Wednesday, March 9, 2016
ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው – ከትግራይ ህዝብ አጓጉዞሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል
“ህወሓት መሬታችንን እንጂ እኛን አይፈልገንም” የሚሉት
የወልቃይት ነዋሪዎች ዛሬ ዛሬ የሚፈፀምባቸው መከራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትቷል፡፡ ግፍና በደሉ ምድሪቷን አጥለቅልቋል፡፡ ቁጥር
ስፍር የሌላቸው ሰዎች በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በስውር እየተገደሉ ነው፡፡ የህወሓቶች
ሰፋፊ እስር ቤቶች በወልቃይት ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል፡፡
የወልቃይት ህዝብ ይህ ሁሉ መከራ፣ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመበት የሚገኘው
“ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” በማለቱ ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ ለመፍታት ያቋቋመው ኮሚቴ
አባላት በህወሓት እየተሳደዱ ነው፡፡ አቶ በለጠ ታደሰ እና አቶ ማሩ ሽፋ የተባሉት የኮሚቴው አባላት የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም
በደህንነቶች ታፍነው “የህዝቡን ሃሳብ አስቀይራችሁ ትግሬ ነኝ እንዲል ካላደረጋችሁ በስተቀር በምድር ላይ አትኖሩም…” የሚል ማስጠንቀቂያ
ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡ ከየካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ኮሚቴዎች የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ ከአካባቢው
ተሰውረዋል፡፡

Friday, March 4, 2016
በአዲስ አበባ በኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ ሲደረግ ዋለ
(የቢቢኤን ራድዮ ዘገባ) የሙስሊሞችን የእምነት ነፃነት መብት በሃይል
እና በአፈ ሙዝ ረግጦ እየቀማ ያለው ኢሓዴግ መራሹ መንግስት በዛሬው እለት በአዲስ አበባው በኒ መስጅድ ተቃውሞ ሊደረግ ይችላል
በሚል ስጋት እና ጥርጣሬ በመስጅዱ መግቢያና አካባቢ በርካታ ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ ሙስሊሞችን በፍተሻ እያዋከበ እንደነበር
ምንጮቻችን ገልፀዋል ።
እንደምንጮቻችን ተጨማሪ ገለፃ መሰረትም ባለፉት ግዜያት በአንዋር እና ፍልውሃ መስጅዶች በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ያደረበት መንግስት ይሄው ተቃውሞ ዛሬ በበኒ መስጅድ ሊደገም ይችላል በማለት እና በመስጋት ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ በሙስሊሙ ላይ ለየት ያለ ፍተሻና ወከባ መፈፀሙ ታውቆ በተለይም መስጅዱ ሞልቶባቸው ውጭ ላይ መስገጃ አንጥፈው ለመስገድ የሞከሩ ሙስሊሞችን ውጭ ላይ አንጥፋችሁ መስገድ አይችሉም በማለት ፓሊሶችና ካድሬዎች ወከባ ሲፈፅሙ እንደነበር ተዘግቧል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው ጅሙዓ የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ሃገራችን ሰላም ናት መንግሥታችንም ጥሩ ነው በአራቱም አቅጣጫ ምንም ችግር የለም ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚውም አድጋለች የህዝቦች መብት ተከብሯል በማለት በግልፅ የፓለቲካ ቅስቀሳ ተልዕኮውን መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን በተለይም የመብት ጠያቂዎችን ” ነውጠኞች ” እና “የሃገር ሰላም የማይፈልጉ “በማለት እና በመፈረጅ መናገሩን ምንጮች ለቢቢኤን ገልፀዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51769
እንደምንጮቻችን ተጨማሪ ገለፃ መሰረትም ባለፉት ግዜያት በአንዋር እና ፍልውሃ መስጅዶች በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ያደረበት መንግስት ይሄው ተቃውሞ ዛሬ በበኒ መስጅድ ሊደገም ይችላል በማለት እና በመስጋት ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ በሙስሊሙ ላይ ለየት ያለ ፍተሻና ወከባ መፈፀሙ ታውቆ በተለይም መስጅዱ ሞልቶባቸው ውጭ ላይ መስገጃ አንጥፈው ለመስገድ የሞከሩ ሙስሊሞችን ውጭ ላይ አንጥፋችሁ መስገድ አይችሉም በማለት ፓሊሶችና ካድሬዎች ወከባ ሲፈፅሙ እንደነበር ተዘግቧል
ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው ጅሙዓ የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ሃገራችን ሰላም ናት መንግሥታችንም ጥሩ ነው በአራቱም አቅጣጫ ምንም ችግር የለም ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚውም አድጋለች የህዝቦች መብት ተከብሯል በማለት በግልፅ የፓለቲካ ቅስቀሳ ተልዕኮውን መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን በተለይም የመብት ጠያቂዎችን ” ነውጠኞች ” እና “የሃገር ሰላም የማይፈልጉ “በማለት እና በመፈረጅ መናገሩን ምንጮች ለቢቢኤን ገልፀዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51769
Subscribe to:
Posts (Atom)