በመከላከያ ደረጃ አየተካሄደ ባለው የሰባት ዓመት ኮንትራት ውል የማስፈረምና የማደስ ተግባር በሰራዊቱ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የሰራዊቱ አዛዦች ውጥረት ውስጥ ገብተዋል::በተለያዩ ግምባሮችን ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል በፌርማቸው ኣንዲያረጋግጡ ቢጠይቁም ፈቃደኛ ሆነው አልተገኙም ። በሁኔታው የተደናገጡ የሰራዊቱ አዛዦች ኮንትራቱን የፈረመ ወታደር በሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ዳርፉር ይላካል ፥ የርቀት ትምህርት እድል ይሰጠዋል፥ የሞያ ስልጠና ቅድሚያ እንዲያገኝ ይደረጋል ወዘተ በሚል የማይተገበር መደለያ በማደናገር ለማታለል እየሞከሩ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል::በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወታደሮች በውትድርና ሞያ እንዲቀጥሉ በኢህአዴግ ስርዓት እየተደረገባቸው ያለን ጫና በመቃወም ክፍላቸውን ጥለው በመጥፋት ላይ ናቸው ። በአማካይ ሲታይ ከአንድ ሃይል ከ 22 እስከ 23 ወታደሮች ኮንትራቱን የማደስ ውል በመቃወም እንደጠፉ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል::
No comments:
Post a Comment