Friday, March 4, 2016

በአዲስ አበባ በኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ ሲደረግ ዋለ

(የቢቢኤን ራድዮ ዘገባ) የሙስሊሞችን የእምነት ነፃነት መብት በሃይል እና በአፈ ሙዝ ረግጦ እየቀማ ያለው ኢሓዴግ መራሹ መንግስት በዛሬው እለት በአዲስ አበባው በኒ መስጅድ ተቃውሞ ሊደረግ ይችላል በሚል ስጋት እና ጥርጣሬ በመስጅዱ መግቢያና አካባቢ በርካታ ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ ሙስሊሞችን በፍተሻ እያዋከበ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ።

እንደምንጮቻችን ተጨማሪ ገለፃ መሰረትም ባለፉት ግዜያት በአንዋር እና ፍልውሃ መስጅዶች በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ያደረበት መንግስት ይሄው ተቃውሞ ዛሬ በበኒ መስጅድ ሊደገም ይችላል በማለት እና በመስጋት ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ በሙስሊሙ ላይ ለየት ያለ ፍተሻና ወከባ መፈፀሙ ታውቆ በተለይም መስጅዱ ሞልቶባቸው ውጭ ላይ መስገጃ አንጥፈው ለመስገድ የሞከሩ ሙስሊሞችን ውጭ ላይ አንጥፋችሁ መስገድ አይችሉም በማለት ፓሊሶችና ካድሬዎች ወከባ ሲፈፅሙ እንደነበር ተዘግቧል 



ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው ጅሙዓ የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ሃገራችን ሰላም ናት መንግሥታችንም ጥሩ ነው በአራቱም አቅጣጫ ምንም ችግር የለም ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚውም አድጋለች የህዝቦች መብት ተከብሯል በማለት በግልፅ የፓለቲካ ቅስቀሳ ተልዕኮውን መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን በተለይም የመብት ጠያቂዎችን ” ነውጠኞች ” እና “የሃገር ሰላም የማይፈልጉ “በማለት እና በመፈረጅ መናገሩን ምንጮች ለቢቢኤን ገልፀዋል 


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51769

No comments:

Post a Comment