Friday, February 19, 2016

በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና በጉደር ዛሬ ብቻ 16 ሰዎች ተገደሉ በምስራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ ዛሬም ሕዝብ ከአጋዚ ጦር ጋር ተፋጧል

        የአጋዚ ጦር በነቀምት (Photo)

(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ አካባቢ በምትገኘው አባሮ መንደር የአጋዚ ጦር 4 ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደሉ ተሰማ:: የሕዝቡ ተቃውሞ በምስራቅ ሐረርጌ የተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች እንደቀጠለ ነው::

በምስራቅ ሐረርጌ በጉራዋ ወረዳ በጨፌ ጃናታ መንደር በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ የአጋዚ ጦር በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ማቁሰሉን ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል::

በምስራቅ ወለጋ ነቀምት በተነሳ የህዝብ ቁጣም የአጋዚ ሠራዊት እንዲሁ በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ያጠቃ ሲሆን ወጣት ሴቶች ሳይቀሩ የአጋዚ ጥይት ሰለባዎች መሆናቸውን ምንጮች ዘግበዋል:: የነቀምት ከተማ ሄልሜት በለበሱና ሙሉ የጦር መሳሪያ በታጠቁ የአጋዚ ሠራዊት የተከበበች ሲሆን በከተማዋ ለሚነሱ ጥቃቅን ጥያቄዎች ሁሉ ጥይት ምላሽ እንደሆነ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ዛሬ ሻሸመኔ አቅራቢያ በምትገኘ አባሮ መንደር በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ ፌደራሎች 4 ወታቶችን መግደላቸው ሲገለጽ በኮፋሌ እና አካባቢዋ ደግሞ 12 ሰዎች መገደላቸውና ከ20 በላይስ ሰዎች በጥይት ክፉኛ መቁሰላቸው ተዘግቧል::


በተለይ ዛሬ በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና በጉደር አካባቢዎች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን የሚገልጹት ምንጮች የሕዝቡም ቁጣም በዚያው ልክ እንደቀጠለ ገልጸዋል:: በተለይ በነቀምት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት የሆኑ ወታደሮች ሳይቀሩ በአጋዚ ሰራዊት በጥይት መቁሰላቸው ተሰምቷል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51251

No comments:

Post a Comment