Sunday, March 16, 2014

የስርዓቱ ደጋፊ የሆነችው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ ለሁለተኛ ጊዜ ከአሜሪካ አፍራ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች

በአፍቃሬ ወያኔነቷ የምትታወቀው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ አዲስ አልበሟን ለማስመረቅና የተለየያዩ ኮንሰርቶችን ለመሥራት ወደሰሜን አሜሪካ መጥታ የነበረ ቢሆንም በደረሰባት ቦይኮት በተመልካች እጦትና በፕሮሞተሮች መጥፋት አፍራ ወደ አዲስ አበባ መመለሷ ታወቀ።


በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊ መብት ጥሶትና ንጹሃንን በእስር ቤት ያሰቃያል እየተባለ በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የሚነገርለትን የወያኔ/ኢሕአዴግ ስርዓት በመደገፍ የምትታወቀው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶ በቨርጂኒያ ክሪስታል ከተማ በሂልተን ሆቴል የሲዲ ማስመረቂያ ኮንሰርት አዘጋጅታ 55 ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን አንድም አርቲስት በሲዲ ምርቃቱ ላይ አለመገኘቱ አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በርካታ አርቲስቶች የሚገኙ እንደመሆኑ መጠን በሃመልማል አባተ ሲዲ ምርቃት ኮንሰርት ላይ አንድም አርቲስት አለመገኘቱ ኢቢኤስ የተባለው ቲቪ ሳይቀር እንዳስገረመው በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።


(ሃመልማል በዲሲ አዘጋጅታቸው የነበረውና በተመልካች ድርቅ የተመታው የሲዲ ምርቃት ኮንሰርት ፍላየር ይህ ነበር)

ሃመልማል በወያኔ/ኢህአዴግ እየተረገጠ ያለውን ሰፊውን ሕዝብን ክዳ ለመሬት ቀሚው፣ ለመሬት ሻጩ፣ ለበዝባዡ፣ ለጨፍጫፊውና ለሰብአዊ መብት ረጋጩ ወያኔ ተቆርቋሪ ሆና በመቅረቧ ከጥቂት ዓመታት በፊት` በጀርመን ሃገር የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅታ ሕዝቡ ቦይኮት በማድረጉ 18 ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን 3 አመት በፊትም እንዲሁ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት ኮንሰርት አዘጋጅታ 12 ያነሰ ሰው ብቻ በመገኘት በተመልካች ድርቅ ተመትታ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች፤ ያሉት የመረጃ ምንጮች ሃመልማል ከስርዓቱ ጋር ያላት የጥቅም ግንኙነት የተረሳላት መስሎ ወደ አሜሪካ በድጋሚ ብትመጣም በዋሽንግተን ዲሲ 55 ሰዎች ተግኝተው አሳፍረዋታል። በዲሲ ኮንሰርት ሲዘጋጅ እስከ 5 ሺህ ሰው እንደሚገባ ልብ ይሏል።

ሃመልማል በዳላስ ከተማ በፋሲል ደመወዝ ስም በመጠቀም፤ (ሕዝቡ የፋሲል ደመውዝ አድናቂ በመሆኑና እርሱን ተከትሎ በመግባቱ) በኮንሰርቱ ላይ ቁጥሩ ጨመር ያለ ሰው ቢገባም በሎስ አንጀለስ ከተማ የቀድሞ ባለቤቷ እና የልጇ አባት በሚያስተዳድረው ሮዝሊን የሲዲ ምርቃትና ኮንሰርት ብታዘጋጅም በተመሳሳይ ቦይኮት ተደርጋ በተመልካች ድርቅ ተመትታለች። በዚህም ሞራሏ የተሰበረው ሃመልማል ከስህተቷ ተምራ ወደ ሕዝብ ከመመለስ ይልቅ ወደ ሃገር ቤት በመመለስ ነገሩን ለማብረድ ብትሞክርም እንዲህ ያለው ቦይኮትና በየከተማው ያሉ ፕሮሞተሮች ያለመጋበዝ ትግል ታግዞበት ወደ ሃገሯ ልትመለስ በቅታለች።
ዲያስፖራው ከወያኔ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ድምጻዊያንን ቦይኮት ማድረጉ የሚያስመሰግን ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ይህ ጉዳይ በርትቶ ሊቀጥል እንደሚገባው አስታውቀዋል። እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ አርቲስቶች በሃገር ቤት ከወያኔ ጋር በመሞዳሞድ የሚያገኙት ጥቅም ውጭ ሲመጡ ሊያገኙ አይገባም ይላሉ። ዲያስፖራው ሃገሩን የሚያከብረውን አርቲስት እንደሚያክብረው ሁሉ ከወያኔ ጋር ለሆዱ ያደረውን ድምጻዊም በማግለል ተመልካች አልባ ማድረግ እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ከሃመልማል አባተ ውጭ ነዋይ ደበበ፣ ሰለሞን ተካልኝና የመሳሰሉት ድምጻዊያን በዲያስፖራው ኪሳራ እንደደረሰባቸው ይታወሳል።

 https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13614

No comments:

Post a Comment