ዕኩለ ቀን ላይ አልፎ አልፎ ይሰማ የነበረው የተኩስ ድምጽ በአሁን ሰዓት ቁሟል(9:20) በጥዋት የጀመረው አፈሳ ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል። በከተማዋ ውስጥ በዋናነት አፈሳ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ቀበሌ 18 ኮለኔል ደመቀ ሰፈር፣ ልደታ፣ብልኮ ፣ ፋሲል፣ አራዳ፣ 09፣ 10፣ 11 ቀበሌ፣ ዕርቅ ቤት፣04 ና05 ቀበሌ በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።
በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ከመጠን በላይ እስረኞችን እያጎሩ ይገኛል።ፖሊስ ጣቢያዎቹ በመሙላታቸው የተነሳ ብልኮ አካባቢ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ.ቤት ግቢ ውስጥ ባለ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ከ1350 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ታጉረው ይገኛሉ። እነዚህ ወጣቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የታሰሩና ቅዳሜና ዕሁድ የተቀላቀሏቸው ተጨማሪ ወጣቶች እንዳሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለእነዚህ እስረኞች ከሰኞ ጀምሮ ቤተሰብ በቀን አንድ ግዜ ምግብ የሚያቀብል ሲሆን፤ፖሊስ ምርመራ አልጀመረም።የውሃ እጥረትና የንጽህና ችግር እንዳጋጠማቸው የሚናገሩት የግፍ እስረኞች በአዳራሹ ውስጥ የትግል መዝሙሮችን ሲዘምሩ ይሰማሉ። ”አትነሳም ወይ ይሄ ባንዴራ ያንተ አይደለም ወይ?” የሚለው ዘመን ተሻጋሪ የትግል መዝሙር የግፍ እስረኞቹ በየዕለቱ ይዘምሩታል።ህዝብን አስሮ የጨረሰ አገዛዝ አይተን አናውቅም።መፍትሄው የግፍ እስረኞችን መልቀቅ ብቻ ሳይሆን ሥልጣንን ለህዝብ መመለስ ነው።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/64091
No comments:
Post a Comment