Tuesday, March 31, 2015

በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡ ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡

1.ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡

2.በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል:-
“የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡

3.እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል::

ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡

4.አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

5.አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

6.ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡

በተቃራኒው ምሳቸውን ችሎት ውስጥ የተመገቡት ሁሉም እስረኞች በጠንካራ መንፈስ ሆነው ሲጨዋወቱ እና ሲነጋገሩ ተስተውለዋል፡፡ የችሎቱ ተሳታፌዎች በምስክሮች መደናበር እየሳቁ ነበረ ሲሆን የዞን9 ወዳጆች አጋሮች ቤተሰብና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

የዞን 9 ማስታወሻ

የዛሬውን አስቂኝ የፍርድ ቤት ውሎ ባልተካደ ነገር ላይ ወርቃማውን የተከሳሾች ሰአትም ሆነ የፍርድ ቤቱን የስራ ሰአት ማባከኑ የሚገርም ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ችሎቱ በግልጽ አንዲካሄድ መፍቀዱን በበጉ መልኩ ተመልክተነዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምስክሮቹ ደህንነት ሳይሆን የራሱን መዋረድ ለመቀነስ ሲል ችሎቱን በዝግ ለማድረግ መሞከሩ ተከትሎ የመጣውም የምስክሮች መወዛገብ ግልጽ የሚያደርገው ነው ፡፡ የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ በተለያየ ቦታ የጻፏቸው የራሳቸው እና የሎሎች የአደባባይ ምሁራን ጽሁፎች በመሆናቸው ጽሁፉ የእኛ መሆኑ ምስክር አያሻውም ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልነው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የታሰሩት ወጣቶች ክስ የጸፉት ጽሁፍ ይዘት ላይ ነው፡፡ የታሰሩ ወዳጆቻችንን ለመፍታት አሁንም አልረፈደም ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለሚያሳዬ የዞን9 ወዳጆች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ይከበር ፡፡

Source: ዞን9

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40181

Monday, March 30, 2015

የእነብርሃኑ፣ ፍቅረማርምና እየሩሳሌም የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል


በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ሶስቱም ወጣት ተጠርጣሪዎች ችሎት ከመግባታቸው በፊት ሳቅ እና ፈገግ እያሉ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውሏል፡፡ ብርሃኑና ፍቅረማሪያም የአንገት ልብስ (ስካርፍ) ያደረጉ ሲሆን እየሩሳሌም ጥቁር እስከርፍ አድርጋ ነበር፡፡

በመጀመሪያ ወደ ችሎት ተጠርተው የገቡት ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌም ሲሆኑ ከጠበቃ ዳዊት ነጋሽ በስተቀር ማንም መግባት አልቻለም ነበር፡፡ [እኔና ጥቂት ሰዎች ግን ከችሎቱ በር ትንሽ ርቀት ላይ ቆመን የፍርድ ቤት ሂደቱን ለማየት ጥረት አድርገገን በመጠኑ ተሳክቶልናል]

ጠበቃ ዳዊት ከችሎት በኋላ እንደነገሩን ከሆነ፣ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ አለመጨረሳቸውን፣ ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና ይሄንንም በማጣራት ላይ እንደሚገኙ፣ የቴክኒክ መረጃዎች (የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ) እንደሚቀራቸው፣ ለሽብር ተግባር ብር ሲቀበሉ እና ሲልኩ የነበረውን የባንክ ቤት መረጃ እየተከታተሉ መሆናቸውና ቢለቀቁ መረጃዎችን ሊያጠፉ ስለሚችሉ የተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡


ጠበቃ ዳዊትም መርማሪ ፖሊስ ይቀሩናል ሲል ለፍርድ ቤቱ ያቀረባቸው መረጃዎች ከተጠርጣሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ ሆነው በቃላሉ የሚገኙ ስለሆነ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤትን ጠይቆ ነበር፡፡ ጠበቃው ምክንያቱን ሲያብራራም፣ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ መረጃዎችን ፖሊስ እስከአሁን ሊያገናቸው ይችል እንደነበረ፣ ከባንክ የሚገኝ መረጃም በአጭር ቀናት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን፣ ግብረ አበሮች አሉ ከተባለም ግብረአበሮች የሚያዙት ተጠርጣሪዎችን በመያዝ አለመሆኑና ተጠርጣሪዎቹ ቢለቀቁም የተለየ ነገር እንደማይመጣ ተናግሯል፡፡

መርማሪ ፖሊስም ‹‹የጦር መሳሪያ ተይዟል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከእስር ቢለቀቁ ወደኤርትራ ሰው ወደመመልመል ስራቸው ይመለሳሉ›› የሚል ተቃውሞ በማሰማት የጦር መሳሪያ የታጠቀ የሰው ምስል ለችሎት ማሳየቱንና መሳሪያ የያዘው ግለሰብ ማን እንደሆነ በግልጽ እንደማይታይ ለዚህ ዜና ዘጋቢ ገልጾለታል፡፡

ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌምም ቃላቸውን፣ የፌስ ቡክና ሌሎች መረጃዎችን በምርመራ ወቅት ለፖሊስ መስጠታቸውን፣ መሳሪያ ከተባለው ነገር ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩንና ይሄም በግልጽ እንደሚታወቅ በመግለጽ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› የሚል ሀሳባቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በኋላ ብርሃኑ ተክለያሬድ ከጠበቃ ዳዊት ጋር ወደ ችሎት ገባ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ፣ ብርሃኑ ላይም ‹‹የጦር መሳሪያ ተገኝቷል›› የሚለውን ቃል ሳይደግም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ያረቀበውን ሀሳብ ለችሎቱ ማስረዳቱን ጠበቃ ዳዊት ይናገራሉ፡፡ ጠበቃውም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ያቀበረቡትን የተቃውሞ ሀሳብ ለብርሃኑም አቅርበዋል፡፡

ብርሃኑም በበኩሉ ‹‹ቃላችንን ለፖሊስና ለፍርድ ቤቱ ሰጥተናል፡፡ የቀረ ነገር የለም፡፡ የእስር ሁኔታችን ከህግ አግባብ ውጪ ነው፡፡ ‹‹ጨለማ ክፍል›› በሚባለው እስር ቤት መብራት 24 ሰዓት ይበራል፡፡፡ እኔ የዓይን ችግር አለብኝ፡፡ በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው ከታሰርኩበት ክፍል ወደ ደጅ የምወጣው፡፡ ቤተሰብና የህግ ጠበቃ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ከጠበቃ ጋር ሳልማከር ነው ቃሌን ለፖሊስ የሰጠሁት፡፡ የመብት ጥሰት አለ፡፡ ቤተሰቦቻችንን፣ ጠበቃና ጠያቂዎቻችንን መግኘት ይፈቀድልን፡፡ ሌሎች ከእኔ ጋር የታሰሩ እስረኞች ግን ቤተሰቦቻቸው ሲመጡ ለጥየቃ ይወጣሉ፡፡ በዚህ ላይ ትዕዛዝ ይሰጥበት፡፡ …መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ብሏል፡፡

[የዚህ ዜና ዘጋቢም ብርሃኑ ድምጹን ከፍ አድርጎ አቤቱታውን ለችሎቱ ሲያቀርብ በከፊል ለማየትና ለመስማት ችሏል]
የችሎቱ ሴት ዳኛም የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንዳለበት ጠቁመው፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከሃይማኖት አባቶቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚል ትዕዛዝ በቃል ሰጥተው በብርሃኑም ላይ የ28 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሠጥተዋል፡፡
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17698

Sunday, March 29, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባው ሰልፍ በህወሃት ፖሊስ በሀይል ተቋርጧል

የሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መንገድ ለማስቀየስ የሞከረው ወያኔ አልተሳካለትም::
         የ‹‹ነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› ዝግጅት

በየከተማው የሚገኙ ሰልፈኞች ሰልፉን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
በደብረ ብርሃን ከተማ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ቅስቀሳውን አጠናክረው ያረፈዱ ሲሆን መነሻው አንኮቨር መገንጠያ፣ መድረሻው ዘራአያቆብ አደባባይ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ በደሴ፣ በአርባ ምንጭ፣ በደብረ ታቦር፣ በጭሮና በጅማ ሰልፈኞቹ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የአርባ ምንጩ ጋሞ አደባባይ ላይ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

ገረ ኢትዮጵያ 

በአዲስ አበባ የሰማያዊ ጽ/ቤት ሰልፈኞቹ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
በየከተማው የሚገኙ ሰልፈኞች ሰልፉን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
በደብረ ብርሃን ከተማ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ቅስቀሳውን አጠናክረው ያረፈዱ ሲሆን መነሻው አንኮቨር መገንጠያ፣ መድረሻው ዘራአያቆብ አደባባይ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ በደሴ፣ በአርባ ምንጭ፣ በደብረ ታቦር፣ በጭሮና በጅማ ሰልፈኞቹ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የአርባ ምንጩ ጋሞ አደባባይ ላይ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡
በአዲስ አበባ የሰማያዊ ጽ/ቤት ሰልፈኞቹ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ነፃነት! ነፃነት! ፍትሕ! ፍትሕ!
      የአዲስ አበባው ሰልፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ጀምሯል!



የአዲስ አበባውን ሰልፍ ፖሊስ በቤተ መንግስት በኩል ማለፍ አይችልም በሚል ካሳንቺስ ላይ ለማስቆም እየጣረ ነው፡፡
ሰልፈኞቹ መፈክር በማሰማት ላይ ናቸው! ድል የህዝብ ነው! ድል የህዝብ ነው! ድል የህዝብ ነው!







ፖሊስ ሰልፈኛው ወደ ቤተ መንግስት እንዳያልፍ ሲያስቆም!
ፖሊስ ሰልፈኛውን ሲያስቆም!



ፖሊስ ሰልፈኛውን በቤተ መንግስት በኩል እንዳያልፍ አስመልሶታል፡፡


http://satenaw.com/amharic/archives/5723

















የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)ድምፅ ፍኖተ ዴሞክራሲ አንድነት ድምጽ ስርጭቱን በሳተላይት (April 1, 2015) ይጀምራል

                                                                                                  መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም March 27, 2015

         ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ስርጭቱን በሳተላይት ይጀምራል
ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያና በጎረቤት አገሮች ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአጭር ሞገድ እንዲሁም በመላው ዓለም ለሚገኙ አድማጮቹ በኢንተርኔት ፕሮግራሞችን ሲያስተላልፍ የቆየ መሆኑ ይታወሳል። ስርጭቱን በአንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ ከሚቀጥለው መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 1, 2015) የራዲዮ ፕሮግራሙን በሳተላይት አማካይነት ማሰራጨት ይጀምራል። ይህን የሳተላይት ስርጭት በተግባር እንዲውል ትብብርና ርዳታ ላደረጋችሁልን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እየገለጽን የራዲዮ ፕርግራሙ የሚተላለፍበት የሳተላይት የስርጭት መስመር የሚከተለው መሆኑን እንገልጻለን። Satellite : Nilesat
Azimuth : 7 deg West
 Frequency : 11.595 MHz
Polarisation : Vertical
Symbol rate : 27500
FEC : 3/4
Channel Name : Finote Democracy

 የኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ማንም ሊገድበው አይችልም!

ድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው !

file:///C:/Users/dawitz/Desktop/PUBLIC%20%20NOTUCE%20ON%20%20SATALLITE.pdf

Thursday, March 26, 2015

ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም  አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውና አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ነገም አይቀበልም ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።

ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባታል ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖች መናገር እንጂ መስማት የማችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝብ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው  ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

ለሚነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች እስር፤ አፈናና ግድያ ከሆነ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው። በእስር ፤በአፈናና በግድያ እንዲሁም በሰራዊት ሀይል ህዝብን በማሸማቀቅ በስልጣን መቆየት የሚቻል ቢሆን ደርግም ከቤተ-መንግስት ባልወጣ፤ ወያኔም ዛሬ ከቤተ-መንግስቱ ባልተንፈላሰሰ ነበር። ይህ ደግሞ ሊያስተምር በተገባ ነበር።

እስከ ዛሬ የትኛውም አንባገነን ስርአት በሚተማመንበት የወታደራዊ ሀይል አማካይነት የመንኮታኮቻቸውን ሰአት በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት የቻለ እንደሌለ ሁሉ ወያኔም ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል ሲያርመሰምስ ውሎ ቢያድር ውድቀቱን በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት እንደማይችል በተለይ እንቢለነፃነቴ፤ እንቢ ለሀገሬ ብለን ለትግል የተነሳን ሀይሎች በመረዳት፤ ይበልጡኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀጣጠለ ያለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይበልጥ እያሰፋን የጀመርነውን የነፃነት ጉዞ ከነፃነታችን አደባባይ ለማድረስ ሌት ተቀን የመስራት ሀላፊነታችናና መወጣት ይገባናል።

በጎንደር የሚታየውን የአልገዛም ባይነት ትንቅንቅ በሌሎች ክልሎችም በማቀጣጠል፤ በደብረወርቅ የታየውን የመምህራን የስራ ማቆም አድማ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት፤ እንደ ድምፃችን ይሰማ ሁሉ ተቃውሞን ወደ እንቢተኝነት በማሸጋገር  ወዘተ የነፃነታችንን ቀን ለማቅረብ መከፈል የሚገባውን መክፈል ይገባናል።


በደርግ ጊ የተነሳው እንቢተኝነት እያየለ ሲመጣ ያሰለፈው ሰራዊት ወያኔን አጅቦ የደርግን ቀብር እንደቆፈረለት ሁሉ ዛሬም በወያኔ ላይ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ እንቢተኝነት እየጠነከረ በመጣ ቁጥር የደረደረው ሰራዊት የወያኔን ቀብር ቆፋሪ ከመሆኑ እንደማይመለስ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን በመማር ነፃነታችንን ለማስከበር የጀመርነውን የእንቢተኝነት ትግል ላው የሀገራችን ክፍሎች በማስፋትና በማቀጣጠል አይቀሬውን የወ ቀብር ለማቅረብ በአንድነት የነፃነት ጉዞውን እንቀላቀል። የጀመርነው የነፃነት ጉዞ መቆሚያው የነፃነታችን አደባባይ መሆኑን በተግባር ከምናሳይበት ወቅት ላይ እንገኛለንና በአንድነት እንነሳ !!

ኢትዬጵያ ለዘላለም ትኑር

http://www.ginbot7.org/2015/03/26/%E1%8C%89%E1%8B%9E%E1%8A%A0%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8A%90%E1%8D%83%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%88%98%E1%8B%B3%E1%88%A8%E1%88%BB%E1%89%BD%E1%8A%95%E1%88%9D-%E1%8B%A8/

Tuesday, March 24, 2015

(ዜና ፎቶ) የኦሮሞን ሕዝብ “ልክ እናስገባዋለን” ያሉት አባይ ጸሐዬ በኦህዴድ ስብሰባ ላይ እንቅልፋቸውን ተኙ

በቅርቡ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ማስፋፋት ተከትሎ የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞና መንግስታቸው ሕዝቡን በመግደል ጭምር እርምጃ በመውሰድ ተቃውሞውን ለማርገብ የሞከሩት የሕወሓቱ ቁልፍ ሰው አባይ ጸሐዬ ካሁን በኋላ የኦሮሞ ሕዝብ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ጥያቄ ቢያነሳ “ልክ እናስገባዋለን; ያሰብነውንም እናደርጋለን” ማለታቸው በድምጽ ወጥቶ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ እና በተለያዩ ድረገጾች ላይ መውጣቱ አይዘነጋም:: ሕወሓቱ አባይ ጸሀዬ ከኦህዴድ አመራሮች ጀርባ ሆነው የኦሮሚያ ክልልን የሚያሽከረክር ሲሆን ሰሞኑን ኦህዴድ 25ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዓል ተገኝተው ነበር:: አባይ ጸሐዬ ሕዝቡን ልክ እናስገባዋለን ማለታቸው ሳያንስ የንቀታቸው ንቀት በስብሰባው ላይ የኦህዴድ አመራሮች ንግግር ሲያደርጉ እንቅልፋቸውን ለጥጠውታል:: ይህም በፎቶ ግራፍ ተደግፎ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል:: ተካፈሏቸው

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39987


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39987


የጦማርያንና ጋዜጠኞቹ አቤቱታዎች ውድቅ ተደረገ

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሦስቱ ወዳጅ ጋዜጠኞች መጋቢት 15/2007 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡

መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች ባቀረቧቸው ሁለት አቤቱታዎች ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም አንደኛ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ካለው ማስረጃ ዝርዝር ውስጥ 12 የኦዲዮ-ቪዲዮ ሲዲዎች አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች እስካሁን ባለመድረሳቸው ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማስረጃ ተመልክተው መልስ ለማዘጋጀት ሲዲዎቹ እንዲሰጧቸው ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ 4ኛ ተከሳሽ ማህሌት ፋንታሁን እና 9ኛ ተከሳሽ ኤዶም ካሳዬ በቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ ከጎብኝዎቻቸው መከልከል ጋር በተያያዘ አቅርበውት በነበረው አቤቱታ ላይ ብይን መስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡

የሲዲ ማስረጃውን በተመለከተ አቃቤ ህግ ማስረጃዎችን ኢግዚቪት ብሎ ስላስመዘገበ አሁን በዚህ ደረጃ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች የሚደርሱበት አግባብ የለም በሚል ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን አቤቱታ እንዳልተቀበለው ገልጹዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ማስረጃ በመስማት ሂደት ወቅት ማስረጃዎችን እየተመለከቱ መልስ እንዲሰጡ እንጂ ቀድሞ እጃቸው የሚደርስበት አሰራር የለም ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡


ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ በሁለቱ ሴት ተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታም ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታ እና የእስር ቤቱ አስተዳደር የሰጠውን መልስ መመልከቱን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ‹‹ለቀረበው አቤቱታ ማስረጃ ተያይዞ ያልቀረበ በመሆኑ…›› በሚል አቤቱታውን ቅድቅ አድርጓል፡፡ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰኞ መጋቢት 21/2007 ጀምሮ ለሦሰት ቀናት ይሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39984

Monday, March 23, 2015

የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።

ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና አዲሱ የተባሉ ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ የልዩ ሃይል አባል
የሆነው እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። 

ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት ሃይሎች ተገድሏል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ  አካባቢውን ጥለው  
መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት 
አልተሳካም ። 

http://satenaw.com/amharic/archives/5502

Saturday, March 21, 2015

9 ፓርቲዎች በ15 ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ
• ሰልፉ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ይደረጋል

የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ፡፡ ትብብሩ በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ቀደም ብሎ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር መጋቢት 20/2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፉን የሚያካሂድባቸው ከተሞች የሚከተሉት ሆነዋል፡፡ እነዚህም አዳማ፣ ባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ደብረ ታቦር፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልቂጤ፣ አሰበ ተፈሪ (ጭሮ)፣ ወላይታ ሶዶ፣ ደሴ፣ ዱራሜ፣ ደብረ ማርቆስ እና ሆሳዕና ናቸው፡፡

ትብብሩ ‹‹መጋቢት 20 በፍጹም አይቀርም›› በሚል ለህዝቡ የድጋፍ ሰልፍ ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ ከተሞቹ የተመረጡትም ፓርቲዎቹ በየአካባቢዎች ባቀረቡት እጩ ብዛት መሰረት እንደሆነ ገልጹዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በተመረጡት ከተሞች የሚደረገው ሰልፍ በተከናወነ በሳምንቱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39908

Friday, March 20, 2015

እናቶችን የሚያስለቅስ አገዛዝ

March 20th, 2015

የካቲት 10/2007 ዓም የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት የነዘመነ ምህረት ችሎት፣ በቀጠሮው መሠረት፣ ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓም ተሰይሟ። ዘመነ ምህረት፣ መለሰ መንገሻና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በማእከላዊ ፓሊሶች ታጅበው 8:ሰአት 20 አካባቢ ፍርድ ቤት ግቢ ገቡ። እንደተለመደው በርቀት እጃቻችንን በማውለብለብ ሰላም አልናቸው። እነሱም ባልታሰረው እጃቸው አፀፋውን መለሱልን።


ዘመነ ምህረት ብዙም አልተጎሳቆለም። መለሰ መንገሻ ግን በጣም ከስቷል። ሰውነቱ ቢጫ ሆኗል። እንደዛም ሆኖ ፈገግታ ግን አልተለያቸው። ችሎት ከመግባታቸው በፊት የተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ላይ ሆነው፣ በምልክት ለመነጋገር ሞክረን ለመግባባት ችለን ነበር። ነገር ግን ፓሊሶች ከኛ ጋር የሚያደርጉት የምልክት መግባባት አይተው፣ ፊታቸውን አዙረው አስቀመጧቸው ። ተስፋ ሳንቆርጥ ሞከርን። አልተሳካም።


የችሎት ሁኔታ እንደሚታወቀው በዝግ የታየ በመሆኑ የነበረውን ሁኔታ ማወቅ አይቻልም። ዘመነና መለሰ መንገሻ ችሎት የገቡት ተለያይተው ነው። ከዚህ መረዳት የሚቻለው የተከሰሱበት መዝገብ ይለያያል ማለት ነው ። ሁለቱም ችሎት ሲገቡ ሌሎች ወጣቶች አብረዋቸው ገብተዋል።


የዛሬው የችሎት ሁኔታ ተጨማሪ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፓሊስ ጠይቆ ለመጋቢት 08/7007 ዓም ተቀጥሯል።
አንድነት ዘመነ ምህረት፣ የዘመነ ምህረት የበኩር ልጅ፣ በፍርድ ቤት አልተገኘም። የሕጻን አንድነትን ቦታ ተክተው፣ ከሰሜን ጎንደር ተጉዘው የመጡት፣ የቆራጡ ታጋይ ዘመነ ምህረት እናት ነበሩ። እኚህ እናት ታማሚ ናቸው። የወለደ አንጀታቸው አልችል ብሏቸው ህመማቸውን ችለው፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከ700 ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው፣ «ልጄ በህይወት መኖሩን ካላየሁ አላምንም» ብለው፣ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል። በጣም ያሳዝናሉ።


የመጡበትን ምክንያት የልጃቸውን በህይወት መኖር አለመኖር ለማረጋገጥ ነበር። በካቴና ታስሮም ቢሆን አይተዋል። በውስጣቸው ምን እንደተሰማቸው ባላውቅም። ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ገብቷቸዋል። ለሰው ከመናገር ዝምታን ። ከኚህ የጀግና እናት ጋር ትንሽ ለመጨዋወት ሞክረን ነበር ። እንባቸው እየቀደማቸው ማውራት አልቻልንም። በመጦሪያቸው ጊዜ መንከራተት በጣም ያማል። እስኪ የኝህ እናት ፀሎት ተሳክቶ ዘመነ ተፈቶ ከመንከራተት 
ያድናቸው ዘንድ እንፀልይላቸው ።

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17639


Thursday, March 19, 2015

የዞን 9 ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ተቀጠሩና


ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው በእነ ሶሊያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያና ጋዜጠኞች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ቀርበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡

አቃቤ ሕግ በተከሻሾች ላይ ያቀረበው የኦዲዮ ሲዲ ማስረጃ እንዲደርሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ችሎቱ ብይኑን ስላልጨረሰ ለመጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


ጋዜጠኛው እንዳለው ሁሉም ተከሳሾች ከችሎት መጀመር በፊት እርስር በእርስ ተቀራርበው እያወጉ እና ፈገግ ሲሉ ተስተውለዋል

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39853s

136 መምህራን የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ‹‹ከአሁን በኋላ ለመምህራን ማህበርና ለአልማ አንከፍልም!››

 በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረወርቅ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 136 መምህራን ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ መምህራን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የአስተዳደር በደል ተከትሎ 92 መምህራን ‹‹እኛ በደል እየደረሰብን ቢሆን መምህራን ማህበር ችግራችን እየፈታልን ባለመሆኑ ከአሁን በኋላ አባል እንዳልሆንን እንዲታወቅ፣ በየወሩ ከደመወዛችን እንዳይቆረጥብን›› በሚል ፊርማ አስገብተዋል፡፡ ከመምህራን ማህበር በተጨማሪ በየወሩ ከደመወዛቸው ለአልማ የሚቆረጠው ገንዘብም እንዲቆም መምህራኑ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ባለፉት የመምህራን ስልጠናዎች የምስራቅ ጎጃም መምህራን ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት ማሳሰቢያ ተሰጥቶ እንደነበር የገለጹት መምህራኑ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ዘላለም ጌታነህ የወረዳው መምህራን ማህበር ፀኃፊ ከሆኑ በኋላ ጫናዎች እንደበዙባቸው ገልጸዋል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና መምህራን ማህበር ፅ/ቤት የሚሰራው አቶ ዘላለም ዕጩ መሆኑ ከታወቀ በኋላ መምህራኑ አራት ጊዜ እንዲፈርሙ የተጠየቁ ሲሆን ይህም አቶ ዘላለም ለመምህራን ማህበሩ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦና በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት እየተፈፀመ ያለ በደል ነው ብለዋል፡፡

የመምህራኑን ፊርማ ተከትሎም መጋቢት 9/2007 ዓ.ም የወረዳው ምክር ቤት 18 ያህል መምህራንን ብቻ ጠርቶ ‹‹እንወያይ›› ባለበት ወቅት መምህራኑ ‹‹ካወያያችሁ ሁላችንም አወያዩን እንጅ እኛን ብቻ ነጥላችሁ ልታወያዩን አይገባም፡፡›› በማለታቸው ምክር ቤቱና መምህራኑ ሳይግባቡ ተለያይተዋል፡፡ መምህራኑ በትናንትናው ዕለት ስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ተጠርተው ‹‹እንወያይ›› ቢባሉም በዝምታ ተቃውሟቸውን በመግለፃቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በለጠ ገሰሰ ‹‹አንወያይም ብላችሁ አምጻችኋል፡፡ ስለዚህ ነገ ስራ እንዳትገቡ፡፡ ስራ ገብታችሁ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሰው ነፍስ ቢጠፋ ተጠያቂዎቹ እናንተ ናችሁ፡፡›› በሚል እንደዛቱባቸው መምህራኑ ገልጸዋል፡፡ የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው በበኩላቸው ‹‹ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ወርም መግባት የለባቸውም›› በሚል መምህራኑ ላይ ቅጣት እንዲወሰን መጠየቃቸው ተገልጾአል፡፡

መምህራኑም ለምክር ቤቱ ‹‹በቃል የነገራችሁንን ውሳኔ በጽሁፍ ስጡን›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም ውሳኔው በጸሁፍ ሊሰጣቸው እንዳልቻለና የወረዳውን ባለስልጣናት ውሳኔ የሰሙት 136 መምህራን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የስራ ማቆም አድማው ዛሬ ጠዋት ከተጀመረ በኋላ ተማሪዎች 3፡20 ላይ ክፍል ጥለው በመውጣት መምህራኑን መደገፋቸው ተገልጾአል፡፡

ደብረወርቅ የሰማያዊ ፓር ሊቀመንበር የኢ/ር ይልቃል ጌትነት የትውልድ ቦታ መሆኑን ተከትሎ የብአዴን ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39848