Wednesday, May 14, 2014

በወለጋ ትናንት ምሽት የአካባቢው ተወላጅ ያልሆኑ ዜጎች ቤት ሲቃጠል አመሸ፤ ህጻናትም ተቃጥለዋል ተባለ

(-ሐበሻ) የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን ለመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የተነሱትን ሰላማዊ ጥያቄዎች የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት ሕዝብን ከሕዝብ ለማፋጀት እየተጠቀመበት እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ገለጹ። ትናንት ምሽት በወለጋ ጊምቢ የአካባቢው ተወላጅ ያልሆኑ ወገኖች በድጋሚ ሲቃጠል፣ በድንጋይ ሲወረወር እንደነበር -ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው ዜጎች የገለጹ ሲሆን ንብረቶች እና ቤቶች ሲቃጠሉ ህጻናትም የቃጠሎው ሰለባ እንደሆኑ ገልጸውልናል።

እናንተ ኦሮሞ ያልሆናችሁ ሁሉ ከሃገራችን ውጡልንበሚል ንብረታቸው እየወደመባቸው እንደሆነ የሚገልጹት እነዚሁ ኢትዮጵያውያንከሃገራችን የት እንደምንሄድ ግራ ገብቶናል፤ ያለንበት ሁኔታም በጣም አስፈሪ ነውሲሉ ገልጸዋል።
ለረዥም ዓመታት በአካባቢው ተዋልደው የኖሩት እነዚሁ ዜጎች ውጡ እየተባሉ ሲደበደቡና ንብረታቸው ሲወድም ወዴት እንደምንሄድ ስለማናውቅ በአሁኑ ወቅት ተደብቀን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት በምግብ እጦት ላይ ነን፤ ሕይወታችንም አደጋ ላይ ነውየሚሉት እነዚሁ ዜጎች በኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ስም ይህን ጥፋት የሚፈጽሙት የኦሕዴድ ካድሬዎች ናቸው ብለዋል።

ይህን ድርጊት እንዴት ኦህዴድ ፈጸመ ብላችሁ ለማመን ቻላችሁ?” በሚል ከዘ-ሐበሻ ለቀረበላቸው ጥያቄ ነዋሪዎቹ ሲመልሱከሕዝቡ ጋር ተዋልደን እና ተፋቅረን ለረዥም ዓመታት ኖረናል፤ አሁን የተነሳውን የሕዝብ ጥያቄ ከብሔር ግጭት ጋር አያይዞ ትግላቸውን ለማብረድ ሲፈልጉ እኛ የአካባቢው ተወላጅ ያልሆን ዜጎች አደጋ ላይ ወድቀናል። የኛን ንብረት በማውደም ያቃጠሉት ኦሮሞዎች ናቸው በማለት ሕዝቡን ለማበጣበጥ የታለመ ሴራ ነው ብለን እናምናለንብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሃገር ቤት ሰላማዊ ጥያቄ በማቅረብ ላይ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን በመሃከላቸው ወያኔ እጁን ከቶ እየተጠቀመባቸው ነው የሚሉት የፖለቲካ ተንታኞች በአዲስ አበባ መስፋፋት ስም የተነሳውን ተቃውሞ ከምኒልክ፣ ከቴዲ አፍሮ፣ ከአማራው ጋር እንዲያያዝ በእጅ አዙር እየሰራባቸው እንደሚገኝ ከምርጫ 97 በኋላ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ቅንጅት ላይ ያደረገውን በማስታወስ ይጠቅሳሉ።የወያኔ መንግስት በዲያስፖራ በተለያዩ ሃገራት በተጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እጁን በማስገባት ጥያቄውን የዘር ለማድረግ ሲሞክር አይተናል፤የሚሉት የፖለቲካ ተንታኞችጥያቄ ያላቸው የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ከወያኔ ድብቅ ሴራ ለመራቅ መሥራትና መጠቀሚያ እንዳይሆኑጠይቀዋል።

ሰሞኑን በአምቦናን በተለያዩ ከተሞች የተገደሉትን ዜጎችየሕወሓቱ አጋዚ ጦር እያለ ኢትዮጵያ እንደገደለች ተደርጎ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ እንዲሰማየሚደረገው ሴራ የኦሕዴድ/ሕወሓት/ኢሕአዴግ ስውር እጅ ያለባቸው ሠዎች በመሆኑ ሕዝቡ ከሌላው ኢትዮጵያውያን ወንድሙና እህቱ ጋር ተቻችችሎ እንዲኖር የትግላቸው አካሄድ በገዢው መንግስት እንዳይጠለፍ ጠይቀዋል።

በወለጋ ውስጥ ለተቃጠሉት ቤቶችና ሕፃናት ተጠያቂዎቹ የኦሕዴድ ካድሬዎች ናቸው፤ ሕዝቡም የሚገባበት አትጥቶ ለመደበቅ መገደዱ ተጠያቂ የሚሆነው ራሱ ኦህዴድ ነውየሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኦሮሞ ልሂቃን እየተደረገ ያለውን ነገር አደባባይ ወጥተው ለሕዝብ የመንግስት የዘር ፖለቲካ መጠቅሚያ እንዳይሆን ማሳወቅና ማስተማር እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30218

No comments:

Post a Comment