Wednesday, March 9, 2016

ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው – ከትግራይ ህዝብ አጓጉዞሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል

“ህወሓት መሬታችንን እንጂ እኛን አይፈልገንም” የሚሉት የወልቃይት ነዋሪዎች ዛሬ ዛሬ የሚፈፀምባቸው መከራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትቷል፡፡ ግፍና በደሉ ምድሪቷን አጥለቅልቋል፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በስውር እየተገደሉ ነው፡፡ የህወሓቶች ሰፋፊ እስር ቤቶች በወልቃይት ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል፡፡

የወልቃይት ህዝብ ይህ ሁሉ መከራ፣ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመበት የሚገኘው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” በማለቱ ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ ለመፍታት ያቋቋመው ኮሚቴ አባላት በህወሓት እየተሳደዱ ነው፡፡ አቶ በለጠ ታደሰ እና አቶ ማሩ ሽፋ የተባሉት የኮሚቴው አባላት የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍነው “የህዝቡን ሃሳብ አስቀይራችሁ ትግሬ ነኝ እንዲል ካላደረጋችሁ በስተቀር በምድር ላይ አትኖሩም…” የሚል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡ ከየካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ኮሚቴዎች የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡

የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማፈን የህወሓት ቡድን ከግድያው፣ አፈና እና እስሩ ባሻገር የተለያዩ ሸፍጦችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ምድር ላይ በአራት ሰፈራ ጣቢያዎች ለማስፈር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በሁመራ እና በሌሎች የወልቃይት ከተሞች የሚገኙትን ሆቴሎች፣ ህንፃዎችና የንግድ ቦታዎች የስርዓቱ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዲከራዩዋቸው እየተደረገ ነው፡፡

በመሆኑም ወልቃይቶች ትዕግስታቸው እንደተሟጠጠና ጠብመንጃቸውን በመወልወል ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ “በግንቦትና ሰኔ አንዱ ይለያል” በማለት ቆርጠው መነሳታቸው ተሰምቷል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51936

1 comment:

  1. please unit Ethiopian people for this bastard TPLF measure.
    This is not regional idea to be Tigre Or Amhara rather getting justices in their natural home!!!!

    ReplyDelete