Saturday, June 21, 2014

ፖሊስ በሐዋሳ ከተማ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አሰረ- የታሰሩትንም ደህንነት ማወቅ አልተቻለም


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በራሪ ወረቀት በማደል ፤ ፖስተር በመለጠፍና በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላትን በሙሉ አስሯል፡፡ በሞንታርቦ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)በነገው እለት በሀዋሳ ሀተማ ለሚያደርገውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ፖስተር በመለጠፍ፡በራሪ ወረቀት በማደልና በሞንታርቦ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተይዘው በተለያዩ በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዊች የሚገኙ ቢሆንም ማንም እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም፡፡የሀዋሳ ከተማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ስማቸውን መግለፅ እንደማይፈልጉና ማንም መጠየቅ እንደማይችል እንዲሁም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርን ስለሁኔታው ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡


በእስር ላይ የሚገኙት አባላት የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በነገው እለት ማለትም ሰኔ 15/2006 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ በፖሊስ ተይዘው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመሀል ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም በባህል አዳራሽ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ የአንድነት አባላት ከማንም ጋር እንዳይገናኙ የሞባይል ስልካቸውን ተቀሙ፡፡ከስልካቸው በተጨማሪም በራሪ ወረቀቶቻቸውን ፖሊስ በሀይል ቀምተዋል፡፡





http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31478




No comments:

Post a Comment