Thursday, September 29, 2016

በጎንደር እና ጎጃም የሚታፈሱ ወጣቶች አያያዝ ከፍተኛ ስጋት በውስጡ ፈጥሯል

በደብረ ማርቆስ እና ጎንደር በርካታ ወጣቶች በአፈሳ መታሰራቸው ተነገረ፡፡ አሁንም ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት በሌለባቸው የሰሜናዊ ምዕራብ አማራ ክልል ከተሞች፣ የመንግስት ወታደሮች በተለይ ወጣቶችን በዘመቻ መልክ እያፈሱ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ ወጣቶች ለመስቀል በዓል የሚዘምሩትን የመዝሙር ግጥም እስከማስለወጥ የደረሱት የመንግስት ወታደሮች፣ በዚህም ምክንያት በነዋሪው እና በደህንነቶቹ መካከል ግጭት መከሰቱን ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

ግጭቱን ተከትሎ ቁጥራቸው በርከት ያለ ወጣቶች መታሰራቸውን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ወታደሮቹ የደመራውን በዓል ለማሰሪያነት እንደ ሰበብ ተጠቀሙበት እንጂ፣ እነማን መታሰር እናዳለባቸው አስቀድሞ ከቀበሌ አስተዳዳሪዎች ጋር መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለዚህም ነው በበዓሉ ወቅት ራሳቸው ሁከት እንዲፈጠር አድርገው ልጆቹን ያሰሯቸው›› ሲሉ ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በጎንደርም ብዙ ወጣቶች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የሰሜን ጎንደር ከተሞችም በህወሓት ጥርስ ውስጥ መግባታቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የጸጥታ ኃይሎቹ በሰሜን ጎንደር ከተሞች ሰማይ ላይ ሄሊኮፍተር እያጓሩ፣ ነዋሪውን ለማሸበር መሞከራቸውም ታውቋል፡፡ በጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች በነበረው የበዓል ስነ-ስርዓት ላይ በመንግስት ወታደሮች አስጀማሪነት በተፈጠረው ሁከት፣ በርከት ያሉ ወጣቶች ለእስር መዳረጋቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል

በአፈሳ መልክ ታስረው የተወሰዱ ሰዎች ኢሰብዓዊ በሆነ የእስር ቤት አያያዝ ስር መውደቃቸውን የገለጹት የመረጃ ምንጮች፣ ታሳሪዎቹ የሚወሰድባቸው እርምጃም ከበድ የሚል እንደሆነ መረጃዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወጣቶችን አፋር ክልል የሚገኙ የበረሃ እስር ቤቶች በመውሰድ ከባድ ቅጣት እንደሚያደርሱባቸው የገለጹት ምንጮች፣ በተወሰደባቸው እርምጃ ህይወታቸውን ያጡ ወጣቶች መኖራቸውንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ልጆቻቸውን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያ ያመሩ ወላጆችም ለጊዜው ልጆቻቸውን ማግኘት እንደማይችሉ ተነግሯቸው መመለሳቸው ታውቋል፡፡


ታፍሰው የተወሰዱ ወጣቶች በተለያዩ ማሰልጠኛ ካምፖች ትምህርት እየተሰጣቸው መሆኑን የሚገልጹት የመንግስት ኃላፊዎች፣ በታሳሪ ወጣቶች ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ዓይን ባወጣ ቅጥፈት ለማስተባበል ሞክረዋል፡፡ ከተያዙት ወጣቶች መካከል 99 ፐርሰንቶቹ የጸባይ ማረሚያ ዓይነት ትምህርት ወስደው እንደሚፈቱ የመንግስት ኃላፊዎች ቢገልጹም፣ ምንጮች ግን የታሳሪዎቹ ህይወት ከባድ አደጋ ላይ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

http://www.satenaw.com/amharic/archives/22108

Thursday, September 22, 2016

በአልሞ ተኳሽ እና በመሬት ስርቆት የታወቀው ህወሓት ለኢትዮጵያ አደጋ ተጠያቂነው አክሎግ ቢራራ (ዶር )


እኛ ጠንካራ ለመሆን የምንችለው በመተባበር ብቻ ነው፤ በተጻራሪው፤ እኛ ደካማ የምንሆነው በመከፋፈልነው። ጀሪ ሮሊንግ፤ የቀድሞው የጋና ፕሬዝደንት ዛሬ ግብጾች ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን ዘገባ ስሰማ ከዚህ በፊት ስለ ተሃድሶ ግድብ በተከታታይ ያቀረብኳቸውን ትንተናዎችና ማስጠንቀቂያዎች አስታወሰኝ። በአጭሩ ያሳሰብኩት ህወሓት/ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎና አፍኖ ይህን ለዚህ ግድብ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም የሚል ነው። መጀመሪያ፤ ህወሓት ለራሱ የበላይነት በማሰብ ብቻ፤ ታላቋን ትግራይን ለመፍጠር ባለው ህልም ብቻ፤ ኢትዮጵያን በፈጠራ የሕዝብ ስርጭት ከፋፈላት፤ መተከልን ወደ ቤን ሻንጉል፤ ብዙ የጎንደርና የወሎ አማራ መሬቶችን ምንም ውይይት ሳይደረግ፤ ፓርላማው ሳያውቅ ወደ ታላቋ ትግራይ ቀላቀለ። የትግራይ ወሰን በአንድ ጊዜ ሱዳንን አካለለ፤ ወደ ደቡብ ሄዶ ቤን ሻንጉል ደረሰ። ታላቁን የተሃድሶ ግድብ ለአደጋ በሚያመች ሁኔታ ወደ ወዳጁ ሰሜን ሱዳን አስጠጋው። የግድቡ የውሃ ፈሰስ ለሱዳኖች እንዲጠቅም አደረገ፤ አደጋውን ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሸከም ወሰነ። ህወሓቶች በበላይነት በቋንቋና በጎሳ ልዩነት ያዋቀሩት ስርዓት ዛሬ በግልጽ ለኢትዮጵያ ዋና የውጭ ጠላቶች መሳሪያ እየሆነ ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጦርነት ቢነሳ ባድሜ እንደሆነው ሕዝብን ከዳር እስከ ዳር ለመቀስቀስ አይችልም። ህወሓት ሕዝብን እየገደለ ከህወሓቶች ጋር አብሮ የሚቆም ያለ አይመስለኝም።
ሆኖም፤ የግብጾች ፕሮፓጋንዳ የሚለውን አልቀበልም። የኦሮሞ ሕዝብ ለግብጽ አጎብዳጅ አይደለም። የሚከፈለውን ዋጋ የሚያውቅ ሕዝብ ነው። የኦሮሞው፤ የአማራውና ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓትን አገዛዝ ተቃወመ እንጅ የኢትዮጵያን ነጻነት፤ ዳር ድንበር፤ አንድነትና ሉዐላዊነት አልተጻረረም። ሕዝቡ ለነጻነቱና ለአገሩ ሉዐላዊነት ከፍተኛ ቦታ ሰጥቶታል፤ እየሞተለት ነው። የህወሓቶች ክፉነት እና ጨካኝነት፤ “ ” ኢሳት እንዳቀረበው የመሬት ስርቆት ሱስ እና የአገርን ኃብት መዝረፍና ከአገር ማውጣት ዋናው ባህሪው መሆኑ በብዙ መረጃዎች ተረጋግጧል። ህወሓቶች አዲስ የመስፋፋት ካርታ ቀርጸው ወጣት ትግሬዎችን እንደሚያስተምሩ፤ የአማራውን ሕዝብ ለማድከምና ድሃ ለማድረግ የደጀን ተራራን፤ ራያና አዘቦን፤ ላሊበላን፤ የዋልድባን ገዳምና ለም መሬት፤ ወልቃይት ጠገዴና ሌሎችን ከወሰዱና ለመውሰድ ከወሰኑ አስር አመታት አልፈዋል። እስካሁን የሕዝቡን አቤቱታ የሚሰማ አልነበረም። ህወሓቶች ሰርቀውና ቀጥፈው“ ” ይቅርታ መጠየቃቸው ወደው ሳይሆን ሕዝቡ ስላስገደዳቸው ነው። ገና፤ ገና ብዙ ይቅርታ የሚጠይቁባቸው አበይት ጉዳዮች አሉ። በተለይ ግድያን በሚመለከት። ይህ ሂደት መተባበርን፤ የሕዝብ አጋር መሆንን ይጠይቃል። ያልተባበረ ሕዝብ ሁልጊዜም ተጠቂ ይሆናል። የተባበረ ግን ጊዜ ቢወስድም፤ ጥቃት ቢደርስበትም ምን ጊዜም አሸናፊ ሆኖ ይወጣል። ለዚህ ትምህርት የሚሆነኝ በጎንደር፤ በደብረ ታቦር፤ በወልቃይት ጠገዴና በሌሎች መንደሮች፤ ከተሞች፤ የገጠር ነዋሪዎችን ጨምሮ የሚደረገው አስደናቂና ብልሃት ያለው የትግል ስልት ነው። በኦሮምያም የሚደረገው ተመሳሳይ ነው። የመገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በተዘጋበትና ሁሉም በህወሓቶችና በአካባቢ ቅጥረኞች የአይን ቁራኛ ስለላ በሚካሄድበት ሁኔታ ተራው ሕዝብ የመጣው አደጋ ይምጣ፤ ያሰሩትን ይሰሩ፤ የገደሉትን ይግደሉ፤ እስር ቤቱን፤ መኖሪያ ቤቱን፤መንደሩን፤ ገበያውን፤ ድልድዩን ወዘተ ያውድሙት፤ የአፈኑትን ያፍኑ፤ ከዚህ የባሰ ምንም ሊመጣ አይችልም እያለ ሕዝባዊ እምቢተኛነቱን ሲያስተጋባ ማየት ታሪክ ሲፈጠርና ሲሰራ እንደማየት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የትምህርት ተቋሞች አይንቀሳቀሱም። አስተማሪዎች ሕዝብ እያለቀ ለምን በዚህ ጉዳይ አንነጋገርም እያሉ ነው። አንድ አስተማሪመሰለኝ እንዲህ ብሏል። እኔ ከአሁን በኋላ በፍርሃት ዓለም አልኖርም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያካሂደው ትግል አስደናቂና ታሪክን ፈጣሪ ሆኗል። በራሱ ጥበብ፤ በራሱ መሪዎች፤ በራሱ መደጋገፍ። የጎንደር ሕዝብ እቀባ አድርጎ ከራሱ ምግብ ተካፍሎ የሌላቸውን ይመግባል። ይህ ነው ታሪክ ፈጣሪ! ይህ ነው ሕዝብ አፍቃሪ! ይህ ነው ከስግብግብነት ይልቅ፤ ርህራሄ፤ ሰብእነት፤ ፍቅር፤ መንፈሳዊነት የሚገዛው ሕዝብ። ለዚህ ነው ትግሉ ችግሩን ተቋቁሞ አሁንም የቀጠለው፤ ማንም አያቆመውም። በውጭ ለምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያ ከዚህ የበለጠ ቆራጥነት፤ ጀግንነት፤ ደፋርነት፤ አገር ወዳድነት ወዘተርፈ ሊመጣልን አይችልም። ሕዝቡ ፍርሃትን ሰብሮና ቀብሮ ጨካኝነትን ለመቋቋም መነሳቱን በተከታታይ አሳይቶናል። . . . September 19, 2016, ጀምሮ የጎንደርና የጎጃም ሕዝብ ተመካክሮና ተባብሮ የኢኮኖሚ እቀባውን በቤቱ እየዋለ መቀጠሉ አስደናቂ ነው። ይህ መተባበርን፤ መቀነትን ሆነ ቀበቶን ጠበቅ ማድረግን፤ ቆራጥነትን፤ መተሳሰብን ይጠይቃል። ነጋዴው፤ የቤት ባለቤቱ፤ የመንግሥት እና የቀን ሰራተኛው፤ አስተማሪው፤ ተማሪው፤ ገበሬውና ሌላው ተባብሮ ይህን እቀባ ማድረጉ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ነጻነትና ፍትህ ለሚፈልጉ ሕዝቦች ሁሉ ከፍተኛ ትምህርት ነው እላለሁ። እኛ የማናደርገውን ተራው፤ ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ እያደረገውነው።ለምን? ብለን ራሳችን እንጠይቅ። ህወሓቶች በበላይነት የሚያሽከረክሩት ስርዓት ከሁሉም በላይ ጨካኝ፤ ለሰው ህይወት ምንም ርህራሄ እንደሌለው በየቦታው እያየን ነው። በኮንሶ የሆነው ለህሊና የሚቀፍ ነው፤ መንግሥት የሚባል ነገር እንደሌለ ያሳያል። . .. September 5-September 19, 2016 ድረስ ቢያንስ “30 ንጹህ ኢትዮጵያዊያን ተረሽነዋል፤ 1,500 በላይ የሚገመቱ ቤቶች ተቃጥለዋል።በጎንደር ከተማ እኔ በልጅነቴ የማስታውሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ያለው ገበያ ተቃጥሏል። በትላንቱ እለት ህወሓቶች ያልተቃጠለውን ሙሉ በሙሉ ለማቃጠል የትግራይ ተወላጆችን፤ አንዲት ሴት ጨምረው ልከው ለማቃጠል ሲዘጋጁ ሕዝቡ ጠቁሞ የከተማው ፖሊሶች ያዟቸው። የተረፈውን ማቃጠል የቂም በቀል ተልእኮ ነው። ህወሓት የዚህን ያክል ጨካኝና ወራዳ መሆኑ ነው። በደብረ ታቦር፤ በጎንደር፤ በባህር ዳር፤ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እስር ቤቶች ተቃጥለዋል። የፖለቲካ እስረኞች ከቃጠሎው ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ የህወሓቶች አልሞ ተኳሾች ሰለባ ሆነዋል። መረጃዎች እንደሚሉት ከሆነ በቅሊንጦ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ምክንያት የፖለቲካ እስረኞች ሆነው በዚህ እስር ቤት ህይወታቸው ያለፈው ብዙ እንደሆነ ይነገራል። ይህ የሚያሳየው ሆነ ተብሎ የአማራውን ወጣት ትውልድ ለማጥፋት የተደረገ፤ የተቀነባበረ ስራና ሴራ መሆኑን ጭምር ነው። በዐማራው ክልል በተከታታይ የሚታየው ስእል አንድና አንድ ብቻ ነው። ይኼውም፤ ህወሓቶችና የእነሱን ድርጊት ፈጻሚና አስፈጻሚ የሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች በወገኖቻቸው ላይ ወንጀል ለመፈጸም ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ነው። ከአንድ ቤት ወደ ሌላ እየሄዱ ወጣቶች ሲያፍኑ ቆይተዋል። በባህር ዳር እና አካባቢ ብቻ 11,000” በላይ የሚገመቱ የዐማራ ወጣቶች የት እንደተወሰዱ፤ ምን አደጋ እንደደረሰባቸው አይታወቅም። ሞቱ? አካላቸው ስንኩል/ ሽባ እንዲሆን ተደረጉ? በጫካና በሸለቆ ተወረወሩ፤ተቀበሩ? መርፌ ተወግተው ወይንም ለህይወታቸው፤ ለጭንቅላታቸው አደንዝዝ መድሃኔት ተሰጣቸው? የሚሉ አግባብ ያላቸው ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ቁም ነገሩ፤ የዐማራው ብሄር ተተኪ መሪዎች፤ ተተኪ ባለሞያዎች፤ ተተኪ ተቆርቋሪዎች እንዳይኖሩት እየተደረገ ነው።ህወሓቶች/ ኢህአዴጎች በወንጀል እንዳይከሰሱ ሁሉንም መረጃ ይደመስሳሉ፤ መገናኛ ብዙሃን እንዳይኖር ያደርጋሉ። በአካባቢው የሚኖረው የተማረ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ስብስብ ማድረግ ያለበት መረጃውን መሰብሰብና መደበቅ፤ ውጭ ለሚኖሩ ተቆርቋሪዎች ማስተላለፍ ነው። ይህን በሚመለከት በቅርቡ በሕዝብ ጥረት፤ ወጣቷ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ፤ ንግሥት ይርጋ የምትሰራውን ጀግንነት እና የደረሰባትን አፈናና ጭካኔ ይፋ መደረጉ በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው። ይህች ወጣት እናትሰቃይ፤ እንዳትገደል አቤቱታ ማቅረብአለብን። የሞቱትንና እንዲሰወሩ የተደረጉትን ወጣቶች ስም ዝርዝር መሰብሰብ አስፈላጊ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ህግ አንድ መንግሥት ወይንም የዚህ መንግሥት ተጠሪ የሆነ ግለሰብ ወይንም ቡድን ግለሰቦችን አስገድዶ መሰወር ሕገ ወጥ መሆኑንና በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን አስምሮበታል (Enforced disappearances are crimes against humanity). በተመሳሳይ በቅሊንጦ ከተረሸኑት መካከል ጀግናው ሻለቃ ይላቅ አሸናፊ ይገኝበታል፤ የሌሎቹን ስም ዝርዝር መሰብሰብ ወሳኝ ነው። የዐማራው ሕዝብ እልቂት ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም አሁን ያለው አደጋ የመኖር / አለመኖር፤ ማለትም የህልውና አደጋ መሆኑን መቀበል ግዴታችን ነው። ህወሓቶች በብዛት የሚጠቀሙበት የዐማራ ሕዝብ እልቂት ዘዴ አስገድዶ መሰወር ነው(enforced disappearances). ይህ የሆነበት ምክንያት የተሰወረ በምንም አይገኝም በሚል የተሳሳተ ስሌት ነው። “ ” ህወሓቶች፤ በተለይ የህወሓት መስራቾች፤ ዐማራውን አህያ ከማለት ደረጃ የደረሱብት የራሳችን ድክመት፤ ዝምታ ማብዛትና በጥቃቅን ነገሮች ለመተባበር አለመቻል ጭምር ነው። አሁንም፤ ብዙ የዐማራ ምሁራንና ባለሞያዎች ከዳር ቆመው ያያሉ፤ ምን እንደሚጠብቁ ምርምር ቢደረግ መልካም ነው። ለአሁኑ ግን እያንዳንዳችን ራሳችን መፈተሽ አለብን እላለሁ። የህወሓቶች ኤታ ማጆር ሹም ጀኔራል ሳሞራ ዩኑስለትግራይ ሕዝብ ንግግር ሲያቀርብ እንዲህ ብሏል። ህወሓት ማለት መስመር ነው! ህወሓት ከሌለ የትግራይ ሕዝብ የለም!” ይህ ብሂል የትግራይን ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መለየት መሆኑን ማሳሰብ ያለበት የትግራይ ምሁርና ሕዝብ ነው። በዚህ ሃተታ ለማሳሰብ የምፈልገው የዐማራው ሕዝብ ከሌለ፤ የኦሮሞው ሕዝብ ከሌለ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ የአማራውና የኦሮሞው ሕዝብ በወንድሞቹ፤ በእህቶቹ በትግራይ ሕዝብ ላይ አልተነሳም፤ አይነሳም፤ መነሳትም የለበትም። የሰላማዊ ሕዝብ እምቢተኛነት ኢላማ የህወሓት ጭካኔና አፋኝነት እንጅ የትግራይ ሕዝብ አለመሆኑን አምናለሁ። ቢቻል ኖሮ፤ ህወሓቶች የጣናን ኃይቅ፤ የአባይን ወንዝ ወደ ትግራይ እንደሚወስዱ መረጃዎች ብዙ ናቸው። አንድ የውጭ አገር ቱሪስት ጎንደር ከተማ ሆቴል አርፎ ምን ልታይ መጣህ? ተብሎ ሲጠየቅ ቤተ “ ” ክርስቲያኖችን፤ የፋሲልን ግንብና በትግራይ ክልል የሚገኘውን የዳሸን ተራራ ብሎ ይመልሳል። ይህ የጎንደር አንጡራ ኃብት የሆነ ተራራ ወደ ትግራይ መጠቃለሉን የማያውቅ ወጣት ገርሞት ተራራው እኮ “ ” በጎንደር እንጅ በትግራይ አይደለም ሲል እኔ የተነገረኝ ትግራይ ውስጥ መሆኑን ነው ሲል ተናግሯል።“ ” ተራራውም ይሰረቃል የሚለው ብሂል የመጣው ከዚህ ነው። የላሊበላ ገዳማት ተነጥቀው ወደ ትግራይ ተላልፈዋል፤ ነገ የፋሲለደስ ግንብ፤ በደብረ ታቦት የኢየሱስ ተራራና ቤተክርስትያን ትግሬ ነው ቢባል ምን ያስደንቃል። ወይ ጉድ! እንዴት ጎንደሬውን፤ እንዴት አማራውን ቢንቁት ነው ተራራ የሚነጥቁት የሚሉ ብዙ “ ” ናቸው። የራስ ዳሸን ትግራይነት የችግሩን ክብደት ያጠናክረዋል። የሰው ዜግነት መከበር ከተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነት ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ይህ በምንም አይነት ማባበል ሊፈታ አይችልም። በባህር ዳር ከተማ እነ በረከት ሰምኦን፤ አዲሱ ለገሰና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮነን ሕዝቡን ለማባበል ያደረጉት ሙከራ በጎንደር ከተደረገው የተለየ አይደለም። ህወሓቶችና ታዛዦቻቸው ወጣቱንእየገደሉ ግድያው እንዲቆም የራሳቸውን የበላይ አዛዥ ህወሓትንና በዐማራው ሕዝብ ላይ ማንኛውንም ” “ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ብሎ ትእዛዝ የሰጠውን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ይህ ትእዛዝበአስቸኳይ ይነሳ በማለት ፋንታ ተጠቂውን የዐማራ ሕዝብ ማነጋገራቸው ለዐማራው ሕዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳያል። በአምባ ጊዎርጊስ የተረሸኑት ወጣቶች ብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዳላቸው ምንም አልተረዱትምÉÉ በእነሱ ግምት የትግሬዎች ኃብት መቃጠል ከህይወት በላይ ሆኗል ማለት ነው። አስደናቂው ቁም ነገር ግን ይህ አይደለም። ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክፍለ ሃገር ድረስ የብአዴን አባላት፤ ዝቅተኛና መካከለኛ ኃላፊዎችወንበራችሁንአንፈልግም፤ ተረከቡን ማለታቸው ነው። ብአዴኖች፤ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ በታሪክ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ከፈለጉ የሕዝቡን ትግል ሙሉ በሙሉ መደገፍ ግዴታቸው ነው። ወገኖቻቸው እንዲገደሉ አጋር መሆን ከወንጀለኛነት አያድናቸውም፤ ተባባሪ ናቸውና። የዩንቨርስቲ አስተማሪዎች የተለመደውን የህሓት ግምገማ እንዲያዳምጡ ተጠርተው ምንም ድምጽ አንሰጥም ብለዋል። አንድ ተማሪእንዲህ ብሏል። እኔ ፈርቸ ፈርቸ ፍርሃቴ ለቆያኛል፤ ለምን አሁን ስላለው እልቂት፤ ስላለው ሁኔታአንወያይም?” የሚል ጥያቄ አቅርቧል፤ ሁሉም የሚፈልገው ጥያቄ። በተደጋጋሚ እንዳሳሰብኩት የዐማራው ወጣት ትውልድ እየታፈነ፤ እየተገደለ፤ እየቆሰለ፤ እየተራበ ነው። አስተማሪው፤ ተማሪው፤ ሰራተኛው በአንድ ላይ፤ ለአንድ ዐላማ መነሳትና መታገል አለበት። በሕዝቡ ዐመጽ ያልተሰበሰበው ህሊናውን መጠየቅ አለበት። ሆዱ ከጎንደሬው ሆድ፤ ከኦሮሞው ሆድ፤ ከኮንሶው ሆድ የተለየ አይደለም። ለአንድ ህይወት ከመሳሳት ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለዲሞክራሲ ራስን መስ ዋእት ለማድረግ መነሳት ይመረጣል። ታሪክ ስሩ። ምክንያቱም፤ ተራው የጎንደር፤ የባህር ዳር፤የደብረ ታቦር፤ የኮንሶ፤ የአዋሳ ወዘተርፈ ሕዝብ ከአሁን በኋላ በህወሓት/ ” ኢህአዴግ አንገዛም እያለ ነው። ታሪክ እንስራ፤ ሕዝቡን እንደግፍ። ተቃውሞን በዝምታ፤ ተቃውሞን በእገባ፤ ወዘተ ሲያሳዩ ችግሩ ስር የሰደደ እና ህወሓት/ “ ኢህአዴግ ሊፈታው ከማይችልበት ደራጃ መድረሱን ያሳያል። ግምገማ የሚባለው ዘዴ እኔንእመኑኝ ከማለቱ ሌላ የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር አይፈታም። የዝግ ችሎት አድርጎ ራሱን መገምገም ያለበት አፋኙ አገዛዝ ነው። ይህን አያደርግም።ለመደምደም፤ በዐማራው ሕዝብ ላይ የብሄር ማጽዳትና እልቂት የሚካሄድ መሆኑን የሚያሳይ በውጭ አገር ባለሞያ ዶኪመንተሪ ቀርቧል፤ ወደፊትም እንደሚቀርብ ይገመታል። በጉዳዩ ክብደትና ስፋት መሰረት በሙሉቀን ተስፋ መጽሃፍ ተጽፎ በአዲስ አበባ እንዳይበተን ተከልክሏል። የተከለከለበት ምክንያት ሕዝቡ ሃቁን እንዳያውቀው ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ይህን እልቂት አያውቅም የሚል ግምት የለኝም፤ “ ” ያውቃል። ይህን ጭካኔ እያወቀ ለህወሓቶች ደህንነትና ሰራዊት የግድያ ፈቃድ መስጠቱ ስርዓቱ በጠቅላላ ለሰው ህይወት ደንታ እንደሌለው በተደጋጋሚ ያሳያል። የህወሓት የስለላና የመከላከያ ኃይል 30 ሚሊየን “ ” የዐማራ ሕዝብ ለመቆጣጠር እንችላለን፤ እንኳን ለዚህ ሕዝብ ለአፍሪካም የሚመጥን ኃይል አለን ብለው ፎክረዋል። ጥናቶች የሚያሳዩት ማንም ኃላፊነት የሚሰማው አመራር በራሱ ሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማያውጅ ነው፤ ከወሰደ ህይወቱ አጭር እንደሚሆን ነው። ነገ ከትግራይ ውጭ የሕዝቡ እምቢተኛነት አገር አቀፍ ቢሆን ሕዝቡን በጀትና በሄሊኮፕተር፤ በታንክና በሌላ መሳሪያ ሊጨፈጭፉት ነው? ምን ይደረግ ?“ ” አንድነት ኃይል ነው ብለን እንነሳ!“ ” አንድ ሰው ሲገደል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መገደል ነው እያልን እናስተጋባ !“ ” አዲስ ዓመት ምንም አዲስ አይደለም ለማለት እንድፈርተራው ገዳይና ተራው ሟች ወንድማማቾች ናቸው ! ተጠያቂው ህወሓት ነው ! ለማለት እንድፈር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብትና እኩልነት አብረን እንስራ!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/66338