Monday, June 17, 2013

የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት የሚገኙበት የተቃውሞ ሰልፍ በብራሰልስ ይካሄዳል


ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
 በተለያዩ የአውርጳ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ያቋቋሙት “በአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ታስክ ፎርስ” የኢህአደግ መንግሥት  በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች  በአስቸኳይ እንዲያቆምና የዜጎችን መብት እንዲያከብር ለመጠየቅ የፊታችን ረቡዕ ጁን 19 ቀን 2013 የአውሮጳ ህብረት መቀመጫ በሆነው ብራስልስ  የህብረቱ ካውንስል ጽ/ቤት ፊት ለፊት ታላቅ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታችውን ለኢሳት ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።
የመላው አፍሪካና ካረቢያን አገራትፓርላማዎች ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ጋር በየስድስት ወሩ የሚያደርጉት የጋራ ስብሰባ በመካሄድ ላይ በሚገኝበት የብራስልስ ከተማ ፣  የአውሮጳ ፓርላማን በመወከል የህብረቱ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ አባል የሆኑትና በምርጫ 97 ወቅት በኢትዮጵያ የአውሮጳ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት  ክብርት  አና ማሪያ ጎሜዝ  ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር እንደሚገኙ ታውቆአል። ከእርሳቸው በተጨማሪ የአውሮጳ ህብረት የሚንስትሮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት ኮሚቴ ተወካይ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለመስማትና የጻፉትን ማመልከቻ ለመቀበል መመደባቸውን ።
በብራስልስ ከተማ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአፍሪካ፤ ካረቢያንና የአውሮጳ ህብረት ፓርላማዎች የጋራ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
“በአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ታስክ ፎርስ” የኢህአዴግ አገዛዝ በዘራቸው ምክንያት ከደቡብና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ስላፈናቀላቸው የአማራ ተወላጆች ጉዳይ፤ በኦጋዴን ወንድሞቻችን ላይ እየተፈጸመ ስላለው ሰቆቃ፤ በጋምቤላ፤ በአፋር ፤ በኦሮሚያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን እያፈናቀሉ መሬትን ለባዕዳን አገራት ባለሀብቶች አሳልፎ መስጠቱን ፤ በዋልድባ ገዳም መነኮሳትና በሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ላይ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት እየተፈጸመ ስላለው ወንጀሎች እንዲሁም በነጻ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጉዳይ ለአውሮጳ ህብረትና ለአባል መንግሥታት አቤቱታውን እንደሚያስገባ አስታውቆአል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ  ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጆች ገልጸዋል።
    Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment