Tuesday, July 8, 2014

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ( የዕለቱ ዜና ዘገባ ) 06.07.2014

የሙስሊሙ ህብረተሰብ ለመብትና ለሀይማኖት ለነፃነት የታሰሩ ታጋዬችን ለማስፈታት የድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ ዓርብ ዕለት በመላው ኢትዬጵያና በአንዋር መስጅድ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ዋሉ ፣፣
የወያኔ ቡድን መጪውን ምርጫ በማሰብ ህዝቡን እያጨናነቀ ነው ፣፣
በኢትዬጵያ የኢንግሊዝ ኤምባሲ 5 የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በኤምባሲው ተርቶ አነጋገረ ፣፣
የወያኔው አፍራሽ ግብረ ሀይል ሀና ማሪያም ሰላም ሰፈር 150 ቤቶችን አፈረሰ ፣፣
እንዲሁም ቦሌ ቡልቡላ የመድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን የንግድ ሱቆችን አፈረሰ ፣፣

http://www.finote.org/Finot06_07_2014.mp3      ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ ፣፣


Monday, July 7, 2014

ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች


ቀሲስ ብርሃነ ቆባዕ (ከእግሪሓሪባ) በሽብር ተጠርጥረው (ከነ አደይ አልጋነሽ ጋ) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30, 2006 ዓም በፖሊስ ታሰሩ። ቀሲስ ብርሃነ እያረሱ እያሉ ነው በአራት ፖሊሶችና ስድስት ምልሻዎች ተከበው ከእርሻ ማሳ ታስረው ፖሊስ ጣብያ የገቡ። የነ ቀሺ ብርሃነ ጉዳይ ሽብር የሚል ነው። ህወሓት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባት በሽብር በመክሰስ ሪከርድ ሰብራለች። ወይስ ቀስን በሽብር የከሰሰች ሌላ ሀገር አለች?

ጉድ ብዪ ሀገሬ ቄሱም፣ ሐጂውም፣ ኡስታዙም አሸባሪ ነው። እናቶችና የሀይማኖት አባቶች አሸባሪ ተሰኝተው የሚታሰሩበት ዘመን ደርሰናል። ካሁን በኋላ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ብቻ አይደሉም በሽብርተኝነት የሚከሰሱ፤ የክርስትና ሀይማኖት አባቶችም አሸባሪዎች እየተባሉ ነው። በህወሓት ዘመን እስላም ክርስትያኑ አሸባሪ ተሰይሟል። አሁን ታድያ በሙስሊሞችና ክርስትያኖች መካከል መተባበር የሚያስፈልግ አይመስላችሁም? በቃ ሁላችን ሀይማኖት፣ ብሄር፣ ጎሳ ምናምን ሳንለይ አምባገነኑ የህወሓት ስርዓት ለመቀየር መተባበር አለብን። ሁላችን የስርዓቱ ሰለባ ነንና።

በሽብር የተከሰሱ የዓረና አባላት ቁጥር 8 ሲደርስ በተለያዩ ቦታዎች የታሰሩ የዓረና አባላት ቁጥር ደግሞ 115 ሆኗል። ቁጥሩ ለሳምንታት ታስረው የሚለቀቁና ደብዛቸው የጠፉ አይጨምርም።

ወይ ሽብር! በቃ ሁላችን አሸባሪዎች ነን።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32146

Wednesday, July 2, 2014

አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

የግንቦት 7 አመራር አባል በየመን መንግስት ታግተው ከተያዙ ከአንድ ሳምንት ወዲህ የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ
ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ በመስጠት ለየመን ኩባንያዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ ተደረገ::



በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡

ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ሲል ሪፖርተር ዘገባውን አጠናቁአል::


ውድ አንባቢያን በኢትዮጵያ አትራፊና ከፍተኛ ታክስ ከፋይ ከሆኑ ትላልቅ የመንግስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አቶ አንዳርጋቸው ከታሰሩ ወዲህ ለየመኑ ኩባንያ በጠቅላይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፍ መደረጉ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31901

Monday, June 30, 2014

ይሉኝታ ቢሱ ወያኔ በሚኒሶታ ቅሌቱን ተከናነበ



ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአላሙዲ የሚደገፈው የወያኔ ቡድን የሚኒሶታን ሕዝብና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለማደናገር በሚኒሶታ ጠቅላይ ግዛት በሴይንት ፓውል ከተማ በሚገኘው ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲት እስፖርት ሜዳ ላይ ባዶ  እስታድየሙን በመያዝ ቅሌቱን ተከናንቧል። ሕዝብን በመፍረት የስታድየሙን ዙሪያ በአረንጓዴ፣ ብጫ ፣ ቀይ ባንድራ  ሰቅለው ነበር። ለተቃውሞ የወጣውም ሕዝብ በአገር ቤትና በወያኔ ቤተክርስቲያኖች የሚጠቀሙበትን ወያኔ በባንድራችን  ላይ የለጠፈውን የሴይጣን ምልክት ያለበትን ባንድራ አለመጠቀማቸውን በማየት በኢትዮጵያ ባንድራ መቀለድ አይቻልም፤ በባንድራ ማታለል አትችሉም። 

ወያኔ ይህ ባንድራ አያውቅም፣ ይህን የኢትዮጵያን ባንድራ(አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ቀለማት  ብቻ ያለበትን ሳንደቅዓላማ) ለሁሌም ተጠቀሙ በማለት ተቃውሞና ማሳሳቢያ ሰጥቷል። በመኪና ማቆሚያ ከዚያም በሽቦ  አጥር እንዲሁም በለመዱበት የፍራቻቸው መከለከያ በሆነው ፖሊስ በውጭና በውስጥ የተከበበውና የተጀበው የኮንኮርዲያ  ዩንቭርሲቲ ስታድየም ወያኔዎች ይበልጥ ከሕዝብ ወለፈን እንዲርቁ ረድቷል።  ወያኔ በኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ላይ ያደረገውን የክፍፍልና በስፖርት ስም በሚኒሶታ ለማካሔድ  ያሰባውን ድርጊት የሚቃወመው ሕዝብ የወያኔና የአላሙዲ ገንዘብ ተቀባዮች ወደሚጫወቱበት ሜዳ ድረስ በመሄድ  ተቃውሙን በመፈክር ፣ በዝማሬና በጩሃት አሳምቷል። በወቅቱ ሕዝቡ ካሰማቸውና ከያዛቸው መፈክሮች ጥቂቶቹ ፡-

  • ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
  • Long Live Ethiopia !!!
  • ዘረኝነት ይቁም !
  • Stop Tribalism!
  • Free Tsegaye Debteraw
  • Free Eskender Nega
  • Free Andoalem Arage
  • Free Rhiot Alemu
  • Free Aberash Berta
  • Free all political prisoners in Ethiopia
  • Stop Killing Ethiopians
  • Stop Arresting Journalists
  • Stop Genocide in Ethiopia
  • We oppose recent killings of Oromo students in Ethiopia
  • Stop selling Ethiopia’ s land for Arabs and others
  • ሕዝብ ማፈናቀሉ ይቁም
  • በደም ገንዘብ ስፖርት ማካሄድ አይቻልም
  • በእስፖርት ስም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይታለልም
  • ሚኒሶታ ለሕዝብ ጠላት መሸሸጊያ አትሆንም
  • አንድ ነን አንከፋፈልም
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል
  • በባዶ ስታደየም ጫወታ የለም። ወያኔን ሕዝብ እንደማይወደው ከዚህ ተማሩ
  • እናንት ተጫዋቾች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ተሰለፋ
  • የደም ገንዘብ ይቅርባችሁ
ከመዝሙሮቹ ውስጥ፡-
  • አትነሰም ወይ አትነሰም ወይ ይሕ ባንድራ ያንተ አይደለም ወይ
  • እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም
ሰልፈኛው በ4፡30 ፕም ላይ በሱተር ታርጌት ተሰብስቦ ወደፊት እቅድ ወጥቶ ተከታታይ ሰልፎች እንዲካሄዱ ወሰኖ  የሚኒሶታ ህዝብ የወያኔን ስታድየም ባዶ በማደረጉ ምስጋና አቅርቧል። በስብሰባው የተገኘው ሰልፈኛ በሚኒሶታ የሚገኙት  ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ከእነዚህ የወያኔ ከፋፈይ ቡድኖች ጋር በማንኛውም ጉዳይ ትብብር እንዳይደርግ  በአክብሮትና በወያኔ እየተበደለ ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ጠይቋል። ዘረኞቹ መገለል ይኖርባቸዋል።ወደፊት  በሚካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች የሚኒሶታ ሕዝብ እንዲገኝ በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረ ኃይል

ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።
በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረኃይል













http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31807



Sunday, June 29, 2014

የዞን 9 ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – ‹‹ያለ ፈቃድ መሬቱንም ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ፖሊስ


ጌታቸው ሽፈራው ከአዲስ አበባ

የጦማሪያኑን የፍርድ ውሎ የሚከታተለው ሰው ዛሬም እንደወትሮው በጠዋት ነው የተገኘው፡፡ አራት ሰዓት ካለፈ በኋላ የጦማሪያኑ ጠበቃ ‹‹መዝገብ ቤቷ ስለሌለች ነገ ከሰዓት ተብሏል›› ብለው ሲነግሩን በርካታ ህዝብ በተገኘበት አንዲት መዝገብ ቤት በመቅረቷ ብቻ የፍርድ ውሎው እንዲራዘም መደረጉ ገርሞን ስለጉዳዩ እያወራን ለጥቂት ደቂቃዎች ግቢው ውስጥ ቆየን፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እየመጡ ነው ተባለ፡፡

የውሎው ትዕይንት እዚህ ላይ ነው የተጀመረው፡፡

ሶስቱም ጦማሪያን ሲመጡ ህዝቡ በጭብጨባ ተቀበላቸው፡፡ በድንገት እዚህ እዚያ የሚራወጡት ፖሊሶች ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ በመምጣት የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አባል የሆነችውን ምኞት መኮንንን ‹‹ፎቶ ግራፍ አንስተሻል፡፡›› በሚል ማንገላላት ጀመሩ፡፡ በኃይል እየጎተቱ ሲወስዷትም ዮናታን ተስፋዬ ‹‹እኔን ውሰዱኝ›› ብሎ ምኞትን በኃይል እየገፈተሩ የሚወስዱት ፖሊሶች መሃል ገባ፡፡ ፖሊስ ግን እሱንም ማንገላላት ጀመረ፡፡ እሱንም አብረው ወሰዱት፡፡ ምኞትና ዮናታን ጦማሪያኑን ተከትለው ችሎቱ ወደሚገኝበት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ ፖሊሶቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስፈራራት ጀመሩ፡፡


ፖሊሶቹ ከሚመጡበት በኩል የርዕዮት ዓለሙ አባት ጠበቃ አለሙ፣ እህቷ እስከዳር አለሙ፣ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ፣ 6 ያህል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት አባላትና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ‹‹ወዴት ነው የምንሄደው?›› በሚል እንደማይወጡ አሳወቁ፡፡ ፖሊሶቹ ‹‹ታዘነ ነው፡፡ ትወጡ እንደሆነ ውጡ!›› እያሉ ማስፈራራት ጀመሩ፡፡ ከፊት ያሉት ሰዎች ‹‹ችሎት መከታተል መብታችን ነው!›› ብለው አንወጣም ሲሏቸው እነ ምኞት ላይ የተወሰደውን እርምጃ ትክክለኛነት ለመግለጽ ፎቶ ማንሳት ክልክል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ማስፈራራት ቀጠሉ፡፡ በተለይ አንዱ ፖሊስ ‹‹ያለ ፈቃድ ፎቶ ማንሳት አይቻልም፡፡ ሳይፈቀድ መሬቱንም ቢሆን ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ያለበት ሁሉንም ያስገረመ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ አባባል የተሰበሰበው ሁሉ እያረረም ቢሆን ፈገግ ብሎበታል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31764

ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ



አማራዎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን አሉ

ከምእራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ ወረዳ እንዲሁም ከቀሌም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከአካባቢው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ፣ ችግራቸውን ለአማራ ክልል ርእሰ ማስተዳድር እንዲሁም ለፌደራሉ መንግስት ቢያመለክቱም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም።

ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል
የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።

በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።
በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።

ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።


በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31736

Thursday, June 26, 2014

በመቀሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

june 26th,2014
ሰኔ ቅዳሜ 21 ቀን ፣ በመቀሌ ከተማ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠራ፣ የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ ገለጹ። ሰልፉ በከተማዋ አስተዳደር እውቅና እንዳገኘ የገለጹት አቶ አብርሃ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከተሞች እንደታየው የመቀሌ ሕዝብ የሕወሃት ደጋፊ እንዳልሆነ የሚያሳይበት አጋጣሚ እንደሚሆን አስረድተዋል።
«የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው» ያሉት አቶ አብርሃ ለሰላማዊ ሰልፍ አስተዳደሩ እውቅና መስጠቱ በራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ገልጸዋል።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ በ 6፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ዉስጡን ዉስጡን ቅስቀሳ የተጀመረ ሲሆን፣ የአደባባይ ቅስቀሳ ነገ አርብ ቀን ሰኔ 20፣ ፖሊሶች ካላስተጓጎሉ እንደሚደረግም ታወቋል።
ከአንድ አመት በፊት በሚሊዮኖች ድምጽ፡ለነጻነት መርህ ሥር በመቀሌ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ጠርቶ እንደነበረ ይታወቃል። በወቅቱ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና ሰጥቶ ፣ በመቀሌ የአንድነት አባላት በአደባባይ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ፣ ሰልፉ ነገ ሊደረግ ዛሬ ማታ፣ የአመራር አባላትን በሙሉ እንዲታሰሩና ለሰልፉ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች/መኪናዎች እንዲታገቱ በመደረጋቸው፣ ሰልፉ መስተጓገሉ ይታወቃል።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15043