Wednesday, June 11, 2014

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ልዩ ስሙ ዱንቻ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቀሉ

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

በጋምቤላ ክልል ከቴፒ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ጎደሬ ልዩ ስሙ ዳንቻ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚኖሩ እና በተለያየ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አማርኛ ተናጋሪ ኢዮጵያውያንን ከሃገራችን ውጡልም በማለት ማፈናቀል መጀመሩን ከአከባቢው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከሶስት ቀን በፊት በለሰለሰ መልኩ የተጀመረው እና በመዠንገር የወያኔ ቅጥረኛ ካድሬዎች የሚመራው የማፈናቀል ድርጊት በአሁኑ ወቅት ወደ ግጭት ተለውጦ ሃይልን በመጠቀም ላይ ሲሆኑ ከአከባቢው የሚኖሩ ውጡ የተባሉ አባወራዎች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ንብረቶቻቸውን በመተው ወደ ቴፒ ከተማ እየተሰደዱ መሆኑን ታውቋል።

በዛሬው እለት የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎችን መኖሪያ እሳት በመለኮስ ያቃጠሉ ሲሆን በአከባቢው የሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና መቋረጡን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል። ትምህርት ቤቶችን እና የመንግስት መስሪያቤቶች የተዘጉ ሲሆን 3 ኦራል መኪኖች መጥቶ ከተማው እና ገጠራማ አከባቢዎች ላይ የፈሰሰው የወያኔ የጦር ሰራዊት ግጭቱን ከማባበስ ውጪ ምንም አይነት መረጋጋት ሊፈጥር ያልቻለ ሲሆን ወታደሮችን ባዩ ጊዜ የአከባቢው ካድሬዎች =ጭራሽ ብሶባቸው ዜጎችን ሲያሳድዱ ተስተውሏል። ሲሉ ምንጮቹ የላኩልን መረጃ ይጠቁማል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31155

No comments:

Post a Comment