(ዘ-ሐበሻ)
ብርሃኑ ተዘራ (ብሬ ላላ) ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ወቅታዊ ዘፈን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ካተረፈ በኋላ አዲስ አበባ
የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ስልኩ በደህንነቶች መጠለፉን እና በስር ዓቱ ሰዎችም ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰው እንደሚገኝ
ለድምጻዊው ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::
ጃኪ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን የደህንነት ኃይሎች ስልኩን በመጥለፍ ከማን ጋር እንደሚያወራ እንደሚከታተሉት ዘፈኑን እንዲያስተባብል ከፍተኛ ጫና እያደረጉበት መሆኑን ለድምፃዊው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል:: ጃኪ ከዚ ቀደም “ማን እንደ ሃገር” የሚል ነጠላ ዘፈን ሰርቶ የለቀቀ ሰሞን ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የድምፅአዊው የቅርብ ወዳጅ ተወዛዋዡ አብዮት መሃል ላይ ሰማያዊ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በኪሊፕ ሰርቶ ሲለቅ ጃኪም ይህን የሙዚቃ ክሊፕ ፌስቡኩ ላይ ሼር ሲያደርግ ደህንነቶች እንዴት ሕገመንግስቱ የማይፈቅደውን ባንዲራ በክሊፑ ላይ ትጠቀማለህ? በሚል ባደረሱበት ማስፈራሪያ ከፌስቡክ ገጹ ዘፈኑን ማስወጣቱን የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ወገኖች አሁንም ደህንነቶች በሚያደርሱበት ወከባ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል::
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39518
No comments:
Post a Comment