Friday, November 14, 2014

ፌደራል ፖሊሶች ለሚፈጽሟቸው ግድያዎች ተጠያቂው ማን ነው?


ይህ ጥያቄ በቀጥታ በመንግስት ትዕዛዝ የተፈጸሙ ግድያዎችን አይመለከትም፡፡እንደውም በፓርላማ ከቀረበው ረቂቅ አዋጅ አንዱ ‹‹በግዳጅ ላይ ያለ የመንግስት ታጣቂ ለሚፈጽመው ጥፋት ተጠያቂ እንዳይሆን ››የሚሞግት ነው፡፡

ፓርላማው 446 ለ 1 የሚመራ በመሆኑም ገዢው ፓርቲ የፈለገውን አዋጅ የማውጣት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡በዚህ ገጽ ግን ለማንሳት የወደድኩት ታጣቂዎች ከስራ ገበታቸው ውጪ እየፈጸሟቸው የሚገኙ ግድያዎች ሀላፊ ማን ይሆናል የሚለውን ነው፡፡


ንፋስ ስልክ አካባቢ የመንግስት የሰላም አስከባሪ አባል የነበረ አንድ መቶ አለቃ ጎረቤቶቹን በ35 የክላሽ ጥይት መግደሉና ህጻናቱን ያለ ወላጅ ማስቀረቱ አይዘነጋም፡፡መቶ አለቃው ከታሰረ በኋላ በልዩ እንክብካቤ ተይዞ ወላጆቻቸውን ባጡ ህጻናት ላይ ይዘት እንደነበርና በኋላም አመለጠ ተባለ፡፡መቶ አለቃው መጨረሻ ላይ ስለመያዙ ተነገረ፡፡

ባህርዳር የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ አንዘነጋውም፡፡አፍቅሪያታለሁ ያለ ፌደራል ፖሊስ የ18 ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሞተ የሚል ወሬ ተናፈሰ፡፡

ቂርቆስ መንደር በምትገኝ የሴተኛ አዳሪዎች ሰፈር እንዲሁ የእኔ የሚላትን ሴተኛ አዳሪ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ በማግኘቱ ፌደራሉ በሁለት ጥይት ደረቷን መትቶ ለህልፈት ዳረጋት ፣ከሴትየዋ ጋር የነበረው ጎልማሳም እግሩን በጥይት ለመቆረጥ በቅቷል፡፡

ይህ ፎቶ ግራፍም በተመሳሳይ መንገድ በፌደራል ፖሊስ ህይወቱን በግፍ ስለ ተነጠቀ ወጣት የሚጮህ ነው፡፡

ጅማን በእንባ፣በድንጋጤና በተቃውሞ የሞላ ክስተት የተስተናገደው በፌደራል ፖሊስ ነው፡፡በምሽት ሰው ቤት ሰብሮ የገባው ፖሊሱ አንዲት አይነ ስውር እናትና ልጃቸውን ቀጥፏል፡፡

ግለሰቡ ስለ መያዙም ተነግሯል፡፡ግን ይህ ነገር በገዳዮቹ መያዝ ብቻ የሚያበቃ መሆን የለበትም፡፡ተጠያቂነቱ ወደ ላይም መውጣት አለበት፡፡መሳሪያ መያዝ የማይገባቸው፣ሰብዓዊነት ምን ማለት እንደሆነ የማይረዱ፣ግደሉ ሲባሉ ከመግደል የማያመነቱ፣መሳሪያ ሲጨብጡ ጭንቅላታቸውን ቃታው ጋር የሚያደርጉ ሰዎችን መለዮ እያለበሱ ስልጣናቸውን ለማራዘም እስከጠቀሟቸው ድረስ ስለሚፈጽሙት ዘግናኝ ድርጊት ደንታ የሌላቸው አካላትም መጠየቅ ግድ ይላቸዋል፡፡


የሟቾቹ ደምም በተኳሾቹ ላይ ብቻ ሳይሆን ነፍጥ ባሸከሟቸው ሀይሎች ላይም ይጮሃል፡፡ 

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36201

Tuesday, November 11, 2014

የታፈኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸው ተሰማ


ከአንድ ሳምንት በፊት በየ ክፍለ ሀገሩ በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የታፈኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አግባው ሰጠኝ እንዲሁም፤ በዚሁ በሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አቶ አንጋው ተገኝ በትናንትናው ዕለት ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡

ሰሞኑን በየ ክፍለ ሀገሩ በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የታፈኑት የሰማያዊ፣ የአንድነት፣ የመኢአድና የአረና አመራሮችና አባላት የደረሱበት ሳይታወቅ የቆየ ሲሆን ከትናንትና ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ እየተዛወሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡


ነገረ ኢትዮጵያ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36094

Sunday, November 9, 2014

Zone 9 Case Sees 11th Court Delay

 VIENNA – An Ethiopian court this week delayed proceedings for an 11th time against six bloggers and three independent journalists, who were arrested in April in connection with their activities as part of the Zone 9 collective.
The court at a hearing on Tuesday adjourned the case until Nov. 12, 2014. The nine defendants, who were arrested in Addis Ababa on April 25 and 26, have now been in pre-trial detention for over six months.
The bloggers and journalists are being held on charges of alleged terrorism and inciting violence as a result of their contact with foreign human rights organisations and opposition political parties. They are being prosecuted under Ethiopia’s controversial, 2009 anti-terrorism law.
After a joint mission to Ethiopia with the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA) last
year, IPI called on Ethiopian authorities to release all journalists convicted under the legislation and urged that the law be amended in a way that does not inhibit constitutionally guaranteed freedom of expression rights.
IPI Senior Press Freedom Adviser Steven M. Ellis said: “The Zone 9 case not only illustrates the stifling press environment in Ethiopia, but the severely impeded judicial proceedings in this case also interfere with the defendants’ due process rights.”
The Zone 9 Trial Tracker blog calls the 11th delay a “record” in a case that has been stalled since the April arrests and marked by repeated delays.
The first delays were a result of police requests for more time to conduct investigations. The defendants were not formally charged until July 17, when they were brought to the Lideta High Court for a hearing without legal representation. When they refused to be tried without a lawyer, the case was adjourned until the next morning. At a July 18 hearing, the trial was adjourned until Aug. 4.
The Trial Tracker blog reported that at Tuesday’s hearing there was confusion regarding changes in the courtroom venue. The blog said that the hearing was pushed back as a result of two presiding judges in the case being replaced with new judges, who were unprepared to make a ruling.
Before last year’s joint IPI/WAN-IFRA mission, African Union Special Rapporteur on Freedom of Expression and Access to Information Pansy Tlakula told IPI: “[F]ollowing the 2005 general elections in Ethiopia, freedom of expression and media freedom [have] been continuously deteriorating.”

In a report released on Jan. 14 following the mission, IPI said that Ethiopia’s use of sweeping anti-terrorism law to imprison journalists and other legislative restrictions were hindering the development of free and independent media in the country.

http://www.dagmawitewodros.net/2014/11/zone-9-case-sees-11th-court-delay.html#Ethiopia

Friday, November 7, 2014

በሀገሪቱ ላሉት ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮች እስርና ወከባ መፍትሄ አይሆንም!

Nov.7.2014

አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ፖለቲካዊ እስርን እንዳንድ ተቀዋሚዎች የማዳከሚያ ስልት በመውስድ ህግ ወጥ በሆነ ሁኔታ አባሎቻችን በማሳርና በማዋከብ ላይ ይገኛል። አንድነት ከምስርታው ጀምሮ አመራሮቹና አባላቱ የተለያየ ሽፋን በመጠቀም ለእስርና ለእንግልት ተዳርጓል፤ አሁንም እየታሰሩና እየተዋከቡ ይገኛሉ፤ በቅርብ ደግሞ ለየት ባለ ሁኔታ አጠቃላይ ፓርቲው በሚያዳክም መልኩ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚገኙ የአንድነት አባላት እያሳደደ በማሰር ላይ እንደሚገኝ ከየአከባቢው የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በወላይታ ዞን የአንድነት የአመራር አባላት ከፍተኛ የሆነ ደብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን እነዚህም አቶ ማሞ ጎሙ የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ፣ አቶ ወኖ መናሳ የዞኑ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና አቶ አልታዬ አቦታ የዞኑ የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ይገኙበታል፤ ይህን ድብደባ በሚፈፀምበት ወቅት የከተማው ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ሌሊሼ ኦፌ በቦታው ቆሞ እያየ የነበረ መሆኑ ደግሞ ህግ አለ በሚባልበት ሀገር ዜጎች ምንም ዓይነት የህግ ከለላ እንደሌላቸው የሚያሳይ እጅግ አሳዛኝ የሆነ እውነታ ነው።

እንደዚሁም ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም. በምዕራብ አምርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ የሚገኙ የአንድነት አባላት አቶ አንጋው ተገኝ የአካባቢው የአንድከት ሰብሳቢ፣ አቶ አባይ ዘውዱና አቶ እንግዳው ዋኘው የአካባቢው የአንድነት አመራር አባላት፣ በሌላ በእኩል አቶ በላይነህ ሲሳይ በመተማ ከተማ የአንድነት ሰብሳቢ፤ አቶ አለባቸው ማሞ በመተማ አባል እና አቶ አለበል ዘለቀ የወረታ የአንድነት የአመራር አባል ምዕራብ ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበ የፌደራል ፖሊሶች የቤታቸውን በር ገንጥለው በመግባት እየደበደቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷቸው፣ ከዚያም ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው እንደሰወሯቸው ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ በመቀሌ የአንድነት አባል የሆነው ወጣት ሺሻይ አዘናው ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም. በመንግስት የድህንነት አካላት ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የተወሰደ ሲሆን ወደ ቤቱ በመሄድ እዚያ ያገኙትን ወረቀት ሁሉ ወስደው በመኪና ወደ አልታወቀ ቦታ ይዞውት ሄደዋል።

በአጠቃላይ በአንድነት አባላት ላይ እየተካሄደ ያለው ህግወጥ የእስር ዘመቻ ሲታይ ገዥው ፓርቲ አንድነትን ለማዳከምና በተሻለ አቋም ላይ እንዳይገኝ ለማድርግ እያካሄደው ካለው ዘርፈ ብዙ ዘመቻዎች አንዱ አካል ነው ብለን እናምናለን። ነገር ግን ይህ በሀገሪቱ ውስጥ ለተንሰራፋው ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሄ አይሆንም ብለን እናስባለን። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የህዝቡን ብሶት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሄዶ ሌላ ያልታሰበ ጥፋት እንዳያስከትል ስጋት አለን። ስለዚህ ስርዓቱ ሁሉም ነገር በኃይል እፈተዋለሁ የሚለው ነገር የትም የሚያደርስ አይሆንም፤ ነገም በህግና በታሪክ ሊያስጠይቅ የሚችል እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል።

አንድነት በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፖለቲካ ፓርቲ እንደሆነ እየታወቀ ገዥው ፓርቲ ይህን ያህል ርቀት ሄዶ ፓርቲውን ለማዳከም መንቀሳቀሱ በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን ለህዝብ ለማስረከብ ፍላጎት እንደሌለው የሚያሳይ ነው። እንግዲህ ኢህአዴግ እንደስርዓት ቆም ብሎ ማሰብ ያለበት ወቅት ላይ እንገኛለን። አሁን እየሄደበት ያለው መንገድ ጠፍቶ ለመጥፋት ካልሆነ በስተቀር ብዙም ሩቅ የሚያደርስ ነው ብለን አናምንም።

በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ የምናስተላልፈው መልዕክት አሁን በመንግስት እየተወሰደ ያለው የእስር ዘመቻና ወከባ ሳይደናገጥና ተስፋ ሳይቆርጥ ትግሉን መደገፍና መቀላቀል አለበት እንላለን። አምባገነኖች በኃይል ስልጣን ላይ ሊቆዩ የሚችሉት ህዝቡ በአንድነት ሆኖ በቃኝ በዚህ መንገድ ከእንግዲህ አልገዛም የሚል ቁርጥ ያለ አቋም እስኪይዝና በአንድነት እስኪነሳ ድረስ መሆኑ መታወቅ አለበት። በመሆኑም፤ በቀጣይነት ለምናደርጋቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ከጎናችን ሆኖ ለለውጥና ለነፃነት በሚደረገው ሰላማዊ ትግል ላይ እንዲሳተፍና የማይተካ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ
ጥቅምት 28/2007 ዓ.ም


http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/16182

Wednesday, November 5, 2014

በአንድ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው! •

ጥቅምት 25፣2007 (ኖቨምበር 4፣2014)

ህወሓት/ኢህአዴግ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ የግፍ ተግባር ማካሄድና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረጉን በሰፊው ቀጥሏል::  በዚህ አኳያበሶማሌ፣ በአማራው፣ በኦሮሞ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣….ወዘተ ተወላጆች ላይ የሚያካሂደው እልቂት በቂ መረጃ ነው::
የዚህ ቀጣይ ረገጣ ተከታታይ ዒላማ የሆነው አንዱ የአማራው፡ተወላጅ ነው:: ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው የአማራ፡ተወላጁን  በጠላትነት ፈርጆ በተለያየ ደረጃየጥቃት ዒላማ አድርጎታል። በዚህም መሠረት በራሱ ትዕዛዝም ሆነ በተለጣፊ ድርጅቶቹ አማካኝነት እጅግ ዘግናኝ ግፍ የተሞላበት ወንጀል ፈጽሟል። ለዘመናት  ከኖረበት ቦታ “ወደ መጣህበት ሂድ” ተብሎ ንብረቱ ተነጥቆ ባዶ እጁን በግዳጅ እንዲባረር ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ ህፃናት ልጆች ሳይቀሩ አሰቃቂ በሆነ ግፍ እንዲታረዱ ዜጎች ወደ ገደል እንዲወረወሩና፣ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በአርባ ጉጉ፣ በወተር ፣በአርሲ .ወዘተ የተካሄደው ይህንኑ ነው የሚያሳየው።

ለዚህ ጨካኝና ህገወጥ ተግባርም የህወሓት/ኢህአዴግ ባለሥልጣኖች በቀጥታም በተዛዋሪም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ታምራት ላይኔ በአማራው ተወላጅ ላይ የኦጋዴን ህዝብ እርምጃ እንዲወስድ ያካሄደው ግልጽ የሆነ መገፋፋት፣ በአርሲ በተካሄደ እልቂት እነ ኩማ ደመቅሳ ዋና ተዋናን እንደነበሩ፣ መለሰ ዜናዊ ከጉራፈርዳ የተባረሩትንና ለአቤቱታ የመጡን ዜጎች እንኳን አባረሯችሁ የሚል አንድምታ  የሚሰጥ መግለጫ በይፋ መስጠቱ ጥቂቶቹ ማስረጃዎች ናቸው።
ይህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚፈጽመውና የሚያበረታታው ህዝብን እርስ በርስ የማጫረስ ተግባር እጅግ እየሰፋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከር በአደገኛፍጥነትመም በመቀጠል ላይ ነው።

ትላንት ከትላንት በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች እንደተደረገው ሁሉ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታትም ባለማቋረጥ በጋምቤላ አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ በዋናነት በዚሁ በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የድብደባ፣ የግድያና የማፈናቀል እርምጃ በሰፊው ተካሂዶ በመዠንገር አካባቢ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲሞቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፣ በሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን፣ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት መንበር ላይ የተቀመጠው ህወሓት/ኢህአዴግ ሁኔታው እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማስቆም የወሰደው ምንም እርምጃ የለም። ችግሩ ከተፈጠረ በኋላም ቢሆን የተጎዱትን ለመንከባከብ፣ ህክምና የሚሹትን ለመርዳት፣ መልሶ ለማቋቋምና ወንጀለኞቹን ለህግ ለማቅረብ የሚያደርገው ይህ ነው የሚባል ሙከራ አይታይም።  ይሀ ሁሉ  የሚያመለክተው ያለው ስርዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ወንጀል አካል እንደሆነ ነው።
ሸንጎው የኢትዮጵያን ህዝብ አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሥልጣኑን ለማራዘም ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያካሂደውን ቀጣይ ሀላፊነት የጎደለው ኢ-ሰብአዊ ግፍ አጥብቆ ያወግዛል። በአማራውም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በተከታታይ እየተካሄደ ያለውን የማፈናቀል፣የግድያ፣ የጅምላ እሰራትና  ሌሎች  ወንጀሎች ባስቸኳይ እንዲቆም ያሳስባል። እስካሁን የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ብቃት ባለው እና  ከሥርዓቱ ባለሟሎች ነፃ በሆነ አካል እንዲጣራ፤ ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ያስገነዝባል።

በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣ በወልቃይት እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ቦታዎች ውስጥ ይህ  ሥርዓት የሚያካሂደውን ማለቂያ የሌለው ግፍ ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል።

ሰዎችን በትውልዳቸው የተነሳ በጅምላ የጥቃት ሰላባ ማድረግ በዓለምአቀፍ ህግም አስጠያቂ እንደሆነ የዚህ ጥፋት ፈጻሚም አስፈጻሚም የሆኑ ሁሉ እንዲገነዘቡት በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የዚህን  የግፍ ሥርዓት መጨረሻ ለማፋጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲነሳ እናሳስባለን፡  በአንድ አካባቢ ኢትዮጳያዊያን ላይ  የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!


 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35951

Tuesday, November 4, 2014

በምእራብ አርማጭሆና በመተማ የአንድነት ፓርቲ አደራጆች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ታፍነው ተወሰዱ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል።
የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አባይ ዘውዱና እንግዳው ዋኘው ከተያዙት መካከል ይገኙበታል። የአቶ በላይነህ ቤት ከሌሊቱ 9 ሰአት የተከበበ ሲሆን፣ አቶ በላይ ሳይነጋ ቤቴን አልከፍትም በማለት፣ ከንጋቱ 11 ሰአት ላይ ቤቱን ሰብረው ገብተው ወስደውታል። ቤተሰቡ በፌደራል ወታደሮች ድርጊት በእጅጉ ተዳንገጠዋል።
ከንጋቱ 11 ሰአት ሲሆን በአብራጅራ የአንድነት ፓርቲ አመራር በሀነው በአቶ አንጋው ተገኝ ቤት የተገኙት የፌደራል ፖሊሶች፣ ቤቱን እንዲከፍት ሲጠይቁ፣ እስኪነጋ እንዲታገሱት ቢጠይቅም፣ ወታደሮቹ በሩን ሰብረው በመግባት ክፉኛ ደብድበው ወስደውታል። አቶ አንጋው ክፉኛ በመደብደቡ ወታደሮች አንስተው መኪና ላይ እንደጫኑት የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ወጣት አባይ ዘውዱን ሊይዙ የሄዱት ፖሊሶች ከቤተሰቦቻቸው በደረሰባቸው ተቃውሞ ውዝግብ ፈጥረው የቆዩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን በሃይል መውሰዳቸውን ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ለቤተሰቡ ብቸኛ የሆነውንና ከዚህ ቀደም ስራ በመከልከልና በእስራት ከፍተኛ እንግልት ሲደርስበት የነበረውን ወጣት አባይን ላለማስወሰድ ሲማጓቱ የነበሩ ሁለት እህቶቹ በሰደፍ በመመታታቸው በአሁኑ ጊዜ ጤና ጣቢያ ውስጥ መተኛታቸውን ቤተሰቦች ገልጸዋል። አንደኛዋ ጡቷ ስር በሰደፍ ስትመታ ሌላኛዋም ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶባት ፈሳሽ ምግብ ወይም ግሉኮስ ተተክሎላት ህክምና እየተደረገላት ነው።  በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ሶስቱ የፓርቲው አመራሮች በተያዙበት ወቅት ነዋሪው ተቃውሞ በማሰማት ውሳኔውን ለማስቀልበስ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካ ቀርቷል። ይሁን እንጅ ድርጊቱ የህዝብ ቁጣ መቀስቀሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
አቶ አንጋው ተገኝ ከዚህ በፊት በከፍተኛ ሁኔታ  ተደብድቦ ታስሮ መፈታቱ ይታወቃል። አባይ ዘውዱም ኤርትራ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ከወር በፊት በመከላከያ አባላት ተይዞ በህዝብ ተቃውሞ እንዲፈታ መደረጉ ይታወቃል።  ሁለቱም መሪዎች ስለሚደርስባቸው እንግልት በቅርቡ ለኢሳት ቃለምልልስ መስጠታቸው ይታወቃል።
ገዢው ፓርቲ የሃይል አፈናውን  አጠናክሮ መቀጠሉን የሰሜን ጎንደር አንድነት ፓርቲ የአመራር አካል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሃ ተናግረዋል በደቡብ ጎንደር ደግሞ የፎገራ ወረዳ የአንድነት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አለበል ዘለቀ ከሚሰሩበት የእርሻ ቦታቸው ላይ በፌዴራል በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ ሲወሰዱ፣ በምዕ/ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ የወረዳው ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበና 3 የአንድነት አባላት ከቤታቸው በፌዴራል ፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል።
ከትናንት በስቲያ ደግሞ የምእራብ ጎጃም የመኢአድ ዋና ጸሃፊ አቶ ጌታቸው መኮንንና የፓርቲው ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ ተስፋየ ታሪኩ  ተይዘው መታሰራቸው መዘገቡ ይታወቃል።  የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል።
http://ethsat.com/amharic/%E1%89%A0%E1%88%9D%E1%8A%A5%E1%88%AB%E1%89%A5-%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%88%9B%E1%8C%AD%E1%88%86%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%90%E1%89%B5/

Sunday, November 2, 2014

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር “የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል” አለ

በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆናና እርዛት እስከመቼ?
ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሠጠ መግለጫ
የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ዘወትር ስልጣናቸውን ለማራዘም ካላቸው ነቢራዊ ፍላጎት የተነሳ በህዝብ ላይ ግድያ እና እስር ከመፈፀም አልፈው ሐገራችን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ማጥ ውስጥ ለመክተት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በአሶሳ ከተማ ንፁሀን የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ይኸውም መንግስትእየተከተለው ብልሹ የዘውግ አስተዳደር ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ እየታየ ነው በሌላ በኩል ይህ ግድያ መንግስት እራሱ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሠለፍ በማሠብ እንደገደላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል እንደምክንያት የጠቀሱት ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ መንግስት ተቃውሞውን ለማባባስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ ወደውጭ ቦንብ በመወርወር 6 ፖሊሶችን በመግደል ፖሊሶችን ለማነሳሳት እና ህዝቡን ለማሳሳት ቢሞክርም በመጨረሻ ጉዳዩን የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ሲያወጣው የመንግስት ሴራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአሶሳው፣ የአምቦው፣ የጎንደሩ እና የወለጋው ግድያም ከዚህ የተለየ አይሆንም፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴም ለመንግስት እና ለህዝቡ የሚከተለውን መልዕክት ማስተላለፍ ይወዳል፡፡

የመምህራኑ መልዕክት ለመንግስት
ማንኛውም መንግስት ህዝቡን ማዳመጥ ይኖርበታል መንግሥት ሕዝብን የሚያዳምጠው በሕገ መንግሥቱ ስለሚገደድ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የሕዝብ ወገን ነኝ የሚል ሥልጣን የያዘ ፓርቲና መንግሥት፣ ሕዝብን ምረጠኝ የሚል ፓርቲና መንግሥት፣ የሕዝብ ከበሬታና አመኔታ ሊያገኝና ዓላማውን በተግባር ላይ ሊያውል የሚችለው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የሚቆየው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሕዝብን ማዳመጥ ለራስ ተብሎም መደረግ ያለበት ነው፡፡ የማያዳምጥ መንግሥት የማይደመጥ መንግሥት ይሆናልና፡፡

የመምህራኑ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሐይማኖትህ፣ ለሐገርህ እና ለቀጣይ ትውልድ አስበህ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል፡፡ መንግስት ህዝቡ ፊቱን ካዞረበት እና ካልተገዛለት ማንንም ሊገዛ እንደማይችል የቅርባችን የጋዳፊ አገዛዝ ምስክር ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከኢህአዴግ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት መመስረት የለብንም ከዚያም አልፎ ከወያኔ ጋር ተለጥፈው ህዝባቸውን የሚያስወጉ ጎረቤቶቻችንን ጭምር ከማንኛውም ማህበራዊ ህይወት በማግለል ትምህርት ልንሠጣቸው ይገባል፡፡


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!!!!!!!!
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35873