የትግራይ ነጻ
አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል። “ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላል” በሚሉና “አንመልስም”
ሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።
አባይ
ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል
ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።
በሌላ ዜና
በህወሃት ውስጥ “ወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው” በሚሉና “ሊመለስ
አይገባም” በሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።
“ወልቃይትን እንመልስ”
ባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ። “ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል? ውርደት
ነው” በሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።
እንደ ዘጋቢያችን
መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩት “አንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።
“ወልቃይት የኖሩት
ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።
በዚህ ሁለት
ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።
ህወሃት ለረጅም
ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ
እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡
http://www.goolgule.com/tplf-discussing-to-give-back-wolkait/
No comments:
Post a Comment