Saturday, August 1, 2015

የሕወሓት መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉት በርካታ ወጣቶችን አፍሶ ወደ አልታወቀ ቦታ ወሰደ


በሰሜን እና በደቡብ በተከፈተበት ወታደራዊ ጥቃት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው የሕወሓት መንግስት ከትናንት ማማሻውን ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ሲያፍስ መዋሉ ተዘገበ::

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከ4 ሺህ የማያንሱ የአዲስ አበባ ወጣቶች በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ታፍሰዋል:: አንዳንድ የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ከሆነ የታፈሱት ወጣቶች በአብዛኛው ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉት ናቸው:: በተለይም የአርበኞች ግንቦት 7ን ጥቃት ተከትሎ እነዚሁ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ ለለውጥ ሊነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት ይህ አፈሳ እንደተካሄደ ይነገራል::


እነዚህ ወጣቶች መገናኛ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ስፍራ ውስጥ ታጉረው ከቆዩ በኋላ ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶቡሶች ተጭነው መወሰዳቸውን የጠቆሙት የዜና ምንጮች ወደየት እንደተወሰዱ ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45501

No comments:

Post a Comment