Friday, February 12, 2016

” ዲሞክራሲ -101″…”መካሪ አያሳጣህ!” ተጳፈ ለሀይሌ ገ/ስላሴ – በኤርምያስ ለገሰ

                    ኤርምያስ ለገሰ

 ተፃፈ ለሀይሌ /ስላሴ

ይቺን አጭር ፅሁፍ ለመጫር የገፋፋኝ በዛሬው እለት አትሌት ሐይሌ ለአንድ የውጭ ሚዲያ የሰጠውን አስተያየት በማዳመጤ ምክንያት ነው። አላማዬ ሐይሌ የተናገረውን ሁሉ ለመቃወም አይደለም። ወይም አንዳንድልወደድ ባይ ደካማሰዎች እንደሚያስቡት አትሌቱ የተጐናፀፈውን ዝና ለማጉደፍ አስቤ አይደለም።

ለእኔም ሆነ ለመላው ኢትዬጲያውያን ሐይሌ በአለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያዊ አርማችን ነው። አርማን ማቆሸሽ ደግሞ ሐገርን ከመክዳት የሚተናነስ አይደለም። ሀይሌ የማይቻል የሚመስል ነገርን በአለም አቀፍ መድረክ እንደሚቻል ያሳየልን በአርአያነት የምናወድሰው ብሔራዊ ሃብታችን ነው። ሐይሌ ሃይላችን ነው። በስደት አለም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ሀገራችንን ጠይቀውን ማወቅ ከተሳናቸው ለማስረዳት ከምናነሳቸው ብርቅዬ ስሞች አንዱ ሐይሌ /ሥላሴ የሚለውን ነው።
ይሔ ማለት ግን አትሌት ሐይሌ ተራራ የሚያካክሉ ስህተቶችን እየሰራ እያየን እና እያዳመጥን ዝምታን እንመርጣለን ማለት አይደለም። አንፃራዊ ትምህርት እና ንቃት የሚጠይቅ ቦታ ላይ እየገባአላዋቂ ሳሚሲሆን በአርምሞ አንመለከተውም አካፋን አካፋ ማለት ይኖርብናል አስተውሎ ለተመለከተው የሀይሌ መውረድ የእኛም መውረድ ነው፣የሀይሌ አልቦነት የእኛም አልቦነት ነው፣የሀይሌ መካሪ ማጣት ሀገሪቷ አዋቂ ሽማግሌ የላትም ወይ የሚያስብል ነው። እንደዚህ አይነት ግድፈቶች በእንጭጩ ካልተስተካከሉ ደግሞ ውርደቱ ከግለሰብ ተሻግሮ አገራዊ ይሆናል። አይበለውና አትሌቱ አሁን የሰጠውን አስተያየትየአውሮፓ ህብረትስብሰባ ላይ በእንግድነት ተገኝቶ ቢናገረው ምን ይውጠን ነበር?…በማርቲን ሉተር ኪንግ ግዛት የሆነችው አትላንታ ተገኝቶ የደሰኮራት ቢሆን ምን ያህል ያሸማቅቀን ነበር?…
( ወግን ወግ አነሳውና አንድ ነገር ትዝ አለኝ ወጉን ያጫወቱኝ በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ናቸው። በተመሳሳይ መንገድ እንደራሴ የማምነው የኢሳት ባልደረባም በቦታው በአካል ተገኝቶ ስለነበር ይህንኑ አውገቶኛል።
እንዲህ ነበር የሆነው፣
በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ክብር ለሚገባው ክብር ለመስጠት ሰፊ ፕሮግራም ያዘጋጃሉ። ከእነዚህ ታላቅ ኢትዬጲያውያን መካከል አትሌት ሐይሌ /ሥላሴ ይገኝበታል። ፕሮግራሙ ሲጀመር ከነሙሉ ክብሩ ወደ መድረክ የተጠራው አትሌት ሐይሌ ሙቀቱ በፈጠረለት ወኔ ተነሳስቶ ታሪካዊ ንግግር አደረገ። ንግግሩ በከፍተኛ ጭብጨባ በመታጀቡ ሐይሌ ማቆም አልቻለም። በማሳረጊያውም በረጅሙ ተንፍሶኢትዬጲያ ብሆን ይሔን አልናገርም ነበር፣ የሚደርስብኝን ስለማውቅ !” በማለት ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ለሕዝቡ በቁጭት አስረዳ ።በድጋሚ ከአዳራሹ የተሰማው ጭብጨባ፣ ፊሽካና ሳቅ ከአትላንታ ተነስቶ፣ አትላንቲክን አቋርጦ የሚኒሊክ ቤተመንግሥት ተሰማ።)
ወደቀደመው ጉዳያችን ስንመለስ አትሌት ሐይሌ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚፎርሸው በምን ምክንያት ነው?… የሚናገረውን ነገር በጥልቀት ያውቀዋል ወይ?…ከጀርባ ሌሎች ምክንያቶች ይኖሩት ይሆን?…ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች ማቅረብ ተገቢ ይሆናል። በእኔ እምነት አምስት መሰረታዊ ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል፣
1• ” የእውነተኛ ዲሞክራሲንትርጉም ያለማወቅ
2• የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ማጠንጠኛየእውነተኛ ዲሞክራሲ እጦትመሆኑን ያለመገንዘብ
3• “ፓለቲካ ሳይንስም ጥበብምመሆኑን ያለማወቅ
4• ለከት የለሽ የሀብት ማሰባሰብ ፍላጐት እና
5• አገዛዙ የደረሰበት ( በድብቅ ሳያውቅ ያስፈፀመው) ከባድ ወንጀል መኖር
ለዚህ አጭር ማስታወሻ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ነጥቦች ላይ ትዝብቴን ማስፈር እፈልጋለሁ
1• “የእውነተኛ ዲሞክራሲንትርጉም ያለማወቅ
እንኳን ለሀይሌ የተለያዩ የፓለቲካል ኢኮኖሚ መጵሀፍቶችን ላገላበጡ ምሁራን የዴሞክራሲ ትርጉም ግልፅ አይደለም። በቃሉ ትርጉም መግባባት ሳይደረስዲሞክራሲ ያስፈልጋል /አያስፈልግም?…አለ ወይስ የለም? ” በሚለው እሰጣገባ ውስጥ የተገባበት አጋጣሚዎች አሉ። በዛ ላይዲሞክራሲየሚለው ቃል እንደ ቃልኪዳን ቀለበት የስም ማስጌጫ ጣቱ ላይ ያላጠለቀ አለመገኘት ትርጓሜውን አደናጋሪ ያደርገዋል። እስቲ ይታያችሁ ባለፋት ሁለት ወራት 150 በላይ ኢትዬጲያውያንን በጠራራ ፀሐይ የገደለው ህውሀት የለበሰውኢሕአዴግየሚባል ጭምብል በውስጡዲሞክራሲየሚል ቃል አለው።
ስለዚህ እንደ አትሌት ሐይሌ ያሉ ሰዎች በትርጉም እና አስፈላጊነት ላይ ተደናግረው ብንመለከት ሊገርመን አይገባም። አብዛኛውን ጊዜ እነ ሐይሌ አዲስ እውቀት የሚጨምሩት በቃላት ትርጉም ላይ ልሂቃን እና ድርጅቶች ተስማምተው ተመሳሳይ ንግግር ሲናገሩ ካዳመጡ ብቻ ነው። ድፍረት ባይሆንብኝ የእነ ሐይሌ የእውቀት መጨበጫ ስልቱ በአይን የሚታይ የተግባር እንቅስቃሴ እንጂ በንባብ እና ምርመራ የሚገኝ አይደለም
በንባብ የሚገኝ ቢሆንማ ኖሮ አንጋፋው ፕሮፌሰር መስፍንዴሞክራሲ ወይም ስልጣነ ሕዝብ ምንድነው? ” በሚለው ፅሁፋቸው ያሰፈሩትን በመመልከት ብቻ ግንዛቤ መጨበጥ በተቻለ ነበር። ፕሮፌሰር እንዲህ ይላሉ
ዴሞክራሲ ማለት የስልጣን ባለቤት ሕዝብ የሆነበት ስርአት ማለት ነው። መነሻው እና መድረሻው ይህ የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ነው። የሥልጣን ኮርቻው ላይ መውጣትም ሆነ ከዚያ ኮርቻ ላይ መውረድ የሚቻለው በሕዝብ ፍቃድ ብቻ ነውበማለት ይገልፁታል።
ፕሮፌሰሩ የዲሞክራሲን ትርጉም ብቻ አልሰጡንም። ዲሞክራሲን በራሳቸው መነጵር ሲመለከቱት ምን እንደሚሰማቸው እንደሚከተለው ገልጸዋል
እኔ ዴሞክራሲን የማየው ምንግዜም ደማቅ ብርሐን ያለበት ለጥ ያለ ሜዳ ላይ እንደተንጣለለና መጨረሻው እንደማይታይ ጥሩ የአስፋልት መንገድ ነው። ቁም ነገሩ እዚያ መንገድ ውስጥ መግባቱ ነው። ብርሃኑ ማንኛውንም ነገር አጋልጦ የሚያሳይ ሲሆን ለጥ ያለው የአስፓልት መንገድ ደግሞ እንደልብ የሚያስጋልብ ነው።
2• የኢትዬጲያ ችግር ማጠንጠኛየዲሞክራሲ እጦትመሆኑን ያለመረዳት
ዛሬ አገራችን ኢትዬጲያ የምትገኝበት ሁኔታ ከመቼውም በባሰ አስቸጋሪ ሆኗል። በተለይም ባለፏት ሩብ ምዕተ አመት በኢትየጵያ ህዝብ ላይ ተንሰራፍቶ የተቀመጠው አገዛዝ ሀገራችን የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ውስጥ እንድትገባ አድርጓል። ስርአቱ በዚህ መልኩ ከቀጠለ እና ስር ነቀል ለውጥ ካልመጣ ይቺ በነጥቆ በራሪ ( roving bandits) የተወረወረች ምስኪን ሀገር ወዴት ልታመራ እንደምትችል መገመት አያዳግትም።
ከአንድ ሳምንት በፊት የአርበኞች ግንቦት ሰባት /መንበር በአሜሪካ ሀገር ሜሪላንድ ግዛት ለህዝብ ንግግር ሲያደርግ ተገኝቼ ነበር። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባደረገው ንግግር ሀገራችን የገባችበት አዘቅት መሰረታዊ ምንጩዲሞክራሲያዊ ስርአትባለመኖሩ እንደሆነ በቀይ ብእር አስምሮበታል። የሕዝብ ከመኖሪያው መፈናቀል፣ የህዝቡ በስርአቱ መማረር፣ የመንግስት በህዝብ ተቀባይነት ማጣት፣ አድሎአዊ የሆነ ስርአት መስፈን፣ የወጣቶች ስደት፣ ረሐብ እና የኢኮኖሚ ድቀት መንስኤው የእውነተኛ ዲሞክራሲ አለመኖሮ መሆኑን አስረድቷል። የሟሸሸና ጭንጋፍ መንግሥት ባለበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ሊመጣ እንደማይችል አስገንዝቧል በዚህ አባባል ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ
ርግጥም ፕሮፌሰሩ እንደተገለፀው በኢትየጵያእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአትእስካልመጣ ድረስ የህግ የበላይነት ሊሰፍን አይችልም። ፀረ ዲሞክራሲ ዙፋኑን በጨበጠበት ሁኔታ ሁሉም ዜጐች በኢትዬጲያዊነታቸው ብቻ በህግ ፊት እኩል የማይታዩበት የዜግነት መብታቸው በተግባር የማይረጋገጥበት ሁኔታ ይፈጠራል። ተፈጥሯልም።
ዛሬ በህዝቦች መካከል በታቀደ መልኩ ጥርጣሬ እና ጥላቻ እንዲሰፍን እየተደረገ ነው። የወጣቱ የወደፊት ተስፋ ጨልሞ ስደትን እንደ አማራጭ ወስዷል። በጥቂት የሞራል ድህነት እና የበታችነት ስሜት በተጠናወታቸው ጠባብ ዘረኞች ሀገራችን ወደ መቀመቅ እየተገፋች ነው። የዜጐች የመናገር፣ የመጳፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መሰረታዊ መብቶች 50 አመቱን ” Golden Jubuilee” እያከበረ ካለው የኢቲቪ መስኮት ውጭ ማየት አልተቻለም።
3• “ፓለቲካ ሳይንስም ጥበብምመሆኑን ያለመገንዘብ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ኦፍ ኬኔዲ በበርካታ ድንቅ ንግግራቸው ይታወቃሉ። በተለይምፓለቲካ ጥበብ (አርት) እና ሙያያውም የተከበረ ሙያ ነውበማለት አጠንክረው መግለጳቸው በብዙዎች ይታወሳል። ታዲያ ይህን ባህርዩን የተከበረ ሙያ እና ላቅ ያለ ማህበራዊ ሳይንስ መሆኑን ባለማወቅ አንዳንድ እንደ ሐይሌ ያሉ ታላላቅ ሰዎችአዳፋ ቃላትንሲናገሩ ይደመጣል።
ክፋቱ ደግሞ የሚናገሩት ከሕዝብ ፊት ስለሆነ ከንፈራቸው ተከፍቶ ሳይዘጋ ጉዳቱ በራሳቸው ላይ ይደርሳል።
እናም አትሌት ሐይሌ ፓለቲካና የዲሞክራሲ ጵንሰ ሐሳብ መረዳት በማለዳ ተነስቶ ” 84 ኪሎ ሜትር ልሩጥእንደ ማለት የቂል ድፍረት አይደለም። የአገር እና ህዝብን ሁለንተናዊ ሕይወት የሚመለከት እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል የህልውና ጥያቄ ነው። የእውነተኛ ዲሞክራሲ መስፈን እና ያለመስፈን ጥያቄ በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ የገባችበትን ቀውስ የመሻገር አሊያም ላታንሰራራ የመውደቅ ነው!!

http://www.satenaw.com/amharic/archives/12710


No comments:

Post a Comment