ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ በደቡብ ኢትዮጵያ በነገሌ ቦረና ከከተማው ስም ስያሜ ጋር በተያያዘ በጉጂ እና በቦረና ማህበረሰቦች መካከል በነገሌ ቦረና አካባቢ በተነሳ ግጭት ከ30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን እና ግጭቱም አለመቆሙን የአከባቢው ባለስልጣናት ምንጮች ማምሻውን በላኩልን መረጃ ገለጹ። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ በአከባቢው የተነሳው ግጭት በመስፋፋት ከፍተኛ የሆነ ንብረት ያወደመ ከመሆኑም በላይ ከነገሌ ከተማ ውጪ ለጉላ እና አርዶታ በተባሉ አከባቢዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ መቀጠሉ ታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ ግዛቴ ግጭቱ ዘልቆ ሊገባ ይሽላል በሚል ፍራቻ ኬንያ ወታደሮቿን በድንበር አከባቢ አስፍራል እያስጠበቀች መሆኑ ታውቋል።
የኢሕአዴግ ፌዴራል ፖሊሶች እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶች በቦታው ደርሰው የነበረ ቢሆንም የአከባቢው ህብረተሰብ ቀየውን በመልቀቅ እየተሰደደ መሆኑን ታውቋል። በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውና የጎሳ ፌዴራሊስም ፖለቲካ ውጤት የሆነው ይህ ግጭት በአካባቢው ባለስልጣናት እና የሃገር ሽማግሌዎች ለመፍታት ቢሞከርም ሳይሳካ ግጭቱ እንደቀጠለ ታውቋል።
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13976