በራያ ዓዘቦ ወረዳ ነው። ህዝብ ማዳበርያ አንገዛም፣ ገንዘብ የለንም በሚል አቋሙ ፀንቷል። የህወሓት ባለስልጣናትም የወረዳና የጣብያ (ቀበሌ) አስተዳዳሪዎችን ህዝብ ማዳበርያ እንዲገዛ እንዲስያገድዱ ያስፈራራሉ። አንዳንድ ካድሬዎች አለቆቻቸውን ለማስደሰት ህዝብን ያስፈራራሉ፣ ያስገድዳሉ። አብዛኞቹ ደግሞ የህዝብን ችግር፣ ጭቆናና በደል ተረድተው ከህዝብ ጎን ይሰለፋሉ።
በራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ ለማሳመን (ለማስፈራራት) ማስፈራርያ የሚደርስባቸው አስተዳዳሪዎች ህዝብን ማስፈራራቱ ሰልችቷቸው ህዝብን አናስገድድም ብለው ከህወሓት ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝብን ችግር መረዳትን መርጠዋል። በዚህ ምክንያት ከአለቆቻቸው ጋር ተጣልተዋል። በመጣላታቸው ምክንያት ዓረና ገብቶብናል በሚል ምክንያት አስሯቸዋል።
ዓረና ናቸው ተብለው ዛሬ ሓሙስ ሰኔ 6, 2006 ዓም ከቀኑ 4:00 የታሰሩ የወረዳው 13 አስተዳዳሪዎች (የተወሰኑ የጣብያና የቁሸት ይገኙባቸዋል) የሚከተሉት ናቸው።
1) አቶ ኢያሱ ሞላ
2) አቶ ጥዑማይ ሻምበል
3) አቶ አሰፋ ገብረየሱስ
4) አቶ ወልዱ ተስፋይ
5) አቶ አወል መሓመድ
6) አቶ ሓዲስ ጣሰው
7) አቶ በየነ ተበጀ
8) አቶ ፈረደ ሞላ
9) አቶ ኪሮስ ስዩም
10) አቶ ተስፋይ ካሳዬ
11) አቶ ሞገስ ቸኮለ
12) አቶ ሻረው አጠና
13) አቶ አሸናፊ ቀሺ ናቸው።
2) አቶ ጥዑማይ ሻምበል
3) አቶ አሰፋ ገብረየሱስ
4) አቶ ወልዱ ተስፋይ
5) አቶ አወል መሓመድ
6) አቶ ሓዲስ ጣሰው
7) አቶ በየነ ተበጀ
8) አቶ ፈረደ ሞላ
9) አቶ ኪሮስ ስዩም
10) አቶ ተስፋይ ካሳዬ
11) አቶ ሞገስ ቸኮለ
12) አቶ ሻረው አጠና
13) አቶ አሸናፊ ቀሺ ናቸው።
እነዚህ አስተዳዳሪዎች በሓዱሽ ቅኚ ጣብያ ባንደራ በተባለ የገጠር ከተማ ታስረው ይገኛሉ። አስተዳዳሪዎቹ የታሰሩት ዓረና ስለሆኑ ነው ከህዝብ ጋር ወግነው ህዝብን ማዳበርያ እንዲገዛ አናስገድድም ብለው አሻፈረን ያሉ በሚል ምክንያት ነው።
ድሮ የህወሓት አባል መሆን የሚያሳስር ወንጀል ነበረ። አሁንም የዓረና አባል መሆን ያው የሚያሳስር ወንጀል ሆነ። ልዩነቱ ግን ህወሓት ሕገወጥ ዓማፂ ድርጅት ነበር፤ ዓረና ግን ሕጋዊ ሰለማዊ ድርጅት ነው።
የነፃነት ትግሉ ይቀጥላል። ታጋዮችን በማሳሰር ትግላችን አይደናቀፍም። ህዝብ ሙሉ ሊታሰር አይችልምና።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/14871
No comments:
Post a Comment