Sunday, August 10, 2014

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ


ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ

አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው


እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር

አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።


በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ

አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ


ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።


እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።

በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ


ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣


በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33334

No comments:

Post a Comment