Tuesday, August 6, 2013

በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም

በዋቤ መስጊድ ማን ቦንብ አፈነዳ? ለምን?

kofelie


ባለፈው ዓርብ በመላው አገሪቱ አንድ ወጥ የ”ድምጻችን ይሰማ” የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት የወጣውን መርሃ ግብር ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ እስከ ግድያ ሊደርስ የሚችል ርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የሚያመላክት መግለጫ አውጥቶ ነበር። የድምጻችን ይሰማ አመራር መሆናቸውን የሚገልጹት ክፍሎች ፌደራል ፖሊስ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ተቃውሞው እንዲቀር መመሪያ ማስተላለፋቸውን ይናገራሉ። በዋቤ መስጊድ ቦንብ ያፈነዳው ማን ነው? ለምን እንዲፈነዳ ተደረገ?
ፖሊስ በከረሩ ቃላቶችና በማስጠንቀቂያ አጅቦ ባወጣው መግለጫ  ” … አክራሪ ወሃቢ ሰለፊዎች ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረጉ ፖሊስ ለሚወስደው ርምጃ ተገቢውንና የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን” በማለት አስፈራርቶ ነበር። “ምንደኛ፣ ከውጪ በሚላክላቸው ንዋይ ዓይናቸው ታውሮ አርብ በመጣ ቁጥር በተመረጡ መስጊዶች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ …” በማለት በመግለጫው አስቀድሞ እንደፎከከረው በኮፈሌ ብቻ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት መድረሱ ተረጋግጧል።
አስፈላጊውን ድርጊት መርሃ ግብርና የተቃውሞ ደንብ በማስተዋወቅ ከአዲስ አበባ ለአሜሪካ ሬዲዮ መግለጫ የሰጡት አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳሉት አቶ መለስ በህይወት እያሉ በ1997 ተቃዋሚዎች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ከሰጡት ትዕዛዝ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መግለጫ በመተላለፉ ተቃውሞው እንዲቀር ተደርጓል።
ሰላማዊ የተባለውን ተቃውሞ ከማከናወን ቢቆጠቡም ከአርብ የጁምአ ስግድት አስቀድሞ በየቤቱ በመዘዋወርና በሰላማዊ መንገድ የአምልኮ ስርአታቸውን ለመፈጸም ወደ ተለያዩ መስጊዶች ካቀኑ ምዕመናን መካከል ቀላል ቁጥር የሌላቸው ታስረዋል። ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የድምጻችን ይሰማ ተወካይ ካንድ ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን አመልክተዋል።
ከመንግስትና የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪ ነን ከሚሉት አካላት የሚወጡትን መረጃዎች ሁለት ጽንፍ የያዙ በመሆናቸው በማጣራትና አግባብነት ያለው ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት የዝግጅት ክፍላችን ተቸግሯል። በዚህም የተነሳ የተሟላ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት እንዳለ ሆኖ ባብዛኛው ዘገባችን ከማህበራዊ ገጽ በሚገኙ ዜናዎችና ከመንግስት ድረገጾች እንዲሁም ከአሜሪካ ሬዲዮ ባገኘነው መረጃ የተወሰነ ሆኗል።
በኦፊሴል በማይገለጹ አድራሻዎች፣ በፌስቡክ፣ በተለያዩ የማህበራዊ አምዶችና ድረገጾች በየአቅጣጫው የሚወጡ ዘገባዎች እንዳሉ ሆነው፣ የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ መረጃ የሚሰጠው “ደምጻችን ይሰማ” የማህበራዊ ገጽ በምዕራብ አርሲ ኮፈሌ ልዩ ስሙ ዋቤ በሚባል ቦታ የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በወሰዱት ርምጃ የሟቾችን ብዛት አስራ አንድ እንደደረሰ አስታውቋል። ዘገባው ከሞቱት መካከል አንድ ህጻንና ሴት ይገኙበታል ብሏል።
የሲኤንኤን የአይን ሪፖርተር ደግሞ በተመሳሳይ ቀን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች 25 ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን አስነብቧል። ዜናው ከ1500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ያመለከተ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል አንድ ህጻን አንደሚገኝ የአይን እማኙን በመግለጽ አመልክቷል።
የአሜሪካ ሬዲዮ ዘጋቢ የአካባቢውን ነዋሪዎች በምንጭነት ጠቅሶ እንደዘገበው ሀምሌ 26 ቀን 2005 ዓ ም የተከሰተው ግጭት መንስዓው በዋቤ መስጊድ ፖሊስ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ተከትሎ ነው። ህዝቡ የፖሊስን ድርጊት እየተቃወመ ሳለ በድንገት ቦምብ መፈንዳቱን ዘገባው አመልክቷል። ቦንቡን ከህዝብ ወገን የሆኑ እንዳላፈነዱትና ቦምቡ እንደፈነዳ ፖሊስ ጥይት በመተኮስ ሰዎችን መግደሉን ያስታወቀው የቪኦኤ ዘጋቢ፣ አስራ ሁለት የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል። የስድስቱን ሟቾች ስም ዝርዝር አስታውቋል። 1ኛ፣ ቱርኬ ሳቶ 2ኛ፣ መሐመድ ሃሰን 3ኛ፣ ሌንጮ 4ኛ፣ ኩርሴ ቱራ 5ኛ፣ ረሺድ ቡርቃ፣ 6ኛ፣ ሳፊ ቴሲሳ በየተራ ዘርዝሯል። ቦንብ ማፈንዳቱ ለምን እንደተፈለገ ዝርዝር መግለጫ አልተሰጠበትም።
በኮፈሌ የደረሰውን አደጋ አስመልክቶ ውስን ሪፖርት ያቀረበውና የመንግስትን አካላትን ለማነጋገር እንዳልቻለ ያመለከተው ይኽው ዘገባ፣ በስተመጨረሻ አገኘሁት ባለው ዘገባ መሰረት የቁስለኞች ቁጥር ሰላሳ አምስት መድረሱን ዘግቧል። መንግሥት ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ከማስታወቁ በስተቀር ተጨማሪ ያለው ነገር የለም። ከዚህ በተቃራኒ “የሙስሊሙ ህብረተሰብ አክራሪዎች የፈጸሙትን ድርጊት ተቃወሙ” የሚል ዜና አሰምቷል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሻሸመኔ ፖሊስ ዘንድ ደጋግሞ በመደወል የተጣራ መረጃ ማግኘት ባይችልም  የሟቾቹ ቁጥር መንግስት እንዳለው ሶስት ሳይሆን ዘጠኝ እንደሚደርስ ስማቸውን ካልገለጹ የፖሊስ አባል መረጃ አግኝቷል። አባሉ ይህ መረጃ በአርሲ ኮፈሌና አካባቢው ብቻ የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አላቸው።
የእንቅስቃሴው መሪ ከሆኑት መካከል የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በድምጽ ያስተላለፈው ዘገባ ሰዎችን በማነጋገር ጭምር ነበር። በዘገባው የእምነቱ ተከታዮች “ትዕግስታችን አልቋል” ማለታቸውንና “መስጊድ በጥይት ተበሳሳ ድረሱልን” የሚል መልዕክት ለጥንቃቄ በሚመስል መልኩ ማንነታቸውንና አድራሻቸውን ካልገለጹ አስተያየት ሰጪዎች በድምጽ አሰምቷል።
“ኢማሞቻችን አትሰሩ፣ ሐይማኖታችንን ለኛ ተው” በማለት ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን የሚገልጹትን ለማፈንና ርምጃ ለመውሰድ መንግስት ከፍተኛ በሚባል ደረጃ የአጋዚ፣ የፌደራልና ፖሊስና የኦሮሚያ   አድማ በታኝ ፖሊስ ሃይል ማሰማራቱን ጋዜጠኛ ሳዲቅ ያነጋገራቸው ምስክርነት ሲሰጡ ለማዳመጥ ተችሏል።
በሙስሊም ሰላማዊ ሰላፈኞች ላይ የደረሰውን አደጋ ደምጻችን ይሰማ እንደሚከተለው አቅርቦታል።
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!በኦሮሚያ አርሲ ዞን የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ!
ትናንት ማለዳ ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ገብተው በሰነዘሩት ጥቃት የሟቾች ቁጥር 11 ደረሰ፡፡ ከሻሸመኔ እስከ ኮፈሌ እና ዶዶላ ድረስ በሚያካልለው በዚህ የመንግስት ወታደሮች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እና የታሰሩ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡ በእለተ ቅዳሜ ምንም አይነት ተቃውሞም ሆነ መሰል እንቅስቃሰሴዎች በማይካሄድበት እና ባልተካሄደበት እለት የመንግስት ወታደሮች እስከገጠር ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ያለርህራሄ የቀጥታ ጥይት በመጠቀም የአካባቢውን ዜጎች ሲገድሉ ውለዋል፡፡
የመንግስት ቴሌቪዥን በተለመደ መልኩ ‹‹ጂሀድ ሲቀሰቅሱ እርምጃ ተወሰደባቸው›› የሚል ዜና ያሰራጨ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 3 ብቻ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ መንግስት ቀድሞ በታሰበበት መልኩ በአካባቢው ከፍተኛ የወታደር ሰፈራ በማድረግና በተጠንቀቅ በማስቆም በፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ በታኝ እና በወታደሮች በመታጀብ በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡ አራት ኦራል መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች አካባቢውን በመክበብ መስጂዶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጭምር ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚሁም የአካባበውን ታዋቂ የሃይማኖት መምህር፣ አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የራሳቸውን መኪና መስታወት በመሳሪያ ሰደፋቸው በመስበር ‹‹ሕዝቡ ሰበረው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት የሚያስችል ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል፡፡
መንግስት ምላሽ መስጠት የተሳነውን ሕገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በጥይት በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ባለፈው አመት በአርሲ ዞን አሳሳ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ አራት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአማራ ክልል ገርባ ከተማና በሐረር ኢማን መስጂድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ በድምሩ ከ13 ሰዎች በላይ ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተቀጥፏል፡፡ መንግስት የገደላቸውን ሰዎች በሙሉ ‹‹ለጂሃድ ሲያነሳሱ ገደልኳቸው›› የሚል ማስተባበያ ሲሰጥ ቢቆይም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አሁንም ይህ የመንግስት ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቀጥሏል፡፡
አሁንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ተጨማሪ ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክተት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡
አላሁ አክበር!
መንግስት በበኩሉ በተቃራኒው “በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ አክራሪ ሃይሎች ጉዳት አደረሱ” ሲል ነው ሶስት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ያመነበትን ዜና ያሰራጨው።
በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ አክራሪ ኃይሎች ጉዳት አደረሱ
በኦሮሚያ ክልል ኮፈሌ ከተማ ዛሬ አክራሪ ኃይሎች በፈጠሩት ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በሰውህይወትና ንብረት ላይ አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ወረዳ ኮፈሌ ከተማ ውስጥ ዛሬ ሀምሌ 27/2005 አክራሪ ኃይሎች በፈጠሩት ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የሽብር እንቅስቃሴው በፖሊስና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም የኦሮሚያ ፖሊስኮሚሽን ጨምሮ አስታቋል፡፡ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ የእስልምና እምነትን ሽፋን በማድረግ ህዝብን የመከፋፈልና ሰላምን የማደፍረስ አጀንዳ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ አክራሪና ፅንፈኛ ቡድኖች በዛሬው ዕለት ከጧቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በምዕራብ አርሲ ዞን ዋቤ ከተማ የጀመሩት ሁከት ወደ ኮፈሌ ከተማ በመሸጋገሩ ፀጥታ ለማስከበር በተሰማራው የአካባቢው የፖሊስ ኃይልና በሁከቱ ተሳታፊዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሶስት ሰው ህይወት ማለፉና በሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በአክራሪ ቡድኖች ተቀናጅቶ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወናበድና ለሁከት በማነሳሳት ኮፈሌ ከተማ ላይ በዛሬው ዕለት ተቀስቅሶ በሰላም ፈላጊ የአካባቢው ህዝብና በፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ የሁከት ድርጊት አክራሪ ኃይሎች ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም በዚያው ዞን ገደብ አሳሳ ላይ ጁሃድ በማወጅ ሞክረውት ከነበረው የጥፋት እንቅስቃሴ የቀጠለ ነው፡፡
በኮፈሌ ከተማ በዛሬው ዕለት የተቀሰቀሰው የአክራሪ ኃይሎች የሁከት እንቅስቃሴ በሰላም ፈላጊው የአካባቢው ህዝብ ትብብርና በክልሉ ፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም ጽንፈኞች ኃይሎቹ ህገ መንግስቱን በመጻረር የህዝብን ፀጥታ ለማወክና በሰላዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የጀመሩትን እንቅስቃሴ ለማምከንና  የጥፋቱ አቀናባሪና ፈጻሚ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለህግ ለማቅረብ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  ከመቼውም በላቀ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጾ ሰላም ወዳዱ ህዝብ ከመንግስት ጋር በመሆን አጥፊዎችን በማጋለጥና የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኦሮሚያ ፖሊስ  ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል።
ከመንግስት ወገን ከላይ እንደተገለጸው ቢቀርብም በአካባቢው መረጋጋት እንደሌለና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል። በከባድ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚጓጓዙት ታጣቂ ሃይሎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መግባባት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በአካባቢው አንጻራዊ መረጋጋት ስለመስፈኑ ከገለልተኛ ወገን የተባለ ነገር የለም። ይልቁኑም ከአያያዝ ጉድለት እየተካረረ የመጣውን የሙስሊሞች ጥያቄና ባገሪቱ እየጠነከረ የመጣውን የጥላቻ ፖለቲካ አገሪቱን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራት ስጋታቸውን የሚገልጹ ተበራክተዋል።
ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረው የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ በግብጽ እንደታየው የአረብ ጸደይ የበርካታውን ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ድጋፍ ያገኘ ባይሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ዘንድ አድማሱን እያሰፋ መሄዱና መንግስትም ከቀን ወደ ቀን የሃይል ርምጃ መምረጡ በአገሪቱ ካለው በርካታ ፖለቲካና የማህበራዊ ችግች ጋር ተዳምሮ አገሪቱን ለከፋ አደጋ እንዳይዳርጋት ስጋት አንዳላቸው የሚገልጹ ክፍሎች “ሁሉም ወገኖች ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡና ችግሩን በሰላም ለመፍታት የሚችሉበት አግባብ ሊፈጠር ይገባል” ብለዋል። የክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ ግልጽ ድጋፍ አለመታየት የድምጻችን ይሰማ ጥያቄዎች (የመጅሊስ አመራር፣ የአህባሽ ጉዳይ፣ …) ሃይማኖታዊ በመሆናቸው ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት በግልጽ የታወቀ ባይሆንም በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይላት ሁኔታው ወደ አረብ ጸደይ እንዲቀየር ገና ከጅምሩ ጥሪ ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በዚህ ሃሳብ ዙሪያ በተከታታይ የሚመለከታቸውንና ያገባናል የሚሉ ዜጎችን አስተያየት እንዲሰጡ በመጋበዝ በእርቅ አስፈላጊነት ላይ ተከታታይ ዘገባ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ያስታውቃል። ከዚህ በፊት በግልጽ እንዳስታወቅነውም አስተያየት ያላቸው ወገኖች በነጻነት ሃሳባቸውን እንዲሰነዝሩ ይጋብዛል። ከጉዳዩ አሳሳቢነትና አገራችንን ከማስቀደም አንጻር ለሚቀርቡ አስተያየቶች ማናቸውንም ገደብ የማናደርግ መሆኑንን ከወዲሁ እናስታውቃለን። ህዝብ ሊያውቅ የሚገባውን ሁሉ ማወቅ ይገባዋል፤ አገር ከሌለ ማንም ሊኖር አይችልም! (Photo: CNNiReport)
Posted Dawit Demelash

Monday, August 5, 2013

ለንጹሃን የደም ጥሪ ተገቢው ምላሽ ትጥቅ አንስቶ ነፍሰ ገዳዮችን መፋለም ብቻ ነው!

August 5, 2013

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል (መግለጫ)
Ginbot 7 Popular Force
Ginbot 7 Popular Force logoከሃምሌ 26 _ 2005 አንስቶ  ይህ መግለጫ እስከወጣበት እስከ ሃምሌ 28_ 2005 አ.ም እለት የወያኔ ዘረኛ ጉጅሌ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮቹን በማሰማራት በመላው ኢትዮጵያ፣ በእስልምና እምነት ተከታይ የሃገሪቱ ዜጎች  ላይ በስፋት የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነው። ክቡር ህይወታቸውን በግፈኛው የወያኔ የአፈና ሃይል ያጡት ወገኖች ቁጥር በርካታ ሆኗል። ክፉኛ የቆሰሉት ወገኖቻችን ቁጥር ከተገደሉት እጅጉን የገዘፈ ነው። ፍጹም አረመኔያዊነት  በተሞላው መንገድ በወያኔ ቅልብ ጦር የተቀጠቀጡትና እንደከብት ተሰብሰብው በየእስር ቤቱ የታጎሩት ወገኖቻችን ቁጥር በሽዎች የሚቆጠር ሆኗል። እጅግ ሰላማዊና  ስልጡን በሆነ  መንገድ ፍትሃዊ ጥያቄ ባነሱ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እልቂት የግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል የራሱ እልቂት አድርጎ  ያየዋል። የደረሰባቸውን  መከራና እንግልት የራሱ መከራና እንግልት አድርጎ  ወስዶታል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ወያኔን አያወግዝም ወይም ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ በገንዘብና በስልጠና  በዲፕሎማሲ ድጋፍ የሚያበረታቱን የምእራብና  ሌሎች የወጭ መንግስታት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አይማጸንም። ባለፉት 22 አመታት ውግዘትና መማጸን የትም እንዳላደረሱን በሚገባ እናውቃለንና። ግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል ደግሞ ደጋግሞ  ግልጽ እንዳደረገው የኢትዮጵያ  ህዝብ መከራ የሚያበቃው ህዝብ የወያኔን በእብሪት የተሞላ ግፈኛ ማንነት የሚመጥንና  የሚስማማ የትግል ስልት መርጦ አምሮ  ወያኔን ታግሎ  በመደምሰስ ብቻ ነው። ሙስሊሙም ሆነ የሌሎች እምነት  ተከታዮች መረዳት የሚገባን ወያኔ ስላማዊና  ስልጡን ከሆነው የእኛ አለምና  መርህ ጋር የማይተዋወቅ ዘረኛ  ገዳይ  ሃይል መሆኑን ነው። ይህ በእብሪትና  በድንቁርና የታጀለ የወያኔ  ሃይል የእናንተን ትእግስት ከፍርሃት፣ አርቆ አሳቢነታችሁን ከሞኝነት ጋር አስተሳስሮ የሚያይ ነው። “የምንገድልለት አላማ ባይኖረን የምንሞትለት አላማ አለን” የሚለውን ድንቅና ክቡር እመነታችሁን ወያኔ የሚያየው እናንተን በመግደል ፍትሃዊ ጥያቂያችሁን ማዳፈን ይቻላል በሚል ትርጓሜ ነው።ወያኔ ይህን የተቀደሰ እምነታችሁንና እንዲሁም  ቅንነትና ትእግስታችሁን ለእናንተ የሚመጥን ስልጡን ምላሽ  ማፈላለጊያ አድርጎ  አያየውም። አላየውም።
የትግል ስልት የሚቀየሰው የባላንጣን ማንነት በሚገባ ግምት ውስጥ በማስገባት እንጂ እኛ የምንፈልገው የትግል ስልት ስለሆነ  ብቻ መሆን አይችልም ብለን እናምናለን። እኛ በግንቦት 7 ውስጥ የተሰባሰብን አባላት የወያኔን የእብሪት አመጽ ማስቆም የሚቻለው የወያኔ አፈሙዝ ብቻ   ሳይሆን የእኛም ጠመንጃ እሳት የሚተፋ እንደሆነ በተግባር በማረጋገጥ ብቻ ነው የሚል ጽኑ እምነት አለን። ምንም አይነት የስልጣኔና የሞራል ማእቀብ  ከማይገዛው  ወያኔን ከመሰለ እኩይ ሃይል እራስን ከጥቃት መከላከል ብሎም በወያኔ መቃብር ላይ ሰላምና ነጻነት ማስፈን የተፈጥሮና የዜግነት መብታችን ብቻ ሳይሆን የአላህም ፈቃድና  ፍላጎት ለመሆኑ ጥርጥር የለንም።  በዚህ አጋጣሚ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ የሚያስተላልፈው ጥሪ የሚከተለው ነው። “የወያኔን የእብሪት አመጽ በፍትሃዊና ህዝባዊ አመጽ ለመመከት በያላችሁበት ተደራጁ። የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ተቀላቀሉ። የወያኔን የግፈኛነት እብጠት በህዝባዊና ፍትሃዊ የመሳሪያ አመጽ እናስተንፍስ” የሚል ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!
ሞት የንጹሃን ደም በከንቱ ለሚያፈሱ በሙሉ !!!!

        Posted By.Dawit Demelash

Sunday, August 4, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደባርቅ አካባቢ ጥቃት ፈጸመ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በቅርቡ በወያኔ ላይ በከፈተው ድንገተኛ የማጥቃት እንቅስቃሴው 65 የሥርዓቱ ታማኝ ታጣቂ ሐይሎችን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው።
አርበኛው የጦርነት ፍልሚያውን ግብግብ ከወያኔው ታጣቂ ሃይሎች ጋር የተካፈለው በጎንደር ደባርቅ ወረዳ የሥፍራው ልዩ ስያሜ በደዊ በመባል በሚታወቀው ሥፍራ ላይ ነው።
ከአርበኛው ሐይል ጋር በዕለቱ በተጠቀሰው ሥፍራ ተገኝተው ውጊያውን የተካፈሉ የወያኔ ታጣቂ ሐይላት የፈጥኖ ደራሽ አባላት ሲሆኑ በአውደ-ውጊያው መጨረሻም 28 አባሎቻቸውን በሞት ያጡት የወያኔ ታጣቂዎች ተጨማሪ ሌሎች 37 የፈጥኖ ደራሽ አባሎቻቸውም ላይ ከፈተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

Posted By.Dawit Demelash

ዛሬ በባህርዳር ከተማ ዝናብ እየዘነበም ቢሆን ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ያለው ምስል በከፊል

August 4, 2013

ፍኖተ ነፃነት
መፈክሮች፣
ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም!
ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ!
የሙስሊም መፍት ሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኩዋይ ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።!
የመሳሰሉት መፈክሮች ተሰምተል!
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F UDJ
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F

Posted By.Dawit Demelash

በኦሮሚያ አርሲ ዞን የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ!

August 4, 2013
Free Our Heroes
አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅ ከሟቾቹ ውስጥ ይገኙበታል!
ትናንት ማለዳ ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ገብተው በሰነዘሩት ጥቃት የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ፡፡ ከሻሸመኔ እስከ ኮፈሌ እና ዶዶላ ድረስ በሚያካልለው በዚህ የመንግስት ወታደሮች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እና የታሰሩ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡ በእለተ ቅዳሜ ምንም አይነት ተቃውሞም ሆነ መሰል እንቅስቃሰሴዎች በማይካሄድበት እና ባልተካሄደበት እለት የመንግስት ወታደሮች እስከገጠር ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ያለርህራሄ የቀጥታ ጥይት በመጠቀም የአካባቢውን ዜጎች ሲገድሉ ውለዋል፡፡
የመንግስት ቴሌቪዥን በተለመደ መልኩ ‹‹ጂሀድ ሲቀሰቅሱ እርምጃ ተወሰደባቸው›› የሚል ዜና ያሰራጨ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 3 ብቻ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ መንግስት ቀድሞ በታሰበበት መልኩ በአካባቢው ከፍተኛ የወታደር ሰፈራ በማድረግና በተጠንቀቅ በማስቆም በፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ በታኝ እና በወታደሮች በመታጀብ በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡ አራት ኦራል መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች አካባቢውን በመክበብ መስጂዶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጭምር ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚሁም የአካባበውን ታዋቂ የሃይማኖት መምህር፣ አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የራሳቸውን መኪና መስታወት በመሳሪያ ሰደፋቸው በመስበር ‹‹ሕዝቡ ሰበረው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት የሚያስችል ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል፡፡
መንግስት ምላሽ መስጠት የተሳነውን ሕገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በጥይት በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ባለፈው አመት በአርሲ ዞን አሳሳ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ አራት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአማራ ክልል ገርባ ከተማና በሐረር ኢማን መስጂድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ በድምሩ ከ13 ሰዎች በላይ ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተቀጥፏል፡፡ መንግስት የገደላቸውን ሰዎች በሙሉ ‹‹ለጂሃድ ሲያነሳሱ ገደልኳቸው›› የሚል ማስተባበያ ሲሰጥ ቢቆይም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አሁንም ይህ የመንግስት ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቀጥሏል፡፡
አሁንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ተጨማሪ ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክተት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡
አላሁ አክበር!
Posted By.Dawit Demelash

Saturday, August 3, 2013

August 3, 2013

አንድነት ፓርቲ እሁድ ሐምሌ 28፣ 2005 “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር ስር በተለያዩ የክልል ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። ይሁንና ከወያኔ አጉራ-ዘለል ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ወከባ ተባብሶ ቀጥሏል። ነብዩ ሀይሉ እና ሌሎችም በፌስ-ቡክ ገጾቻቸው ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልጹታል፣
UDJ calling for protest in Bahirdar
በባህርዳር የአድነት ፓርቲ አባላት በቅስቀሳ ላይ። ፎቶ Bisrat Woldemichael
በወላይታ የተሸጠ ጀነሬተር እንዲመለስ ተደረገ
በወላይታ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ(አዳራሹ ከ200 ሰው በላይ የመያዝ አቅም የለውም) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚያከናውነው ስብሰባ ህዝቡን ለመቀስቀስ ሞንታርቦና ጀነሬተር የሚያከራይ ነጋዴ በመጥፋቱ(በከተማው ጀነሬተር በማከራየት ህይወታቸውን የሚገፉ ነጋዴዎች በብዛት የሚገኙ ቢሆንም ካድሬዎች ቀጠን ያለ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው መከራየት አልተቻለም)የጄነሬተር መጥፋት ያሳሰባት ወ/ሮ ጸሀይ ወ/ጊዮርጊስ አነስተኛ ጀነሬተር በ2300ብር ትገዛለች፡፡
ሻጩ ጀነሬተሩን በህጋዊ መንገድ ከሸጠና መኪናው ላይ እንዲጫን ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ እንባውን እያዝረከረከ የተከፈለውን ገንዘብ በመያዝ ጀነሬተሬን መልሱልኝ በስህተት ነው የሸጥኩላችሁ››ይላል ፡፡ነጋዴው ለምን እንደዚህ እንደህጻን እያለቀሰ መልሱልኝ ማለቱን የተረዱ የፓርቲው አባሎችም ጀነሬቱን መልሰውለታል፡፡
—————————
መቀሌ፣ የአንድነት አመራሮች ከነ መቀስቀሻ ሞንታረቮአቸው በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ
የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አርአያ፣ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ ከነ መቀስቀሺያ ሞንታረቮአቸው ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሩ፡፡ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና አቶ ክብሮም ብርሀነ ለሁለተኛ ጊዜ እንደታሰሩ ልብ በሉ!!! የመቀሌ ነዋሪዎች አመራሮቹን ለማስፈታት ከፖሊስ ጋር እየተከራከሩ ነው፡፡‪
—————————-
ባህርዳር፣ አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ነገ ሐምሌ 28 ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተጠናከረ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው
የባህር ዳር እና የአካባቢዋ ነዋሪዎችም በተቃውሞው ሰልፉ ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢዎች ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግም የባህር ዳር ህዝብ ባሳየው ንቁ ተሳትፎ በመደናገጡ በተለያዩ ቤተ ክርስትያኖች ቅዳሴ ዘግይቶ እንዲጀምር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ቀበሌዎችም የተለያዩ ስብሰባዎችን አስጠርቷል፡፡ ባህር ዳሮችም ነገ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድመቅ የተለያዩ መፈክሮችን በየቤታቸው በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡
—————————-
አርባምንጭ፣ በአንድነት ፓርቲ በሁለት መኪናዎች አርባምንጭን በቅስቀሳ አድምቋታል፡
በራሪ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው ፖስተሮችም በብዛት እየተለጠፉ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች “ሰልፉ ላይ እንዳትወጡ” የሚል ቅስቀሳ ቢያደርጉም የአርባምንጭ ነዋሪዎች በሰልፍ ላይ ለመገኘት መወሰናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
—————————-
ጅንካ፣ ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው
ከአጎራባች አካባቢዎች በሰልፉ ላይ የሚሳተፉ ዜጎች ወደ ጅንካ እየገቡ ነው፡፡ ከትላንት ጀምሮ ፖስተሮች እንዳይቀደዱ የአካባቢው ህዝብ እየጠበቀ ነው፡፡ በኢህአዴግ ካድሬዎች በ 1 ለ 5 መዋቅር ሰልፍ አትውጡ በሚል የጀመረው ቅስቀሳ ከሽፏል፡፡
   Posted By.Dawit Demelash

Friday, August 2, 2013

እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው

የኢህአዴግ መልስ በጉጉት ይጠበቃል
chris smithAugust 2, 2013 09:58 am 


አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር “… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል።
“ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችንም ይሁን ከሙስሊሙ ኅብረተሰብ በግፍ ለእስር የተዳረጉትን እንዲያስጎበኝ ለሚቀርብለት ጥያቄና በጸረ ሽብርና ህጉ ዙሪያ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።
ምክክሩን ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፣ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” በማለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ፣ ከባልደረባቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን አቋም ለመመርመር የሚያስችላትን ስራ ለመስራት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ከምክክሩ በፊትና በኋላ ክሪስ ስሚዝ በሰጡት ጠንካራ አስተያየት የተደናገጠው ኢህአዴግ አዲስ ዘመን በሚባለው ልሳኑ “አሜሪካ የኢትዮጵያ አጋርና ወዳጅ መሆንዋን አረጋገጠች” በማለት የሌሎች ተናጋሪዎችን  ወደጎን በመተው የአምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶን ብቻ አንድ ሃረግ ንግግር ቀንጭቦ ዘግቦ ነበር። በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ባልተለመደ ሁኔታ የተብጠለጠለው ኢህአዴግ ወዳጆቹን ለማረጋጋት ያማሞቶን ጠቅሶ ያሰራጨው ዜና በወቅቱ በደጋፊዎቹ የፌስቡክ ገጽ ላይ በስፋት ተበትኖ ነበር።
Bass
እንደራሴ ኬረን ባስ
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ መሆኗን ያመላክታል የተባለው የአዲስ አበባ ጉብኝት አስመልክቶ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኢህአዴግ የፖለተካውን ምህዳር በማጥበብ፣ በጸረ ሽብር ህጉ እያሳበበ የመናገርና የመሰብሰብ መብትን ማፈኑ፣ የነጻ ሚዲያና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማነቁ፣ በተለይም በእስር ቤት የሚሰቃዩ ወገኖችን በአካል በመገኘት በማነጋገር አቋም ለመውሰድ መታቀዱን አመልክተዋል። ይህም ከፖለቲካ እስረኞች ጀምሮ፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ጥያቄ ከፍ አድገው በማንሳታቸው ለእስር የተዳረጉትን ወዘተ የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡
“የሚሆነው እስከሚሆን መጠበቅ ነው” በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ አንድ ዲፕሎማት እንዳሉት ነሐሴ 10 ወይም 11 ቀን 2005 (ኦገስት 16 ወይም 17፤ 2013) ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩት ሁለቱ እንደራሴዎች፤ ለኢህአዴግ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ እንደሆኑ ይናገራሉ።
“ጉብኝቱ የሽርሽርና እንደተለመደው አይነት የሁለትዮሽ ስብሰባና ስምምነት ለማድረግ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም” ብለዋል። ሲያስረዱም “በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ኡደት፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም።”
“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነበር። ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበትና የወቅቱ የቡሽ አስተዳደር “እንዝላልነት” ታክሎበት ሊመክን ችሏል። ይህን ህግ እንደገና ለማጸደቅ እንደሚሰሩ በግልጽ የተናገሩት ስሚዝ፣ “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገው ነበር።
በዚህ ይሁን በሌላ ምክንያት የመለስ ምትክ የሆኑት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የስኳር ሚኒስትሩ አቶ አባይ ጸሐዬ ሰሞኑንን “የዲሞክራሲ ማበብ የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት ለተለያዩ መገናኛዎች በየፊናቸው የተናገሩትን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በስፋት ዘግቦታል። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታው ከመለስ እጅ በተካሄደው ርክክብ መሰረት አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ ስለመሆኑ ከየአቅጣጫው የሚጎርፈው መረጃ ከወትሮው በተለየ ይፋ እየሆነ ነው።
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየመራ ያለው ህወሃት በራሳቸው በአሜሪካኖቹ ቋንቋ ‘አሸባሪን መዋጋት’ በሚል ሰበብ ምዕራባውያንን ሲያልባቸው ቢቆይም “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” ሲሉ በጀርመን ሬዲዮ የመረረ ንግግር ንግግር የተናገሩት እንደራሴ ስሚዝ “ዛሬ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ጊዜ ላይ ነች” በማለት ከሁለት ወር በፊት የተናገሩትን ከዳር ያደርሱት ይሆን የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ወቅት ተደርሷል፡፡