Friday, January 15, 2016

በማዕከላዊ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ የደረሰበት ሙባረክ ይመር ቂሊንጦ ውስጥ ሞተ

(ቢቢኤን) የአላህ ውሳኔ ሁኖ ወደ አኪራ የሄደው ሙባረክ ይመር ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ እንደነበር አብረውት የታሰሩት በሀዘን ገለጹ::
ሙባረክ ቁሞ መራመድ እንደማይችል እንደደከመ እየተነገራቸው ከፈለገ ተንበርክኮ ይሂድ በማለት የማረሚያ ቤት ፖሊሶች መሳለቃቸውም ታውቋል
ከ2005 ጀምሮ በአህመድ ኢንዲሪስ የክስ መዝገብ የተከሰሰው እና ከደሴ ተይዞ በግፍ በቂሊንጦ ዞን3 ቁጥር 6 ታስሮ የነበረው ወጣት ሙባረክ ይመር ወደ አኬራ ሄደ

ኢና ሊላሂ ወኢነ ኢለይሂ ራጁዑን

በ2005 ሃምሌ 4 በብሄራዊ መረጃ እና በደህንነት ሰራተኞች ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ በቂሊጦ ማረሚያ ቤት ታስሮ የነበረው ወጣት ሙባረክ ይመር በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በህክምና እጦት ሳብያ በትላንትናው 
ለሊት ወደ አኬራ ሄደ::
ወጣት ሙባረክ ይመር በአባቱ አቶ ይመር አየነ እና ከእናቱ ወ/ሮ ወርቅነሽ ንጉሴ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ከተማ 04 ቀበሌ በ1974 ተወለደ እድሜው ለትምህርት ሲደረስ እውቀት ጮራ በሚባል ትምህርት ቤት እስከ 8ኛ ክፍል ተማረ ወጣቱ ሙባረክ ይመር 1996 መርየም መሃመድ ኑር ከተባለች እህት ጋር ትዳር መስርቶ 3 የልጆች አባት ነበር።

ትላንት ጥር 5 በአባሪዎቹ ተብለው ከታሰሩት ከነ አህመድ ኢንዲሪስ ጋር በልደታው ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ከምሽቱ 5 ሰዓት ታስሮበት በሚገኘው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ዞን 3 ቀጥር 6ተኛው ቤት የማጎሪያው አዳራሽ በር በከፍተኛው በመደብደብ ፓሊሶቹ ግን የመጡት ከረጅም ግዜ ቡሃላ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ሙባረክ ይመርን ታሳሪዎቹ ተሸክመው ሊወስዱ ሲሉ ፖሊሶቹ እናንተ አትወጥም ከፈለገ ራሱ በእግሩ ይሂድ በሚል ከልክለዋል፡፡ ሙባረክ ቁሞ መራመድ እንደማይችል እንደደከመ እየተነገራቸው ከፈለገ ተንበርክኮ ይሂድ በማለት መሳለቃቸውም ታውቋል፡፡ ከብዙ ጭቅጭቅ በሁላ ሙባረክ ሊሞት ገርገራ ላይ ሆኖ ነብስ ግቢ ውጪ በደረሰበት ሰአት ላይ ወደ ክሊኒክ እንደተወሰደ ህይዎቱ ማለፉን በሀዘንታ አብረውት የታሰሩ ይገልጻሉይገልፃሉ።ቢቢኤን በምሽት ፕሮግራማችን ወጣት ሙባራክ ይመር የመጨረሻዎቹ ሰዓታትን ጨምሮ ስለ ወጣት ሙባረክ ይመር የምናቀርብላቹህ ይሆናል::


የወጣት ሙባረክ ይመር ጀናዛ በአወሊያ ከታጠበ ቡሃላ ወደ ደሴ ተወስዱዋል፡፡ በነገው እለት የቀብር ስነስርአቱ የሚፈጸም ሲሆን የደሴ ሙስሊሞችም በነቂስ በመውጣት እንዲቀብሩ ጥሪ ቀርብዋል

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50013


No comments:

Post a Comment