በሙስሊም ሃይማኖት ስረአት እና ደንብ መሰረት ማንዲራ ከተማ ውስጥ ማክሰኞ እለት ስርአተ ቀብሩ የተፈጸመው ሰማእቱ ሳሊህ በኬኒያ መንግስት ዘንድ እውነተኛ ብሔራዊ ጀግና የሚል ስያሚ የተሰጠው ሲሆን የሞምባሳ አካባቢ የሙስሊሞች ካውንስል ሰብሳቤ የሆኑት ሺክ ጁማ ናጎው “ፋራህ ቅዱስ ቁራን የአንደን ሰው ህይወት ማዳን የአጠቃላይ የሰው ልጅ ዘርን ማዳን ነው የሚለውን አሰተምሮትን በተግባር የፈጸመ ትክክለኛ ሙስሊም ነው ።” ብለውታል። ሰማእቱ ሳሊህ ስላደረገው ሃይማኖታዊ እና ሰብ አዊ ተጋድሎ በክርስቲያን ወገኖቹም በኩል ታላቅ አክብሮት እና አድናቆት አልተለየውም። የኬኔያ ባብቲስት ኮንቨንሽን ቤ/ክን አስተዳዳሪ የሆኑት ዊሊንግተን ሙቲሶ “ነፍሱን ሰለክርስቲያኖች ህይወት ሲል በመያዣነት ያቀረበ ታላቅ ሰማእት ፣በሞቱ የብዙዎችን የተዛባ ሃይማኖታዊ አመለካከትን የቀየረ(ሁሉም ሙስሊሞች አክራሪነትን ይደግፋሉ ተብሎ የሚወራው ፍጹም ሃሰት መሆኑን በተግባር ያሰመሰከረ) ወገናችን ፣ ክርሰቲያኖች ዘወትር የሚኮሩበት እና የሚዘክሩት ታላቅ ሰው ነው ።”ብለውታል ።
በማንዲራ አካባቢ የሮማን ካቶሊክ ቤ/ክ ሃላፊ የሆኑት ጆን ሞሶዮካ እንዲሁ” አሸባሪዎች ሃይማኖትን ሸፋን ማድረግ እንደማይችሉ ፣ሃይማኖትም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር መገናኛ እንጂ የሰዎች መከፋፈያ መሳሪያ ያለመሆኑን ወንድማችን ፋራህ በሚገባ አሰተምሮናል ።” በማለት ክርስቲያናዊ እና አባታዊ የሆነው ምስክረነታቸውን ሰጥተዋል። ራሺድ የተባለው የሳሊህ ወንድም በበኩሉ ለኬኒያው “ዘ ስታር “ጋዜጣ ሰለ ሟቹ ወንድሙ መሰዋትነት ሲገልጽ”የወንደሜ መሞት በኬኒያዎች መካከል የተለያዩ ሃይማኖተኞች እና የማህበረሰብ ክፍሎች እንዴት ተቻችለው እንደሚኖሩ መንገድ ጠራጊ ነው ብዩ ተሰፋ አደርጋለሁ።” ሲል ተናገሯል።
ሳሊህ ምንም እንኳን የጎረቤት ኬኒያ ተወላጅ ቢሆንም የከፈለው መሰዋትነት በየትኛውም ጠርዝ ይሁን በየትኛውም ስፍራ በጎሳ ፡በጽንፈኝነት እና በጠባብነት ለወደቁ ወገኖች ትልቅ ትምህርት አለው አርሱም ተቻችሎ እና ተፈቃቅሮ ለመኖር ዋንኛ መለኪያው የጎሳችን፣ የቋንቋችን፣ የሃይማኖታችን እና የእውቀታችን ግዝፈት እና ምጥቀት ወይም የውጫዊ አካላችን ልዩነት ሳይሆን ክቡር የሆነው ሰው መሆናችን ብቻውን ከበቂ በላይ መሆኑን ነው። ፈጣሪያችን እግዚአብሔር/አላህ የወንድማችን የሳሊህ ነፈሱን ይማረው !!!!።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50178
No comments:
Post a Comment