Tuesday, January 27, 2015

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


ቀን፡ 01/26/2015
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።

የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።

በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don’t support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል::

እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን  ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።

ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን!

ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የወጣቶች ክፍል

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=38409

Sunday, January 25, 2015

ወያኔ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ



https://www.youtube.com/watch?v=qjs0LHqUy6o

የአንድነት አባላት ላይ የታጠቁ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰዋል፡፡


 በዛሬው ዕለት አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ሰልፈኞቹ ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ጽ/ቤት መንቀሳቀስ እንደጀመሩ በህወሃት/ኢህአዴግ የታጠቁ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ የአንድነት በርካታ አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!! ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ወደ ሀኪም ቤት ተወሰደው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡ ። ሴቶች እህቶቻችን እየተደበደቡም ብትፈልጉም ግደሉን እያሉ ወደ ፊት ለመሄድ እየተሞከረ ነው። እጅግ በጣም ጭካኔ የተሞላበት ፣ አረመኔያዊ ተግባር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ነው። 





http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17060





Saturday, January 24, 2015

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ የነገው የ “አንድነት” ሠልፍ እውቅና የለውም ብሏል

ፓርቲው ሠልፉን ከማካሄድ ወደ ኋላ እንደማይል አስታውቋል ፓርቲው በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት አጥቷል
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ነገ ሊያካሂደው ያቀደው ሠላማዊ ሠልፍ እውቅና እንደሌለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስታወቀ ሲሆን፤ ፓርቲው ሠልፉን ከማካሄድ ወደ ኋላ እንደማይል አስታውቋል፡፡ 

የከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ እነ አቶ በላይ ፍቃዱ የሚመሩት የአንድነት ቡድን “የሠላማዊ ሠልፍ መስፈርትን ስለማያሟሉ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አላገኘም” ብለዋል፡፡ ፓርቲው ሠልፉን የሚያካሄድባቸውን ቦታዎች በአግባቡ ባለመጥቀሱና በሠልፉ ላይ የሚንፀባረቁ መፈክሮች ባለማቅረቡ ሠልፉ እውቅና ማግኘት እንደማይችል ሃላፊው ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ሌላኛው የአንድነት ፓርቲ አመራር ቡድን የእነ አቶ በላይ ቡድን ሊያካሂድ ያሰበው ሠልፍ እንዳይፈቀድ የሚጠይቅ ማመልከቻ ተፈራርመው ለአስተዳደሩ ማስገባታቸውን ሃላፊው ጠቁመው፤ በነዚህ ምክንያቶች በከተማዋ የትኛውም አካባቢ ሰልፍ ማካሄድ እንደማይቻል አስገንዝቧል፡፡ 

በእነ አቶ በላይ ፍቃድ የሚመራው አንድነት፤ ነገ አካሂዳለሁ ብሎ ባቀደው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ፓርቲው ያልተከፋፈለና አንድ መሆኑን በመጠቆም ምርጫ ቦርድና ሚዲያዎች ፓርቲው እንደተከፋፈለ አድርገው የሚያቀርቡትን መረጃ በመቃወም አባላቱ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ ሲያስተላልፍ ሰንብቷል፡፡ 

ፓርቲው ሠላማዊ ሠልፉን ለማካሄድ ያሰበው አዲስ አበባን ጨምሮ በደብረማርቆስ፣ በጂንካ እና በሸዋሮቢት ከተሞች መሆኑን የጠቆሙት የፓርቲው አመራሮች፤ በአዲስ አበባ የሚካሄደው መነሻውን ቀበና ከሚገኘው የፓርቲው ፅ/ቤት በማድረግ፣ በፒያሳ በኩል በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት አደባባይ ላይ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ በከፍተኛው ፍ/ቤት የፍትሃ ብሄር ክስ ባለፈው አርብ ጥር 8 ቀን 2007 መመስረቱን ያስታወቀ ቢሆንም እስከ ትናንት ድረስ ክሱን ተቀብሎ የሚያስተናግደው ችሎት ማጣቱን የፓርቲው የህግ ባለሙያ አቶ ገበየሁ ይርዳው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በቦርዱ ላይ የቀረበው የፍትሃብሄር ክስ ምርጫ ቦርድ ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት እንዲቀበል፣ ጠቅላላ ጉባኤው የመረጠውን ፕሬዚዳንት ተቀብሎ እንዲያፀድቅ እንዲሁም የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ እንዲቀበል የሚጠይቅ እና ሚዲያዎች በፓርቲው ላይ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ በሩን የከፈተው ቦርዱ በመሆኑ፣ በጉዳዩ ላይ የማስተባበያ መግለጫ እንዲያወጣና ፓርቲው ሁለት ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠራ የደረሰበትን በመቶ ሺህ ብር የሚቆጠር  ኪሳራ ቦርዱ እንዲከፍል የሚጠይቅ መሆኑን ጠበቃው አስታውቀዋል፡፡ 

ባለፈው አርብ መዝገቡን የተቀበለው ችሎት፤ ለሃሙስ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በቀጠሮው እለት ጉዳዩን የመመልከት ስልጣን እንደሌለው ገልፆ መዝገቡን ወደ ሌላ ችሎት መምራቱን የጠቀሱት የህግ ባለሙያው አቶ ገበየሁ፤ ችሎቱ መዝገቡን እየተቀባበሉ የማየት ስልጣን የለንም የሚል ምላሽ እንደሰጧቸውና ክሱ ተቀባይነት ማጣቱን እንዳረጋገጡ አስታውቀዋል፡፡ 

በሌላ በኩል እነ አቶ በላይን ሲቃወሙ የነበሩትና ለብቻቸው ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው ነበር የተባሉት አቶ አየለ ስሜነህ ሃሙስ እለት ወደ ፓርቲው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=15517:%E1%8B%A8%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B0%E1%88%A9-%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%8C%88%E1%8B%8D-%E1%8B%A8-%E2%80%9C%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%90%E1%89%B5%E2%80%9D-%E1%88%A0%E1%88%8D%E1%8D%8D-%E1%8A%A5%E1%8B%8D%E1%89%85%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%8B%8D%E1%88%9D-%E1%89%A5%E1%88%8F%E1%88%8D&Itemid=101

Friday, January 23, 2015

አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል! አርማጭሆ ሆይ! ዛሬም እንደትላንቱ ከጎንህ ነን!


ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ !

የኢትዮጵያ ሃገርህና የህዝቦቿ ቀደምት ጠላቶች በተደጋጋሚ ያጠመዱብህን እኩዩን በዘር፣ በጎጥና፣ በመንደር የመከፋፈል ሴራ
በማክሸፍ በአንድነትህ አደባይተህ ወደ መጡበት እንደመለስካቸውና ህዝብህን ከውርደት፣ ሃገርህን ከጥፋት እንደታደግክ
ታሪክ ህያው ምስክር ነው፡፡

ዛሬም ባንዳውንና ተላላኪውን የህወሃት ዘራፊ ቡድን ሃገርህ ኢትዮጵያን ሲያፈርስ፣ ወደብና ድንበር አልባ ሲያደርግ፣ ህዝቦቿን
በዘር፣ በጎሳና፣ በጎጥ እየከፋፈለ ሲያተራምስና ሲያጫርስ እያየህ በድንዛዜ የምትቆዝምበት ጊዜ አይደለምና ዛሬ ነገ ሳትል
ለነፃነትህና ለአንድነትህ ቆርጠህ በመነሳት ታሪካዊ ጠላቶቹን በጀግንነት እየተፋለመ ከሚገኘው የጎንደር ህዝብ ጎን ዛሬውኑ
ተሰለፍ!

ጎንደር ሆይ !

ባንዳውና ተላላኪው የትግራይ ወራሪ ሃይል በአለፉት አስርት አመታት ለም መሬቶችህን ለመንጠቅ ተከዜ ድንበርህን በማን
አለብኝነትና በሃይል ተሻግሮ ከመጣ ወዲህ የወልቃይት፣ የጠገዴና፣ የጠለምት ዘርህ ላይ የፈፀመው የማጽዳትና በትግሪያዊነት
የመተካት ወንጀልና ግፍ እንዳለ ሆኖ፤ እነሆ ዛሬም እንደገና በእብሪት አርማጭሆ፣ መተማንና፣ ቋራን በመውረር ወደ ትግራይ
ለመጠቅለልና ዘርህንም በትግሪያዊነት ለመተካት እነሆ በእብሪት ዘምቶብሃል፡፡

ጀግንነት ማንነትህ ነውና ጨርቄን ማቄን ሳትል በጀግንነትና በፅናት እራሱን ከወረራ ለመከላከል እየተፋለመ ከሚገኘው
ከጀግናው የአርማጭሆና አካባቢው ማህበረሰብ ጎን በመሰለፍ ጠላትህ የሆነውን የትግራይ ወራሪ ሃይል በማንበርከክ ወገንህን
ከጥቃት፣ ሃገርህን ከጥፋት፣ ታሪክህን ከውርደት ትታደግ ዘንድ አደራችን ፅኑ ነው! 

የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወገናችን !

ለአለፉት አራት አስርት አመታት በባንዳውና በተላላኪው የህወሃት እኩይ ቡድን በተከፈተብህ ዕርስትህን፣ ማንነትህንና፣ ዘርህን
ከምድረ-ገፅ የማጥፋት ሁለገብ ዘመቻ ሳትበገር፤ ይልቁንም በገቡበት እየገባህ፣ በሚያሴሩበት እየደረስክ ባንዳዊ ተልዕኳቸውንና
እኩዩን የወረራና የመስፋፋት አባዜያቸውን በአንድትህ የመከትክበትና ያኮላሸህበት ታሪክህ ለትውልድና ለሃገር ታላቅ ኩራት

ሆኖ ለዘለዓለም ሲያበራ ይኖራል

እነሆ ዛሬም ድረስ እራሱን “የትግራይ ነፃ አውጭ” እያለ የሚጠራው የባንዳዎችና የዘራፊዎች ቡድን እንደ ጌቶቹ ወደ
ማይቀርለት የወራሪዎችና የከሃዲያን ታሪካዊ መቃብር ከመውረዱ በፊት በጣረሞት ላይ የምትገኘውን እንጥፍጣፊ እኩይ
እስትንፋሱን አሰባስቦ የአጥፍቶ መጥፋት መርዙን በወገንህ ላይ ሊረጭ በመቃተት ላይ ይገኛል፡፡

ይልቁንም ዛሬ ደጀንህን የአርማጭሆንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ማንነቱን ለማጥፋትና በትግሪያዊነት ለመተካት ከፍተኛ የሆነ
ሁለገብ ወረራ ተፈፅሞበታል፡፡ በተለይም ይህ ከትግራይ የዘመተው ወራሪ ሃይል በባዕዳን የወረራ ዘመን እንኳን ታይቶ
በማይታወቅ ሁኔታ አካባቢውን እያመሰ ይገኛል፡፡

አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል ነውና! በቀደመው ማንነትህና አኩሪ ታሪከህ ላይ በፅናትና በአንድነት በመቆም፣ ጠላቶችህ
በደገሱልህ የጎጠኝነትና የመንደርተኝነት ወጥመድ ሳትጠለፍ፣ ይልቁንም በአንድነትህና በኢትዮጵያዊ ማንነትህ እየታገዝክ እኩይ
ሴራቸውን እየበጣጠስክ፣ ዛሬ ነገ ሳትል በህብረት በመነሳት ታላቅና ታሪካዊ ተጋድሎን እያደረገ ከሚገኘው የአርማጭሆና
አካባቢው ወገንህ ጎን በመሰለፍ ጥንተ ጠላትህን ዛሬም እንደ ትላንቱ ታደባዬው ዘንድ ታሪካዊ ጥሪ አቅርበንልሃል!

እኛም በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምንገኝ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ተወላጆች ዛሬም እንደ ትላንቱ በአንድነትና በፅናት
ከጎንህ መሰለፋችንን ስናረጋግጥልህ በታላቅ ኩራት ነው !

ድል ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች !


ታህሳስ 2007 ዓ.ም

http://ethiolion.com/Pdf/01092015Support_Armacheho.pdf



Monday, January 19, 2015

ወከባ፣እስር፣እና፣ ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም ።

ይህ የተገፋ ህዝብ እንዳጎነበሰ አይኖርም ቀና ያለ እለት !!! ወህኒ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም!!

ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያልተመዘገቡ ህገወጥ እና አሸባሪ ከሆኑ የተወነጀሉበት ተቀባይነት ያለው ክራይቴሪያ ይነገረን እና እናውግዘው:: አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄያቸው ግልጽ እና ግልጽ ነው ካልሆነ የሚዋከቡበት ምክንያት የለም ካለ ይነገረን እና እናውግዝ ተደጋጋሚ ጸሎት አንፈልግም መንግስታዊ አሸባሪነትን እያወገዝን ወያኔን በትእግስት እየጠበቅነት ነው ይህ ያበጠ ነገር የፈነዳ እለት ወዮላቹ…የምትገቡበት አታገኙም:: እንደ ደርግ ባለስልጣናት ወህኒ አንወሽቃችሁም:: ወህኒ እኮ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም::

መፈክር እና ባንድራ ይዞ የወጣን የህዝብ ጥያቄ ያነገቡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን እና ደጋፊዎችን ማዋከብ እንዲሁም ባዶ እጁን ሙስላያ ይዞ ወደ መስኪድ የሚተመውን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ማዋከብ እና ማሰር ማፈስ ከሽብር ተለይቶ አይታይም:: ይህ የሕወሓት ደባ የያዘውን ወታደር እና መሳሪያ ተማምኖ መንግስታዊ ሽብር በዜጎች ላይ ፈጥራል:: ይህንን መንግስታዊ ሽብር እያንዳንዳችን ልናወግዘው ይገባል::

ለይስሙላ በወረቀት የታተመው የሃገሪቱ የበላይ ህግ ተብየው ህገ መንግስት በየት ቦታ በየትኛው አገር በየትኛው ቀን እና ሰአት በእነማ እየተተረጎመ እንደሆን ግልጽ ሊሆንልን አልቻለም እንደዜጋ የሃገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለን እስከተነሳን ድረስ አቤቱታችን ሊታይ ይገባዋል:: አሸባሪ የሆኑ ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል::


ህገመንግስታዊ መብቶችን የተጠቀሙ ግለሰቦች ካለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወደ እስር ቤት መወርወር የት ነን ያለነው ወዴትስ እያመራን ነው የሚል ጥያቄዎች ደጋግመን እንድናነሳ አስገድዶናል:: ችግር ካለ ይነገረን እና አስፈላጊውን እርምጃ መንግስት ቢወስድ እንስማማለን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ወረቀት ይዘው ነው ለነጻነት የዘመቱት ይህም የሚያሳድድ የሚያዋክብ ከሆነ በህገመንግስቱ ውስጥ ይካተት እና የነጻነት ጥያቄው ይቆማል:: ወገናችን ቀላል እና ሊመለስ የሚችል ጥያቄዎችን ይዞ ነው የተነሳው ይህም የሚያስገድል የሚያዋክብ የሚያሳስር ከሆነ የዜጎች መብት በህግ አግባብ ይገደብ እና ነጻነት ፈላጊው ህዝብ ዜግነት አልባ ሆኖ ይሰደድ:: ወከባ እና እስር በህገመንግስቱ እውቅና ይሰጣቸው ይህ ካልሆነ ወያኔ ህጎችን ይሰርዝልን::

የህዝቦች ጥያቄ ማለት ለወያኔ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚተረጎም አልተረዳንም ስልጣንን ለማራዘም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የባለስልጣናት እርስ በእርስ አለመነባበብ የሚያስከትሉት ግድፈቶች በሃገር እና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላሉ:: በወከባ እና በእስር ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም:: የማይነጋ መስሏት…….እንዳይሆን ነገን ለሃገር እና ለህዝብ እናስብ…ድንጋይ እየቆለሉ ይኸው ፎቅ ሰራንልህ.. በብድር እየተከናነቡ መንገድ አሰራንልህ …. ወዘተ ቢባል ይህ ህዝብ ቅድሚያ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ነጻነት ይፈልጋል እና በጥሞና እና በአትኩሮት ሊታይለት ይገባል::
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/16967

Saturday, January 17, 2015

ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና እየፈጸመ እንደሆነ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ።

የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል ከካድሬዎቹም ህዝቡን እያስፈራሩ በግድ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያደረጉ ነው።
በግድ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑና ኢህአዴግን እንዲመርጡ እየተገደዱ መሆናቸውንም የገለጹ በርካቶች ናቸው። ከዚህም በላይ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ኢህአዴግ አንዳንድ ሰዎችን ያለፍላጎታቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ጫና በመፍጠር ለሱ እንዲሰሩለት በማስጠንቀቅ በየምርጫ ጣቢያው በገለልተኛ ስም ማስቀመጡ የተጋለጠ ሲሆን፤ ሰዎቹ-ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ቢቀርብላቸው የሚል ምላሽ ይሰጡ ዘንድ መመሪያ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።

በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል። ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም በባህርዳር ከተማ የኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መድረክ አባላት – በስርዓቱ አገልጋዮች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ታፍነው ከተወሰዱት የመድረክ አባላት መካከል፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የታፈኑበት ምክንያትም ሆነ ፤ያሉበት ስፍራ እስካሁን ድረስ አልታወቀም።

እንዲሁም ” ኢቲቪ ውሸታም ነው ፣ ኢህአዴግ ሌባ ነው”ብለሀል ተብሎ ክስ የተመሰረተበትና የሶስት ዓመት እስራት የተፈረደበት የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን፤ በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባና ግርፋት እየተፈጸመበት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። የደቡብ ወሎ የመኢአድ አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን ፍርደኛ እስረኛ ሆኖ ከድብደባና ግርፋት ማረፍ አለመቻሉ፤ በኢትዮጰያ እስር ቤቶች ለሚፈጸሙ የከፉ ሰብ ዓዊ መብት ጥሰቶች አንድ ማሳያ ነው ብለዋል-መረጃውን ያደረሱን የመኢአድ አባል።

ከሰሞኑ ብቻ ብቻ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አባላት የፐጻርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ወደቤታቸው ሲያቀኑ መደብደባቸው እና በወላይታ የሰማያዊ ፓርቲ አስተረባባሪዎች መታሰራቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ፓርቲና የኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች ላይ በተለይም በሰማያዊ፣ በአንድነትና በ መ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ የሚፈጽሙትን ዛቻና በደል እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት በመቻላቸው ስጋት የተፈጠረበት ገዥው ፓርቲ – ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን በመጥቀስ፤<> ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው-ገዥው ፓርቲ -በፓርቲዎቹ ላይ እየፈጸመ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድመረ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፤ አሳስበዋል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38155