመርማሪውን ስም አንናገርም ይዞ ፍ/ቤት የሚያቀርበውን ፖሊስ ስም ብቻ ነው የምንናገረው በማለት መልሰዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምርመራ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ ፍ/ቤቱ የ28 ቀን ቀጠሮውን ፈቅዶ ለነሐሴ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት እንዲቀርብ አዟል፡፡ የፍርድ ቤቱን ሂደት ለመከታተል አረና፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ፣የጌዴኦ የፓርቲ አመራሮችና አባሎቻቸው፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች በርካታ ሰዎች ተገኝተው አብርሃ ወደ ፍ/ቤት ግቢ በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ በጭብጨባና አይዞህ በማለት አጋርነታቸውን ሲገልጹ ብርሃ ደስታም አንገቱን ዝቅ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33307

Tuesday, August 5, 2014

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

"ኦባማ ዝምታው ይብቃ"
ethio usAugust 4, 2014 11:44

ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።
ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡
ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል – አምባሳደር ሺን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ ቤን ሮድስ ተናግረዋል፡፡
ሚስተር ሮድስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ ጉባዔውን አስመልክቶ ከትናንት በስተያ ምሽት ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት የአንድ ሰዓት የስልክ ቃለ-ምልልስ የመጭውን ሣምንት ጉባዔ ይዘትና አካሄድ አብራርተዋል፡፡
  በድምጽ የተጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ:: http://amharic.voanews.com/audio/Audio/441270.html
http://www.goolgule.com/ethiopians-rally-against-africa-us-summit/

Monday, August 4, 2014

በሁለት ካርቶን ታሽጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው ወርቅ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ትዕዛዝ እንዲወጣ መደረጉ ተዘገበ

Aug.4th,2014

በሁለት ካርቶን ታሽጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው ወርቅ በሳሞራ የኑስ ትዕዛዝ እንዲወጣ መደረጉን ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።
እንደዘገባው ከሆነ የጄኔራል ሳሞራ የኑስ እንደሆነ የሚጠረጠረው አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከአገር ሊወጣ ሲል ተይዞ የነበረ ቢሆንም በጄኔራሉ ትእዛዝ ከአገር እንዲወጣ መደረጉን የአየር መንገዱ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ በሁለት ካርቶን ታሽጎ በበረራ ቁጥር 600 እና 612 ወደ ዱባይ ሊሻገር ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅ በጊዜው ባለንብረቱ ተፈልገው ባለመገኘታቸው እንዲቆይ ቢደረግም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ቦታው ድረስ አሽከሮቹን በመላክ እንዲለቀቅ እና እንዲያልፍ/እንዲጫን የተደረገ መሆኑ ታውቋል።
ዘገባው ጨምሮም ይህ የሃገር ሃብት የሆነን ወርቅ የወያኔ ባለስልጣናት ካለምንም ገደብ በማሸሽ እና በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው በአፍሪካ ወርቅ ቤት ሽፋን እንዳልካቸው እና ዳንኤል በሚባሉ ስሞች በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት የወርቅ መጠን ከአገር በማስወጣት እና እንዲሁም የውጪ ወርቆችን ካለምንም የቀረጥ ክፍያ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ስራ ላይ መሰማራታቸው በተጨማሪም ሃገሪቷ የምታገኛቸው የውጪ ምንዛሬዎች በጥሬው እየታሸጉ ከሃገር እንደሚወጡ ታውቋል ሲል ጠቁሟል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33167