Thursday, August 28, 2014

13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው

 Aug.28.2014
(ኢሳት ሰበር ዜና) 13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው ሲል ኢሳት በሰበር ዜናው ዘገበ።

እንደ ኢሳት ቲቪ ዘገባ አርከበ እቁባይ፣ በረከት ስምኦን፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አባይ ጸሃየ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ ሃሰን ሺፋ፣ ሙሉጌታ በርሄ፣ ነጋ በርሄ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ኮማንደር ሰመረ እና አንድ ስሙ ያልተገለጸ ሰው በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በስቃይ፣ ሰዎችን በማንገላታትና በህገወጥ መንገድ በማሰርና ሌሎችንም ተመሳሳይ ወንጀሎች በመፈጸም በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የስዊድን ታዋቂ ጠበቆች ያዘጋጁት የክስ ቻርጅ የስዊድ የአለማቀፉ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ተረክቧል።
ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንም የ130 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ካሳ መጠየቁን የዘገበው ቴሌቭዥኑ ከስዊድን አለማቀፍ የወንጀል መርማሪ ፖሊስ የተሰጠው መልስ እጅግ አስደሳች መሆኑን አዘጋጆች ለኢሳት መግለጻቸውን ዘግቧል።

የስዊድን ፖሊሶች ምርመራ መጀመራቸውን ያስታወቁ ሲሆን የክሱ አላማ በምርጫ 97 ወቅት ለተገደሉትና ለቆሰሉት ፍትህ መስጠት ነው። 

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34045

Saturday, August 23, 2014

አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት የ 7 ጋዜጠኞች (ፎቶዎች)

 


 



ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ

       ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው

የኢህአዴግ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ተከትሎ ከሀገር የተሰደዱትን የሎሚ፣ ጃኖ እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጠኞችን ፎቶ ከዚህ እንደሚከተለው ይዘን ቀርበናል፡፡
1.ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ የሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር
2. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው የአፍሮ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
3. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር
4. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ
5. ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር
6. ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር
7.ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ የጃኖ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33886

Friday, August 22, 2014

የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የዞን9 ጦማርያኑን እና የጋዜጠኞቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ

Aug.22.2014

ስድስቱን የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ማኅሌት ፋታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና አጥናፍ ብርሃነ እንዲሁም በሌለችበት ክሷ እየታየ ያለው በሶልያና ሽመልስ እንዲሁም በጋዜጠኞቹ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ በልደታ 19ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት የተሰየመ ሲሆን ከሙስሊም ኮሚቴ አመራሮች ጋር በአንድ ችሎት እንዲታደሙ በመደረጉ የታሳሪዎችን ቤተሰቦችም ሆነ ወዳጆችን ለማስተናገድ ቦታ የለም በሚል ለጋዜጠኞች ብቻ የፍርድ ሂደቱ እንዲታይ በፖሊስ ተፈቅዶ ነበር፡፡

በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ መጥሪያ በጋዜጣ መውጣቱን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የዋስትና መብትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት በአንቀጽ 3 የሽብር ተግባራት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድም ወይም ሁለትም ከዚያም በላይ ወንጀል የፈጸመ መሆኑ ወይም ለመፈጸም ያቀደ ለመሆኑ ተገልጾ ክስ ሲቀርብ ነው በተመሰረተባቸው ክስ ዋስትናን ሊያሳጣቸው የሚችለው ብለው ጠበቆቻቸው የተከራከሩ ሲሆን ደንበኞቻቸው በአዋጁ መሰረት የሰሩት የሽብር ተግባር ክስ አልቀረበባቸውም ስለዚህ በአዋጁ ተጠቀሰ ማለት በአዋጁ መሰረት ክስ ቀርቧል ማለት ስለማይቻል የዋስትናው ጥያቄ በመደበኛ ስርዓት እንጂ በጸረ­ሽብር ሕጉ መሰረት ሊታይ አይገባም፤ በተጨማሪም አዋጁ ፡፡

ዋስትና ይከለክላል ተብሎ ቢተረጎምም ከሕገ­መንግስቱ ጋር ስለሚጋጭ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ አንቀጽ ተጠቅሶ መከሰሳቸውን እንጂ በዚህ መከሰስ ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም ብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ አይገደድም እንዲሁም የጸረ­ሽብር አዋጁ ከሕገ­መንግስቱ ጋር አይጋጭም ብለዋል በዚሁም መሰረት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ተደርጎ ለጥቅምት 5 ቀን 2007ዓ.ም ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ችሎት የተጠናቀቀ ሲሆን ጠበቆቻቸውም የዋስትና ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍረድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡


ችሎት ውስጥ መግባት የቻሉት ጥቂት ጋዜጠኞች እና ጉዳዩን ለመታዘብ የተገኙ ዲፕሎማቶች ብቻ ናቸው፡፡ በቦታው በመገኘት አጋርነታችሁን ላሳያችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33827

Saturday, August 16, 2014

ወያኔ ለተቃዋሚዎች የሚያወጣው ታርጋ

17.08.2014
አምባገነኑ የወያኔ  መንግስት 1997 ዓ/ም ወጣቶችን እያፈሰ አደገኛ ቦዘኔ፣ ወንጀል ሊፈፅሙ ሲመክሩ ፣አመፅ ለመቀስቀስ ሲሞክሩ፣ ባንክ ሲዘርፉ ደረስንባቸው እያለ ሲያስር ሲገድል አይተናል::እውነት የ 11 ዓመቱ  ነብዩ ሳሙኤል  በየትኛው ጉልበቱ ነው ባንክ ሊዘርፍ ሲል ተገኝቶ ነው ተብሎ በጠራራ ፀሀይ በአረመኔዎቹ የአጋዚ ወታደሮች ልጅነቱን ዘሎ ሳይጨርስ በአጭር ያስቀሩት ??

1997 ተሻግረን ደግሞ 2002 ዓ/ም ላይ ስንደርስ አደገኛ ቦዘኔ የምትለዋን ስም በመቀየር ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ ሲሞክሩ ተያዙ አያለ ሲያስር ሲያሰቃይና ሲገድል አይተናል::

አሁን ደግሞ ምርጫ 2007 ደረሰና ከወዲሁ እንዴት አድርጌ 2007 ልሻገር ብሎ እንቅልፍ አጥቶ ሲመክር የሰነበተው የሰው በላውና አረመኔው የወያኔ መንግስት  አሸባሪ የምትለዋን ቋንቋ አሻሽሎና ፈብርኮ በማምጣት ወጣት ጀግኖች የፖለቲካ መሪዎችን ማስር ማሰቃየት ማንገላታቱን ይዞታል :::

እኛም ደግሞ ለህዝብ ሁሉ የሚጠቅም ቀና አስተሳሰብ ይዞ ክፉ አሳቢ አምባገነኖችን ማሸበር እንደሚቻል በታሰሩ ወጣት ጀግኖቻችን እያየን ትግላችንን ቀጥለናል ፣፣
 
ድል ለሰፊው ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ!!

 Posted By Dawit Demelash

Thursday, August 14, 2014

ወያኔ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል

'

አሁን በስልጣን የሚገኘው የወያኔው ስርአት ላለፉት 22 አመታት የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያለ ጆሮአችንን ቢያደነቁረውም እሱ የሚለው የዲሞክራሲ ስርዓትና ትክክለኛው ዲሞክራሲያዊ ስርአት አራምባና ቆቦ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲያዊ ስርአትን በገመድ ለክቶና መጥኖ የናንተ መብትና ነጻነት እስከመጨፈር እንጂ የኔን ስልጣንና ጥቅም የሚነካ ከሆነ ቢላ ባንገቴ ካለን ሰነባበተ:: ለዚህም ይመስላል በተለይም ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ለሚያሰሙ ጋዜጠኞችም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኙ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚለው::

ከዚህም የነጻነት እጦት እና ፍጹም አምባገነናዊ አፈናዎች መካከል እንደ አንድ ማሳያ የሚሆነው በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል ሲሆን ዛሬ በወያኔው ስርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚታዩት እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ሳይሆን ሃገርን ለማፍረስ እንደተዘጋጁ አሸባሪዎች ተደርገው ነው:: በጣም የሚያሳዝነውነና አደገኛው አካሄዱ ደግሞ ይህን እምነቱን ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምንና እንዲቀበል ፍጹም ህገወጥ በሆነና ከዕውነት በራቀ ውንጀላ ተቃዋሚዎችን ለማጠልሸት የሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግሉ ነው::

ስርዓቱ በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ተቃዋሚዎችን ለማዳከምና ለማጥፋት ፍጹም ኢ-ፍትሃዊና ህገወጥ በሆነ መልኩ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በሁለት ስትራቴጂዎች የተዋቀረ ነው::
የመጀመሪያውና ቀጥተኛው ስትራቴጂ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አሸባሪና እሱ ራሱ አሸባሪ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር ማያያዝ (ማዛመድ) ነው:: ይህንንም ለማሳካት የተቃዋሚ ድርጅት አባሎችን ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የፈጠራ ክስ መወንጀል ሲሆን በጣም በሚያሳፍርና በሚያሳዝን መልኩ በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ ይቃወሙኛል ብሎ ያሰባቸውን የነጻው ሚዲያ ጋዜጠኞችንም ይጨምራል:: እንግዲህ ይህ ስትራቴጂ የተወሰኑ ግለሰቦችን በአሸባሪነት ክስ ወደ ዘብጥያ በማውረድ ብቻ የተገታ ወይም የተቋጨ ነው ብሎ የሚያስብ የዋህ ይኖራል ብዬ አላስብም ዋናው አላማ አማራጭ ሚዲያና እውነተኛ መረጃ የተነፈገው ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በፍርሃት ውስጥ እንዲሸማቀቅና ለትክክለኛ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚኖረውን የጋለ የህዝብ ስሜት ጥቁር ጥላ እንዲያጠላበት የሚያደርግ እንጂ::

በዚህ ስትራቴጂ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔውን ስርአት የሃሰት ውንጀላ ጠንቅቆ የሚያውቅ ቢሆንም ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ አንድ ለናቱ በሆነው የገዢው ስርአት ሚዲያ በየቀኑ የሚቀርበው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ ለተቃዋሚዎች፣ ለገዢው ፓርቲም ይሁን ለጠቅላላ የፓለቲካው ድባብ የሚኖረው ስሜት በፍራቻ፣ በጥርጣሬና ቀላል በማይባል ሁኔታ በፓለቲካው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ እንዲገባ የማድረግ ሃይሉ እጅግ ከፍተኛ ነው::

ከዚህም በተጨማሪ ይህንን አደገኛ አካሄድ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ተቃዋሚዎች ምንም አይነት ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ነጻ ሚዲያ ሰለሌላቸው (ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እንኳን እንደታፈነች ነች)በፈጠራ ክስ ለታሰሩ አባሎቻቸውም ሆነ ለደረሰባቸው የመልካም ገጽታ (Good Will) መበላሸት ማስተባበያ የመስጠትም ሆነ የመከላከል አቅሙ የሌላቸው መሆኑ ነው::
ሁለተኛውና ቀጥተኛ ያልሆነው ስትራቴጂ ከመጀመሪያው ስትራቴጂ ጋር የሚያያዝ ሲሆን ተቃዋሚዎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀት ከህዝቡና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የመገናኘትና የመቀስቀስ ስራዎቻቸውን እንዳይሰሩ በእጃዙርም ይሁን ባስ ሲልም በቀጥታ የማፈንና የማሰናከል ተግባር ነው::

ይህንን እቅዱን እውን ለማድረግም ተቃዋሚዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን እንዳያገኙ የተለያዩ መሰናክሎችን መፍጠር፣ ራሳቸውን በገቢም ይሁን በተለያዩ ነገሮች ለማጠናከር የሚደረጉ ዝግጅቶችን ማስቆም፣ ማሰናከል፣ ተቃዋሚዎች የሚጠሩትን ሰላማዊ ሰልፎች አለመፍቀድ ወይም መሰረዝ፣ ምንም አይነት ነጻ ሚዲያ እንዳያገኙ መዝጋትና ሌሎችንም ዘዴዎች ይጠቀማል:፡

ሌላውን ሁሉ ትተን ዛሬ በጣም በሚሳዝን ሁኔታ በሃገራችን ለተቃዋሚዎች አንዱ ከባዱ ስራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማግኘት ነው:: ከተወሰኑ ጊዚያቶች በፊት ሰማያዊ ፓርቲ የመመስረቻ ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያደርግበት አዳራሽ አጥቶ ምን ያህል እንደተቸገረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው::ዛሬ ለአንድ ህጻን ልጅ ልደት ለማክበር እንኳን አዳራሽ በሽ በሆነበት ሃገር ተቃዋሚዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ አጥተው በሰው ቤት ጓሮ ዳስ እየጣሉ ግማሹ ተሰብሳቢ ጸሃይ እየበላው ነው ስብሰባቸውን የሚያካሂዱት:: የሆቴል ቤት ባለቤቶችና አዳራሽ አከራዮች በወያኔው ስርዓት በሚደርስባቸው ከባድ ተጸዕኖ ለተቃዋሚዎች አዳራሾቻቸውን ለማከራየት ፈቃደኞች አይደሉም::

የሃገሪቷ ሃብት በወያኔዎች እጅ በወደቀበት በዚህ ሰዓት ኣንድ የሆቴል ቤት ባለቤት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች ቢያከራይ በህብረተሰቡ ውስጥ በዘሩት የተቃዋሚዎችን ስም በሀሰት የማጠልሸት ተግባር፣ ፍራቻና የስጋት ድባብ እንዲሁም ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው በሆቴሉ ላይ በሚጀምሩት የሃሰት አሉባልታ ሆቴሉ ቀስ በቀስ ከገበያ ውጭ ሊሆን ስለሚችልና ምናልባትም ካስፈለገ ሆቴሉን እስከማሳሸግ ሊደርሱ እንደሚችሉ ስለሚታወቅ ነው ( በ1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት የመርካቶው ምዕራብ ሆቴልና ሌሎችም ሆቴሎች ተቃዋሚዎችን ትረዳላቹ ተብለው ታሽገው እንደነበር አይዘነጋም::)


እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተቃውሞው ጎራ መሰለፍ እንደ ሃገር ጠላት የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን ባስ ካለም አሸባሪ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ወህኒ ሊያስወረውር የሚያስችልበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያኖችን በነጻነት የሚፈልጉትን ደግፈው ወይም ተቃውመው መኖር እንዳይችሉ ብቻ ሳይሆን በፍርሃት እንዲሸማቀቁና እንዲሰጉ ምክንያት ሆኗል:: ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔን ስርዓት መቃወም ስትጀምር በዚያውም ወደ እስር ቤት መቃረብህን ትረዳለህ:: አንተን ለመክሰስ የማስረጃ ጉዳይ ብዙም አያስጨንቅም በኢ- ማይልህ ላይ አንዳንድ መረጃዎችን ወይም ሞባይልህ ላይ ጥቂት መልእክቶችን መላክ (SMS) ማድረግ አንተን ዘብጥያ ለማውረድ በቂ ናቸው:: ( ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከወንድሙ ጋር በኢ-ሜይል ስለአባታቸው የህክምና ኦፕሬሽን (Operation) የተጻጻፉትን ኦፕሬሽን የሚለው ቃል ሌላ አላማ ተብሎ እንደማስረጃ የቀረበበት ሁኔታን ልብ ይሏል::)

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33549

Wednesday, August 13, 2014

በነኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ የተፈጸመውን ግፍ ”በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን አልተፈጸመም”

Aug.12th.2014
(ቢቢኤን ራድዮ) የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳኞች አልተሟሉም በሚል ያልተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ለሁለቱ ዳኞች ግን እየደረሰባቸው ያለውን ነገር አህመድ ሙስጠፋና ኡስታዝ በድሩ ሁሴን በዝርዝር ማስረዳታቸው ታዉቐል፡፡ 

ቁልፍ ባለው ሰንሰለት በጨለማ ክፍል እንዳሰሩዋቸው ምግብም እንደከለከሏቸው የገለጹ ሲሆን ዳኛውም ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደዚህ ይደረጋል በዚህ ዘመን ቀርቶ በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን አይፈጸምም ነበር በማለት መኮነናቸው ታዉቐል፡፡ ዳኛውም አያይዘው እንኳን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀርቶ አስርቱ ትእዛዛት በሚፈጸሙበት ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገሮች አይደረጉም ነበር ማለታቸው ታዉቋል፡፡

ኮሚቴዎቹም አሰቃቂ ስቃይ በሚፈጸምበት በማእከላዊ እንኳን የምግብ ክልከላ እንደማይፈጸምባቸው ተናግረዋል፡፡

 ኡስታዝ በድሩ ሁሴን የታሰረበት ሰንሰለት ረዥም ጥልፍልፍ ሲሆን ዙርያ ጥምም በማሰር ቆልፈውበት እንደነበር ገልጾ ካቴናውም የተፈታለት ፍርድ ቤት ሊመጣ ሲል ከ85 ሰአታት እስር በሁላ እንደሆነ ገልጽዋል፡፡

ጠዋት ወደ ፍርድ ቤት ሊመጡ ሲሉ ኮሚቴዎቹ የበድሩ ሰንሰለት ሳይፈታ ይሂድ ለፍርድ ቤት ማሳየት እንፈልጋለን ብለው የነበረ ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ በግዳጅ ሰንሰለቱን ፈተው ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ እንዳደረጉ ለመረዳት ተችሏል።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33492

Monday, August 11, 2014

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው !!

Aug.11.2014
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።


እንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።

ከሕወሃት ከአንድ ብሄር ከተመለመሉ መርማሪዎች ጋር በጋራ በምርመራ ላይ የተሰማሩት ሶስቱ የግንቦት ሰባት ከሃዲ አባላት አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ላይ ያሉት -
1) ሽታው ሽፈራው ኤርትራ የነበረ የጎጃም ሰው
2) ቴዎድሮስ ስዩም ኤርትራ የነበረ ከአዲስ አበባ የሄደ
3) ኢልያስ ጥረት ጎንደር ውስጥ የነበረ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሲሰራ የነበረ ናቸው ሲል በዝርዝር የጠቆመው ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ በወያኔ ተንኮል ተተብትበው ግንቦት ሰባትን በመክዳት ለምቾታቸው የሕዝብን ትግል በጥቅም በመለወጥ በዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሱ በአዲስ አበባ እና ደብረዘይት ምርጥ ሆቴሎች ውስጥ እየተዝናኑ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አንዳርጋቸውን በቶርች በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።


ምርመርውን በመሪነት የሚያንቀሳቅሱት የሕወሓት ደህንነቶች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በአከባቤው አንዳርጋቸውን በተመለከተ ለብአዴን ይሁን ለ ኦሕዴድ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጣቸውና ወደ ማሰቃያ ክፍሉ ምንም እንዳይቀርቡ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ ለማረጋገጥ መቻሉን የገለጸው ጦማሪው ከአንዳርጋቸው ጋር የተያያዘውን የሃገር ውስጥ ኔትወርክ በማፈራረስ ረገድ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ከሃዲዎች እስከ ክፍለሃገር ድረስ በስፋት እየሰሩ ሲሆን እስካሁን በማፈራረስ ሙከራው ምንም አይነት ውጤት እንዳልገኙ ታውቋል ብሏል።


ጦማሪው ዘገባውን ሲቋጭም “ከአንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ከየክልሉ የግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ አሉ የተባሉ እየተለቀሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከጎንደር ክፍለሃገር መምህር ተስፋዬ ተፈሪ እና መምህር ጌታቸው የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንደሆነ የሚነግረው አቶ አበራ በከሃዲዎች ጥቆማ ከሃምሌ አጋማሽ ጀምሮ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የት እንደታሰሩ እንኳን እንደማይታወቅ ተገልጿል።” ብሏል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33388

Sunday, August 10, 2014

የወያኔ መንግስት ገድሎ ደብዛቸውን ላጠፋቸው ከፍተኛ የኢህአፓ አመራሮች የተዘጋጀ የፎቶ ኢግዚቪሽን። EPRPYL, Norway

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ


ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ

አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው


እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር

አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።


በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ

አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነው የሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ


ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።


እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።

በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ


ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣


በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33334

Thursday, August 7, 2014

ታዋቂው ፖለቲከኛና መምህር ወጣት አብርሃ ደስታ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ አለ

Aug.7.2014
በአራዳ መጀመሪያ ፍ/ቤት ችሎት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይቀርባል ቢባልም ዘግይቶ 10 ሰዓት ከ25 ላይ ቀርቧል፡፡ ፖሊስ ሀምሌ 3 ቀን ፍ/ቤት ቀርቦ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በሽፋን ትሰራለህ በሚል በቁጥጥር ስር አድርጎ ለምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት የነበረ ሲሆን በ28 ቀን ውስጥም ምንም ማስረጃ ለችሎቱ አላቀረበም፡፡ በችሎቱ ላይ የአረና አመራር አቶ ካህሳይ፣የአብርሃ እህት በችሎቱ እንዲታደሙ ተፈቅዶላቸው ገብተዋል፡፡ አብርሃ ደስታ በእስርቤት የደረሰበትን ለችሎቱ ሲያስረዳ እያስገደዱ ቃል ተቀብለውኛል፣ ተደብድቤያለሁ፣ ከውጪ የመጡ የደህንነት ኃይሎች ምርመራ አድርገውብኛል፣ ጨለማ ቤት ለቀናቶች ነበርኩ፣ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ፣ የጨጓራ በሽተኛ ሆኜ በግድ እንጀራ እንድበላ ተደርጌያለሁ በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል ፡፡ ፖሊስ እነዚህ ድርጊቶች በፖሊስ ጣቢያው እንደማይደረጉና ማስረጃ የሌላቸው ውንጀላዎች ናቸው በማለት ያስተባበለ ሲሆን፣ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ደንበኛቸውን የሚመረምረውን መርማሪ ስም እንዲገለጽ ቢጠይቁም የመርማሪውን ስም አንናገርም ይዞ ፍ/ቤት የሚያቀርበውን ፖሊስ ስም ብቻ ነው የምንናገረው በማለት መልሰዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምርመራ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ ፍ/ቤቱ የ28 ቀን ቀጠሮውን ፈቅዶ ለነሐሴ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት እንዲቀርብ አዟል፡፡ የፍርድ ቤቱን ሂደት ለመከታተል አረና፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ፣የጌዴኦ የፓርቲ አመራሮችና አባሎቻቸው፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች በርካታ ሰዎች ተገኝተው አብርሃ ወደ ፍ/ቤት ግቢ በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ በጭብጨባና አይዞህ በማለት አጋርነታቸውን ሲገልጹ ብርሃ ደስታም አንገቱን ዝቅ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33307

Tuesday, August 5, 2014

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

"ኦባማ ዝምታው ይብቃ"
ethio usAugust 4, 2014 11:44

ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።
ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡
ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል – አምባሳደር ሺን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ ቤን ሮድስ ተናግረዋል፡፡
ሚስተር ሮድስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ ጉባዔውን አስመልክቶ ከትናንት በስተያ ምሽት ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት የአንድ ሰዓት የስልክ ቃለ-ምልልስ የመጭውን ሣምንት ጉባዔ ይዘትና አካሄድ አብራርተዋል፡፡
  በድምጽ የተጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ:: http://amharic.voanews.com/audio/Audio/441270.html
http://www.goolgule.com/ethiopians-rally-against-africa-us-summit/

Monday, August 4, 2014

በሁለት ካርቶን ታሽጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው ወርቅ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ትዕዛዝ እንዲወጣ መደረጉ ተዘገበ

Aug.4th,2014

በሁለት ካርቶን ታሽጎ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው ወርቅ በሳሞራ የኑስ ትዕዛዝ እንዲወጣ መደረጉን ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።
እንደዘገባው ከሆነ የጄኔራል ሳሞራ የኑስ እንደሆነ የሚጠረጠረው አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከአገር ሊወጣ ሲል ተይዞ የነበረ ቢሆንም በጄኔራሉ ትእዛዝ ከአገር እንዲወጣ መደረጉን የአየር መንገዱ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ በሁለት ካርቶን ታሽጎ በበረራ ቁጥር 600 እና 612 ወደ ዱባይ ሊሻገር ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅ በጊዜው ባለንብረቱ ተፈልገው ባለመገኘታቸው እንዲቆይ ቢደረግም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ቦታው ድረስ አሽከሮቹን በመላክ እንዲለቀቅ እና እንዲያልፍ/እንዲጫን የተደረገ መሆኑ ታውቋል።
ዘገባው ጨምሮም ይህ የሃገር ሃብት የሆነን ወርቅ የወያኔ ባለስልጣናት ካለምንም ገደብ በማሸሽ እና በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው በአፍሪካ ወርቅ ቤት ሽፋን እንዳልካቸው እና ዳንኤል በሚባሉ ስሞች በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት የወርቅ መጠን ከአገር በማስወጣት እና እንዲሁም የውጪ ወርቆችን ካለምንም የቀረጥ ክፍያ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ስራ ላይ መሰማራታቸው በተጨማሪም ሃገሪቷ የምታገኛቸው የውጪ ምንዛሬዎች በጥሬው እየታሸጉ ከሃገር እንደሚወጡ ታውቋል ሲል ጠቁሟል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33167